December 26, 2021
32 mins read

አያ ጅቦ ሳታመሃኝ ብላኝ!!  (በአገሬ አዲስ)    

አማራን ለመዋጥ ነጣጥሎ ማስቀመጥ፣ለመደራደር ክልል አትሻገር!

ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓም (25-12-2021)  በአገሬ አዲስ

ላለፉት ሦስት ዓመታት የኦሮሞን የበላይነት ያስከበረው ኦህዴድ በብልጽግና ስም ከሌሎቹ አጋር ቡችሎቹ ጋር ሆኖ  በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጽመው በደልና ክህደት ከቀን ወደ ቀን እዬጨመረ እንጂ እዬቀነሰ አልሄደም።ይህንን ክህደቱን እንደ አስተዋይነትና ችሎታ የሚቆጥሩና የሚያሞግሱ አድር ባዮችም  ህሊናቸውን በመሸጥ (ዱሮስ ህሊና ቢኖራቸው አይደለም?) ምለው ተገዝተው መሪውን  አብይ አህመድን ከሰው የተለዬ ፍጡር ፣ የሚሠራው እንደ አማልእክት፣ የሚናገረው እንደ መጽሓፍ ቅዱስ ወይም ቁርዓን ቃል አድርገው በመቁጠር ተደናግረው ሕዝቡንም ያደናግሩታል።የበላ ውሻ ሲጮህ ሰፈሩን ይረብሻል እንዲሉ! አብይ አህመድ በስህተት ላይ ስህተት ሲሠራ ከማረም ይልቅ ብልሁ! ግፋ! በርታ!፣ጀግናው! የድሉ ባለቤት እያሉ ለበለጠ ጥፋት ያበረታቱታል። እሱ ግን ቃሉን አክባሪ ነው።የሚፈልጉትን ስጣቸውና ወደምትፈልገው ውሰዳቸው የሚለውን ፍልስፍናውን በደንብ እዬተጠቀመበት ይጋልባቸዋል።

OLF Shane and Oromo Liberation Army OLA
OLF Shane and Oromo Liberation Army (OLA)

ሰሞኑን ሁለት የጥፋት መርዞችን በትኗል።አንዱ በካርታ መልክ ያሰበውን አገራዊ አወቃቀር  የሚያሳይ ሲሆን  ሌላው  ደግሞ ዘመቻውን በሚመለከት በአዋጅ(ትዕዛዝ) መልክ ያስተላለፈው ውሳኔ ነው። ከቀድሞ ጌታው ከወያኔ በሥልጣን ግብግብ አገራችንን በተለይም የአማራውን ማህበረሰብ ለጥፋትና ለውድመት ከዳረገ በዃላ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ አሁን ደግሞ አሸባሪ ብሎ በራሱ ምክር ቤት ከፈረጀው የጥፋት ሃይል ጋር ለመደራደር ዳር ዳር እያለ መሆኑ ተስተውሏል።ለዚያም ያመቸው ዘንድ የፈረደበትን አማራ ነጣጥሎ ለመምታትና የወልቃይትን፣ የወሎንና የሸዋን ክፍለሃገር ከሌሎቹ ያማራ ክፍላተሃገር ነጥሎ ለመዋጥና ለማስዋጥ አዲስ የአስተዳደር ክፍፍል የሚያሳይ ፣ መጀመሪያ የሰውን ስነልቦና ከፈተሸ በዃላ በተግባር የሚገልጸውን ካርታ ይዞ ብቅ ብሏል።ይህም እንደሌሎቹ እኩይ ዓላማዎቹ ካልታገሉትና ካላሶገዱት የአማራው ማህበረሰብ ተነጣጥሎ ለከፋ ወረራና ጥቃት የተጋለጠ፣ብሎም እርስ በርሱ በጠላትነት የሚዋጋ  ለማድረግ  የታሰበ ሴራ ለመሆኑ የወጣውን የካርታ ሰነድ ማዬቱ በቂ ማስረጃ ነው። ይህ አዲስ ካርታ መላ አገሪቱን በሃያ ክልሎች ከፋፍሎ አምስት ቋንቋ መድቦ እንዳይግባባ ለማድረግ የተሸረበ ሴራ የተሸከመ ነው። ክልል ይፍረስ ሲባል በክልል ላይ ክልል እየፈለፈለ የመደመርን ፍልስፍና በማባዛት ፍልስፍና ቀይሮታል።አሥሩን ክልል በሁለት አባዝቶ ሃያ ክልል አድርጎታል።ኢትዮጵያ አንድ ትልቅ አገር፣ ሕዝቧም የአንድ አገር ዜጋ ከመሆን ይልቅ የብዙ ሃገራት ዜጎች ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ወጥመድ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም።ካለፈው የወያኔ  የቀጠለ በመሰሪ ገመድ የተተበተበ የኦሮሙማ አገር አጥፊ ስልት ነው። ከመምህሩ የደቀመዝሙሩ እንዲባል።ወያኔ ለዘጠኝ የከፋፈላትን አገር ኦህዴድ ኦነግ ከማን አንሼ ብሎ አሥር ካደረገ በዃላ አሁን ደግሞ በካርታው ሃያ ክልል በማድረግ የክፋት ደረጃው እንደሚበልጥ  ያሳዬበት ሂደት ነው። በጣም የሚገርመው ነገር በካርታው ላይ የሰፈሩት ከባቢዎች ግማሾቹ በጎሳ  ማንነት ፣ግማሾቹ በክፍለሃገር መጠሪያ ስማቸው መቀመጣቸው ነው።ጎጃምና ጎንደር አማራ ፣አሩሲ፣ከፋና ባሌ ከተነጠቁ አጎራባች መሬቶች ጋር  ኦሮሞ፣ሶማሌ፣…የሚሉ ክልላዊ ስያሜዎች ሲይዙ ወሎ ፣ሸዋ፣ወለጋ፣የጎጃም አካል የነበረው ከባቢም እራሱን ችሎ  መተክል፣…ወዘተ በመባል ተቀምጠዋል። ቤንሻንጉልም እንዲሁ።የሕዳሴው ግድብ ባለቤት ማን ይሆን?

ወልቃይት ለብቻዋ  ተከባ ተቀምጣለች፣ይህም ከአማራው እጅ ፈልቅቆ በማውጣት ለሱዳንና ለወያኔ ወረራ የተመቸች አድርጓታል።ወይም በድርድሩ ሕዝባዊ ውሳኔ በሚል ትያትር ለወያኔ አሳልፎ ለመስጠት የታሰበ ሊሆን ይችላል።የጎንደር አማራ የእኔ ናት ብሎ እንዳይከራከርና ከወራሪዎች እንዳያድናት የባለቤትነቱን መብት በአዲሱ ካርታ ነፍጎታል። አዲስ አበባንም ዋጋ ቢስ ከተማ  (irrelevant city)እናደርጋታለን ባሉት መሠረት ሌሎች ሦስት ከተሞች ለመመስረት መታቀዱን በዚሁ የካርታ ንድፍ ውስጥ የቀረበው ዝርዝር ማስረጃ ያሳያል።የክፍላተ ሃገር ከተሞች እራሳቸውን ችለው ከተማ የመሆኑና የአዲስ አበባም የኢትዮጵያ መናገሻ ከተማነቷ ያከትምላታል ማለት ነው።የንግድና የኢንዱስትሪ ማእከልም በየክፍላተ ሃገሩ መስፋፋታቸው ቀርቶ በአንድ ና በሁለት ቦታዎች ብቻ ይከማቻሉ ማለት ነው።የፈለገ የቀናት ወይም የሳምንት ጉዞ ተጉዞ ይገበያል፣ይሸጣል ወይም ይገዛል ማለት ነው። ኢንዱስትሪ በከባቢው ባለው ምርትና ማዕድን ዙሪያ መገንባት  ሲገባውና ከሌሎቹም አገራት ተመክሮ መቅሰም ሲቻል ነጣጥሎ ለፈለጉት አካባቢ ብቻ መጠቀሚያ ፣ሌላውን የድሃና የሥራ አጥ መኖሪያ ሊያደርግ የሚችል ንድፈ ሃሳብ ነው።።ወርቅ በሌለበት ከባቢ የወርቅ ጌጣጌጥ  ፋብሪካ አይቋቋምም፣የሌላውም እንዲሁ።እንደ ወያኔ ከሌላው ቦታ ጥሬ ምርቱን እዬዘረፉ በመቀሌና አካባቢዋ በተቋቋሙ ፋብሪካዎች ላምርት ካልተባለ በስተቀር የሚሆን አይደለም፣ሊሆንም አይገባውም። ጥጡ አፋር፣ጣቃና ልብስ ፋብሪካው መቀሌ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመልካም አስተዳደር፣ ለእኩልነት፣ለፍትሕ፣ለዴሞክራሲ ስርዓት መስፈን ታገለ እንጂ የሚኖርበት ክፍለሃገር ስም ይቀዬርልኝ፣በጎሳ ስያሜና ማንነት መሬት ተሸንሽኖ ድንበር ተከልሎልኝ ልኑር ብሎ አልጠዬቀም ።ወያኔና ኦነግ ለእኩይ ዓላማቸውና ኢትዮጵያን ለመበታተን ሲሉ ከሰላሳ ዓመት ወዲህ ሕዝቡን በቋንቋ ለያይተው የሚኖርበትንም መሬት የጎሳ ማንነት ሰጥተው እስከአሁን ድረስ ላለው ቀውስ ዳርገውታል።ከችግሩ፣ከብዝበዛው፣ከፍትሕ እጦቱ ጋር የእርስ በርስ ግጭት እንዲፋፋም፣ስደትና መፈናቀል እንዲስፋፋ አደረጉት እንጂ  ሕዝቡ የታገለለት የሰብአዊና የዜግነት መብት ተከብሮለት የመኖር ጥያቄው መልስ አላገኘም።

የትልቅና የተከበረች አገር ዜጋ ከመሆን የጠባብና የመንደር እስረኛ በማድረግ ለከፋ ኑሮ የዳረገው  የክልል አወቃቀር መፍረስ ሲገባው አሁንም ደግሞ ክልል አይሉት ክፍለሃገር ፣አንዱን በጎሳ ስያሜ ሌላውን በቀድሞ ክፍለሃገር ስያሜ ሸንሽኖ ለማዋቀር አዲስ ካርታ ተነድፎ በሚስጥር  መሰራጨቱን ተከትሎ ለበለጠ ቀውስና አደጋ እንደሚያጋልጥ ከብዙዎች እዬተነገረ ነው። በጎሳ ማንነት የተዘረጋው የክልል አስተዳደር ይፍረስ ከተባለ አገራችን በቀድሞው  ክፍላተሃገር(Provinces) ወይም በአዲስ በከባቢ የመልክዓምድራዊ አቀማመጥ (Regions) ሰሜን፣ደቡብ፣ምዕራብ፣ምስራቅና ማእከላዊ ኢትዮጵያ በሚል ቢዋቀር የተሻለ ይሆናል።ሕዝቡም በነጻነት ድምጽ ቢሰጥበት ተገቢ ነው። ከዚህ ውጭ ግን ግማሹን በጎሳ ስም የአማራ፣የኦሮሞ…ወዘተ እያሉ ሌላውን የነባሩን ክፍለሃገር ስም ሰጥቶ ዲቃላ አወቃቀር  መፍጠሩ የተሻለ ሳይሆን ለተንኮል የተዘረጋ ማጥመጃ መረብ ነው።

ምንም እንኳን ከጅምሩ አገርና ሕዝቡ በቋንቋና በጎሳ ማንነቱ መሸንሸኑ ተገቢና ትክክል እንዳልሆነ ቢታወቅም የሕዝቡን አሰፋፈር ለመግለጽ በአብዛኛው ሰፋሪ ጎሳ ስም መታወቁ ክፋት አልነበረውም።ይህ ማለት ግን በአንድ ጎሳ በታወቀ መሬት ውስጥ ሌላ ጎሳ ተወላጅ አይኖርም፣እኩል የባለቤትነት መብትም የለውም ማለት አይደለም። ባሕሉ፣ ቋንቋው፣ እምነቱ ተከብሮለት፣በአስተዳደሩም ውስጥ ቦታ ኖሮት የመኖር መብቱ ከተከበረለት የቦታው ስያሜ ጉዳት የለውም ለማለት ነው። እንግሊዝን እንግሊዝ ያሰኘው እንግሊዝኛ በመናገሩ፣ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ጀርመንና ሌሎቹም ቢሆኑ በቋንቋቸው ስያሜ ያገኙ አገራት ናቸው።በውስጣቸው ግን የብዙ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ጎሳዎች ይኖራሉ።በእኛም ኢትዮጵያ እንዲሁ በክፍላተሃገር ደረጃ የአማራው ክፍለሃገር፣የኦሮሞ ክፍለሃገር፣የትግሬ ክፍለሃገር፣የሲዳማ፣ክፍለሃገር …ወዘተ እያለ ቢጠራ ጉዳት አይኖረውም። ከዚህ ሁሉ ምስቅልቅልና ችግር ፈጣሪ ስያሜ የተሻለው ግን በቀድሞ የክፍላተሃገር ስያሜ ማዋቀሩ ነው።ምክንያቱም የጎሳ ባህሪያትን አያንጸባርቅምና ነው።ይህንን አይነት  አገራዊ አወቃቀር ላሰፈኑት ብልህ ለቀድሞ አባቶቻችን ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል።ከዘመኑ ተማርኩ ብሎ በጎሳ ወረርሽን ከተለከፈ አገር ለመበተን ከሚቅበዘበዝ ትውልድ የተሻሉ ሊቃውንቶች መሆናቸውን መካድ አይገባም።

ወሎ(ላኮመዛ ወይም ቤተ አማራ)  አማራ የሚበዛበትና የአማራው አጽመ እርስት መሆኑ ሲታወቅ በውስጡ ብዙ አናሳ ጎሳዎች ይኖሩበታል። ኦሮሞው፣አርጎባው፣አፋሩ፣ትግሬው፣አገው ለዘመናት ተከባብረው፣ተዋልደው ኖረዋል።ለሥራም መጥተው ከሕዝቡ ጋር ተቀላቅለው በሰላምና በፍቅር የሚኖሩ የደቡብና የምስራቅ፣የሰሜንና የምዕራብ ኢትዮጵያ ተወላጆች መኖራቸው አይካድም፤ከመኖርም በላይ ከከባቢው ተወላጅ ጋር ተጋብተው፣በደምና በሥጋ፣ በእትብት ተሳስረዋል። በወል መጠሪያቸው በሆነው በወሎዬነታቸው እንጂ በነጠላ የጎሳ ማንነታቸው እራሳቸውን አልገለጹም ነበር።ይህ የተበተነው ካርታ ተብዬው የሴራ ሰነድ እራሱ ክልል ብሎ ከፈጠረው ወሎን  ከሌሎቹ የአማራ መሬቶች ከሸዋ፣ከጎንደር፣ከጎጃም ነጥሎ ብቻውን በአጥር ውስጥ ከቦ በማስቀመጥ፣ወልቃይትንም ከታሪካዊ ትስስሩ ከቤጌምድር ነጥሎ ለብቻው የተንጠለጠለና ለሱዳንና ለትግራይ ተስፋፊ ሃይሎች የተጋለጠ ደካማ ክልል ማድረጉ፣ሸዋንም እንዲሁ ዋና ከተማዋን አዲስ አበባን ቀምቶ ፊንፊኔ በሚል መጠሪያ ለኦሮሞ ተስፋፊዎች ማጋለጡ   የአማራውን ሃይል ለማመናመንና ለመዋጥ፣ ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ይሏታል ጅግራ እንደሚሉት  የታሰበ የነ አባ ቀማው ዘዴ ነው። አገርን በጎሳ ስምሪትና  አወቃቀር መሸነሸኑ ይቅር ሲባል ምን ታመጣላችሁ በሚል እብሪት ወያኔ  በዘጠኝ የከፋፈለውን አገር ኦሕዴድ/ኦነግ ወደ አስር ከዚያም ወደ አስራአንድ  አሁን ደግሞ ሃያ ክልል አድርሶ ብቅ ብሏል።ከዚህ የበለጠ ሕዝብን መናቅና መድፈር አይኖርም።

የኦሮሙማ የመስፋፋት ዓላማ በዚህ ብቻ አይቆምም፤ ቀጣዩ ሸዋ፣ጎጃም ከዚያም ጎንደር እንደሚሆን አንዱ ቀዳዳ የኦነግ አባል በድፍረትና በይፋ ተናግሯል።  በዚያም አያበቃም! ትግራይ እስከ ኤርትራ ድንበር የኦነግ ካራ እንደሚያርፍበትና ትልቋ ኦሮሚያ የተባለች የቅዠት አገር ለመፍጠርም ጉጉት እንዳላቸው ዘላብዷል።ለዚያም መንደርደሪያ የኩሽ ነገድ የሚል የማሰባሰቢያ ስልት ሲያናፍሱ ተሰምቷል። ይኸው ሰው የኦነግን የጭካኔ ከፍታ  ሲያብራራው አማራዎች እንኳንስ በህይወት የሚኖሩት ቀርቶ  የሞቱትም ቢሆኑ ከተቀበሩት መሬታቸው ሳይቀር መቃብራቸው ተቆፍሮ አጽማቸው ይወረወራል ብሏል። ከማለትም በላይ የአማራ ነፍሰጡር ሆድ እዬተቀደደ ጽንስ ተጎትቶ ሲወጣ አይተናል፣ የሰው ኩላሊት ሲበላ ታዝበናል፤  የአዲስ አበባ ሕዝብ ከኮንዶም ያመለጠ የሸርሙጣ ልጅ ነው ሲባልም በጆሯችን ሰምተናል። ይህንን ሁሉ ድፍረት፣ ግፍና በደል የፈጸሙት ግን ሲሾሙና ሲሸለሙ ብሎም በፓርላማ ውስጥ ገቡ እንጂ በሕግ ሲቀጡ አላዬንም። ይህን እዬሰማ ፣የግፉን ከፍታና ጥልቀት በዓይኑ እያዬ ከኦህዴድ-ኦነግ መራሹ ብልጽግና የተሻለ ስርዓት የሚጠብቅ ካለ በሰው ደረጃ ያልተፈጠረ ገና በድን ፍጡር ብቻ ነው።  ከሰሞኑም የኦሮሙማው ባለሥልጣን የሆነው ታከለ ኡማ ሸኔ የተባለውን በራሳቸው የሚታገዝ  የጥፋት ቡድን ለይስሙላ በተቸበት አፉ ኦነግ አራት ኪሎ ቤተመንግሥት ገብቷል፣ኦሮሞ ከዚህ የበለጠ ድል አያገኝም ሲል የአብይንና የሌሎቹን፣የመንግሥቱንም  ኦነግነት ይፋ አድርጓል።

ከቀጣዩ ውድመትና ጥፋት ከአገርም መበታተን አደጋ ለመውጣት ያለው አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ነው።ያም በኢትዮጵያዊነት ማንነት ላይ የቆመ ድርጅት ፈጥሮ በጋራ መታገል ነው። በጎሳ ተዋረድ የተሸነሸነችዋን ኢትዮጵያን በነባር የክፍላተ ሃገር አወቃቀር መተካት ነው። ለዚያ ደግሞ ትልቁ አስተማማኝ ደጀንና ዋልታ የአማራው ማህበረሰብ ነው።ሃይሉን ለመበታተን የሚሸረበውን ተንኮልና የሚበጠበጠውን መርዝ ለማምከን አማራው በአንድ ድርጅት ስር ተሰባስቦ ፣አንድ አመራር ፈጥሮ መቆም አለበት። ከሌሎቹም በኢትዮጵያዊነታቸው ከማይደራደሩት መሰል ወገኖቹ ጋር አብሮ ለመታገል እቅድና ዘዴ መፍጠር ይኖርበታል።በሌሎች ዘንድ ክብርና ተቀባይነት ለማግኘት እምነታቸውንም እንዲጥሉበት የግድ የሱ መጠናከር ወሳኝ ነው።በጎጥና በሃይማኖት የመነጠሉ ሴራም መኖሩን አውቆ ሴራውን ማክሸፍ ተገቢ ነው።የሁሉም ክፍላተሃገር ነዋሪ  ቋንቋና እምነት ሳይለዬው የክርስቲያንና የሙስሊም ቤተሰብ ያፈራ፣የሁለቱም ቤተእምነት ተከታዮች በጋብቻና በዝምድና ሃረግ ተሳስረው፣ባህላቸውንና ቋንቋቸውን ተጋርተው የኖሩበት፣ በብዙ ማህበረሰብአዊ መስተጋብሮች የተሳሰሩ ለሌላው የአብሮነትን ትርጉም ያሳዩና ያስመሰከሩ የደጋጎች መኖሪያ  መሆኑን  ባዕዳን ሳይቀሩ ያውቁታል። ያም ትስስር ነው ሃይል ሆኖ የመጣውን የውጭ ወራሪ  ድል አድርጎ የነጻ አገር ባለቤት ያደረገው።ይህንን አብሮነት የሚጠሉት የውስጥና የውጭ ጠላቶቹ ግን መሬቱን ነጥቀው ባህሉንና ወጉን፣ታሪኩን አውድመው አገረ ቢስ ለማድረግ ሌት ተቀን  በመሥራት ላይ  ናቸው።የሚያሳብዳቸውም በከፍተኛ ሰብአዊ ደረጃ ላይ መታዬቱ፣ የእነሱን ጭንጋፍ ተክለአውሬነት አለመላበሱ ነው። ከሱ ተምረው እሱን ከመሆን ይልቅ እነሱን እንዲሆንላቸው የእብደት ጉዞ ጀምረዋል። ይህንን ጉዟቸውን ከጅምሩ መቅጨት የህልውና ግዴታ ነው።ከመምሸቱ በፊት መክሮና ዘክሮ መወሰኛው ጊዜ አሁን ነው።

ሁለተኛው የኦህዴድ ድፍረት ደግሞ  በታህሳስ 14 ቀን 2014 ዓም በመንግሥት በኩል የተላለፈው የጦር አቁም ትዕዛዝ ነው።ወያኔን ከምድር ገጽ አጥፍተን፣ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ሁለተኛ አደጋ እንዳይሆን ሳናደርግ፣ትግራይንና ሕዝቧንም ከዚህ አውሬ እጅ ነጻ ሳናወጣ አንመለስም ብሎ የፎከረው መንግሥት ነኝ ባይ ቡድን ከማን በኩል እንደመጣ ባልታወቀ ትዕዛዝ ብዙ መስዋዕትነት እዬከፈለ ወያኔን ድባቅ ለመምታት በጉዞ ላይ ያለውን አገር ወዳድ ሳያስበውና ሳይጠብቀው የጦርነቱ ምዕራፍ ተጠናቋል፣ባለህበት እርጋ፣የመንግሥት ሰራተኛም የሆንክ ወደ ሥራህ ተመለስ፣ገበሬውም ሚሊሽያ፣ፋኖና ልዩ ሃይል ትጥቅህን ፈተህ ወደ ቤትህ ግባ የሚል ለወያኔ ብሥራት ለሌላው ስብራት የሆነ ትዕዛዝ ተላልፏል። የታቀደውን የወያኔ ሴራ ለማክሸፍ፣የጥሞና ጊዜ ለመስጠት በሚል ሽፋን የታጀበው ትዕዛዝ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ከተፈጸሙት ክህደቶች ሁሉ  ከፍተኛው ሆኖ ይቆጠራል።ወያኔ በነጻ ከትግራይ ተጉዞ በአማራውና በአፋሩ ማህበረሰብ ላይ እጅግ ዘግናኝና ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ከፈጸመና ያለ የሌለ ንብረት ዘርፎና አውድሞ በመጣበት መንገድ አስፋልት ይዞ ተዝናንቶ ትግራይ እንዲገባ የማድረጉ ጥምር ሴራ ሳያንስ አሁን ደግሞ ለቀጣይ ወረራ አቅሙን እንዲገነባ ጊዜና ዕድል ለመስጠት ይህንን ዱብእዳ ትዕዛዝ እምቦጭ አድርጎታል።የሚገርመው አብይ አህመድ በሰጠው ማብራሪያ ወያኔ ከወረረው ከአማራውና ከአፋሩ መሬት ሙሉ ለሙሉ(100%)ለቆ ወጥቷል ማለቱ ነው።እውነቱ ግን የወሎ ምዕራብ ሰሜን የራያ፣የጎንደር ምዕራብ መሬት በወያኔ ቁጥጥር ሥር መሆኑ ነው።ይህ ግን የሚያሳዬን ወያኔ የእኔ ናቸው የሚላቸውን መሬቶች እውቅና በመስጠት ለቀጣዩ ድርድር እጅ መንሻና ማረጋገጫ እንዳደረገ ግልጽ ነው። የክህደት ክህደቱም ማሳያ ይህ ነው።ይህንን የጦር ስልት ነው እያሉ ከበሮ የሚደልቁት ነገ ወያኔና የአብይ መንግሥት ለድርድር ሲቀርቡ ምን ሊሉ እንደሚችሉ ሲታሰብ ስለነሱ ያሳፍራል።፣ውስጥ ለውስጥ ሲካሄድ የነበረውን ውይይት በዚህም በዚያም ብሎ ተግባራዊ ማድረጋቸው አይቀሬ ነው።የአሜሪካኖቹም መለሳለስና ውሳኔውን መደገፋቸው ያንኑ የሚያመላክት ነው።የነሱም ጥያቄ ይኸው ነው። ወያኔ ገና ካሁኑ የመደራደር አቅሙን ለማሳደግ ቁስለኛ ሳይቀር የተበታተነ ሃይሉን አሰባስቦ ለዳግመኛ ጦርነት ተዘጋጅቷል፤መዘጋጀትም ብቻ ሳይሆን ወረራውን በማጠናከር ላይ ነው።የያዘው ሳይለቅ ያልያዘውን ለመያዝ እዬገሰገሰ ነው።በሃይልም ሆነ በድርድር  ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ካልቻለ ትግራይን የመገንጠሉን ፍላጎት በነደፈውና ባልተወገደው ሕገ-መንግሥት ከማረጋገጥ አይመለስም።ያንንም ከዃላው የተሰለፉት አገሮች እውቅና ይሰጡታል።ሌላውም በተለይም የኦሕዴድ/ኦነግ ስብስብ በተመሳሳይ የድርሻውን ቦጭቆ ነጻ አገር መስርቻለሁ ለማለት የሚሳነው አይሆንም።የቀረውም ያንኑ ፈለግ መከተሉ አይቀሬ ነው።ለዚያም ነው አብይ አህመድና ተባባሪዎቹ ሕገ-መንግሥቱ እንዳይለወጥ እስከአሁን ድረስ የሙጥኝ ያሉት።

ይህንን የተረዳና የተገነዘበ ኢትዮጵያዊ በተለይም የአማራ ማህበረሰብ የጀመረውን የህልውናና አገር አድን ትግል በቅንጅት መምራት የግድ ይለዋል።አለበለዚያ ለጠላቶች አመቺ ጊዜና ሁኔታ መፍጠር ነው።ይህን አለማድረግና መዘናጋት መቀበሪያ ጉድጓድ ለሚቆፍር ጠላት ዶማ ማቀበል ነው።አገር ወዳዱ ሕዝብ ሆይ! በቃ!ንቃ፣ተደራጅ፣ታጠቅ። በኦህዴድ መራሹ ሰላም ይወርድልኛል፣መብቴ ይከበርልኛል ብለህ ትጥቅህን አትፍታ፤የጎደለህን አሟላ።እነሱ እዬተደራጁና እዬታጠቁ ነው።የሚደራጁት ለቲማቲም ወይም ለድንች ተከላ ወይም ለመንገድ ሥራ  አይምሰልህ፤ ከላይ ለተዘረዘሩት ዓላማቸው ነው። በዋናነት አማራውን ማጥፋት ተቀዳሚ ዓላማቸው መሆኑን ተረዳ።ወሎን ቁርስ አድርገው ሌላውን ምሳና እራታቸው ለማድረግ ያቀዱ መሆናቸውን ተረድቶ ማምከን ተገቢ ነው።

ወሎ ሆይ!ሸዋ ሆይ! ወልቃይት ሆይ!ከሌሎቹ አማራ ወገኖችህ ከጎጃምና ከጎንደር ነጥለው ሊበሉህ የቀየሱትን የነ አባ ብላው፣የነአባ ቀማውን እቅድ አትቀበል፤ እምቢ በል!የጀመርከውን የፋኖ፣የሚሊሽያና ልዩ ሃይል አሰላለፍ አዋህደህ አጠናክር።በኢትዮጵያዊነት ከተሰለፉትም የመከላከያ አባላት ጋር ምክር ዝከር።እራስህን አፍርሰህ ተቀላቀል የሚሉህን አትስማቸው።በእውነተኛና በማይፈታ ቃል ኪዳን የተገነባ አገራዊ ሃይል ለመፍጠር አትቦዝን። እራስህን አድነህ አገርህ ኢትዮጵያን አድን።እኩልነት፣ትልቅነትና ክብር የሚወድ ይከተልሃል።እምቢ አልሰማም ካለም ለሚደርስበት መከራ ተጠያቂው እራሱ እንጂ አንተ አትሆንም።አንዳንዱም የሚጠጋበትን ዋሻ በመተማመን ለጥሪውና ለግዳጁ ጆሮ ዳባ ሊል ይችላል።የቤት ሥራህን አንተ ሥራ!አለበለዚያ ለዳግመኛ ጊዜ እናትህ፣ልጅህ፣ሚስትህ፣እህትህ፣አክስትህ ግፋ ሲልም መለኩሴዋ አያትህ ተደፍረው አንተም የካራ ሲሳይ ከመሆን አታመልጥም።እውነቱ ይህ ነው፣ያለፈውም የሚያስተምርህ ይህንኑ ነው።በተጨማሪም በዬቦታው ተበትነው የጥቃት ሰለባ የሆኑትንና ድረሱልን የሚሉትን ለማዳን ክተት! ብለህ ተንቀሳቀስ። ባለቤት ያቀለለውን ባለዕዳ አይቀበለውምና እራስህን  አስከብር!!

የአማራው መዳን የኢትዮጵያ መዳን ነው!

አያ ጅቦ ሊበላህ ሲመጣ ፣ አንተ ብላውና ተቀደስ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop