በኦሮሚያ ክልል በጎሀ ፅዮን ከተማ የሚኖሩ በቁጥር 30 የሚሆኑ ዐማሮችና በኦነግ ሸኔ አማካኝነት መታረዳቸው ተነግሯል

“…በኦሮሚያ ክልል በጎሀ ፅዮን ከተማ የሚኖሩ በቁጥር 30 የሚሆኑ ዐማሮችና ኦርቶዶክሳውያን የሰላሌ ሸዋ ኦሮሞዎች በዐቢይ አሕመድና በሽመልስ አብዲሳ ፕላንB የዐማራና የኦርቶዶክስ ማጽጃና ማረጃ ደርጅታቸው በሆነው ኦነግ ሸኔ አማካኝነት መታረዳቸው ተነግሯል።

“…ዐማሮቹ በኦነግ ከመታረዳቸው በፊት መንግሥት የግል መሣሪያ ያላቸውን በሙሉ ነጠቀ። ቀጠለና በከተማ አስተዳደሩ አማካኝነት ሰሞኑን በየታራጆቹ ቤት በራፍ ላይ የቀለም ምልክት አስቀባ። ከዚያም ትናንት ምሽት ግን የታጠቁ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ቀደም ሲል መንግሥት የተለየ ቀለም በቀባባቸው ዐማሮች ቤት በመዞር ሁሉንም ዐማሮች እና የኦሮሞ ኦርቶዶክሶች ለቅመው ይዘው በመውሰድ ዛሬ ሁሉንም እንዳረዷቸው ነው መረጃው የሚያመለክተው።

“…ኦነግሸኔ ተብዬው ቀን ቀን ፖሊስጣቢያ ቁጭ ብሎ የሚውለው ቡድን አሁን በምሽት መጥቶ ንፁሐንን ከማረዱ በፊት በቅድሚያ የኦሮሚያ ፖሊስ ከከተማዋ እንዲወጣ፣ የአስተዳደር ሓላፊዎቹ እንዲወጡ፣ የፀጥታ ክፍሉ ቦታውን እንዲለቅ ከፌደራል መልእክት እንደደረሳቸውና የኦሮሚያ ፀጥታ ሓይሎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ እንደተነገረም ተነግሯል። ብዙዎች በሁኔታው ተደናግጠው የነበረ ቢሆንም የዚህን ያህል የዘር ማጥፋት በመንግሥት ፈቃድ ይፈጸማል ብለው አምነው እንዳልነበረም ነው በስልክ ያነጋገርኳቸው የመረጃ ምንጮቼ የነገሩኝ።

“…አሁን ከጎጃም ወደ አዲስ አበባ የሚሄደው መንገድ ተዘግቷል። አንድም የፀጥታ ኃይል በአካባቢው የለም። ድፍን የከተማው ህዝብ ወጥቶ እያለቀሰ ነው። ገንዘብ አምጡ ተብለው ወደ ጫካ ለኦነጉ ለመስጠት የሄዱትም ሳይታረዱ እንዳልቀረም እየተነገረ ነው። ምንአልባት የዐማራ መንግሥት ቢደርስልን ንገሩልን የሚሉ ዐማሮችና ኦርቶዶክስ ኦሮሞዎች መንገድ ተዘግቶባቸው የቆሙ ሹፌሮችን ሲማጸኑም ታይተዋል።

“…የዐቢይ አሕመድ መንግሥት በፀጥታ፣ ያለምንም ተቃውሞና ኮሽታ ዐማራና ኦርቶዶክስን እያጸዳ ነው። ብአዴን ደንተው አይደለም። ህዝቡም መርዶ መስማቱ የተስማማው ይመስላል። የዐማራ አክቲቪስት በጎጥ ተከፋፍሎ ይጠዛጠዛል። ወገኑ ግን በቀን በፀሐይ እያለቀ ነው። ነገ ተረኛው ከተማ ማን ይሆን?

ተጨማሪ ያንብቡ:  “እኛም ከሚሊዮኖቹ ውስጥ ነን” (የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)

“… ነፍስ ይማር !!

ጀነራልና ፊልድ ማርሻል ተሾሞ ከአዲስ አበባ 100 ኪሎሜትር ገደማ ላይ የኦረሞ ሽፍቶች መንገድ እየዘጉ የንግድና የሰው እንቅስቃሴውን ሲያግቱ፣ መንገደኛ ሲዘርፉና ሲገድሉ ማስቆም እንኳ አልቻለም….

2 Comments

  1. በኢትዮጲያ የሚካሄዱ ዘግናኝ ግድያዎችን ለውጭ ሚዲያዎች በእንግሊዝና የማቅረብ ችግር በኢትዮጲያ መንግስትም ሆነ በግል ሚዲኣዎች ይታያል:: በቲውተርና በሌሎቹ መድረኮች ለተመደ ለአሜሪካና ሃያላኑ መንግስታትና የሰብ አዊ ድርጅቶች የወያኔ ወኪሎች በሚገባ በእንግሊዝኛ ስለሚያቀርቡ ለተፈለገም ለሎቢስቶችም ስለሚከፍል በጉግል ሰርች ቢፈለግ ባብዛኛው ያለው የትግራይ መጎዳት እንጂ በአፋርና ኣአምራ ወገኖች ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ ምንም አይዘገብም:: በአማርኛ ብቻ ማቅረቡ ከራሳችን የማያልፍ ነውና በእንግሊዝና ለአለም ማህበረሰብ ማቅረቡ ይለመድ

  2. ይህን እያየ/እየሰማ ዛሬም አብይን ያሻግረናል ብሎ የሚደግፍ ሰው ነው ግራ የሚገባኝ። ወደ እልቂት እያሻገረን በአይነ ስጋው እያየ። ደጋፊዎቹ የሚሉት “የዚህ አይነት ግጭት በፊትም ነበር። ወያኔ አፍኖ ስለያዘው ነው እንጂ የማትሰማው በፊትም ነበር። ማን ይመስልሃል ይሄን ሁሉ አሁን የሚሰራው? የበፊቱንም ያባባሰው የጁንታው እጅ እንደሆነ አታውቅም? አብይ በብዙ ችግር እኮ ነው የተጠመደው”
    እንግዲህ ሰውዬው ምንም አይነት ጥፋት ሊሰራ የሚችል ሰው አይደለም ማለት ነው። ደጋፊዎቹ እንዲህ ሲያመልኩት ታድያ ስዩመ-እግዚአብሄር ነኝ ብሎ ለምን አይመን።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share