በኢትዮጰያ የነፃነት እና የአንድነት ሰንኮፍ  መነቀል  ያለበት ጊዜ አሁን ነዉ !

በኢትዮጵያ ከዘመነ ጥፋት እና ሞት መባቻ አስካሁን ጊዜ  ድረስ ለዘመናት ድህነት ፣ ስደት ፣ ዉርደት እና ሞት ሀሁ ካለበት ግንቦት ፳ ቀን አስራ ዘጠኝ መቶ ሠማንያ ሶስት ዓ.ም. ጀምሯል፡፡

ግንቦት ፳ ቀን አስራ ዘጠኝ መቶ ሠማንያ ሶስት ዓ.ም

በኢትዮጵያ ሉዓላዊ ዳር ድንበር መደፈር እና ህዝብን ከህዝብ ለይቶ በጠላትነት የመፈረጂ ብሄራዊ ክህደት እና ፍጂት መነሻዉ  ከአስራ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ስምንት የሚነሳዉ የጥፋት ስምምነት ( ት.ህ.ነ.ግ. መደራደሪያ ስምምነት / manifesto) የግልባጭ ፍሬ የአስራ ዘጠኝ መቶ ሠማንያ ሠባት ዓ.ም. ህገ -ኢ.ኃ.ዴ.ግ. የተጠነሰሰበት እና የተተከለበት ጊዜ እንደነበር የሚታስ ነዉ ፡፡

በቅድመ ህገ -መንግስት ( ማንፌስቶ) ሆነ የዚህ ቅጅ  ህገ-መንግስት  ከመተከል እና ከመፅደቅ አንስቶ  የሆኑትን አንኳር ብሄራዊ ፤ታሪካዊ ሁነቶች ሲታዩ  ለአንድ አገር መሰረቱ እና ህልዎቱ ህዝብ /ትዉልድ ነዉ ወይስ አላፊ እና ጠፊ የህግ እና የፖለቲካ ጥቅም ነዉ የሚለዉን ማየት የሚያስችል  ግንዛቤ ከ፫ ስት  አስርተ ዓመታት በላይ ከደረሰ ችግር ለመያዝ አለመቻል፡፡

በግርድፍ በኢትዮጵያ ከህዝብ እና አገር ደህንነት እና አንድነት በላይ ለፖለቲካ ስልጣን እና ተዛማጂ  ጥቅም ማስበለጥ እና ለዚህም ህገ ኢህአዴግን እንደ ዓይነተኛ የሽፋን መሳሪያ መጠቀም ዛሬም የዘመናት ችግሮቻችን ተስፋፍተዉ እና ፋፍተዉ ቀጥለዋል ፡፡

ይህም የችግር እና የመከራ ምንጭ የሆነዉን እና ለአገር አንድነት መጠናከር እና ለህዝባዊ ወገንተኝነት መስፋፋት በተቃራኒ የሆነ ስርዓት እንዲስተካከል  እና ሁሉም ህዝብ የሚወክል ብሄራዊ የህግ እና የህዝብ አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር እና እንዲስፋፋ አለመደረግ ወይም አለመፈለግ ነበር ፤ ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቀነኒሳ በቀለ ያሸነፈበት ቪድዮ - Video

በኢትዮጵያ የ፴ ዓመት የድንግርግር   የመከራ እና የጭለማ ዓማት የሆኑትን  በጨርፍታ ማየት ለአገር እና ህዝብ ክብር እና ጥቅም ከመስራት ይልቅ ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል ጥፋተኝነት እና ብክነት ህጋዊነት ፤ ቅቡልነት ያላቸዉ ይመስላሉ ፡፡ ይኸዉም ፡-

፩) ኢትዮጵያ በዓለም ላይ የራሱ የጠፈጥሮ የባህር በር የነበራት ሉዓላዊ አገር ካለህዝብ እና ያለምን የታሪክ እና የህግ መሰረት የባህር በሯን አሳልፎ የሰጠ የፖለቲካ ዉሳኔ ብቻ መሆን ፣

፪) በዓለም ታሪክ ከትጥቅ ትግል አንስቶ በማዕከላዊ መንግስት ስልጣን  ላይ ከተወጣበት አስከ ስልጣን መገለል ጠላት ብሎ አንድን ማህበረሰብ በማንነት( ኢትዮጵያዊነት- ዓማራ) ማግለል፣ መግደል እና መበደል የትህነግ / ኢህዴግ የፖለቲካ ዉሳኔ እና ያስከተለዉ መዘዝ፣

፫) የ1987 ዓ.ም. ህገ ኢህዴግ ስራ ላይ ከመዋሉ አስቀድሞ ሆነ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ በኢትዮጵያ የአስተዳር ግዛቶች ላይ ተግባራዊ የሆነ ያልተማከለ የክልል አስተዳደር ይህም በግልፅ በኅዝብም ሆነ ቅቡል በሆነ የህግ መሰረት ያልቆ እና የፖለቲካ ኃይል ወይም የቡድን ጥቅም ተጋሩ ጫና የነበረበት እና ያለበት መሆኑ፣

፫) በምዕራብ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር በሚዋሰን የኢትዮጵያ የድንበር ወሰን እና ይህም የታሪክ እና ጠፈጥሮ ምስክር ሆኖ እያለ ለሰዶ ማሳደድ እና ለትዉልድ የሚተላለፍ ቅራኔ በይደር የማዘግየት እና የማዘናጋት ጉዳይ   እና የመሳሰሉት ከህግ እና ታሪክ ዉጭ የአገርን እና ህዝብን ጥቅም የሚጎዱ ናቸዉ ፡፡

እነኝህ እና ዝርዝር ጉዳዮች ሲታዩ በኢትዮጵያችን በህዝብ እና አገር ላይ ያልሆነ ግፍ እና መከራ ቢኖር ከኢትዮጵያ በላይ ቢኖር በሌላ ዓለም ካልሆነ በምድር ላይ ሊኖር አይችልም ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአገር መጥፋትና የአማራ ዘር እልቂት በተረኛው የኦሮሙማ ሰደድ እሳት - ወይራው እርገጤ

ለዚህ ሁሉ የመግደል ሰንኮፉን ከለላ እና ባላ በማድረግ የልባቸዉ የሰሩ እና እየሰሩ ያሉት በጥፋታቸዉ ህዝብን ይቅርታ እንዲሉ እና እንዲጠየቁ የሚያደረግ ቁርጠኝነት ከማጣት ነዉ ፡፡

የአገርን እና ህዝብን ኃላፊነትን ከመወጣት ይልቅ  ከመጉዳት ( ማፈናቀል፣ ማስገደል፣ ድህነት……) በላይ ምን ወንጀል ሊገኝ ይችላል ፡፡

ዛሬም ቢሆን ሠይጣን የማየደርገዉን ክፋት ምቀኝነት በወገን እና አገር ላይ  ዘግናኝ ጥቃት እና ዉርደት የሚያደርሱት መጠጊያ፣ መሸሻ እና ማስፈራሪ ጦራቸዉ ሀዝብን የሚያገል የእነርሱ ህግ ( ህገ-ኢህዴግ) ነዉ ፡፡

ለዚህ ሁሉ በምድር ላይ በአንድ አገር ሉዓላዊነት ጉዳይ ከህዝብ እና አገር ዉጭ ሁሉም ሠዉ ሠራሽ እና ጊዜያዊ ነገሮች የሚቀየሩ እና የሚቀሩ መሆናቸዉ እየታወቀ እና በተለይም በአለፉት ሶስት ዓመታት ከሠላሳ ዓመታት በላይ ለቆየዉ መጠነ ሠፊ የብሄራዊ ግጭት ፣ስደት ፣ሞት እና ሉዓላዊነት አደጋ በዕዉን ገዝፎ እና ዕምነት መንምኖ እየታየ ለዚህ ሁሉ ስር እና መሰረት የሆነዉ የህገ – መንግስት /ህገ-ኢህዴግ እንዲቀር አለመደረጉ ለአገር እና ህዝብ የሚያስብ አለመኖሩን የሚያሳይ ለመሆኑ በዚህ እጅግ ወሳኝ በሆነ ስዓት እንኳን የችግራችን አስኳል ይህ ነዉ የሚል አለመኖር ነዉ ፡፡

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር መንግስት የዕድሜ ልክ መሪዉን አልበሽር ከስልጣን ባስወገደ አጭር ቀናት ዉስጥ ለሱዳን አንድነት እና ለህዝቦች አብሮነት ሲባል የነበረዉን የአልበሽር ህግ( የሡዳን  ህገ መንግስት) እና የፖለተካ ድርጂቱን አግዷል፡፡

ሁለቱም አልበሽርም ሆነ ህወኃጽ  ኢህዴግ  እንደ ብዙ የአፍረካ አገር መሪዎች በመፈንቅለ መንግስት ወታራዊ አገዛዝ መስርተዉ የነበሩ አስከ ሆነ የዕኛ   ቢብስ እንጂ ሊያንስ አይችልም ፡፡ እዚህ ጋ ወታደራዊ አገዛዝ በእኛ አገር  በኢህዴግ አልነበረም የሚሉ ይኖራሉ  መብት ነዉ ፡፡ ነገር ግን ወታደራዊ አገዛዝ ማለት በኃይል ህዝብን በባርነት ፤አገርን በገባርነት ወይም በግዞት ከመያዝ ዉጭ ሌላ ትርጉም ሊኖረዉ አይችልም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  እንኳን ለ128ኛው ዓመት የታላቁ አድዋ ድል መታሰቢያ አደረሳችሁ።

ጨቋኝ  እና አፋኝ አገዛዝ  በጊዜዉ ተራማጂ እና ዲሞክራሲ የሚለዉ ራሱ እንጂ ሌላዉ ሊሆን አይችልም፡፡  ክፉ አገዛዝ ክፍቱ የሚገለጠዉ በተግባሩ እና በቀጣይ ትዉልድ በሚኖረዉ ሚዛን እንጂ በጭለማ ዉስጥ ያለን ስለብርኃን መንገር ከጭለማ ህይወት አያድነዉም ፡፡

የአገር ሠላም ፤ የህዝብ ደህንነት እና ሉዓላዊነት ክብር  የሚያሳስበን ከሆነ ያለምን ቅድመ ሁኔታ እና መዘግየት ዛሬ የጥላቻ ፣ዉድቀት እማ ሞት መንስዔ እና መሠረት የሆነዉን ለያይ ሰንኮፍ ከስሩ መንቀል እና መጣል ጊዜዉ አሁን እና አሁን ነዉ ፡፡

ህግ እና ወግ ሁሉም በአገር ነዉ ፤ አገርም ሠዉ ነዉ ፤ የግለሰብ ነፃነት እና መብት በማይከበርበት ሁለንተናዊ ዕድገት እና አንድነት ዘበት ነዉ ፡፡

 

አንድነት ኃይል ነዉ

ማላጂ

“ኮሶን በኮሶ ” – ማላጂ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share