እስከ መቼ በጦርነት ውስጥ እንድንቆይ ነው የሚፈለገው??? – ወገን ደጀን ነኝ ከአውስትራሊያ

ታሪክ እንደሚነግረን አፄ ሚኒሊክ ወታደሩ እረፍት ያድረግ ሰንቃንችንም እያለቀ ነው በሚል ልዩ ልዩ ምክንያቶች የኢትዮጵያ ጦር ተከዜን እንዳይሻገር አድረጉ መጨረሻው ምን እንደሆነ ሁላችንም እናውቀውለን።

ከኤርትራ ጋር በተደረገው ጦርነትም የኢትዮጵያ ጦር ወደ አስመራ ገብቶ ከኤርትራ ሊመጣ የሚችለውን ሰጋት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በድል እንዳይደመደም አቶ መለስ ዜናዊ ጦርነቱን በማስቆም አስራ ሰባት አመት ሙሉ ሀገራችን በጦርነት ሰጋት ውስጥ እንድትቆይ እና በኢኮኖሚያቸ እና በልማታችን ላይ ምን ያህል ተዕዕኖ እንዳሳደረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

ታሪክ አሁንም እራሱን ደግሞ ከሁለቱም ጊዜ በከፋ ሁኔታ የሀገራችንን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ፣ ህዝቧን ሰላም የሚያሳጣ  ፣ ኢኮኖሚያዋን የሚያደቅ ፣ ልማትዋን የሚጎትት እና ከሁሉም በላይ የተግራይ አጎራባች ክልሎችን በሰጋት እና በፍርሀት እንዲኖሩ የሚያደርግ ውሳኔ መተላለፉ በጥሞና መታየት ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል።

ዶክተር አቢይ እያሳየ ላለው አመራር  ከፍተኛ አድናቆት ከሚሰጡት ኢትዮጵያኖች መካከል አንደኛው ነኝ። ከማንም ስጋ ለባሽ የሆን የሰው ፍጡር ሁሉ ፍፁምነት ስለማይጠበቅ ዶ/ር አቢይ የሚሰጠው ውሳኔ ሁሉ ትክክል ነው ማለት ግን አይደለም። እንደውም የጥሩ ስብዕና ባለቤት ስለሆነ እና በፈሪሀ እግዚአብሄር የታነፀ በመሆኑ በሚያራምደው የተለሳለሰ አስተሳሰብ እና በሚሰጠው አስተዋይነት በተሞላው አመራር ኢትዮጵያን ብዙ ዋጋ እያስከፈላት እንደሆነ ግልፅ ነው። ሆኖም ግን ዶ/ር አቢይ ጥሩ ተናጋሪ ብቻ ሳይሆን ጥሩ አድማጭም ስለሆነ ቢዘገይም እና ብዙ ዋጋም ቢያስከፍልም በሂደት ጥሩ ለውጦችን እያየን ነው። ይህንንም  ፅሁፍ ሳዘጋጅ ዶ/ር አቢይ  ሀሳቤን ከግምት ውስጥ በማስገባት ጦሩ ወደ መቀሌ እንዳይገባ የወሰነውን ውሳኔ ድጋሚ እንደሚያስብበት  እምነት አሳድሬ ነው።

በሀገር ላይ የሚወሰን በተለይ ደግሞ እንደዚህ አይነት ከባድ የሁሉንም ቤት የሚያንኳኳ ውሳኔ መስጠት እንደምፅፈው ቀላል አለመሆኑን እረዳለሁ። በመንግስት ደረጃም ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ሁሉም አማራጮች ጠረጴዛ ላይ ቀርበው ያላችወ ጥቅም እና ስጋት ተመዝኖ እንደሚወሰን አምናለሁ። ሆኖም ግን ወደ መቀሌ እንዳይገባ የተላለፈው ውሳኔ  ግን ከጥቅሙ ስጋቱ ሚዛን ይደፋል የሚል እምነት ነው ያለኝ። ከጁንታው በቀር ለትግራይ ህዝብም አይበጅም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአንድ አገርና ህዝብ ዕድል ሊወሰን የሚችለው ከ2-5% በሚሆነውየህብረተሰብ ክፍል ብቻ

ምክንያቱም ከአምስት ወር በፊት የኢትዮጵያ ጦር ሙሉ ትግራይን ከተቆጣጠረ በኋላ ለትግራይ ህዝብ የጥሞና ጊዜ ለመስጠት፣ለትግራይ ህዝብ እርዳታ እንዲደርስ እና ገበሬው የእርሻ ጊዜው እንጋይስተጓጎልብት በሚል ህሳቤ መቀሌን ለቆ እንዲወጣ መድረጉ ይታወቃል።

ነገር ግን ጦሩ  መቀሌን ለቆ በመውጣቱ ምንድነው ያተረፍነው? የታሰበው ውጤት ተገኝቷል? የትግራይ ህዝብ ተታሰበውን የጥሞና ጊዜ አግኝቷል? ለትግራይ ህዝብ የእህል እርዳታ ያለምንም ችግር እንዲገባ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል? ገበሬው እርሻውን አርሷል? የአለም አቀፉ ህብረተሰብ ኢትዮጵያ የወሰደችውን ውሳኔ ደግፎ የሚያደርሰውን ጫና ቀንሷል?

እውነታው የሚያሳየው ጁንታው ለመዋጊያ የሚሆን ሰንቅ እና ነዳጅ እንዲሁም የመገናኛ መሳሪያዎቸን በእርዳታ ስም እንደልብ እንዲያገኝ እና እንዲጠናከር ነው ያደረገው። የአለም አቀፉ ህብረተሰብም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ከኢትዮጵያ  በተፃራሪው ጎን በመቆም የሚችለውን ሁሉ አፍራሽ ደርጊት ከማድረግ ወደኋላ አላለም። እንደ አሜሪካ ያሉ ሀገርም መንግስትን ለመገልብጥ ወደ ኋላ እንደማይሉ በተግባር አሳይተዋል። ሰለዚህ ጦሩ ወደ መቀሌ ባለመግባቱ ማን ነው ያተረፈው???

በመሰረቱ ውሳኔው ሲሰጥ ሶስት መሰረታዊ ክፍተቶች ነበሩ ። ለዚህም ነው ውሳኔው አስከፊ ውጤቶችን አስከትሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠር የንፁሀንን ሕይወት እንዲቀጠፍ ፣በሚሊየን የሚቆጠሩ ወገኖቻቸን ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ እና በቢሊየን ዶላር የሚቆጠር ንብረት እንዲወድም ያደረገው። የነበሩት ክፍተቶችም፣

  • መንግስት በተሳሳተ መረጃ ጁንታው ለኢትዮጵያ ዳግም ስጋት እንዳይሆን ተደርጎ ተደምስሷል በሚል ለጁንታው የሰጠው አነስተኛ ግምት ያስከፈለው ዋጋ፣
  • መንግስት ወቀሌ ከተቆጣጠረ በኋላ መላውን ትግራይን በአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ አድርጎ በኮማንድ ፖስት የማረጋጋት እርምጃ ማድረግ ሲገባው የጊዜያዊ አስተዳድር በመሾሙ ድሉን እንዲቀለበስ ምክንያት መሆኑ፣
  • መንግስት ከመቀሌው ድል በኋላ ባንዳዎችን የማጥራት እርምጃ እና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሕወሀት እና ከኢሀድግ ጋር የጥቅም ግንኙነት ያላቸውን ግለሰቦች ላይ ልዩ ክትትል በማድረግ እንቅስቃሴያቸውን መገደብ ሲገባው በነፃነት በመለቀቃችው በአንድም በሌላ መልኩ ጁንታው እንዲጠናከር እና ብዙ የኢትዮጵያ ቦታውችን እንዲቆጣጠር ማድረጉ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  አውስትራሊያን ከኢትዮጵያ ጋር የማመሳሰል ሕልም

የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት  የአፈፃፀም ስህተትም እንደሚያሳየው  ጦርነቱ ከአለቀ በኋላ ከ 17 አመት በላይ ሰላምም ጦርነትም በሌለበት ሁኔታ ጦሩ ድንበር ላይ ሰፍሮ በመቆየቱ ምንም መፍትሔ ሳያመጣ ምን ያህል ዋጋ እንዳስከፈለን ይታወቃል።

ስለዚህ ከስህተታችን ተምረን አሁን ያለውን የሰራዊታችንን አስተማማኝ ድል እና የተፈጠረውን አጋጣሚ ተጠቅመን ጦርነቱን አሁን መቋጨት ካልቻልን መቼ እና እንዴት ተደርጎ ነው ዘላቂ ሰላም የሚመጣው? ኢኮኖሚያችንስ ያንን ለመሸከም የሚችል አቅም አለው ወይ? ሕዝቡስ በኑሮ ውድነት እና በጦርነት አዙሪት ወስጥ ሆኖ እስከ መቼ ነው የሚቆየው?

እውነቱን እንነጋገር ካልን  መቼም ጦርነት ነው የሀገር አንድነት እና በሀገር ላይ ያንዣበበውን አደጋ መቀልበስ ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑ ነው እንጂ በልቶ ማደር የተቸገረውን ህዝብ ብዛት የእያንዳንዱ ቤት ይቁጠረው። ይሄስ እስክመቼስ ይህ መቀጠል አለበት?

የመንግስትን ሰጋት እና ጦሩ ወደ መቀሌ እንጋይገባ የተሰጡትን ምክንያቶች በተወሰነ መልኩ እጋራለሁ ። ግን ጦሩ መቀሌ ባለመግባቱ ጁንታው የተለያዩ አሻጥሮችን ከመስራት ይቆጠባል? ወደ ትግራይ የሚገባውን እርዳታ እና የእርዳታ ድርጀቶች የሚሰጡትን መልካም አጋጣሚዎችን በመጠቀምስ እንደገና እንደማያንሰራራ ምንድነው መተማመኛው? የተፈራውስ የአለም አቀፉ ተፅዕኖ ይቀራል? ያን ሁሉ የእርዳታ እህል ይዞ የተጓዙትን መኪኖች አግቶ ለጦርነት ሲያውል የአለም አቀፉ ምላሽ ምን ነበር? ጁንታው በአማራ እና በአፋር ላይ ላደረሰው ኢሰብአዊ ድርጊት እና ውድመትስ የአለም አቀፉ ሕብረተሰብ ምን አለ? የአለም አቀፉ እና የኢትጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በጋራ ያወጡትን የምርመራ ውጢትን ለመቀልበስ የአውሮፓ ህብረት እና የአሜሪክ መንግስት የሄዱበት እርቅት ለተገነዘበ ከነሱ ምን ይጠብቃል? አውቆ የተኛን እንደሚሉት አሜሪካ እና ተባባሪዎቿ በሁሉም መልኩ አትዮጵያን ለማፈራረስ ቆርጠው ሰለተነሱ የነሱን ተፅዕኖ መቋቋም የሚቻለው እንደጀመርነው አንድነታችንን አጠናክረን ሁላችንም በምንችለው አቅም አንድ ሆነን ወደፊት በመጋፈጥ እንጂ ለነሱ ድንጋይ በማቀበል አይደለም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕዝብ ሆይ! እንደማመጥ እንጅ! ጋሰለ አረሩ፤ አዴፓ ብአዴን፤ ብልጽግናም ይህ አድግ ነው!  

ሰለዚህ ለተጀመረው ጦርነት በማንኛውም መንገድ መቋጫ ማበጀት የግድ ይላል። እንደ እኔ አስተሳሰብ የሚሻለው መፍትሔ።

1ኛ/  መከላከያው ወደፊት በመገስገስ መላው ትግራይን መቆጣጠር ። የአማራ እና የአፋር ልዩ ሀይል እንዲሁም ፋኖ ከኋላ ደጀን ሆኖ  እንዲቆይ።

2ኛ/  በወንጀል የሚፈለጉ እና ለጦርነቱ ምክንያት የሆኑትን የጁንታውን ከፍተኛ እና መካከእኛ አመራሮችን በሙሉ ለፍርድ ማቅረብ

3ኛ/ ትግራይን ለአንድ አመት ላልበለጠ ጊዜ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የኮማንድ ፖስት ወስጥ በማቆየት የትግራይ ህዝብ እውነተኛ የጥሞና ጊዜ እንዲያገኝ እና ቀጣይ እድሉን እንዲወስን ማመቻቸት።

4ኛ/ አለማቀፍ ህጉ በሚፈቅደው ህግ መሰረት የትግራይ ህዝብ በሪፈረንደም ውሳኔ እንዲሰጥ ማድረግ። በአሁን ሰአት ይህ ሳይደረግ ቢቀር በእርግጠኛ የምናገረው ወደፊት በዙ መስዋእት አስከፍሎ ፍፃሜው ሪፈረንደም መሆኑ የማይቀር ነው።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!

ወገን ደጀን ነኝ ከአውስትራሊያ

 

1 Comment

  1. I am sorry to say but I have to say that it is very embarrassing to see our intellectuals being victims of very shallow, emotion-driven, highly skewed, short-sighted, unproductive, and above all opportunistic way of dealing with a highly toxic and deadly political system of ethnic identity. Needless to say, the system created by TPLF a long time ago and became constitutional and operational three decades ago has continued with no meaningful elements of a desirable change.
    The only difference is that those who had been very instrumental in carrying out the policies and programs of the deadly politics of ethnic identity took over the throne by purged out their creator and master (TPLF). They kept the very chronically ill system in a much worse manner of bitterness and scope under their hegemonic control of power simply by renaming themselves as Prosperity, a name directly driven from a religious sect which is the product of a highly deceptive or misleading way of interpretation of the Great BOOK (the Bible).
    Yes, TPLF should be hold responsible and accountable for what it did and what it is doing and must be rejected and defeated if a democratic and peaceful Ethiopia should become a reality. But it is politically stupid and morally bankrupt not to reject and defeat those who let the very deadly criminal political system of TPLF/EPRDF continue under their much more ruthless hegemonic political grab.
    Outrageously enough, many of our intellectuals totally lost the very real sense and value of intellectualism which is supposed to rescue society from any catastrophic situation, including a political system of tyranny of ethnocentrism.
    I hate to say but I have to say that it is painful to witness many compatriots including well–educated and experienced intellectuals being victims of losing or abandoning the very demand of the people for a change of a fundamental democratic political system, not to see the continuation of the same if not a much worse political system of ethnocentrism driven by a faction of EPRDF.
    Yes, it is embarrassing to witness those intellectuals being victims of the very dirty politics of blaming others whereas losing the courage to stay firm on the very principle and objective of making a truly democratic society by forcing those who keep playing a very hypocritical, cynical, conspiratorial, dishonest, and above all criminal political game either to come to the negotiating table or getting rid of them with a legitimate and well-organized political action of the people.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share