በእነ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው 62 ግለሰቦች ክሳቸው እንዲነሳ መደረጉን አስታውቋል

የፍትህ ሚኒስቴር ዛሬ አርብ ታህሳስ 29 ምሽት ባወጣው መግለጫ፤ በእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ስር ያሉ 20 ተከሳሾች እና በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ስር ያሉ አራት ተከሳሾች ክሳቸው እንዲነሳ መደረጉን አስታውቋል። የተከሳሾቹ ክስ እንዲነሳ የተደረገው “ሃገራዊ የምክክር መድረክ ሂደት ውጤታማነት እና አካታችነት ከፍ ለማድረግ በማሰብ” መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በእነ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው 62 ግለሰቦች እና ድርጅቶች ውስጥ የስድስት ግለሰቦች ክስ እንዲነሳ መደረጉን ሚኒስቴሩ በዛሬ ምሽት መግለጫው ጠቅሷል። “የጤና እና የዕድሜ ሁኔታቸውን ከግምት በማስገባት” ክሳቸው እንዲነሳላቸው የተደረጉት አቶ ስብሐት ነጋ፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ አቶ ዓባይ ወልዱ፣ አቶ አባዲ ዘሙ፣ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር እና ወ/ሮ ኪሮስ ሐጎስ ናቸው።
በእነ ጃዋር መሐመድ እና ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል መዝገብ የተካተቱ ተከሳሾችን ማንነት ለመመልከት ከታች የተያያዙትን ምስላዊ መረጃዎች ይመልከቱ።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
ተጨማሪ ያንብቡ:  ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በፕላዝማ ስልጠና እየተሰጠ ነው

1 Comment

  1. ያሳዝናል ምን ዲስኩር ሊሰጠን ነው ከዚህ በሗላ ለትግሬ ወንጀለኞች ስድ ልብ እንዳለው ብናውቅም አሳዳጊዎቹ በመሆናቸው በዚህ ልክ ይወርዳል ብለን አልገመትንም ነበር የፈለገው ቢጎነበስላቸው የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ መልሰው እንደ በሉት ቁርጥ ነውና ጥያቄው ካሁን በሗላ የኢትዮጵያ መከላከያ ሀይል ይታዘዘዋል ወይ? ከኢሳይያስ ጋር ያለው ግንኙነት ይቀጥላል ወይ? አብይ ሆይ ስራህ ያውጣህ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share