እስክንድር፣ ጃዋር፣ በቀለ ገርባና ስብሃት ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ የነበሩ የፖለቲካ መሪዎች በምህረት ተፈቱ

eewww
መንግሥት በእነ እስክንድር ነጋና ጃዋር ሲራጅ መሐመድ መዝገብ የተከፈቱትን እንዲሁም የእነ ስብሃት ነጋን ክሶች እንዲቋረጡና በምህረት እንዲፈቱ መወሰኑን ተከትሎ እስረኞቹ 271587518 6784535434951938 7101932089793020034 nከማረሚያ ቤት እንዲወጡ ሆኗል፡፡
ከእሥር በምሕረት እንዲፈቱ የተወሰነላቸው
1. አቶ ስብሐት ነጋ
2. ወሮ ቅዱሳን ነጋ
3. አቶ ዓባይ ወልዱ
4. አቶ አባዲ ዘሙ
5. ወ/ሮ ሙሉ ገብረእግዚአብሔር
6. አቶ ኪሮስ ሐጎስ
7. አቶ ጁሐር ሲራጅ መሐመድና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ
8. አቶ እስክንድር ነጋና በእርሱ መዝ
ታኅሣሥ 29/2014 (ዋልታ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  Ethiopia, Famine and the Oxford Dictionary

1 Comment

  1. ይህቺ ናት የፓለቲካ ቀልድ። አይ ሃገር። የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ ይሉሃል ይሄ ነው። ከበፊት ጀመሮ የሃበሻው ፓለቲካ የገበጣ ጫወታ ነው የምንለው በሂሳብ እንጂ ሂሳብ ለማወራረድ እዳ ኖሮብን አይደለም። አይገርምም የስበሃት ነጋና ተከታዪቹ መፈታት? ጀዋር አደረገ የተባለው በጊዜው የተናፈሰ በመሆኑ መድገም አያስፈልግም። እኔ በመፈታቱ ችግር የለብኝም። ግን የጅዋርን መታሰር ማጣጫ እንዲሆን የታሰረው እስክንድር ነጋ ጉዳይ ግን በፊትም ያለፍትህ ስለሆነ ፍቺው አከራካሪ አይሆንም። የጃዋር ተባባሪና በጠባብ ብሄርተኝነት ስሜት የሚናውዘው በቀለ ገርባ ወያኔ ጠፍሮ ዘብጥያ ሲያወርደው ” ደምህ ደሜ ነው” በማለት የጮኽለት ያ የአማራ ህዝብ አሁን በወያኔ የደረሰበትን ሰቆቃ ሂዶ ቢመለከት ምን ይለን ይሆን? እኔ ጀዋርን ሆነ በቀለ ገርባን የዘር ጥሩንባ ነፊ ይሆናሉ ብዬ ገምቼ አላውቅም ነበር እያደሩ ግን እይታቸው ሸውራራ እየሆነ ሂዶ ለመታሰር ዳርጓቸዋል። አሁን የጠራ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ብሎም ሃገራዊ እይታ ይኖራቸው ይሆን? ቆይቶ ማየት ነው።
    የተለቀቁ ሰዎችን የስም ዝርዝር ልብ ብሎ ለተመለከተ ለጠ/ሚር አብይ በውጭ ሃይሎች የቀረበለት የስም ዝርዝር እንጂ ፍትህና ርትዕን ተከትሎ የተደረገ ምህረት አይደለም። ስንቶች ናቸው በሌሎች አካባቢዎች ባልሰሩት ስራ ታጉረው እየተሰቃዪ ያሉት። ሰብሃት ነጋን የመሰለ የግፍ ሰው የፈታ መንግስት ለምንድን ነው አቶ በረከትንና በጄ/ አሳምነው ጽጌ ግድያ ያለምንም ፍትህ እስር ቤት ያሉትን የማይለቀው? የሃገሬ ሰው ያልሞተ ሰው ይላል። እንዲህ ያለ ጉድ ለማየት ነው። ወያኔ መቀሌ ላይ ሆኖ እየተንፈራገጠ እልፎ ዘርፎ፤ አፍርሶ፤ ገድሎ አሁን ምን የሚሉት የሰላም ጡርንባ ነው አብይ የሚነፋው? ይብላኝ ለድሃው ሰው በሜዳ ለቀረው፤ ለወሎ፤ ለጎንደር፤ ለአፋርና ሽዋ እንዲሁም ለትግራይ እናትና አባቶች። ለነጩ ዓለም እንኳን እስረኛ መፍታት ቀርቶ በጉልበትህ ተጎብሰህ ብትሄድ ሃገር ከማፍረስና አዘናግተው የመንግስት ግልበጣ ከማድረግ አይመለሱም። የኢራን ታሪክ ዋንኛ ማሳያ ነው።
    ሲጀመር የጠ/ሚሩ የቃላት ጋጋታ ሰው ያደክማል። ሰው በትንሹ ተናግሮ በትልቁ ይሰራል። በሃገሪቱ ላይ ቃላት በቅሎ ስንዴ ይሆን ይመስል ለፍላፊ በዝቷል። የተማሩትም ሙያቸውን ትተው በየመድረኩ ማይክሮፎን በመያዝ እኔን ስሙኝ የሚሉ ጅሎች ሆነዋል። የሚናገሩትና የሚያደጉትን ተግባር ለመዘነ ግን የተዛባ ነው። የወያኔን ሰዎች ለዚያውም መሪውን አቶ ስብሃትና ዘመዶቹን ፈትቶ ጌታቸው ረዳንና ሌሎችን እጅ ስጡ ማለት ቂል መሆን ነው። በዚህ ሁሉ እሰጣ ገባ በየክልሉ የአማራን ቤት አቃጣዮችና ከክልላችን ውጡልን የሚሉት የብሄር ሰካራሞች በሚያደርሱት ግፍ ዛሬም ነገም የአማራ ህዝብ ፍዳውን እያየ ነው። ከእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንዲሉ ወያኔ ሽዋ ሮቢት ድረስ ገብቶ የአማራንና የአፋርን ክልል ሲያበራይ ሰራዊቱ የት ነበር? ግን አማራን ለማስጎበስ ሆን ተብሎ የተደረገ ሴራ ለመሆኑ አሁን ግልጽ እንደሆነ ይታያል። የዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን መውጣት ለኢትዪጵያ ብርሃንን ሳይሆን ጨለማንና መተላለቅን ነው ያመጣው። አሁንም ቢሆን እልፍ ወያኔ ቢፈታ፤ አሜሪካም ሆነች ሌላው እንዲህና እንዲያ አድርጉ እያሉ እጅ ቢጠመዝዙ ወያኔና ኦነግ ሸኔ ሌሎችም በዋሽንግተን መሪነት በሱዳን በኩል እየተዘጋጅ ያሉት ሃገራችን ከማመስ ወደ ኋላ አይሉም። ይህ ተግባር ሰላምን የሚያመጣ ሳይሆን ለወያኔ የልብ ልብ የሚሰጥ፤ ወያኔን ሲፋለሙ የሞቱና የቆሰሉ የተፈናቀሉ ወገኖችን እንባ ያቃለለ ነው። አሁን ማን ይሙት በቅርቡ የታፈኑትና እስርቤት ያሉት ጋዜጠኞች ከስብሃት ነጋ የላቀ በደል ፈጽመዋል? ፍትህ በሃበሻ ምድር የለም። ከዘመን ዘመን የምናየው ይህን ነው። የአሁኑም የምህረት ጋጋታ ደመናና ጭጋግን አምጪ እንጂ ሰላምን አያመጣም። በቃኝ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.