“ኮሶን በኮሶ ” – ማላጂ

እንደዛሬ ሳይሆን እንደ ትናንትና ፤ታች አምና ስናይ ኢትዮጵያን ለማክሰም ኢትዮጵያዊነት እና አማራ ማንነት ማዉደም ብሎ ጠላት ከጀመረበት አስከ ጥፋት እና ሞት አዋጂ ግንቦት ፳ ቀን አስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ዓ.. ማግስት የህልዉና እና ነፃነት ጥሪ አስቀድሞ የተረዱት የነፃነት እና ህልዉና ሀዋርያት አብሪ ክዋክብቶች ብቅ ብለዉ የነፃነት ፋና ወጊ ሆነዉ አልፈዋል፡፡

ልበ ሙሉ እና ጥበብን ከስብዕና ጋር የተፈጠሩት ገና ከጥዋት የዛሬዎች የኢትዮጵያን አንድነት እና ኢትዮጵያዉያን ነፃነት ለማስከበር ከዕብሪተኞች እና የናት ጡት ነካሾች ከሀዲዎች በሆዳቸዉ ይዘዉ የሽግግር መንግስት ምስረታ ዕለት ጀምሮ በዓማራ ህዝብ ላይ ይደርስ በነበር አድሎ እና መድሎ ከሞት አስከ መፈናቀል /ስደት ያሳሰባቸዉ ፕ/ር አስራት ወ/የስ በግንባር ቀደም የሚጠቀሱ የቅርብ ዘመናት የነፃነት የትግል ፋና ዋጊ ነበሩ ፤ናቸዉ ፡፡

/ር አስራት ወ/የስ በኢትዮጵያ አንድነት ፣ የባህር በር ማሳጣት፣ የዓማራን ህዝብ በተቀነባበረ ዘዴ ማሳደድ፣ መግደል እና ማስገደል ለተዉልድ እና ለአገር ማይበጂ መሆኑን አስቀድሞ በመረዳት እና በማስረዳት የመላዉ ዓማራ ህዝብ ድርጅት በማቆቋም፣ ህዝብን በማንቃት እና ማደራጀት በግልፅ እና በቀጥታ ከፖለቲካ አስከ ፊት ለፊት የኃይል ትግል የጀመሩት ያን ጊዜ ቀድመዉ የኢትዮጵያን ህዝብ በተለይም ግንባር ቀደም የጥቃት ሰለባ የሆነዉን የዓማራ ህዝብ ለህልዉና እና ነፃነት እንዲቆም ፤እንዲታገል የመጀመሪያዉ የህልዉና እና ነፃነት ጥሪ ያስተጋቡ ክቡር ፕ/ር አስራት እና ክብርት ወ/ሮ አልማዝ ኃይለ ማርያም ….የመሳሰሉት ዕንቁ ኢትዮጵያን ነበሩ ፡፡

/ር አስራት የኢትዮጵያ ስጦታ ፣ ብስራት እና ኩራት (አስራት ) መሆናቸዉን ወዳጂ ብቻ ሳይሆን ጠላት የማይክደዉ መራር ሀቅ ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሀይማኖት እና ፖለቲካ በኢትዮጵያ - ሰሎሞን ጌጡ

አስራት የያን ጊዜ ለኢትዮጵያዉያን በተለይም ዓማራ ለቀረበለት “ራስህን እና አገርን ታደግ ” “የህልዉና እና ነፃነት ተጋድሎ ጥሪ ” በሙሉ መረዳት እና ዝግጂት በህብረት እና አንድነት ተቀብሎ ቢሆን በህዝቦች ላይ ከተመከረባቸዉ እና ከተጫነባቸዉ የሞት እና ጥፋት ቀንበር ከጂምሩ ማሽቀንጠር እና መስበር በተቻለ ነበር ፡፡

የአስራትን ትንቢት እና እምቢባይነት አለመቀበል እና አለማስተዋል ዛሬ ህዝብ እና አገር ከግማሽ ክ/ዘመን ያላነሰ የመከራ ዋጋ እና ዘመን ዛሬም እንዲቀጥል ሆኗል፡፡

ዛሬም ከአደዋ የክተት ጥሪ ዕምየ ምኒሊክን፣ ለኢትዮጵያ ዕድገት እና አንድነት ጥሪ ዐፄ ቴወድሮስን፣ ዕምቢ ለአገሬ ፤ለነጻነቴ ..ደጃች በላይ ዘለቀን ፣ የናት አገርን ዳር ድንበር በመቁረስ/ በማፍረስ፣ ህዝብ በባርነት ለማስተዳደር፣ ለማስለቀስ በሚቆቋም…..ስመ መንግስት ምስረታ መሳተፍ ታሪካዊ እና ትዉልድ ይቅር የማይለዉ ክህደት ነዉ ያሉትን ፕ/ር አስራት ወልደ የስን እና መሰሎቻቸዉን ዛሬ ላይ ሆነን ኢትዮጵያን ከኋላ እና ወደፊት ለምንመለከት የህልዉና እና ነጻነት ጥሪ ምንጊዜም ሳንረሳ ሊወሳ ይገባል፡፡

/ር አስራት በወቅቱ የህወኃት / ኢህዴግ መንግስት ሲመሰረት በክህደት እና በጥፋት ህብረት መሳተፍ ሞቶ እንደ መኖር በመቁጠር ዕምቢ ባይነታቸዉን በተግባር ያረጋገጡ ታሪክ እና ትዉልድ ዝንተ ዓለም የሚዘክራቸው ይሆናሉ ፡፡

የዛሬዉን ብሄራዊ ህልዉና እና ነጻነት ተጋድሎ ክተት ጥሪ ያን ጊዜ ከነኝህ ዕንቁ ደማቅ ባለ ራዕይ ታላላቅ ዋኖች አደራ ዛሬ ማደስ እና ለጋራ ህልዉና እና ነጻነት በአንድነት እና ህብረት መቆም አለብን ፡፡

በእኛ ዘመን የራሱን አገር እና ህዝብ ጥቅም እና መብት አሳልፎ ለጠላት የሸጠ ስመ መንግስት ህወኃት / ኢህዴግ ህግ፣ ህገ መንግስት፣ ስነ ዜጋ ፣ ግብረ ገብነት …..እያለ ህዝብን እና አገርን ማስፈራሪያ እና መጠፈሪያ ከማድረግ ዉጭ ይህን አምኖበት ሁሉን ለማድረግ ያስቻለዉ ጉልበት እንጂ ሌላ አልነበርም ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዝርው ዓመፃ እና ከዋናው ጉዳይ የተናጠበ ጽሑፍና ንግግር - ከይኄይስ እውነቱ

ለዚህም ነበር ፕ/ር አስራት አስቀድመዉ ለሆዳም በሬ ….ያዝዙለታል የሚለዉን ዕዉነተኛ እና ሁነኛ ኢትዮጵያዊ ብሂል በመረዳት ኮሶ እንዲሽር “ኮሶ ን በኮሶ ” ብለዉ ራሳቸዉን ለህዝብ ነጻነት እና ለአገር ህልዉና ሲሉ ጥርስ ዉስጥ ሲያስገቡ የኃይል ትግል ነበር ፡፡ ይህም ዕዉነተኛ እና ትክክለኛ ህልዉና እና ነፃነት ዕዉን የሚሆነዉ በኃይል ሚዛን ብቻ ነዉ ፡፡ ምንጊዜም ዓለም ከአሸናፊዎች ጋር ናት ፡፡ አሸናፊነትም የኃይል ፍሬ ነዉ ፡፡

ማላጂ

አንድነት ኃይል ነዉ”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share