አምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ በተለያዩ ኃላፊነቶች አገራቸውን ያገለገሉ አንጋፋ ዲፕሎማት አረፉ

ዶ/ር አምባሳደር ካሳ ከበደ በ1934 ዓም በኢትዮጵያ የአርበኝነት ታሪክ ከሚታወቁት አባታቸው ከደጃዝማች ከበደ ተሰማ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ይታጠቁ ኪዳኔ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተወለዱ፡፡

ዶ/ር አምባሳደር ካሳ ከበድ የመጀመርያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እዚሁ አዲስ አበባ ከተማ ከተከታተሉ በ=ላ ወደ እስራኤል በማቅናት የውትድርና ትምህርት እና የማህበራዊ አገልግሎት ትምህርት ተከታትለዋል፡፡

ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ሕዝባዊ ኑሮ ዕድገት እና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በ=ላም የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተብሎ በተጠራው ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ውስጥ እስከ 1962 ዓ.ም ድረስ አገልግለዋል፡፡

ቀጥሎም የችግረኞች መርጃ ድርጅት የሚባል ተቋም በዚሁ ሚኒስቴር ስር ሲመሰረት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው አገልግለዋል፡፡
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በ1965 ዓ.ም ድርቅ በመግባቱ ምክንያት በመንግስት በከፍተኛ ደረጃ ብሔራዊ ማስተባበርያ ተgም ሲመሰረት በዚሁ ተgም በሃላፊነት በማገልገል በሀገር ላይ የመጣውን ከፍተኛውን የድርቅ አደጋ በመቀነስ በኩል ታላቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡
ከዚያም ቀደም ሲል ስጋ ሜዳ ተብሎ በሚታወቀው ቦታ ላይ የጉዳተኞች ድርጅት ተመስርቶ በሃላፊነት በመምራት ላይ እያሉ የመንግስት ለውጥ ተካሄደ፡፡

አምባሳደር ካሳ በአዲሱ መንግስት ውስጥ ሀገሪቱ በተከፈተባት ጦርነት ምክንያት ስፍራው ወደ ታጠቅ ጦር ሰፈርነት በመዛወሩ ሀገር ለመከላከል የመጣውን ሚሊሽያ የጦር ሰፈሩን አስተዳደራዊና ሎጂስቲክስ ስራዎች አቀናጅተው እንዲመሩ ከበላይ አካል በመወሰኑ ሰራዊቱን በሃላፊነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ከዚያም ወላጆቻቸው በጦር ሜዳ የተሰውባቸውን ህፃናት ለማስተማር የህፃናት አምባን በማደራጀት እና ሕፃናቱን ለተጨማሪ ትምህርት ወደ ውጭ ሀገር በመላክ ዛሬ ሀገራቸውን እና ወገናቸውን በማገልገል ላይ ያሉ ዜጎችን አፍርተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

በመቀጠልም በማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትርነት እና በአሜሪካ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት ሀገራቸውን ለረጅም ጊዜያት ያገለገሉ ሲሆኑ ሕዝብ ለሕዝብ የሚባለውን የኪነት ቡድን በመላው ዓለም ተዘዋውሮ ኢትዮጵያን እንዲያስተዋውቅ ሲደረግ ቡድኑን የመሩ ታላቅ ባለ ውለታ ነበሩ፡፡

አምባሳደር ዶ/ር ካሳ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነውም ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

ዶ/ር አምባሳደር ካሳ ኢሳትን እዚህ ደረጃ ለማድረስ ጉልህ ሚና ከተጫወቱ አንጋፋ ባለውለታዎች መካካል ግንባር ቀደሙ ሲሆኑ ህልፈተ ሕይወታቸው እስከተሰማ ድረስ የኢሳት ስራ አመራር ቦርድ አባል ሆነው እያገለገሉ ነበር፡፡

አምባሳደር ካሳ በተወለዱ በ80 ዓመታቸው ትላንት ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም አሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

የኢሳት ቴሌቪዥን ማኔጅመንት ቦርድ እና ሰራተኞች ለቤተሰቦቻቸው በሙሉ መፅናናትን ይመኛሉ፡፡

ESAT

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share