January 7, 2022
32 mins read

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የኖቤል የሰላም ሽልማትን ያጽድቁ ወይም ይሻሩ

በአፍሪካም ሆነ በአለም ዙሪያ ያሉ ንቃተ ህሊና ያላቸው ሰዎች በአፍሪካ መሪዎች ላይ የሚደረግ አይን ያወጣ የማቃለል/የማናናቅ ፍረጃን ከሹክሹክታ ባለፈ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ማጉላት አለባቸው ሲሉ ዮናስ ብሩ ይጽፋሉ።

Abiy 3ጽሁፍ: ዮናስ ብሩ
ትርጉም: መስከረም ባልከው

በቅርብ ጊዜ ትውስታ የአለም አቀፍ ሚዲያዎችን ፣ የአለምአቀፍ ጥናትና ምርምር ተቋማት ከፍተኛ ቁጣን እና የተባበሩት መንግስታት፣ የአውሮፓ ህብረት እና የአሜሪካ ባለስልጣናትን ነቀፋ እንደ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር (ጠ/ሚ) አቢይ አህመድን ያሰተናገደ ሌላ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ የለም።

ዋሽንግተን ፖስት የሰላም ሽልማቱን ለጠቅላይ ሚኒስትር (ጠ/ሚ) አቢይ አህመድን ለመስጠት መወሰኑን “የዓለምን ታዋቂ ሽልማትን ማቆሸሽ ” ሲል ገልጾታል ነበር።ሲ ኤን ኤን በበኩሉ አለም እንዴት ለ”በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ውስጥ የተገለለ” ሰው ተታለለች ሲል፣ ዘ ጋርዲያን ደግሞ ጉዳዩን ይበልጥ በማጋጋል፣ ፣ጠ/ሚ አብይ አህመድ በትግራይ ፈጽመዋል በተባለው ግፍ “የኖቤል ሽልማት ኮሚቴው ከስልጣን እንዲነሳ” ሲል ጠይቋል።

እንደ አሜሪካን ኢንተርፕራይዝ ኢንስቲትዩት እና ናሽናል ወርልድ ሴንተር ያሉ የምክረ ሃሳብ አፍላቂ የባለሙያዎች ሰብሰብ ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን “የኖቤል የሰላም ሽልማት ማፈሪያ” ብለው ሲስላቸው፤የዓለም የሰላም ፋውንዴሽን ደግሞ፣ “ረሃብን እንደ ጦርነት መሣሪያ የተጠቀመ” ሲል ከሷቸዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሃፊ “ፆታዊ ጥቃትን እንደ ጦርነት መሳሪያነት እንደዋለ ምንም ጥርጥር የለንም” ሲሉ፤ ሌላ ስማቸው ያልተገለጸ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣን ፣ጠ/ሚ አብይ አህመድ ረሃብን “ህዝቡን/ትግራይን ለማንበርከክ አልያም ከህልውና ውጭ ለማድረግ”ተጠቅመውበታል ሲሉ ተናግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ሴናተር ፓትሪክ ሌሂ፣ ይኸን ከቁጥጥር ውጭ የወጣ የውንጀላ ማእበልን በማባባስ፣ “በትግራይ ውስጥ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እና የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመ ነው” ሲሉ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በበኩላቸው ስለ “እየተካሄደ ያለ የዘር ማፅዳት” ተናግረዋል። የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ደግሞ ጠ/ሚ አብይን “ትግራይን ለ100 ዓመታት ለማጥፋት እቅድ አውጥተዋል” ሲሉ ከሰዋቸዋል።

ሆኖም ግን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮምሽን የጋራ የምርመራ ሪፖርት፣ “ሆን ተብሎ ወይም ታቅዶ/ተፈልጎ በትግራይ በሚኖሩ ሲቪሎች ላይ የሰብአዊ እርዳታ መከልከል ወይም ረሃብን እንደ ጦርነት መሳርያ መጠቀሙን ማረጋገጥ አልቻለም”ይላል። የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባቼሌት፣ መርማሪዎቹ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል ብሎ የሚያሳይ ማስረጃ አላገኙም ብለዋል። በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት የስነ ህዝብ ፈንድ ባለስልጣናት፣ አስገድዶ መድፈርን እንደ ጦርነት መሳሪያ በመጠቀም ተብሎ የቀረበውን ውንጀላ እንደ “በሚዲያ የተጋነነ ማስታወቂያ” እና “በጣም ስሜት ቀስቃሽ” በማለት ገልጸውታል። እንደ አለመታደል ሆኖ ግን፣ እውነታው፣ አሜሪካንን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ከመጣል እንዲሁም 115 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በጣም የሚያስፈልጋቸውን ዓለም አቀፍ ዕርዳታ ከመንፈግ አላገዳትም።

የዚህ ጽሁፍ አላማ ጠ/ሚ አብይ አህመድንም ሆነ መንግስታቸውን ለመከላከል ሳይሆን በአፍሪካ መሪዎች ላይ የሚፈጸሙ ተገቢ ያልሆኑ ስልታዊ ጥቃቶችን አጉልቶ ለማሳየት ያለመ ነው። በጠ/ሚ አብይ አህመድ ላይ የተሰነዘረው በማሰረጃ ያልተደገፈ ውንጀላ እና የተጣለው የኢኮኖሚ ማዕቀብ አስከፊ መዘዞች ያስከተለ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በዋናነት፣ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ “ለብዙ ዜጎች የተሻለ ህይወት እና ብሩህ የወደፊት ተስፋ የሚሰጡ ጠቃሚ ማሻሻያዎች” ብሎ ለሽልማቱ መሰረት ያደረጋቸው ጉዳዮችን ዋጋ ያሳጣ መሆኑ ነው።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ፣ በኢትዮጵያ መንግሰት ላይ ከባድ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች የማጣራት ውሳኔን ባሳለፈበት ወቅት ከ28ቱ የአፍሪካ፣ የእስያ እና የመካከለኛው ምስራቅ ታዳጊ ሀገራት 26ቱ ውድቅ ያደረጉበትን ወይም ድምጸ ተአቅቦ ያደረጉበትን ምክንያት አለም አቀፉ ማህበረሰብ በቸልታ ሊያየው አይችልም/አይገባም። የተባበሩት መንግስታት እና የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ባለስልጣናት በጠ/ሚ አህመድ ላይ በእጅጉ የተጋነነ ውንጀላ ሲሰነዝሩ መቆየታቸውን ከግምት ውስጥ ላሰገባ የመንግስታቱ ድርጅት በአውሮፓ ህብረት ጥያቄ መሰረት እያሰባሰበ ያለው የምርመራ ኮሚሽን ላይ እምነት ለመጣል በእጅጉ ያዳግተዋል።

አብዛኛውን ጊዜ በአፍሪካ መሪዎች ላይ ተለይተው የሚሰነዘሩ አስከፊ ትችቶች/ነቀፋዎች ተፈጥሮ እና ይዘት፣ ተፈጸመ የተባለውን ውንጀላ ለማጣራት ከተለመደው ወጣ ያሉ እርምጃዎችን ይፈልጋል። ስለዚህ የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ ህብረት የውንጀላውን ትክክለኛነት (ወይም አለመፈጸሙን) የሚያጣራ ኮሚሽን በጋራ መሰየም አለባቸው። የተባበሩት መንግስታት ጥያቄውን ውድቅ ካደረገ የአፍሪካ ህብረት ብቻውን ማድረግ አለበት።

የምርመራው ውጤት የዘር ማጥፋት ውንጀላ ወይም ሆን ተብሎ አስገድዶ መድፈርን እና ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያነት ተጠቅመዋል የሚል ድምዳሜ ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል የሰላም ሽልማትን መመለስ ፣ህዝብን ይቅርታ መጠየቅ እና የሚደርሰባቸውን ቅጣት መቀበል ይሆናል። በሌላ መልኩ ምርመራው የክሱን ሀሰትነት ካረጋገጠ፣ ውንጀላውን ያቀነባበሩት አካላት በሙሉ በህግ መጠየቅ አለባቸው።
የጦርነቱ መንስኤ እና ባህሪ

በጠ/ሚ አብይ አህመድ መንግስት እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሀት) መካከል የተፈጠረው ግጭት በከፊል በኢኮኖሚ ልማት ርዕዮተ ዓለም ልዩነት የተነሳ ነው። በህወሓት የ27 ዓመታት የግዛት ዘመን ኢትዮጵያ የሶሻሊስት የኢኮኖሚ ሥርዓትን ትከተል ነበር።የአሜሪካን የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን እንደተናገሩት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ “ተሰፋ ሰጪ የኢኮኖሚ እና የዴሞክራሲ ማሻሻያ መርሃ ግብሮችን አስገብተዋል/አሰተዋውቀዋል፣ እንዲሁም ተቁባይነት ያጡትን የማርክሲስት ፅንሰ-ሀሳቦችን በቆራጥነት ውድቅ “አድርገዋል”።

አንድ ታዋቂ የኦክስፎርድ የኢኮኖሚ ልማት ፕሮፌሰር በፋይናንሺያል ታይምስ ላይ ሲጽፉ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ማሻሻያዎች በመላው አፍሪካ “ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ሊያቀጣጥል ይችላል” ሲሉ ጠቁመው የነበረ ስሆን እንደ ፍራንስ 24 ያሉ ከደርዘን በላይ አለም አቀፍ ሚዲያዎችም ማሻሻያዎቹ “የአገሩን ማህበረሰብ ሁለንተና ከፍ ከማድረግ ባለፈ ድንበሮችን ተሻግሮ ለውጦችን የመቅረጽ አቅም አለው”ሲሉ ተመሳሳይ ሀሳብ አስተጋብተው ነበር።

እንደ አለመታደል ሆኖ ግን፣ ህወሓት “ልማታዊ መንግስት” ከሚለው የሶሻሊስት አስተሳሰብ “አንድ ስንዝር”ፈቀቅ” ለማለት ፈቃደኛ አልሆነም። ህወአት ጦርነት ጅማሮ መነሾም “ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመጣል” እና “የስልጣን እና የገንዘብ ሰጪእና ነሺነትን ” ስልጣን መልሶ ለመቆጣጠር ያለመ ነበር። ህወሃት “ልማታዊ መንግስትን” ለ27 ዓመታት ለመቆጣጠር መቻሉ፣ መሪዎቹ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር መንገድ 30 ቢሊየን ዶላር ወደ ውጭ ሃገር ባንኮች እንዲዘዋወሩ ያስቻላቸው የሀብት ምንጭ ነበር።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመጉ) በጋራ ያደረጉት ምርመራ ግኝት “በሰሜን እዝ ላይ በህዳር 3፣2020 የተፈጸመው ጥቃት፣ በደንብ በተዘጋጀ እና በተጠና እቅድ ኢትዮጵያ እንድትበታተን እና ታላቋ ትግራይ የበላይ ሆና የምትነግስባቸው በርካታ ትንንሽ ነፃ ወይም ነፃ መሰል መንግስታት የመተካት የመጀመሪያው እርምጃ ብቻ ነበር ይላል። “

የህወሓት ባለስልጣን የነበሩት ሰኮቱሬ ጌታቸው ፓርቲያቸው በኢትዩጵያ መንግሰት ላይ የከፈተውን ጦርነት “በፌዴራል ሃይሎች ላይ ውዥንብር ለመፍጠር እና ለማፍረስ” የተፈጸመ “መብረቃዊ ጥቃት” ሲሉ ገልጸውታል። አያይዘውም “ከጥቂት የመከላከል ጥረቶች በሰተቀር ቁጥሩ 30,000 የሆነ ወታደር እና ከ70 እስከ 80 በመቶ የሚሆነውን የአገሪቱን ወታደራዊ ሃይል ያቀፈውን መላውን የሰሜኑ እዝ በኛ ቁጥጥር ስር ለማድረግ ችለናል ብሎ ነበር።” ብዙም ሳይቆይ የትግራይ ክልል ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድን መንግስት “ህጋዊ አይደለም” በማለት እንዲፈርስ ጠይቀው ነበር።

ግልጽ ባልሆነ መንገድ፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሃፊ ማርክ አንድሪው ሎውኮክ (2017-2021) ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድን “ጦርነትን መርጠዋል” እና “መሰረቱ የፖለቲካ ክርክር የሆነውን ግጭት ለመፍታት የፌደራል ወታደሮችን ወደ ትግራይ ልከዋል” ሲሉም ከሰዋል። እውነተኛና ገለልተኛ የሆነ አጣሪ አካል ብቻ ግልጽ ሊያደርገው በሚችለው ምክንያት የተነሳ የተባበሩት መንግስታት ፣ የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ ፣የአውሮፓ እና አሜሪካ ሚዲያዎች ፣ አሜሪካ ቀደም ሲል በደረጃ ሶስት አሸባሪ ብላ ከፈረጀው ፓርቲ ከህወሓት ጎን በመቆም አንድ ግንባር ፈጥረዋል።

የኖቤል የሰላም ሽልማት ውዝግብ

ጠ/ሚ አብይ በኖቤል ሽልማት አቀባበል ስነስርአት ላይ ያደረጉት ንግግር በተለይ በሁለት ጭብጦች ላይ ያተኮረ ነበር፦ የጦርነት ሁከት የገሃነም ምሳሌ እና የሰላም ታላቅነት የደህንነት እና የብልጽግና መሰረት መሆንን ነው ነበር። እንደ እጣ ፈንታ ሆኖ ፣ በሽልማት መቀበያ ወቅት ያደረጉት ንግግራቸው “የሰላም ህልም በአብዛኛው ወደ ጦርነት አስፈሪ ቅዥት ይቀየራል” በማለት የገለጽት ስጋት እ ኤ.አ ህዳር 3 ቀን 2020 እውን ሆኗል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የነበራቸው ምርጫ በሁለት አጣብቂኝ መካከል ነበር፡- ለህወሓት እጅ መስጠት ወይም በህወሓት ላይ ወታደራዊ ዘመቻ መክፈት። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከአገር ውስጥ እና ከውጭ ጠላቶች ለመከላከል ቃለ መሃላ በመፈጸማቸው ለሕወሃት እጅ መሰጠት የማይታሰብ ነበር። እጅ መስጠት ማለት ደግሞ ወያኔን ለማስወገድ ለሶስት አመታት በተካሄደው አገራዊ ትግል ወቅት የተሰው/ህይወታቸው ያለፉ ኢትዮጵያውያንን መክዳት እና የተጀመረውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማሻሻያ መቀልበስ ማለት ነው። በህጋዊ ሆነ በሥነ ምግባር ደረጃ የነበረው ብቸኛ ምርጫ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ማስከበር ብቻ ነበር።

ዓለም አቀፍ አበላላጭ መመዘኛ/ደረጃ

የጠ/ሚ አብይ የሰላም ፍላጎት እና የጦርነት የማወጅ ግዴታ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እ.ኤ.አ.2009 የየኖቤል የሰላም ሽልማት በተቀበሉበት ወቅት ያደረጉት ንግግራቸው በደንብ ይገልጸዋል። ኦባማ ንግግራቸውን ያደረጉት የታሊባንን እንቅስቃሴ ለመቀልበስ 30,000 የአሜሪካ ወታደሮች ወደ አፍጋኒስታን እንዲገቡ ካዘዙ ከዘጠኝ ቀናት በኋላ ነበር። ፕሬዝዳንት ኦባማ በወቅቱ እንዲህ ብለው ነበር፦

“አገሮች የኃይል እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን በሞራልም ህግም ተቀባይነት ያለው ሆኖ የሚያገኙበት ጊዜ ይኖራል… በዓለም ላይ ክፋት አለ። ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሂትለርን ጦር ሊያቆመው አይችልም ነበር። ድርድር የአልቃይዳ መሪዎችን መሳሪያ እንዲያስቀምጡ ማሳመን አይችልም ነበር። ሃይል አንዳንዴ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል ብሎ መናገር ሽሙጥን መጋበዝ አይደለም ።ለታሪክ እውቅና ፣የሰው ልጅ ፍጹም አለመሆንን እንዲሁም የምክንያት ውስንነትን እውቅና የመሰጠት እንጂ።”

እንደ የምርመራ ጋዜጠኝነት ቢሮ ፣ “በፕሬዚዳንት ኦባማ የፕሬዚዳንትነት ዘመን በሽብር ላይ በተደረገው ስውር ጦርነት፣ ከፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ ዘመን አሥር እጥፍ የሚበልጡ የአየር ድብደባዎች ተደርገዋል ይላል።” በአፍጋኒስታን ጦርነት የተከፈለው ዋጋ በጣም ብዙ ነበር። በፕሬዚዳንት ኦባማ ዘመን ቢያንስ 31,000 የአፍጋኒስታን ሲቪሎች ተገድለዋል እንዲሁም ከ40,000 በላይ ንፁሀን ዜጎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከዚህም በላይ ከአራት ሚሊዮን በላይ አፍጋኒስታን በአገር ወስጥ ተፈናቃይ ወይም የትውልድ ቀያቸዉን ለቀው በስደተኛነት ለመኖር ተገደዋል።

ወደ ኋላ መለስ ስንል፣ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በጠ/ሚ አህመድ ላይ ያደረሱትን አስከፊ ውንጀላ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ በአ ሜሪካዊው የኖቤል ተሸላሚ ላይ ከፍተኛ ጥቃት የሚወረውር የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ጎልቶ አለመታየቱ ያስገርማል። ስለ የሰላም ሽልማቱ “ቆሽሽ” ተብሎ የተባለ ነገርም የለም። የኖቤል ኮሚቴ ስራውን እንዲለቅም ጥያቄም አልነበረም።

የአለም አቀፍ ሚዲያዎች ፕሬዝዳንት ኦባማን ያዩበት መንገድ ከወትሮው የተለየ አልነበረም። የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የአገሮችን ሉዓላዊነት እና አንድነት ለመጠበቅ አስፈላጊ ናቸው ብለው ይሁንታ/ድጋፍ የሰጡባቸው ጦርነቶች ታሪክ የተሞላ ነው። የአሜሪካ የኩዌት ጦርነት፣ የታላቋ ብሪታንያ የፎክላንድ ደሴቶች ጦርነት እና በቅርቡ በአሜሪካእ ኤ.አ በጥር 6፣2020 በአሸባሪዎች ላይ የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻን እና ኢትዮጵያን ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ እያደረገች ያለውን ጦርነትን የአለም አቀፍ ሚዲያዎች ያዩበት መንገድ ግን በጣም በተቃራኒ ጎልተው የሚታዩ ናቸው።

የጦርነቱ የከፋ ጭካኔዎች እና የሰብአዊ ቀውስ

ጦርነቱ ያደረሰውን ሰብአዊ ቀውስ ማንም አይክድም። የተባበሩት መንግስታት እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በጋራ ባወጡት ሪፖርት ሁሉም ተዋጊ ወገኖች “ከባድ በደል እና የሰብአዊ መብት ረገጣ” ፈጽመዋል ብለዋል።

ሆኖም ግን፣ ማስረጃው እንደሚያሳየው፣ ህወሓት በኢትዮጵያ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ ለማስወገድ ምንም ፍላጎት አለማሳየቱን ነው። እ ኤ.አ በሐምሌ 2021፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ በዋነኛነት እየከፋ በመጣው የሰብአዊ ሁኔታዎች ምክንያት የአንድ ወገን የተኩስ አቁም አወጁ። በጣም የሚያሳዝነው ግን ፣ህወሓት “ አፀያፊ ቀልድ ነው” በማለት ውድቅ አድርጎት ከክልላዊ ግዛቱ ውጭ ባሉት ሶስት ግንባሮች ላይ የተቀናጀ ጥቃት ፈጽሟል። በአማራ እና አፋር ክልል ውስጥ ያሉት እነዚህ ሶስት ግንባሮች ለሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ወሳኝ ቦታዎች ነበሩ። የሕወሃት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ለሮይተርስ እንደተናገሩት” የግንባሩ ዋና ትኩረት የጠላትን የትግል አቅም ማዋረድ ነው”ነበር።

የህወሃት ሃይሎች “የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ተራእዶ ድርጅት መጋዘኖችን” እና “የተባበሩት መንግስታት የድንገተኛ አደጋ የምግብ አቅርቦትን በጠመንጃ አፈሙዝ” መዝረፋቸውም የአደባባይ ሚስጥር ነው። 400,000 የትግራይ ተወላጆች የረሃብ አደጋ ተጋርጦባቸው አለም ወደ ትግራይ የምግብ እህል የሚላክበት መንገድ እንዲፈለግ ሲማጸን ህወሃት ቁጥሩ ወደ 800,000 ሺህ የሚጠጋው ሚሊሻውን ለመመገብ የሰብአዊ ድርጅቶች መጋዘኖችን እየዘረፈ ነበር።

በተጨማሪም፣ እ ኤ.አ በመስከረም 16 ፣2021 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በትዊተር ገፁ ላይ “ወደ ትግራይ ከገቡት 466 (የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ) መኪናዎች 38ቱ ብቻ ተመልሰዋል” ሲል ወቀሰ። ህወዋት ሚሊሺያ እና ወታደራዊ ቁሳቁሱን ለማጓጓዝ መኪናዎቹን ተጠቅሞበታል። እንደ አለመታደል ሆኖ፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጠ/ሚ አቢይ አህመድ ተጨማሪ የጭነት መኪናዎች ወደ ትግራይ እንዲገቡ ግፊት እያደረገ ነው፣ ይው የመኪኖቹ መጨረሻ በሰው ሞገድ ሆነው ወደ ማይቀረው ሞታቸው የሚጋዙትን የህጻናት ወታደሮችን ጨምሮ ለወታደራዊ አገልግሎት የሚታገቱ ይሆናል።

የሐሰት ውንጀላዎች እውነትን መዋጥ/ማፈን

በመረጃ መጋለጥ የሚችሉ ሶስት የውሸት ውንጀላዎች እውነትን በማፈን ተቀባይ የአለም አቀፍ ትረካዎች በመሆን እንዴት ያለ ስጋት እንዳሰነሱ እናያለን። በመጀመሪያ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀድሞ ረዳት ሚኒስትር በሰጡት የጽሁፍ መግለጫ ላይ “የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የትግራይን ሁኔታ ከእውነታው የተባባሰ እንዲመስል የሚያደርጉ ጋዜጠኞችን በገንዘብ ገዝቷል ” ሲሉ አስጠንቅቀው ነበር።

ሁለተኛ፣ የተባበሩት መንግስታት፣ የአውሮፓ ህብረት እና የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት የተፅዕኖ ኃይላቸውን በመጠቀም መረጃ ሊቀርብባቸው የሚችሉ የሀሰት ውንጀላዎችን በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲዘዋወር ተጠቅመውበታል።የቀድሞ የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ፣የዘር ማጥፋት እና አስገድዶ መድፈር ወንጀልን እንደ መሳሪያ እያሉ በተደጋጋሚ ትዊት ያደርጉ ነበር። ይባስ ብሎ በትዊተር ገጻቸው ላይ የ10 አመት ልጆች የሆኑ የትግራይ ወታደሮችን ፎቶ “ኩራት” በሚል ሙገሳ ሰጥተዋል። ትዊቱ አሁንም አለ ግን ምስሉ ተወግዷል።

በሦስተኛ ደረጃ፣ “አንዳንድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣናት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ[ህወሃት] ሃይሎች የሚያደርጉትን ድጋፍን ያጋለጡ” የአፍሪካ ተወላጅ የሆኑ ሁለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ አጋላጮች በግድ አስተዳደራዊ የ እረፍት ፍቃድ እንዲወሰዱ ተደግርዋል ወይም የሰራ ውላቸው እንዲቋጥ ተደር ጓል።

ተዓማኒነት ያለው ገለልተኛ የማጣራት ሰራ የግድ አስፈላጊ ነው
የጦርነቱ መነሾ እና በሁሉም ወገን ተፈጽሟል ለሚሉት ግፍ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ሁሉ በአለም አቀፍ ባለስልጣናት በሐሰት ለተፈበረኩ ውንጀላዎችም/ጥቃቶችም ተጠያቂነት መኖር አለበት። ይህ ካልታረመ፣ የአፍሪካ መሪዎች የሚዳኙበት በግላጭ ያለው አለማቀፋዊ አበላላጭ መመዘኛ/ ደረጃ በአፍሪካ ያለውን የፖለቲካ ሃይል ስሌት በማዛባት የፖለቲካ ስምምነትን ሽብርን እንደ መሳሪያ ለሚጠቀሙ አጭበርባሪ ፓርቲዎች መጠቀሚያነ እንዲውል ይሆናል። ይህ የአፍሪካ ሀገራት በዘላለማዊ ግጭት እና ድህነት ውስጥ እንዲኖሩ ለዘላለም መፍረድ ይሆናል።

በአፍሪካም ሆነ በአለም ዙሪያ ያሉ ንቃተ ህሊና ያላቸው ሰዎች በአፍሪካ መሪዎች ላይ የሚደረግ አይን ያወጣ የማቃለል/የማናናቅ ፍረጃን ከሹክሹክታ ባለፈ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ማጉላት አለባቸው።
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን የኖቤል የሰላም ሽልማት ለመዋጀት ወይም ለመሻር አንድ ዓለም አቀፋዊ የሞራል ድምፅ ከጫጫታው መካከል መውጣት አለበት። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩን በውግዘት የጠፋ ስም ለማደስ/ከመዋጀት እና የለውጥ ተሃድሶዎቹን ለመጠበቅ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ሀገራትን ከመጠን ያለፈ አለም አቀፍዊ ውግዘትም ለማላቀቅም በጣም ወሳኝ ነው። ከዚህ በመለስ ያለ ማንኛውም ነገር ተስፋ የሚጣልባቸው የአፍሪካ መሪዎች ከስልጣን ሲወገዱ ቸልተኛ መሆን እና ተባባሪ መሆን ነው።

…………

ዮናስ ብሩ፣ በአለም ባንክ ውስጥ ለሁለት አስርት አመታት ያህል ሰርተዋልል። በስልጣን ዘመናቸው ባለፉት ሰባት አመታት የአለም አቀፍ የንፅፅር ፕሮግራም (ICP) ምክትል ግሎባል ስራ አስኪያጅ ሆነው አገልግለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ነፃ የኢኮኖሚ አማካሪ ምክር ቤት ጊዜያዊ ሊቀመንበር እና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን የሚያማክሩ የናይል ክለብ ሰብሳቢ ሆነውም አገልግለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop