የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የፓርላማው ደራማ! – ሰርፀ ደስታ

እንደኖሕ ዘመን ሰዎች ማዕበሉ አንገታቸው ደርሶ እንኳን እነሱ አሁንም ከሴራቸው ውጭ አንዳች በጎ ነገር እንዳያስቡ አእምሮአቸው ለተገዙለት ሰይጣናዊ አስተሳሰብ ተሰጥቷል፡፡ እንጂማ 27 ዓመት ሙሉ የሆነው ሆኖ አሳዳጊያቸው ወያኔ በመጨረሻ የደረሰበትን እያዩ በወያኔ እንዳደጉ ከወያኔ ጋር ሲገድሉትና ሲያስገድሉት የነበሩ በለውጥ ሥም የሕዝብ ቅቡልነት አግኝተው ዳግም ወያኔ በሄደችበት ላለመሄድ ሲገባቸው ለዘመናት የሰሩት ግፍ እነሱም ቀናቸውን ጠብቀው እስኪጎነጯት ግድ ስለሆነ ይሄው ዛሬ የሚያደረጉትን እያየን ነው፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡ ወያኔ ከሥልጣን ስትወገድ ዛሬ ብልጽግና ነኝ የሚለው በኦሮሞ አረመኔ ፖለቲከኞች የሚመራው ቡድን በግልጽ ዜጎችን በማንነታቸው ለማጥፋት አቅዶ በለዩ ሁኔታ ዜጎችን የሚያርዱ ቅልቦቹን ኦነግ ሸኔ በሚል ሽፋን አስፈላጊውን የጦር ትጥቅና የሚፈልጉትን ሁሉ አሟልቶ በከፍተኛ ድግስ በስቴዲዮሞች ነብሰበላዎቹን እያስመረቀ እያየን ማስተዋል ምነው ተሳነን?

ኦነግ ሸኔ የሚባል ነገር የለም፡፡ ቃሉ ከየት መጣ ካላችሁ፡፡ ኦነግ በአንድ ወቅት ወሳኝ የተባሉ አምስት ሰዎችን ያካተተ ሥራ አስፈጻሚ ነበረው፡፡ ይሄው ሥራአስፈጻሚ የሚታወቀው ሸኔ በመባል ነው፡፡ ሸኔ ዛሬ ገዳዩን ቡድን እቅድ የሚሰጥ፣ ትጥቅና ስንቅ የሚያቀብል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ያለ የኦነግ/ኦህዴድ ከፍተኛ ሥልጣን ያለው ቡድን እንጂ በጫካ ያለ አደለም፡፡ ዛሬ በኮንቪንስና ኮንፊውዝ ድራማ ልክ ኦነግ ሸኔ የሚባል እነሱ የማይቆጣጠሩት ሌላ ያለ በማስመሰል ቡዙውን ሕዝብ እያጃጃሉት ይገኛል፡፡

እውነታው ግን ዛሬ ዜጎችን በማንነታቸው እየገደለ ያለው ቡድን የታጠቀው መሳሪያ ሳይቀር አብይ አህመድ ለሪፐብሊካን ጋርድ በሚል ከአሜሪካ ሳይቀር ያገኘውን መሳሪያ ነው፡፡ ያን የሚያል የገዳይ ሰራዊት በስቴዲያም ሳይቀር ሲያሰለጥን ገንዘቡን ከየት ያገኛሉ ብሎ መጠየቅ እንዴት ያቅታል፡፡ ዛሬ ዜጎችን የሚያርዱትን ገዳይ የአብይ አህመድና ሌሎች ኦነጋውያን ሸኔ በሚል የሚጠራው ቡድን ገንዘብ እየተላለፈለት ያለው በአገሪቱ ዋነኛ ባንክ በሆነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደሆን አስተውሉ፡፡ መጀመሪያ ላይ ተዘረፈ በሚል ትንሽ የማያዘልቅ ድራማ ጀምረው ነበር፡፡ ኋላ ላይ ሲያዩት ሁሌም ተዘረፈ በሚል መሸወድ ስለማይቻል የባንኩን መዋቅር በመያዝ በውስጥ በቀጥታ ማስተላለፍ የሚቻልበትን ሥልት ነደፉ ዛሬ እየሆነ ያለው ይሄ ነው፡፡ ለዚህ ሲባል አብይ አህመድ በመጀመሪያ የአዲስ አበባን ከተማና መከላከያውን በኦሮሞ ከመተካት ጋር  ትኩረት የሰጠበት ተቋም ቢኖር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነበር፡፡ አብይ አህመድ ወዲያው ነበር የባንኩን ሥራ አስፈጻሚ ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ በኦሮሞ የተካው፡፡ ሊያውም ባንክ የማስተዳደር ልምድ የሌለውን ግለሰብ ከአዋሽ በማምጣት፡፡ ያን ሲያደርግ የሥራ አስፈሚውንም ከስምንቱ አምስቱን እንዲሁ በኦሮሞ በመተካት ነበር፡፡ ሁሉም የመጡት ደግሞ ከራሱ ከባንኩ ነባር ሰራተኞች ሳይሆን ከአዋሽና ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ነው፡፡  ልብ በሉ ከየት እንደመጡ፡፡

አንዳች ነውር የሚባል ባልፈጠረበት አብይ ይሄን እያደረገ ነበር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ሕዝብ ሲያጃጅል የከረመው፡፡ ቀጥሎ እንደነገርኳችሁ በመጀመሪያ የባንክ ሥራ አስኪያጅ ያደረገው ግለሰብ የባንክ የማስተዳደር ልምድም ስላልነበረው ብዙም ሳይቆይ ብዙ ነገሮችን አበላሽቶ እሱ ወደ አምባሳደርነት ሲላክ አሁንም ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥራ እስኪያጅ አመጣ፡፡ ዛሬ ባንኩን የሚመራው ግለሰብ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ትልቅ የአክሲዮን ድርሻ ያለው የኦሮሚያ ኢንተርናሽናነል ባንክን ከመሰረቱት አንዱ ነው፡፡ እንግዲህ አስቡት ይህ ግለሰብ የኢትዮጵያን ንግድግ ባንክ ሲመራ ምን ዓይነት ሥራ ለኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ እንደሚሰራ፡፡ በግልጽ የዛሬው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ቅርንጫፍ ቢባል ይሻላል፡፡ በአለፉት አራት ዓመታት የኦሮሞ የሆኑ ባንኮች የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክና የኦሮሚያ ሕብረት ባንክ በምን ያህል እጥፍ እየተስፋፉ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ለሸኔ ገንዘብ ለማስተላለፍ የተመቻቹ ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከብሔረሰብ በዓል ወደ ለታላቁ ሩጫ! - በእውቀቱ ስዩም

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንጻ ሰራ ተብሎ ሲመረቅ አስተውያለሁ፡፡ አንዳንዶች እንደውም እንዲህ ያለ ድንቅ ሥራ እየተሰራ ባለበት ትንንሽ የሆነን ጉዳይ ማለትም የሰዎች እልቂት የከተሞች መውደምና የመሳሰሉትን ጉዳዮች እንዴት ታወራላችሁ ብለው ሲደነፉ ሰምቻለሁ፡፡ እንዲህ ነው የምትሆነው፡፡ ማስተዋል የጎደለው ትውልድ፡፡ ሲጀምር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንጻ ከተቋሙ መስራቤትና የባንክ አገልግሎት ውጭ ሌላ ሊሰጥ የሚችልው ምንም ዓይት ጥቅም የለውም፡፡ ለሕዝብ የሚተርፍ ምንም ዓይነት ጠቀሜታ የለውም፡፡ አለው የምትሉ እስኪ ንገሩን፡፡ ሕንጻው እንደሕንጻነት መሠራቱ ለተቋሙም ቢሆን መልካም ነው፡፡ እንኳን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትላንት መጥተው እነ ንብም የምናየውን የሚመስል ሕንጻ ሰርተዋል፡፡ ምኑ ሊደነቅ እንደሚችል አይገባኝም፡፡ ደግሞ እኮ በአሜሪካና አውሮፓ ባሉት ይብሳል አድናቂነቱ፡፡ ባለፈውም መናፈሻ ሲሰራ እነዚሁ ነበሩ ከነዋረው በከፋ ብርቅ ሆኖባቸው ሲያጃጅሉን የከረሙት፡፡ የሚገርመው እኮ ከሚሰሩበትና ከሚኖሩበት ውጭ አያውቁ እንደሆነ እንጂ በሚኖሩባቸው ከተሞች በየክፍለከተማው አብይ አህመድ በቢሊየን አውጥቶ ሰራሁት የሚለውን መናፈሻ የሚያስከነዱ መናፈሻዎች ሞልተዋል፡፡ ሲጀምር የመናፈሻ ሥራ ለእንደነአዲስአበባ ለመሳሰሉት ከተሞች የከተማው እንኳን ሥራ ባልሆነ፡፡ መናፈሻው ከሚሰራበት ክፍለከተማ ያለፈ ሥራ አደለም፡፡

በቀደምም የመከላከያ ሕንጻ በሚል ሲመረቅ አይቻለሁ፡፡ ልብ በሉ ከተሟለ ሕንጻዎቹ መሠራታቸው መልካም፡፡ ሆኖም ግን ችግሩ ይሄ ሁሉ የአገር ተቀዳሚ ጉዳይ አለመሆን ብቻም ሳይሆን ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ውድመት እያስከተለ ያለ ያለ ምንም ማሰብ ሳያስፈልግ ገንዘብ የሚሰራው ነው፡፡ ቀጥሎ የሚኖረውን አገልግሎት ስናይ ደግሞ ለሕዝብ የሚኖራቸው ፋይዳ ባዶ ነው፡፡ የመከላከያ ሕንጻ ተሰራ አልተሰራ ሳይሆን ምን አይነት መከላከያ ተቋም አለኝ የሚለው ጉዳይ ያው እንደምታዩት ነው፡፡ ከትግሬ ወያኔ ወደ ኦሮሞ ኦነግ የተቀየረ ብቻም ሳይሆን አገሪቱን በሁሉም አቅጣጫ እያስወረረ ያለ የወደቀ ተቋም፡፡ ይሄንን ተቋም የሚመሩትን አገርን ያዋረዱትን ያው እንዳያችሁት ማዕረግ በማዕረግ ተደርገዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ደመራ {በሃይማኖታችን፥ በታሪካችንና በባሕላችን አንጻር} – (በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ)

ለማንኛውም ከመጀመሪያው ጀምሮ ጥቂቶች እየመጣ ስላለው አደጋ ስናስጠነቅቅ ነበር፡፡ አሁን ሁሉም እየለየለት መጥቷል፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ሌላ ድራማ እያየን ነው፡፡ አነጋጋሪው የፓርላማ ውሎ በሚል ብዙዎች ሲያሰራጩት ያየሁት የአንድ የኢዲስ አበባን ተወላጅ በመስደብ ፓርላማ የገባን የአብይ አህመድ ምልምል ነው፡፡ ግለሰቡ ለአማራና አፋራ ያሰበ መሆኑን ለማሳየት ነው ሆን ተብሎ የተለቀቀው፡፡ ሌላው ኮንቪንስና ኮንፊውዝ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ቀጥሎም ተመሳሳይ ነገር ይናገርላችኋል፡፡ ከዛ እሱ ጎበዝ ነው ማለት ይጀመራል፡፡ ከዛ ቲፎዞ ማፍራት ነው በቃ፡፡ ድራማው ይሄ ነው፡፡ አስቂኙ ነገር ግን ፓርላማ ተብዬው የተሰበሰበበት ነገር ነው፡፡ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ስለማሳት የሚል ነው፡፡ ለመሆኑ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አለ? አዋጁስ ለምን ዓላማ ታወጀ፡፡ ወንጀል ለመስራት ወይስ ወንጀል ለማስቀረት? በዚህ አስቸኳይ አዋጅ በተባለበት ጊዜ ያየንው እውነት ቢኖር የአብይ አህመድ መርዘኛ ቡድን ሴራውን አጠናክሮ መቀጠሉ ነው፡፡ ስለኢትዮጵያና ሕዝብ ደህንነት የሚናገሩትን ታምራት ነገራንና መሠል ጋዜጠኞችን አስሮ ወንጀለኞችን ለቆ ተመልክተናል፡፡ በይፋ ፍትህ የምትባለውን እርማችንን እንድናወጣ አድርጎናል፡፡ ታምራት በኢደስ አበባ ፌደራል ፖሊስ ተይዞ ለሽመልስ አብዲሳ ቅልቦች ተሰጥቷል፡፡ ሌሎችም ብዙ ተደርገዋል፡፡ በገፍ በትግሬነት ሥምም የታሰሩ አሉ፡፡ ዋናዎቹ ግን ተለቀቁ፡፡ በይፋ የፍትህ ሚኒስቴሩ ከሕግ ውጭ መስራት ትክክል ነው ብሎ ነግሮናል፡፡ እንኳንስ የታወቁት ወንጀለኞች ይቅርና አንዳች ወንጀል ሳይኖርባቸው በግፍ ከአመት በላይ ታስረው ክስ ማቋረጥ በሚል ከተፈቱ ጋር የተፈቱት እነእስክንድርም ቢሆኑ ከሕግ ውጭ ነው እንዲፈቱ የተደረገው፡፡ ልብ በሉ፡፡ እንዲህ ያለ አሰራር የሚሰራው ሆን ተብሎ ነው፡፡ ፍርድ ቤት በእነእስክንድር ላይ የነበረውን ድራማ እናስታውሳለን፡፡ ፍትህ ቢኖር ፍርድ ቤቱ ያ ሁሉ ሲሆን ብይን ሊሰጥ በተገባው ነበር፡፡ ዛሬ ክስ ማቋረጡ እነሱንም የሚመለከት ሆኗል፡፡ ካቋረጠም በኋላ መልሰን የማሰር መብት አለን የሚል ድንፋታ ሰምተናል፡፡ እነዚህ ሁሉ ሂደቶች የለየለት የወሮበላነት አሰራርን በመንግስት መዋቅር ማሰፈጸም ነው፡፡

ሰሞኑን ብዙ ሲያነጋገር የነበረውን የመስቀል አደባባይን ጉዳይ ቅዱስ ሲኖዶስ ካልተሳሳትሁ በአግባቡ የያዘው ይመስላል፡፡ እንግዲህ ቅዱስ እግዚአብሔር ያበርታችሁ ነው የምለው፡፡ አዎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ለዓለም ሳይቀር ለክርስቲያኑ ማመሳከሪያ ምልክት እንደሆነች ግልጽ ነው፡፡ የዚህች የደሀዋ አገር ቤተክርስቲያን ክርስቲያናዊ ፍልስፍናና አስትምሮ ዛሬ ዓለም የገባበትን የክርስትና ውዥንብር ወደኋላ ለማየት የሚችልባት ነች፡፡ ዓለም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው ለጉብኝት ብቻም ሳይሆን ከዚህች ቤተክርስቲያን የሚገኝ አንዳች የቆየ የእምነት መሠረትና ፍልስፍናም ለማነፍነፍ ነው፡፡ ለዚህ ማሳያው ዛሬ በሁሉም ክርስቲያኖች ዘንድ አነጋጋሪ የሆነው የመጻፈ ሔኖክ ጉዳይ አንዱ ነው፡፡ የእኛዎቹ ግን ከቤትክርስቲያኒቱ አስተምህሮትና ፍልስፍና ወጥተው ይሄው ዛሬ የምናየውን እያደረጉ ነው፡፡ በእርግጥም በቤተክርስቲያን አባቶች ድክመት አለ፡፡ ከዘመነ ሔኖክ (የመጀመሪያው ሰው) እሰክ ዛሬ ያለውን እውነት በየዋሻው ይዛ ለሕዝብ ባለመገለጡ ብዙዎች ከቤተክርስቲያን ወጥተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ “የብሄር ፖለቲካ” እና “የዘረኝነት ስርአት”፤ ያስከተለው መዘዝና መፍትሄዉ (ክፍል-3) - ዓቢዩ ብርሌ (ጌራ)

ለመሆኑ ግን መስቀል አደባባይም በሉት ጃንሜዳ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሥር ባይቆይ ኖሩ እስከዛሬ ይኖሩ ነበር? በፍፁም አይኖሩም ነበር፡፡ ገና ድሮ ጃን ሜዳም መንደር መስቀል አደባባይም ቢያንስ የአከርከበ ሱቆች አይምሩትም ነበር፡፡ እንግዲህ የነበረውን ለማጥፋት ነው ይሄ ሁሉ ምቀኛዊ አካሄድ፡፡ መስቀል አደባባይም ሆነ ጃንሜዳ የቤተክርስቲያኒቱን ሥርዓት የሚጠብቁ ወይም የማይጣረሱ የሕዝብ አገልግሎቶች መስጠታቸውን ቤተክርስቲያኒቱ አልተቃወመችም፡፡ ወደፊትም ይሄ ይቀጥላል፡፡ እነዚህ ቦታዎች በእርግጥም ቤተክርስቲያኒቱ ለዛሬ ያቆየቻቸው ትልልቅ ቅርሶች ናቸው፡፡ እንዳልኩት ነው በቤተክርስቲያኒቱ ሥር ባይሆኑ ይጠፋሉና፡፡ ይቺ ቤተክርስቲያን እንደሌላው የተንኮል ተቋም ሳትሆን በቅንነት እግዚአብሔርን ስለማገልገል ብዙ ሰዎች የሚኖሩባት ነች፡፡ ዛሬ በዓለም ሁሉ ኢትዮጵያን ውክላ የምትታየውም ለዛ ነው፡፡ እስኪነ ንገሩን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውጭ በሌላው ዓለም አገርን ወክሎ የኢትዮጵያውያን የሚባል የእምነት ብትሉት ሌላ ተቋም ምን አለ? ዛሬ በየአገሩ ለአገር ሲሆን የቆመው ሕዝብ በዋናነት የዚህችው ቤተክርስቲያን የሰበሰበቸው አደለም?

ዛሬ በብልጸግና የፀረ ኦርቶዶክሱ መንግስት ነኝ በሚለው ቡድን ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ በየትኛውም ሥልጣን እንዳይኖር እየተሰራ ያለበትንም እያስተዋልን ነው፡፡ እንግዲህ የመስቀል አደባባይ ጉዳይ ብቻ አደለም ነገሩ፡፡ በተለያየ ቦታ ቤተክርስቲያኒቱን በጠላትነት የሚገፉ ብዙ ሴራዎች አሉ፡፡ መሥቀል እንደባሕል የአብዛኛው የደቡብ ሕዝብ የሚያከብረው ነበር፡፡ ድንቅ ባሕል፡፡ ዛሬ ግን የመስቀልና ጥምቀት ቦታዎች በደቡብ በምን አይነት ሴራ ከቤተክርስቲያን እየተነጠቁ እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ በኢትዮጵያዊ ማንነት ለመቆየትና በራስ መተማመን እንዲኖረን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ለተከታዮቿ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያውያን ሁሉ በአለም ዙሪያ ክብራቸው መሠብሰቢያቸውም ነች፡፡ ይሄን ስል የኤርትራ ቤተክርስቲያንን ረስቼ አደለም፡፡ ትላንት በሴረኞች ቢለያዩም ከእነሙሉ ሥርዓታቸው አንደ እንደሆኑ አውቃለሁና፡፡ የግብጽ ቤተክርስቲያን እንኳን እንደእኛው ቤተክርስቲያን የታሪክ፣ የትምህርትና የፍልስፍና ሐብታም አደለችም፡፡ በእርግጥ የግብጽ ቤተክርስቲያን በተደራጀ ሁኔታ ስለምትመራ በአነስተኛ ቁጥር ጠንካራ ነች፡፡

የኢትዮጵያ ጉዳይ አሁንም ብዙ አሳሳቢ ነው፡፡ ሆኖም የቆየው ይቆያል እንጂ ወንጀለኞች ፍርዳቸውን የሚያገኙበት ቀን ይመጣል፡፡ አንዳንዶች በአለፉት አራት ዓመታት ከአዲሱ ከወያኔ ማደጎውች ጋር የወንጀል ተሳታፊ ሆኗል፡፡ ይሄ ዛሬ ያለው ቡድን እንደ ወያኔ እንኳን የሚታለፍ አይመስለኝም፡፡ ታላላቅ የተባሉ ዓለም ዓቀፍ ወነጀለኛነትን የሚያረጋግጡ ወንጀሎችን በመረጃ አስመዝግቧልና፡፡ በኢትዮጵያ በግልጽ የዘር ማጥፋትና ሌሎች ከፍተኛ የተባሉ ወንጀሎች በግልጽ እየተሰሩ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ በመረጃ እየተያዙ ይመስለኛል፡፡ በሂደቱ በቀጥታ ተሳታፊ የሆኑት ብቻም ሳይሆን ተባባሪዎቻቸውም የሚቀርላቸው አይመስለኝም፡፡ በዚህ ሂደት አንዳንደ በጋዜጠኝነትና አክቲቪስትነትም እንሰራለን የሚሉ ወደፊት ሊጠቁ እንደሚችሉ እያስተዋሉ አልመሰለኝም፡፡ ሁሉም ለራሱ ሲል ቢጠነቀቅ እላለሁ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከመከራ ይታደግ ይጠብቅ! አሜን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share