በአፋር ክልል የሚገኙት መጋሌ እና አብአላ የተባሉ አካቢዎች በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ገቡ

DW
ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
+

በአፋር ክልል የሚገኙት መጋሌ እና አብአላ የተባሉ አካቢዎች በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ሥር መግባታቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ። የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አሕመድ የአብአላ ከተማ በህወሓት በሚመራቸው ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር መግባቱን መረጃ እንደደረሳቸው ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ ሰኞ ባወጣው መግለጫ ኪልበቲ በተባለው ዞን አብአላ እና መጋሌ ወረዳዎች በኩል ህወሓት ጦርነት እንደከፈተ ገልጿል። የአፋር ክልላዊ መንግሥት በከባድ መሣሪያ የታገዘ ባለው እና በአብአላ፣ በመጋሌ እና በበራህሌ በኩል በሚካሔደው ጦርነት “በርካታ ንፁሀን” መጎዳታቸውን በፌስቡክ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርነት ማቆሙን ካሳወቀ ጀምሮ ቂልበቲ ረሱ ተብሎ በሚጠራው ዞን ሁለት አካባቢ በሶስት ወረዳዎች ጦርነት ሲካሔድ እንደቆየ የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አሕመድ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

አቶ ጋአስ የአብአላ ከተማ በዛሬው ዕለት በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ሥር መግባታቸውን የሚጠቁም መረጃ እንደደረሳቸውም ገልጸዋል። እስካሁን ድረስ በህወሓት ተያዘ ስለተባለው አባላም ሆነ ስለደረሰው ጉዳት የኢትዪጵያ መንግሥት የሰጠው መግለጫ የለም።

ህወሓት በአብአላ በኩል በከፈተው ጥቃት ምክንያት ለትግራይ ሕዝብ ሰብዓዊ ዕርዳታ ይዘው ወደ መቀሌ እየተጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ኋላ መመለሳቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አሰታወቀ።

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሠላማዊት ካሣ ማምሻውን ለአሜሪካ ድምፅ እንዳሉት ህወሓት ጥቃት የከፈተዉ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት በአካባቢው በሌለበት ሁኔታ ነው ብለዋል።

ጉዳዩን አስመልክቶ ቀደም ሲል በትዊተር ገፃቸው ላይ የጻፉት የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው “ከሰመራ ታጅበው ወደ ትግራይ ሊገቡ ነበር” ተብሎ የተነገሯቸው ሰብአዊ ዕርዳታ የጫኑ የዓለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም 27 የጭነት መኪኖች ወደ መቀሌ እንዳይገቡ ተደርገዋል ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቀነኒሳ በቀለ ያሸነፈበት ቪድዮ - Video

በሌላ በኩል የህወሓት ኃይሎች በስድስት የአፋር ግምባሮች ከትናንት ጀምረው ከባድ ጦርነት መክፈታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ አስተያየታቸውን የሰጡ የአፋር ክልል ነዋሪ ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share