ይድረስ ለአገር ወዳድ ወገኖቼ በያላችሁበት- ምንድነው የተፈለገው? – ከአባዊርቱ!

ቆም ብላችሁ አስተውሉ በተለይም ብዙ የማከብራችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖች:: እንዴት በ 4ኛውም አመት አንድ አይነት ስህተት እንሰራለን? እንደምንስ ወያኔ ዛሬም በስሜታችን ይጫወታል? እንደምንስ የነ ጄ/አበባውን የቀጥታ ቃለመጠይቅ ለተከታተለ እውነቱን መረዳት አቃተን?? 45000 ጦር እኮ ነው ሺንት እየጠጡ ከ 300000 የፅልመት እስካፍንጫው ከታጠቀ የጥፋት ሀይል ጋር የተላተሙት:: ሃሎ? ይሰማል ወገኖች? ዛሬ ጄኔራሉ ይፋ ስላወጡት እንጅ አደባባይ ይህን መፃፉ እራሱ ብርክ ያሲዛል:: በበኩሌ ይህን ከሰማሁ በሁዋላ እንኩዋንስ መከላከያንና አቢይን ላንጉዋጥጥ ቀርቶ በቅጡም መተኛቱ ተስኖኛል:: እነ ጌታቸው ረዳ በጤናም አልነበረም ሸዋሮቢት ድረስ በረው የመጡልን አፍረው ተሰብረው ፈረጠጡ እንጅ:: ከሱዳን አቅም እንኳ ለምን እንደተዳፈሩን ከአበባው ገለፃ በሁዋላ ለኔ ግልፅ ሆኗል – ለብዙዎቻችሁ እንደምን ይህ ግልፅ እንዳልሆነ ያማል:: እንዴት አቢይ ሆኑ አበባው: ብርሃኑ ሆኑ ባጫ አቃቂር ይወጣላቸዋል? አገርን ስለታደጉ? ጭራሽ በአፋርና አማራ ክህደት በግላጭ ሊታሙ? ከማልጠብቃቸው ሰዎች? በግልፅ እናፍርጠው እስቲ: አቢይን ሸኔ ወይም ዖነግ ነው ለማለት: አማራና አፋርን ከዳ ለማለት ወይም በዳርዳርታው ለመፎተት ፈጣሪ ይወደዋል? ከዚህ መድረክ ጠፍቼ ነበርአካሄዳችን በጣም ስለሚያም:: ሆኖም አንድ ወገን የሸዋን ዖሮሞ ክእንቅልፍ የሚያባንን ነገር ፅፈው  አባነውኝ : እኔውም ስሜታዊ ሆኜ ከፃፍኩ በሁዋላ ፀፀተኝና ተውኩት እንጅ::

ውድ ወገኖች!!

ወገን የተባለው ሁሉ አጀንዳ እንደቀለብ ተሰፍሮለት ሲባላ ሰዎቹ ልዩ መጅሊስና ሲኖዶስ እየፈጠሩልን ነው:: ገና በኛው ንዝህላልነት ብዙ ጉድ እንሰማለን:: ይህ “እኛ ለየት ያልን ህዝቦች ነን” መዘዝ የእርያንን ነገድ አመድ እንዳደረጋቸው በእብሪት ያበጠው ቀፈታቸው ገና የተረዳው አይመስልም:: ጊዜውን ጠብቆ መፈንዳቱ  ግን አይቀሬ ነው::  የሰሞኑ በከንቲባዋና ሲኖዶሱ መሃል የነበረውን ፈጣሪ ምስጋና ይግባውና ክብርት አዳነች በብልሃት ይዘውታልና ብዙ መናገር አልፈልግም:: እኚህን ብርቱ እህት/ልጅ ቢቻል በሞራል ካልሆነም በፀሎት ማገዝ እንጅ ያልሆነ ስም እየሰጡ መበሻሸቅ አገር አያሻግርም:: የለየላቸው ከሃዲዎችን ሳይሆን ስሜታቸው የተነካውን አገር ወዳድ ወገኖችን ነው እየለመንኩ ያለሁት::

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ከሚመጣው ጥፋት ለመዳን ሳይረፍድብን ራሳችንን እንወቅ”  መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ወገኖች : እንድተጠነሰስልን ጥንስስ ቢሆን የሩዋንዳው ቻይልድ ፕሌይ ነበር የሚሆነው እኮ በአገራችን::  ከዚህ መአት የተረፍነው የተጋመድንበቱ የሺህ አመታት መጫኛ እጅግ ጥብቅ በመሆኑ ብቻ ነው!!

ምን እናድርግ?

ሀ) እስቲ የሚሰሩትን ከመውቀስ መፆም:: ቢቻል ማበረታታት : ካጠፉ ከመሰለን ከነቀፌታው መፍትሄ ያልናቸውን አደባባይ ማስጣት:: ግድየላችሁም እነ ቢለኔ ስዩም እየቀመሩ አቢይ ዴስክ ያደርሳሉ:: በስድብና ዛቻ የምትተዳደሩትን ጡረተኞች አይመለከትም

ለ) እርዳታውን በደንብ ወርሃዊ አድርጎ ማሳለጥ:: እንኳንስ እኛ በቁጥር የታደልነው ከኤርትራውያንና ዋናዋ ሱማሌ ወገኖች ብዙ መማማር ይቻላል:: ባለፈው በአይዞን ከ 30ሺ በማይበልጡ ወገኖች ያ ሁሉ ሚሊዮን መሰብሰቡ ተስፋ ሰጪና የማንም ፈረንጅ ተመፅዋች ሆንን እንደማንቀር አመልካች ነው:: ታድያ የፅልመት ጆሮ ይደፈንና የሆነ ችግር ሰምቻለሁ በዚህ አካውንት – ታሪኩ ይቆየንና

ሐ) አገሪቱ የተደቀነባትን አደጋ ከልብ መረዳት:: በገንዘብ፣ ፀሎትና ዱአ በኑሮ ውድነት የሚሰቃየውን ወገን ማሰብ:: ብዙ መረዳዳት ይቻላል ወገኖች ከልብ ከተፈለገ::

 መ) በዖሮሚያ እየሆነ ያለው አንገት አስደፊ ክስተት መቆም አለበት:: የሚቆመው ደግሞ በጎሳ መደጋገፍ ወይም ጏደኝነት መተሳሰብ ላይ በተመሰረተ አመራር ሳይሆን በብቃትና ቆራጥነት ላይ መቆም ይገባዋል እላለሁ:: ለዚህም እጩ አለኝ:: አዳነች አቤቤ ዖሮሚያን ቢመሩ ለውጥ ይመጣል:: የጠቅላይ አቃቤን ቤት ነፍስ የዘራችበት አዳነች ዖሮሚያን ልክ ታገባለች ባይ ነኝ:: እባካችሁ ይህን አቢይ ጆሮ አድርሱልኝ:: ኦቦ ሺመልስ ምን መልካም ቢሆን ያለውን ችግር ለመጋፈጥ ምን እንደያዘውና ምን እንደተፈለገ ግራ  ገብቶኛል:: በንዲህ አይነት ጉዞ እንደምን ለውጥ ይመጣል? ሰላምስ ከሌለ ምንስ ትርፍ አለው ? ለምንስ ከፍ ያለ ትኩረት አይሰጥም? በቃ! እነ ኦቦ ቀጄላ መርዳሳና ኢብሳ ነገዎም ምነው ዝም አላችሁ? ተረዳዱ እንጅ:: እስከመቼ የንፁሃን ደም በኢትዮጵያ ምድር ይፈሳል? ይብቃን ::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ አንድነት ፈተናዎች - ከአበበ ከበደ

ሠ) ማን አዳነችን ይተካ ለከንቲባነት? በኔ አተያይ አለችን በእሳት የተፈተነች ሌላዋ ቆፍጣና አንደበተ ሸጋና ስማርት ዳኛ ብርቱ ሚ’ደቅሣ!!! የፈረንሳይ ልጅ የሸገር ትክል አንበሲት:: ስራዋና ባህሪዋ ይመስክር:: የሷን ምክትል ወጣት ሌላዋን ሶሊያና (ባልሳሳት)ጀግና ቦታዋ ተክቶ ቡርቴን ቶሎ ማምጣት ወደ ማዘጋጃ:: ይህው ነው::

ረ) የአቢቹን ብረሰልስ ጉዞ አስመልክቶ በዚያ ያላችሁ አገር ወዳዶች ለአርብ የኢትዮጵያ ድጋፍ ስልፍ ያቀዳችሁ እንዲህ ነው ወገን ማለት::ስሜታችሁን ሳይሆን ኢትዮጵያን እያስባችሁ ይሁን:: በአንፃሩ ኢትዮጵያን ለማዋረድ ከነአሉላ ሰለሞን ቡራኬ ተቀብላችሁ ያውም ኢትዮጵያን የሚጎዳ የአሜሪካንን ህግ ለመደገፍ ላይ ታች የምትሉ እናት ኢትዮጵያን የከዳችሁ ከሀዲያን ያውም በ 11ኛው ሰአት ላይ ፈጣሪ ይፍረደው:: ለፖለቲካ  ዓላማ ልትሉን ነው? እነ አሉላስ ለጌቶቻቸው ነው ሌሎች ወገኖችን ማለቴ ነው::

በመጨረሻም!

በዚህ ልሰናበት:: ይህ የፈተና ጊዜ ያልፋል:: ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያ ፈጣሪዋንና ህዝቧን ብቻ ተማምና እስካሁን ቆይታለች:: ወደፊትም እንዲሁ ትቀጥላለች:: እየሞትንም ትሻገራለች ይቺ ጉደኛ አገር:: ይብላኝ እናጠፋታለን እያላችሁ በቁም እየከሰማችሁ ላላችሁ የኢትዮጵያ ሁሉ ምቀኞች::ብዛታችሁ ላይጣል ቢሆንም አታሽንፉም:: ለምን? ሀቁ እናንተ ዘንድ አይደለምና! ይህው ነው!!!

ሰላም ሁኑ!!

8 Comments

  1. አባዊርቱ ጥሩ ሀተታ እና ትንታኔ አቅርበዋል ግን አብይ አህመድ መጨረሻ ላይ መዝመቱ ላልቀረ ወያኔ ደብረሲና እስኪደርስ እና ያንሁሉ ህይወትና ሀብት እስኪያጠፋለምንተጠበቀ? ጦርነቱንስ ‘ወያኔን ከአማራ ና አፋር ክልሎች ሳያስወጣ ለምን አስቆመ? አሁንስ አፋር በወያኔ ዘግናኝ ወረራ ዳግም ሲሰቃይ መንግሥት ለምን ዝምታን መረጠ? ብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ዐማሮች በማንነታቸው ሲታረዱ አንድም ቀን ወጥቶ የሀዘን መግለጫ ሲሰጥ አይታይም። የዘር ጪፍጨፋዉን ለማስቆም ፍላጎትም ሆነ ቁርጠኝነት የለዉም። ለተቃውሞ ሰልፍ ጥሪምክንያቶችም እነዚህ ይመስሉኛል። ባጠቃላይ አብይ የአመራር ብቃቱ አጠያያቂ ነው። ለእነዚህ ትችቶች አባዊርቱ ምን መልስ አለዎት ?

  2. የለምጨኑ አባዊርቱ ጋር ልትጣሉ ነው። ያነሳኸው አጀንዳ አይስማማቸውም ሰው የሚያለቅስባቸው ለሳቸው ጀግኖች ናቸው። ብትችል ታየ ደንዳን፤ ታከለ ኡማን፤አዳነች አቤቤን፤ሽመልስ አብዲሳን፤ሌንጮ ለታን፤ዳውድ ኢብሳን የመሳሰሉትንም አትንካባቸው። አብይ በአማራው እልቂት ጣልቃ አልገባም ማለት ለሳቸው አይመቻቸውም። በተረፈ መልካሟን ኢትዮጵያን ካጣጣሙት መሀል አንዱ ነበሩ ዳሩ ምን ያደርጋል።

  3. ጥያቄ፣ አብይ አህመድ መጨረሻ ላይ መዝመቱ ላልቀረ ወያኔ ደብረሲና እስኪደርስ እና ያንሁሉ ህይወትና ሀብት እስኪያጠፋለምንተጠበቀ?

    መልስ ፣ አቢይ አህመድ ብርቅዬው የኢትዮጵያ ልጅ ከሰራዊትም፣ ከሰው ሀይልም፣ ያልታደለው ነገርዬው አለሱ ቀጥታ ተሳትፎ አለመሆኑን ባለቀ ሰአት ከተረዳስ? አብረውት የተሰለፉት ወይም በስሩ ያሉት ውሽልሽል በዝቶባቸው እንደሆነ ብዬ ልቤ ይጠረጥራል። በሱ ጫማ ገብቶ ማየትን ግድ ይላል ። የጄ/ አበባውም ገለፃ ይኮረኩራል። ሰዎቹ የኢትዮጵያ አምላክ ቆሞልን እንጅ ሸገር አፋፉስ ቢደርሱ ምን ይደንቃል? 45k ጦሩን አይዘንጉት እንጅ።

    ጥያቄ፣ ጦርነቱንስ ‘ወያኔን ከአማራ ና አፋር ክልሎች ሳያስወጣ ለምን አስቆመ? አሁንስ አፋር በወያኔ ዘግናኝ ወረራ ዳግም ሲሰቃይ መንግሥት ለምን ዝምታን መረጠ? ብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ዐማሮች በማንነታቸው ሲታረዱ አንድም ቀን ወጥቶ የሀዘን መግለጫ ሲሰጥ አይታይም። የዘር ጪፍጨፋዉን ለማስቆም ፍላጎትም ሆነ ቁርጠኝነት የለዉም።

    መልስ:

    ማስቆሙን በምን ገመቱ? እስቲ ደጋግመው ጄ/አበባውን ይስሟቸው። የፈረደበት አቢይስ ዖሮሞ ነው፣ የአማራውና አፋሩ ደም አይገደውም ይሁንሎት። ከተባረረበት እመር ብሎ ለናት አገሩ በመከራ ሰአት የቆመውን ቆፍጣና ጄኔራል የተናገሩትን ይስሟቸው በፅሞና። በደርግና ንጉሱ ዘመን ያን ያህል ሜካናይዝድና ለብዙ ዘመናት የተገነባው ድንቁና አስደማሚው የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት የአውራጎዳና ካምፕ ጠባቂ በምታክል 45ሺህ ቁጥር አሳንሰውት ገድለውንና አፈር ለውሰውን ፣ ውስጣችንን አውቀውት በየሚዲያ እየወጡ እየቦረቁብን፣ በአንፃሩ ከመከራ የተረፉት ልጆቻችን ሽንት እየጠጡ ገትረው ይዘው እንደው ትንሽ ትንፋሻቸውን ለመሰብሰብና አስቤዛ ለመሸመት ቆም እንዳሉ ነው ለኔ የገባኝ። አበባውን ያለማጋነን ፣፫ቴ ነው የሰማሁዋቸው። ለአራተኛው ውስጤን ስላመመኝ በይደር ተውኩት እንጅ ። ዝምታ አሉት? እስቲ ምን ዝም የሚያሰኝ ፍላጎት ይኖራል ሰውዬው ህይወቱን ሁሉ ማግዶ በአራቱ ማእዘን ከወገንና ጠላት ግልምጫ፣ የአሜሪካና አውሮፓ መላው አለም ዛቻ እያስተናገደ? ምንስ የፖለቲካ ትርፍ ይኖረዋል ብለው ነው? ሀዘንም ለመቀመጥ እዬዬው ቢደላው አይደለ? ካዝናችን እኮ እርቃኑን ነው ያለው። ሰውዬው ከየወዳጅ መንግስታቱ እርጥባን እየቀፈለ ይቺን መከረኛ አገር በእግር ለማቆም ላይ ታች ይበል ወይስ ጎዝጉዞ ተቀምጦ አብሮን ያልቅስ? የመሪነትን የመከራ ጊዜ ብቃትን በተግባር ያሳየ ድንቅ ወጣት መሪ ለመሆኑ በህይወት ከቆየሁ ከ ሁለት አመት በሁዋላ ይጠይቁኝና አብረን እንደመም ይሆናል። በፈጣሪ ይሁንብዎ አቢይ አይደለም የአፋርና አማራው እልቂት ኢፍትሃዊ የእንስሳት ን ሞት የሚወድ ሰው አይመስለኝም። በተግባር ፅናቱንና ትእግስቱን እያየነው? በጭራሽ! ዝምታ ሳይሆን ግራ ቢገባው ይመስለኛል። ከስሩ ያሉቱ ባብላጫው የተነካኩና የተወሳሰቡ ቀበሮዎችና ተኩላዎች ስለሚበዙ ጊዜና የህዝቡ ንቃት ካላጋለጣቸው በቀር እንደምንስ አድርጎ አጥርቶ ይዘልቀዋል ብለው ነው? የርስዎ ቢጤ ከሳሽ በበዛበት አገር በጣም ጥቂት የአቢይ ቢጤ ሰልፍለስ ዜጎች እንደምንስ አገሪቱን ሊያራምዱ ይችላሉ?

    ጥያቄ፣ ለተቃውሞ ሰልፍ ጥሪምክንያቶችም እነዚህ ይመስሉኛል። ባጠቃላይ አብይ የአመራር ብቃቱ አጠያያቂ ነው። ለእነዚህ ትችቶች አባዊርቱ ምን መልስ አለዎት ?

    የመጨረሻ መልስ

    የአቢይ አመራር ብቃትን ለመገምገም አልሞክረውም። ለምን? በህይወት ዘመኔ አገሬን በቁም ገድለው፣ ንብረቷን ተቀራምተው፣ የራሳቸውን ወገን ህፃናት አፈር አስለብሰው፣ በውጭው ምእራቡ አለም ወጥመድ ውስጥ አስከትተውን እንዳንሞት እንዳንሽር የፊጥኝ አሳስረውን ይህ ሰውዬ አይዟችሁ ወገን፣ አንገት አትድፉ፣ ይቺን የመከራን ዘመን በጋራ እንሻገራታለን ያለና ጭቃ ነክቶ፣ እርፍ ጨብጦ ፣ ሁሉን እንዳመጣጡ እየተቀበለ በፈገግታ አገሬን በዘዴ ሊያሻግር ታች ወርዶን የተቀመጠ ሰው ለመገምገም ድፍረት አይኖረኝም። ከሆነልኝ በገንዘብ፣ ካልሆነም በማይከፈልበት ፀሎት እረዳው ይሆናል እንጅ ጉልበቱስ ከድቶኛል። እናም ወገን የተቃውሞ ሰልፉ ጥሪ ትክክል አለመሆኑን እያደር ይረዱታል፣ ወይም እንዲረዱ ፈጣሪ ይርዳዎ ታድያ ኢትዮጵያዊ ወገን ከሆኑ ነው። የአሉላ ሰለሞን ኢትዮጵያዊ አይደለሁም አይነት ቀላዋጭ ከሃዲ ከሆኑ ግን ጠቅለው አሜሪካ ይቀመጡና የዘረፋችሁትን ገንዘብ እስኪተናነቃችሁ አርፋችሁ ብሉ። ይህው ነው በኔ በኩል።

  4. @Nebeyu, ዳፍንትና ከሃዲ ከየጎሳው አለ:: በጎሳ ማነቆ ተሸብቤም አላውቅም:: በነገር ከሚጎሽሙኝ እንደ “የለምጨኑ” ጥያቄ ወይም አስተያየት አይሻልም ብለው ነው? በነገራችን ላይ አጋጣሚውን ስለማላገኝ እንዲህ ብዬ ልውጣ::መንግስት የፅልመት ሀይል ምርኮኞችን አስሮ ከመቀለብ አማራውና አፋር ግዛቶች አሰማርቶ እያንዳንዷን ያፈረሷትን እንዲገነቡ : በአፋር ደግሞ እስከሚቀጥለው ምርጫ በአፋር በረሃ የመስኖ እርሻ ስምሪት ላይ በማሳተፍ ምርታማነትን እንዲያሳድጉ እመክራለሁ:: ወጣቶችም ስለሆኑ ይለምዱታል:: የሰሩትን በደል በዚህ እንኳ ይክፈሉ:: የትግራይ እናቶችን ፊት ምን ብለው ይሆን የወያኔ ሹመኛ የሚያየው? መቼስ ይህ ጦርነት ይቋጫል አንድ ቀን:: ጨርሻለሁ::

  5. አባዊርቱ ለመልስዎ አመሰግናለሁ። ግን ርስዎም ተገለባባጭና ወገንተኛ ግለሰብ ነዎት -ከዚህ በፊት የፃፏቸዉን ትችቶች በመገምገም አሁን 360 ዲግሪ ሲገለበጡ ሳይ።

  6. እርስዎ ደግሞ ጨለምተኛ ቀጣፊ ነዎት። እስቲ በዘር ውገና አንዲት የፃፍኳትን እዚህ ለጥፈው ያሳፍሩኝ! የለማ! ምን የሚያስገለብጥስና የሚያስቀና ነገር አለና ነው ባገራችን? የፃፍኳቸውን አላዩትም። በግምት ነው። የናንተ የጎሳ ሰንዱቅ ሊከቱኝ በከንቱ አይድከሙ። መልሱ ካልተመቾት መተው እያለ ለምን ይዋሻል?

  7. ለአባዊርቱ የመጨረሻ አስተያየት። ወያኔ ደሴን መያዙ አይቀሬ ነው በዚያ ጊዜ አቢቹ አገር ጥሎ እንደሚፈረጥጥ በግርጌ በኩል ሃሳብ አልሰጡም ወይ። አሁን አቢቹን እንደታምራዊ መሪ ሲስሏቸዉ ይህ መገልበጥ ካልሆነ ተሳስቻለሁ።

  8. ከሌላ የርስዎ ቢጤ ሰው ጋር አማተውኛል። በግርጌ ሆነ በራስጌ ጥንትም አይመቸኝም – የፊት ለፊት ነኝና። እርስዎን የለምጨኑን እመኑኝ ነው? ካልሆነ ለምን እዚህ ፔስት ወይም አታች አርገው ሊንኩን አያቀብሉንምና በስርአቱ ይቅርታ አንጠያየቅም? ፣ ወይስ አባዊርቱ ተመልሶ መጥቶ አይዘኝም ነው? ያሁኑ ይባስ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share