የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሃዘን ሞልቶ ደም እንደ ጎርፍ የፈሰሰባት ቀን!!!

የካቲት 12 የፋሽስት ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን – ተረፈ ወርቁ

ከየካቲት 12 እስከየካቲት 14 ቀን 1929 ዓ.ም. በሦስት ቀናት ብቻ 30 000 ( ሠላሳ ሺህ) የሚሆን ህዝብ ተጨፈጨፈ፡

ራስን ካንገት ላይ ቆራርጦ እየጣለ
በችንካር ቸንክሮ ሰው እየገደለ
ሰውን ከነቤቱ አብሮ እያቃጠለ
ማነው እንደ ፋሽስት በሰው ግፍ የዋለ

ከ85 ዓመታት በፊት የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም.  በፋሺስት ጣሊያን ጭፍራ ማርሻል ሮዶልፎ ግራዚያኒ አማካይነት በአዲስ አበባ ከተማና በዙርያዋ ለሦስት ቀናት በዘለቀው ጭፍጨፋ ሰማዕት ለሆኑት 30000 ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በቆመው ሐውልት ግርጌ ከሰፈረው ግጥም ከፊሉ ነው፡፡

ይህ የአፅሞች ማረፊያ በጣሊያን ፋሺስታውያን እጅ በግፍ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም.  የተገደሉ የብዙኃን ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ ነው በሚል የሚንደረደረው በግዕዝ የተጻፈው የሐውልቱ ጽሑፍ አገዳደላቸው በድንጋይ በመወገር፣  በዱላ በመቀጥቀጥ፣  በአካፋ፣  በዶማ፣  መትረየስ፣  በየቤታቸው ውስጥ በእሳት በመቃጠል፣ ወዘተ እንደሆነ ይዘረዝራል፡  የግፍ አገዳደሉ በተፈጸመ በአራተኛው ዓመት ከብሪታኒያ በድል አድራጊነት የተመለሱት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የነፃነት ምልክት የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ ካቆሙ በኋላ በግፍ የተገደሉትን አፅሞች ከየቦታው እንዲሰበሰቡ ሹማምንቱን በማዘዝ ለዝክረ ነገር እንዲሆንም በቅዱስ ስፍራም መታሰቢያውን አቆሙላቸው፡፡

ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1848 እስከ 1966›› በተሰኘውና በ1989 ዓ.ም. በታተመው መጽሐፋቸው እንደገለጹት፣ የኢጣሊያ ፋሺዝም ጽልመታዊ ገጽታ ቁልጭ ብሎ የወጣው በየካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. ነው፡

አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የተባሉ ሁለት ወጣቶች በግራዚያኒ ላይ ቦምብ ጥለው ካቆሰሉት በኋላ አዲስ አበባ ላይ መዓት ወረደባት፡፡ ‹‹ጥቁር ሸሚዝ›› እየተባሉ የሚታወቁት የፋሽስት ደቀመዛሙርት መንግሥት አይዟችሁ እያላቸው አዲስ አበባን ቄራ አደረጓት፡፡ የሰው ልጅ ጭንቅላት እንደ ዶሮ እየተቀነጠሰ ወደቀ፡፡ ቤቶች ከነነዋሪዎቻቸው ጋዩ፡፡ እርጉዝ ሴቶች በሳንጃ ተወጉ፡፡ የጭፍጨፋው ተቀዳሚ ዒላማ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡ በተለይም የጥቁር አንበሳ አባላት ከራስ እምሩ ጋር እጃቸውን ከሰጡ በኋላ በከተማይቱ ይገኙ ስለነበር በወረንጦ እየተለቀሙ ተረሸኑ፡፡ ይህ የምሁራን ጭፍጭፋ አንድ ትውልድ እንዳለ ያጠፋ በመሆኑም ባገሪቱ የፖለቲካና ምሁራዊ ታሪክ ላይ የማይሽር ቁስል ጥሎ አለፈ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች ላይ በተሰነዘረ ጥቃት 7 ቤተክርስቲያኖች ተቃጠሉ | በሰዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት ደረሰ

ስድስት ኪሎ በሚገኘው የያኔው ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት ያሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በወቅቱ የነበረውን የፋሽስት ጣሊያን ጭፍጨፋ የታዘበው ሀንጋሪያዊው ሐኪም ላዲስላስ ሳቫ ዓይኑ ያየውንና የታዘበውን በማስታወሻው መግለጹን በጳውሎስ ኞኞ ‹‹የኢትዮጵያና የኢጣሊያ ጦርነት›› መጽሐፍ ላይ እንዲህ ተመልክቷል፡-

‹‹…ከዚህ በኋላ በግቢውና በአካባቢው ወዲያውኑ ጅምላ ጭፍጨፋ ተጀመረ፡፡ … በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት ግቢ ውስጥ ከነበሩት ኢትዮጵያውያን አንድም በሕይወት የተረፈ ሰው አልነበረም፡፡ ቦታው ላይ የተካሄደው የጅምላ ጭፍጨፋ የተሰበሰቡት ሰዎች ዕድሜያቸው የገፋ፣ ዓይነ ስውራን፣ አካል ጉዳተኞች፣ የኔብጤዎችና ሕፃናትን የያዙ ድሃ እናቶች ስለነበሩ በዚህ ቦታ የተፈጸመው ሰቆቃ ትርጉም የሌለው፣ የሚሰቀጥጥና የሚያሳፍር ነበር፡፡›› ፋሽስት በ1928 ዓ.ም. ተዘጋጅቶና የዐድዋውን ሽንፈት ለመበቀል የመርዝ ጋዝ ጭስ ሣይቀር ታጥቆ ከመምጣቱ በፊት ሕዝቡን በዘር፣ በጎሳና በቋንቋ በመከፋፈል በአንድነቱ እንዳይቆም፣ ስለ አንድነቱና ነጻነቱ የሚያስተምሩና በጽናት እንዲቆሙ የሚመክሩ እንደ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ያሉትን የሃይማኖት ተቋማት ለማዳከምና ለማፍረስ ከተቻለም በሮም ቁጥጥር ሥር እንዲሆኑ ለማድረግ ከፍተኛ ዘመቻ ከፍቶ ነበር።

በዚህ ዘመቻው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ዋንኛ ዒላማው አድርጓት ነበር። የሰማዕታቱ የአቡነ ጴጥሮስና የአቡነ ሚካኤል የግፍ ግድያ፣ የበርካታ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት መቃጠል፣ መዘረፍና መውደም እንዲሁም የበርካታ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች የኾኑ ካህናት፣ መነኮሳት፣ መናኒያን፣ ዲያቆናትና ምእመናን ጭፍጨፋ የከፋና የእኩይ አቋሙ ማሳያዎች ነበሩ።

ፋሽስቱ ቤኒቶ ሞሶሎኒ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የነበረውን ንቀትና ጥላቻ ያሳየበትና ቢቻለውም ቤተ ክርስቲያኒቱን በፋሽስት ወይም በሮማ አስተዳደር ሥር ለማድረግ የነበረውን ሕልም የሚያጋልጠው እ.ኤ.አ. ታኅሣሥ 16/1935 በአስመራ ለሚገኘው የጦር አዝማቹ ለማርሻል ባዶሊዮ ያስተላለፈው ጥብቅ ምሥጢራዊ ቴሌግራም እንዲህ ይላል፡-

በቁጥር 421M እና በቁጥር 426 ዳግም ያስተላለፍክልኝ የምስጢር ቴሌግራም ደርሶኝ በሚገባ አይቼዋለሁ። የአክሱም ገዳም የተቀደሰ ሥፍራ እንደመሆኑና ካለውም ጥንታዊ ታሪክና ቅርስ አኳያ በጦር መሣሪያም ሆነ በማናቸውም ዓይነት ወረራ እንዳይነካና የኢትዮጵያዊነቱን እንደያዘ መቆየት አለበት የሚለውን የውጭ መንግሥታት አሳብ ከምንም አልቆጥረውም ማለትህና ወደፊትም ይህን አሳብ የምቀበል ሰው አይደለሁኝም ማለትህ ትክክለኛ ነህ፤ ጥሩም አድርገኻል። አሁን የቀረህ ደግሞ የአክሱምን ገዳም ካህናትና መነኮሳት ብዛታቸውንና ማዕረጋቸውን ጠይቀህ ካወቅህ በኋላ በገናናዋ በሮምና በሞሶሎኒ ዙፋን ሥር እንተዳደራለን የሚሉ እንደሆነም በውል አጽፈህና እያንዳንዳቸውን አስፈርመህ ቃል የገቡበትን ሰነድ ወደ እኔ እንድትልክልኝ ነው።

የኢትዮጵያ ታላቅ ባለውለታ የነበሩትና የኢጣሊያን ፋሽስት ጭካኔና ግፍ ለዓለም ሁሉ በማጋለጥ ከኢትዮጵያውያን ጎን የቆሙት


የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሃዘን ሞልቶ ደም እንደ ጎርፍ የፈሰሰባት ቀን

ያ ያ ዘልደታ ያሬድ

በአዲስ አበባ የፋሽስት ኃይል በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል አይተው ህሊናቸው እጀግ የቆረቆራቸው ሞገስ አስገዶምና አብርሃም ደቦጭ የተባሉ ወጣት ኢትዮጵያዊያን የሙሶሉኒ ቀኝ እጅ የነበረውና ኢትዮጵያን እንዲያስተዳድር የተላከውን ሩዶልፎ ግራዚያኒን ለመግደል የወረወሩበት ቦምብ ሳይገድለው ቀረ፡፡
ግን ክፉኛ ቆሰለ፡፡ ሆኖም በድርጊቱ እጅግ የተበሳጨው ግራዚያኒ ጥቁር ሸሚዝ ለባሽ የተባሉትን የፋሽስት ጦር ጨካኝ ቡድን በአዲስ አበባ ሕዝብ ሊይ አዘመተ፡፡

ከየካቲት 12 እስከየካቲት 14 ቀን 1929 ዓ.ም. በሦስት ቀናት
ብቻ 30 000 ( ሠላሳ ሺህ) የሚሆን ህዝብ ተጨፈጨፈ፡፡

ጭፍጨፋውም በርሸና፣ በስቅላት፣ በድብደባ እና በእሳት በመለብለብ እንደነበር ሕያው ምስከሮች በመሃላችን አሉ፡፡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እና አቡነ ሚካኤል ሕዝቡ ለፋሽስት ኃይል እንዳይገዛ ያወገዙት አባቶች ያለርህራሄ ተረሽነዋል፡፡

በደብረ ሊባኖስ ገዳም ይገኙ የነበሩ 300( ሦስት መቶ) መነኮሳት በግፍ ተጨፍጭፈዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሺህ የሚቆጠር ህዝብ በአዲስ አበባና ከዚያም ውጭ በሚገኙ እስር ቤቶች ተወርውረው እንዲማቅቁ ተደርገዋል፡፡

ያቺን ቀን እናስባት! አንርሳት!
የኢትዮጵያ ሰማዕታት የክብር አክሊል የተቀበሉባትን ደማቸው እንደጎርፍ በግፍ የፈሰሰበትን ስጋቸው እንደ እህል የተፈጨበት አጥንታቸው እንደ ገል የተከሰከሰባትን ዕለት!!

ማስታወሻ፦ ይህ ጭፍጨፋ በተካሔደበት ቦታ አቅራቢያ
ለሰማዕታቱ የሚሆን መታሰቢያ ሃውልት ቆሞላቸዋል

1ኛ/ የስድስት ኪሎ የሰማዕታት ሐውልት
2ኛ/ የካቲት 12 ት/ቤት የቀድሞ እቴጌ መነን
3ኛ/ የካቲት 12 ሆስፒታል

ሰማዕታቱን ሲያስታውሱና ሲዘክሩ ይኖራሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ብርሀኑ ጁላ መልቀቂያ አስገባ | "መከላከያው ፈርሷል ተሸንፈናል" አበባው ታደሰ | “ከብዶናል” አረጋ ከፋኖ ጋር አስታርቁኝ | ኤርትራ ቁርጡን አሳወቀች ‹‹አሸማግሉን›› ጌታቸው፣

ያ ያ ዘልደታ ያሬድ

የካቲት 12, 1929 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሃዘን ሞልቶ የፈሰሰበት ቀን

የካቲት 12 ቀን የፋሺስት ሰማዕታት 80ኛው ዓመት ለምን ትኩረት ተነፈገው? – ሔኖክ ያሬድ

2 Comments

  1. ተረፈ ወርቁ ትውልዱ ለነጻነት የሞቱለትን አባቶቹን ከወራሪነት ባልተናነሰ መልኩ ሲመለከታቸው ተጋድሏቸውንና የከፈሉትን መስዋእትነት አስበህ በመዘከርህ ልትመሰገን ይገባል። ከላይ ስሙን የጠቀስከው ግለሰብ እንኳ ለዚህ ታላቅ ታሪክ ማጣቀሻ ባልሆነ ነበር ግፋ በለው፣ጨቋኝ ፣ትጨቋኝ፣ተራማጅ፣ተራጋጭ መንደር ነበርና ነው።

  2. ፋሺሽት ኢጣልያ፤ በቫቲካን ያልተቆጠበ ድጋፍ፤ ለፈጸመችው እጅግ አሰቃቂ ወንጀል፤ ማለትም፤ የአንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መገደል፤ ከዚሁ ውስጥ በአደሲ አበባ፤ በ3 ቀኖች ብቻ፤ 30000 ሰው መጨፍጨፉ፤ በተጨማሪም፤ 525000 ቤቶችና 2000 ቤተ ክርስቲያኖች መውደማቸው፤ እጅግ ብዙ ንብረት መዘረፉ፤ ወዘተ፤ ኢትዮጵያ ተገቢውን ካሣና ፍትሕ ሳታገኝ ቀርታለች፡፡

    ለበለጠ ዝርዝር (www.globalallianceforethiopia.net) መመልከት ይቻላል፡፡ ቫቲካንም የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ በመጠየቅ ድረገጹ ላይ የቀረበውን አቤቱታ በመፈረም ለሐገራችን ስለሚያስፈልገው ፍትሕ ድጋፍ ማበርከት ይጠቅማል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share