በኢትዮጵያ ለዘመናት የዜጎችን ሞት እና የአገር ክህደት ሲያስተናግድ የነበረዉን የግፍ ስርዓት ዕድሜ ለማራዘም ሲባል የኢትዮጵያን እና ህዝቧን የመከራ መጠን እና ዘመን የሚያራዝም መዉዘምዘም ምንም ሊባል የማይችል የኢትዮጵያን ዉድቀት እና ዜጎች ሞት ዕርደ ከል ለማስቀረት የሚደረግ ይመስላል፡፡
ለመሆኑ የኢትዮጵያዉያን የዓመታት ቀዉስ እና ህዝባዊ ዕሮሮ ማበስ የሚቻለዉ በህዝባዊ እና ሠባዊ ሚዛን በመለካት እንጂ ምን ይመጣል ማለት ብሄራዊ እና ህዝባዊ ክህደት ላለመሆኑ ማንም የ፴ ዓመት ወይም ግማሽ ምዕተ ዓመት የተገለሉ ፣ የተገደሉ ፣ የተታለሉ፣ የተሳደዱ እንዲሁም ዕልግ አዕላፉ ኢትዮጵያዉያን በአገራቸዉ ሞት ፣ስደት እና ዉርደት ከደረሰባቸዉ እና ከደረሰበት በላይ ማንም ምን ሊል የግብረ ገብነት ወይም የሌላ ልዕልና ቁመና ሊኖረዉ አይችልም፡፡
ለመሆኑ የአገር እና የህዝብ ሞት ዋጋ ስንት እንደሆን ካለወቅን አገር እና ህዝብ ከዉድቀት መታደግ እንዴት ይቻል ይሆን ?
በኢትዮጵያ ከደረሰ ብሄራዊ ጥፋት ፣ክህደት ፣ የዘር ፍጂት ፣ ድህነት ፣ ስደት …..ማን ነዉ ተጠያቂ ….፡፡
ጠያቂ እና ተጠያቂ በሌለበት እንዴት ዘላቂ እና አመርቂ መግባባት፣ ዕድገት እና ሉዓላዊነት ሊመጣ ይችላል፡፡
በኢትዮጵያ ቀርቶ በዓለም ታይቶ ለማይታወቅ በራስ አገር እና ህዝብ ላይ ለደረሰ መጠነ ሠፊ መከራ እና አሳር በዳይ እና ተበዳይ በዉል ሳይለይ ምራቅ ሳይደርቅ እንደ ጨርቅ እንደሚቀደድ እንዲሁም የጥላቻ እና ሞት ጥቁር መጋረጃ ጨርቅ ሳይቀደድ መግባባት እንዴት እንደሚቻል ከማሰብ ይልቅ ማወሳሰብ ለህዝብ ነጻነት እና ለአገር ሉዓላዊነት የተከፈለዉን ፴ ዓመታት የህይወት ፣ደም ፣ አጥንት እና ሁለንተናዊ ዋጋ ከማሳነስ እና ከማድበስበስ ያለፈ አለመሆኑን ምንም ማስረጃ ሆነ አስረጂ አይጠበቅም ፡፡
ማላጂ
“አንድነት ኃይል ነዉ ”