ለአማራ የሕልውና ፈተና የአማራ ልሂቃን ሚና – መስፍን አረጋ

Amhara
amhara

የአፍሪቃውያንን ሕልውና ለማረጋገጥ የበኩሉን ከፍተኛ ሚና የተጫወተው ትልቁ የአማራ ሕዝብ፣ ዛሬ ላይ ግን ነገሮች ተገልብጠው የገዛ ራሱን ሕልውና ለማረጋገጥ የሞት ሽረት ትግል እያደረገና የአፍሪቃውያንን ድጋፍ እየጠየቀ ይገኛል፡፡  እጅጉን የሚያሳዝነው ደግሞ የአውሮጳ ቅኝ ገዥወችን በጀግንነት መክቶ፣ አሳፍሮ በመመለስ የራሱን ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ሕልውና ያረጋገጠው ጀግናው የአማራ ሕዝብ፣ ሕልውናው ጥያቄ ውስጥ የገባው፣ እዚህ ግቡ በማይባሉ አገር በቀል ጎጠኞች መሆኑ ነው፡፡  ስለዚህም፣ የአማራን የሕልውና ፈተና በተመለከተ አንገብጋቢው ጥያቄ የሚከተለው ነው፡፡  ጥያቄውም ትናንሾቹ ጎጠኞች የትልቁን የአማራን ሕዝብ ሕልውና ጥያቄ ውስጥ ሊያስገቡ የቻሉበት ምክኒያት ምንድን ነው የሚለው ነው፡፡

ጠላት የሚገባው በደካማ ጎን ስለሆነ፣ የሽንፈት መንስዔው የራስ ድክመት እንጅ የጠላት ጥንካሬ አይደለም፡፡  ስለዚህም፣ የአማራ ሕዝብ ሕልውና ጥያቄ ውስጥ የገባው ከራሱ ከአማራ ሕዝብ በመነጨ ድክምት እንጅ በጎጠኞች ጥንካሬ አይደለም፡፡  በኔ በመስፍን አረጋ አመለካከት ደግሞ የአማራን ሕዝብ ለጎጠኞች እንዲጋለጥና ሕልውናው ጥያቄ ላይ እንዲወድቅ ያደረጉት ከአማራ ሕዝብ የፈለቁ ልሂቆች ወይም ልሂቅ ነን ባዮች ናቸው፡፡  የአማራን ሕዝብ ሕልውና ፈተና ውስጥ ለማስገባት ትልቁን ሚና የተጫወቱት ከአማራ ሕዝብ የፈለቁ፣ ጉራማይሌ ስለተናገሩ ብቻ ልሂቅነት የሚሰማቸው፣ ቢከፍቷቸው ተልባ የሆኑ የራሱ የአማራ ሕዝብ ጉዶች ናቸው፡፡   የአማራን ሕዝብ በጎጠኞች ያስጠቁት ደግሞ፣ ጎጠኞችን መደገፍን ከምሁርነት ስለሚቆጥሩ፣ ወይም ደግሞ የጎጠኞችን ነቀፋና ዘለፋ ስለሚፈሩ፣ ወይም ደግሞ ለሆዳቸው ብቻ የሚያድሩ ሆዳደሮች ስለሆኑ፣ ወይም ደግሞ በአማራነታቸው የሚያፍሩ ወይም እንዲያፍሩ የተደረጉ ራስጠሎች ስለሆኑ ነው፡፡  ለምሳሌ ያህል ትልቁን የጎጠኞች ባለውለታ ዋለልኝ መኮንንን ብንወስድ፣ በወሎ አማረኛው ይሳቅበት ስለነበር፣ በንግሊዘኛ እንጅ ባማረኛ አታናግሩኝ እስከሚል ደረስ በማንነት ቀውስ ውስጥ ገብቶ ራሱን እንዲጠላ የተደረገ ፀራማራ ጥራዝነጠቅ ነበር፡፡

የአማራ ልሂቆች ወይም ልሂቅ ነን ባዮች፣ የሕዝባቸውን ችግር ለመፍታት የራሳቸውን አጀንዳ ከመቅረጽ ይልቅ፣ ዋና ሥራቸው የጎጠኝነት ልሂቆች በተለይም ደግሞ የትግሬ ልሂቆች በሚሰጧቸው አጀንዳወች ላይ መፈትፈት ነው፡፡  የትግሬ ልሂቆች ስለ ብሔረሰብ መብት ሲናገሩ፣ እነሱም ተከትለው ስለ ብሔረሰብ መብት የሚደሰኩሩ፣ ስለ ፌዴሬሽን አደረጃጀት ሲያወሩ እነሱም ተከትለው ስለ ፌዴሬሽን ዓይነቶች የሚያብራሩ፣ ስለ ኮንፌዴሬሽን ጥቅሞች ሲደረድሩ ስለ ኮንፌዴሬሽን አመሠራረት ለማስተማር የሚሞክሩ፣ ባጠቃላይ ደግሞ የትግሬ ልሂቆች የሚሰጧቸውን ሁሉ ሳያላምጡ ውጠው በአማራ ሕዝብ ላይ የሚያቀረሹ ናቸው፡፡

የትግሬ ሕዝብ ቁጥሩ ከሱማሌና ከወላይታ ሕዝብ የሚያንስ ንዑስ ሕዝብ (minority) ነው፡፡  የትግሬ ልሂቆች ግን አኳኋናቸው ሁሉ እንወክለዋለን የሚሉት የትግሬ ሕዝብ የኢትዮጵያ ብዙሃን የሆነ ያህል ነው፡፡  እንዲህ የሚሆኑት ደግሞ የኢትዮጵያ ብዙሃን ከሆነው የአማራ ሕዝብ የሚፈልቁትን ልሂቆች አጅግ ስለሚንቋቸው ነው፡፡  እጅግ የሚንቋቸው ደግሞ ጎጠኞችን በመደገፍ ስልጡን መስለው ለመታየት የሚጥሩ ተመጻዳቂወች፣ ወይም ደግሞ ጎመን በጤና የሚሉ አድርባዮች መሆናቸውን በደንብ ስለሚያውቁ ነው፡፡  አለበለዚያማ በአማራ ልሂቃን መኻል ያደጉት እነ መለስ ዜናዊ፣ አማራን እናጠፋለን ብለው በይፋ ለመለፈፍ (ማኒፌስቶ ለማውጣት) ባልደፈሩ ነበር፡፡

አገር የምትቆመው አገር አፍራሾችን በሁሉም ግንባሮች በጽኑ በመዋጋት እንጅ በመለማመጥ አይደለም፡፡  አብናቶቻችን (አባቶቻቸንና እናቶቻችን) እንደሚሉት እንጨት ሳይቆረጥ ቤት አይሠራም፡፡   አገርን የሚያህል ትልቅ ቤት የሚሠራው ደግሞ እልፍ አእላፍ አገር አፍራሽ እንጨቶችን በመቆራረጥ ነው፡፡  ለምሳሌ ያህል አጤ ቴድሮስ የኢትዮጵያን የአንድነት ቤት በድጋሚ የገነቡት የትግሬውን ደጃች ውቤን የመሳሰሉ ትላልቅ አገር አፍራሽ እንጨቶችን ቆራርጠው ነበር፡፡

አገር አፍራሽ ጎጠኞች ጋር መደራደር ወይም መከራከር ማለት አገር አፍራሽነትን ማበረታታት ማለት ነው፡፡  አገር አፍራሽ ጎጠኞች ይቀየማሉ በማለት ሊነገራቸው የሚገባቸውን ሁሉ በግልጽ አለመንገር ደግሞ የአገር አፍራሾቹ አጋር መሆን ነው፡፡  አብዛኞቹ የትግሬ ልሂቆች ደግሞ ትሕትናና ጨዋነትን እንደ ሰናይ ፀጋወች (virtues) ሳይሆን እንደ ፈሪነት የሚመለከቱ፣ አፋቸው ለከት የሌለው ስዶች ናቸው፡፡  አማራን ሲሳደቡና፣ የአማራ ናቸው የሚሏቸውን ትውፊቶች ሲያንቋሽሹ ደም የሚያሸኑ ፀያፍ ቃሎችን የሚጠቀሙት፣ በነሱ እይታ አፈ ክፍትነት ልበ ቆራጥነትን ስለሚያሳይ ነው፡፡

ስለዚህም እነዚህ ጨዋነትን ከፈሪነት የሚቆጥሩ፣ ንዑስነታቸውን ረስተው መረን የለቀቁ የትግሬ ልሂቆች እንዲገባቸው ከተፈለገ፣ በሚገባቸው ቋንቋ ቋቅ እስኪላቸው መነገር አለባቸው፡፡  በተለይም ደግሞ የንዑስነታቸውን ልክ እንዲያውቁና፣ ንዑስ ሁነው ብዙሁን የአማራን ሕዝብ እናጠፋለን ቢሉ ራሳቸው እንደሚጠፉ በማያሻማ ቋንቋ በግልጽና በይፋ ሊነገራቸው ይገባል፡፡  አጥፊን ሳያጠፋ በፊት ማጥፋት አልሞት ባይ ተጋዳይነት ስለሆነ በምድርም በመሰማይም አያስጠይቅም፡፡

የትግሬ ልሂቆች ኢትዮጵያ መተዳደር ያለባት በፌዴሬሽን ወይም በኮንፌደሬሽን ነው የሚል አጀንዳ ሲያመጡ፣ እንሱ ባመጡት አጀንዳ ላይ ከመከራከር ይልቅ፣ ኢትዮጵያ የምትተዳደርበትን ስርዓት የሚመርጠው የኢትዮጵያ ብዙሃን ሕዝብ እንጅ እናንተ ንዑሶቹ አይደላችሁም የሚል ቁርጥ ያለ መልስ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡  ንዑስ ስለሆናችሁ ብዙሃኑ ሕዝብ የምተዳደረው በአሃዳዊ ስርዓት ነው ብሎ ከወሰነ፣ ወደዳችሁም ጠላችሁም የብዙሃኑን ውሳኔ በመቀበል በአሃዳዊ ስርዓት መተዳደር አለባችሁ፡፡  ማድረግ የምትችሉት በዚህ ብዙሃኑ በመረጠው አሃዳዊ ስርዓት ውስጥ የንዑስነት መብታችሁ እንዳይጣስ መታገል ብቻ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብዙሃን ሕዝብ በመረጠው አሃዳዊ ስርዓት ውስጥ አልተዳደርም ካላችሁ ደግሞ ሂዱ፣ መንገዱን ጨርቅ ያርግላችሁ ሊባሉ ይገባል፡፡  መንገዱን ጨርቅ ያርግላችሁ ተብለው ሲሸኙ ደግሞ ወልቃይትና ራያ ቀርቶ ተንቤንም አጠያያቂ እንደሆነና፣ ሽሬም የነሱ ሳይሆን የኩናማ መሆኑ ሊነገራቸው ይገባል፡፡  መሸኘት ያለባቸው ደግሞ ኢትዮጵያ የጨዋ ሕዝብ መኖርያ ቤት እንጅ እንዳሻቸው የሚገቡባትና የሚወጡባት መሸታ ቤት እንዳልሆነች አውቀው ባንዴና በመጨረሻ ሽኝት ነው፡፡

ሕገመንግሥትን በተመለከተ ደግሞ፣ የትግሬ ልሂቆች ከወያኔ የጫካ ሰነድ አንዲት ቃል አትለወጥም እያሉ ሲፎክሩ፣ ኢትዮጰያ የምትተዳደርበትን ሕገ መንግሥት የሚመርጠው የኢትዮጵያ ብዙሃን ሕዝብ እንጅ እናነት ንዑሶቹ አይደላችሁም፡፡  ኢትዮጵዊነትን እስከመረጣችሁ ድረስ ብዙሃኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚመሠርተው ሕገመንግሥት ሥር መተዳደር የውዴታ ግዴታችሁ ነው፡፡  ማድረግ የምትችሉት የብዙሃኑ ሕገመንግሥት የናንተን ዓይነት የንዑሶችን መብት እንዳማይጋፋ ማረጋገጥ ብቻ ነው እየተባሉ እስኪገባቸው ድረስ ሊነገሩ ይገባል፡፡

ሰፊው የትግሬ ሕዝብ ፀራማራ አይደለም፣ በፊትም አልነበረም፣ ወደፊትም አይሆንም፡፡  ባለመታደል ግን  ሰፊው የትግሬ ሕዝብ የሚዘወረው ወያኔ በዘራው የአማራ ጥላቻ ተመርዘው በሰከሩ የትግሬ ልሂቆች ነው፡፡   የነዚህ የትግሬ ልሂቆች ፀራማራ ስካር ደግሞ እየባሰ እንጅ እየበረደ አልሄደም፡፡  በአሁኑ አያያዙ ደግሞ መቸም የሚበርድ አይመስልም፡፡  ስለዚህም ሰፊው የትግራይ ሕዝብ ቢያንስ ቢያንስ ለሚቀጥሉት ሃምሳ ዓመታት የሚዘወረው ፀራማራ ስካራቸው እየባሰ በሚሄድ ሰካራም ልሂቆች ነው ማለት ነው፡፡  በመሆኑም የአማራ ሕዝብ የሚከተለውን መሠረታዊ ጥያቄ ራሱን በራሱ ደጋግሞ ሊጠይቅ ይገባል፡፡  ጥያቄውም የትግሬ ሕዝብ ወንድሜ ቢሆንም፣ በአማራ ጥላቻ በታወሩ የትግሬ ልሂቆች ከሚዘወረው ከዚህ ወንድሜ ከሆነ ከትግሬ ሕዝብ ጋር ባንድ አገር ውስጥ አብሬ መኖሬ የሚያስገኝልኝ ጥቅም ምንድን ነው የሚለው ነው፡፡

በኔ እይታ ደግሞ ከአጋም እንደተጠጋ ቁልቋል ዘላለም ከማልቀስ በስተቀር ያገኘውና ወደፊትም የሚያገኘው ምንም ጥቅም የለም፡፡  ባንድ ቀን ጀንበር ሚሊየነሮችና ቢሊየነሮች የሆኑባትን፣ ሁሉን በጃቸው በደጃቸው አድርገው ለሃያ ሰባት ዓመታት የፈነጩባትን፣ አማራዊ ናት የሚሏትን ኢትዮጵያን እጅግ ከመጥላታቸው የተነሳ፣ ስሟ በመታወቂያ ላይ እንኳን እንዳይጻፍ የከለከሉ ጉዶች፣ ንዑስነታችሁ ተከብሮላችሁ እንደ ንዑስነታችሁ ኑሩ ሲባሉ፣ ኢትዮጵያዊነታቸውን ሊወዱ የሚችሉበት ሁኔታ በጭራሽ አይታየኝም፡፡  ኢትዮጵያን በበላይነት እየገዙ ኢትዮጵያን ከጠሉ፣ በእኩልነት እየኖሩ ኢትዮጵያን ሊወዱ አይችሉም፡፡

የአማራ ሕዝብ እይታው ሩቅ፣ አውዱ ሰፊ የሆነ፣ ከኢትዮጵያ አልፎ ሁላፍሪቀኝነትን (panafricanism) የሚያቀነቅን፣ በጥቁርነቱ የሚኮራ፣ ነጭን ከመጤፍ የማይቆጥር፣ ቅኝ ገዥወችን እንቅልፍ የሚነሳ ጥቁር ብሔርተኛ (black nationalist) ሕዝብ ነው፡፡  አሁንም ቢሆን በአማራነት የተነሳው ጎጠኛ ሁኖ ሳይሆን፣ የጥቁር ሕዝብ ነጻነትና ሉዓላዊነት ተምሳሌት የሆነችውን ኢትዮጵያን  ማዳን የሚችልበት ሌላ ምርጫ ስላጣ ብቻ ነው፡፡  ምዕራባውያንም አማራን ብቻ መርጠው ነክሰው የያዙበት ምክኒያት የአማራ ብሔርተኝነት ከኢትዮጵያ ብሔርተኝነት አልፎ የአፍሪቃ ብሔርተኝነት እንደሆነ ስለሚያውቁ ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የትግሬና የኦሮሞ ጎጠኞች ከአማራ ሕዝብ ጋር በጥቁርነታቸው እየኮሩ ከመኖር ይልቅ የነጭ ባርያ መሆንን የሚመርጡ ነጭ አምላኪወች ናቸው፡፡  በተለይም ደግሞ የትግሬ ልሂቆችን የመሰለ፣ ለነጮች የሚንከባለል የነጭ አሽቃባጭ የትም ዓለም ላይ የሚገኝ አይመስለኝም፡፡  ነጮች እግራቸው እስኪነቃ ቢሄዱ፣ ወያኔን የመሰለ ሎሌ አያገኙም፣ እንደማያገኙም በደንብ ያውቁታል፡፡  የአጼ ምኒሊክ የአድዋ ድል እንደ እግር እሳት ይለበልበው የነበረው፣ ነምሳዊው (Austro-Hungarian Empire) የናዚ ባላባት (baron) ሮማን ፕሮቻዝካ (Roman Prochazka)

የጦቢያን አያሌ ብሔረሰቦች የነጭ ባርያ የመሆን ምርጫቸውን የነፈጓቸው፣ ዓላማቸው በነጭ የባህል  (እና የሐይማኖት) ወረራ መቃብር ላይ የጥቁርን ልዕልና መገንባት የሆነው የሐበሻ መሪወች ናቸው፡፡ (The numerous tribes who inhabit the Ethiopian state are being forcibly kept from European colonialism by Abyssinian rulers whose aim is to act as champions of all black people so as to attack and destroy Western culture)

በማለት የጻፈው የጊዜወቹን የትግሬና የኦሮሞ ባላባቶች ለነጭ ባርያ የመሆን ምርጫ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነበር፡፡  አደገኛው ጥቁር (die Schwarze Gefahr) በሚል ርዕስ በጀርመንኛ የጻፈው መጽሐፍ ፍሬ ሐሳብ ደግሞ በጥቁርነታቸው የሚኮሩት የጥቁሮች አገር ጦቢያ፣ ለነጭ ዘር መቅሰፍት ስለሆነች፣ ባገር በቀል ጎጠኞች ተጎጥጉጣ መገነጣጠል አለባት የሚለው ነው፡፡

ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ከነዚህ ነጭ አምላኪ ጎጠኞች ባንድም በሌላም መንገድ ተላቀቀ ማለት፣ ፕሮቻዝካ እንዳለው በነጭ የባሕልና የሐይማኖት ወረራ መቃብር ላይ ሐይማኖቱን፣ ባሕሉን፣ ቋንቋውንና ሌሎች ድንቅ እሴቶችን ባፍሪቃ ውስጥ ለማስፋፋት እንቅፋቶቹ ተወገዱለት ማለት ነው፡፡

ለምሳሌ ያህል ቋንቋ ላይ ብቻ እናተኩርና አማረኛንና ኪስዋሂሊን እናነጻጽር፡፡  ኪስዋሂሊ የተፈጠረው ታንጋኒካ በምትባለው በታንዛንያ ንዑስ ደሴት ውስጥ በሚኖሩ ንዑሶች ነው፡፡  ኬንያውያንና ታንዛንያውያን ግን ቅን ሕዝቦች ስለሆኑ፣ ኪስዋሂሊ አፍሪቃዊ ቋንቋ መሆኑን እንጅ የንዑስ ቋንቋነቱን ሳይመለከቱ፣ አስፋፉትና የቅኝ ገዥወችን ቋንቋ ለማስወገድ ተጠቀሙበት፡፡ ኪስዋሂሊም የምሥራቅ አፍሪቃ ወልቋንቋ (lingua franca) ለመሆን በቃ፡፡ የትግሬ ልሂቆች ግን ትልቁ ምኞታቸው፣ እንዳበጁት የሚበጀውን ትልቁን ቋንቋ አማረኛን አጥፍተው፣ ባምላኮቻቸው ቋንቋ በእንግሊዘኛ ለመተካት ነው፡፡  አፍሪቃውያን እንግሊዘኛን ካፍሪቃ ለማጥፋት በሚጥሩበት ዘመን፣ የኢትዮጵያን የሥራ ቋንቋ እንግሊዘኛ ለማድረግ ዘመቻ የከፈቱትም በዚሁ ምክኒያት ነው፡፡   እንግሊዝን ደግሞ አሁን ላይ ቀጥ አድርጎ የያዛት ምርቷ ወይም ቴክኖሎጂዋ ሳይሆን እንግሊዘኛ ስለሆነና፣ እንግሊዘኛ የዓለማችን የወል ቋንቋ ባይሆን ባጭር ጊዜ ውስጥ የድሃወች ድሃ እንደምትሆን ስለምታውቅ፣ ወያኔን የመሰሉ አማረኛ ጠል እንግሊዘኛ አምላኪወችን በጽኑ ብትደግፍ አይፈረድባትም፡፡

የትግሬ ልሂቆች ልሂቅነታቸውን የሚያሳዩት ባማራ ጥላቻቸው ስለሆነ፣ ማናቸውም ድርጊት አማራን ኢምንት የሚጎዳ እስከሆነ ድረስ የትግሬን ሕዝብ እጅግ ቢጎዳም ከበሮ ያነሱለታል፡፡  ማናቸውም እሳት አማራን በወላፈኑ እስከገረፈ ድረስ ትግሬን የሚያንጨረጭር ቢሆንም እሳቱን ለመለኮስ፣ ለኩሰው ለማቀጣጠል፣ አቀጣጥለው ለማንቦግቦግ አያንገራግሩም፡፡  ያማራ ደሳሳ ጎጆ እስከፈረሰ ድረስ የትግሬ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ቢደረመስ፣ ያማራ ሐብት እስከተዘገነ ድረስ የትግሬ ሐብት ቢታፈስ፣ ያማራ ስም እስከጠለሸ ድረስ የትግሬ ሐበሻዊ ስም ቢጠቀርሽ፣ የአማራ ሐይማኖት፣ ባህል፣ ቋንቋና ፊደል እስከጠፋ ድረስ የትግሬ ሐይማኖት፣ ባህል፣ ቋንቋና ፊደል ቢጠፋ፣ ባጠቃላይ ደግሞ ያማራ አንድ ዓይን እስከጠፋ ድረስ የትግሬ ሁለቱም ቢደረገም ዴንታ የላቸውም፡፡  ደስታ የሚያገኙት በአማራ ሕዝብ ሐዘን እንጅ በትግሬ ሕዝብ ሐሴት አይደለም፡፡  አንድ የአማራ ቀበሌ ተቆጣጠርን በማለት በፈረንጅ ጌቶቻቸው ለመደነቅ ሲሉ ብቻ፣ አስር ሺ የትግሬ ወጣቶችን ፈንጅ የሚያስረግጡ፣ ጭካኔያቸው ወደር የሌለው አረመኔወች ናቸው፡፡  አማራንና አማራነትን ይጠላሉ እንጅ ትግሬንና ትግሬነትን አይወዱም፡፡  እንዲያውም የሚያፍሩበት ይመስለኛል፡፡

ለምሳሌ ያህል የወያኔ ልሂቆች ከኦነግ ልሂቆች ጋር የመሠረቱትን ያልተቀደሰ ጋብቻ እንመልከት፡፡  የኦነጋውያን እሳት አማራን ቢበላ፣ ቀጥሎ የሚበላው ትግሬን እንደሆነ የትግሬ ልሂቆች በርግጠኝነት ያውቃሉ፡፡  እያወቁ ግን እሳቱን ለማንቀልቀል ይንቀለቀላሉ፣ ለነሱ የሚታያቸው የአማራ ሕዝብ በእሳቱ መለብለብ እንጅ የትግሬ ሕዝብ በእሳቱ መንጨርጨር አይደለምና፡፡    ኦነጋውያን አዲሳባ የኦሮሞ ናት ሲሉ፣ የትግሬ ልሂቆች ምንትሳቸው ቄጠማ ይቆርጣል፡፡  ይህን የሚያደርጉት ደግሞ አብዛኞቹ የአዲስ አበባ ሕንጻወች፣ ትግሬወች በወያኔ ዘመን የገነቧቸው የምዝበራ ውጤቶች እንደሆኑና፣  የኦነጋውያን እቅድ ቢሳካ ከማንም በላይ የሚጎዱት ትግሬወች እንደሆኑ በደንብ እያወቁ ነው፡፡  እነሱን የሚያስደስታቸው የአማራ መደህየት እንጅ የትግሬ መበልጸግ አይደለምና፡፡

አንድነት (unity) ኃይል የሚሆነው የአንድነት መንፈስ ሲኖር ነው፡፡  የትግሬ ለሂቆች ግን ከአማራ ሕዝብ ጋር ያንድነት መንፈስ እንዳይኖራቸው፣ ወያኔ ፀራማራ መርፌ ክንዳቸው ላይ መውጋት ብቻ ሳይሆን፣ ያልተገራውን አፋቸውንና ረዥም ምላሳቸውን ጨምሮ ሁለመናቸውን ጠቅጥቋቸዋል፡፡  ስለዚህም ሰፊው የአማራ ሕዝብ ሆይ፣ ባንድነት በመኖር ላይ ብቻ አተኩረህ፣ ካንተ ጋር የአንድነት መንፈስ የሌላቸውንና መቸም የማይኖራቸውን እነዚህን እሾሃም አጋሞች አስጠግተህ፣  ምዕራባውያን እፍ ባሏቸው ቁጥር በንፋሱ ታግዘው በእሾሃቸው እየወጉህ፣ እንደ ብሂሉ ቁልቋል ደምህን እያፈሰሰክ ስታለቅስ የምትኖረው እሰከመቸ ድረስ ነው?

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

1 Comment

 1. ከአምሃራ ልሂቃን መሓል ነኝ የሚለው መስፍኔ ዛሬ ደግሞ እንዲህ ብሏል፦
  “የአፍሪቃውያንን ሕልውና ለማረጋገጥ የበኩሉን ከፍተኛ ሚና የተጫወተው ትልቁ የአማራ ሕዝብ (በከፊሉ እውነት ነው)…የአውሮጳ ቅኝ ገዥወችን በጀግንነት መክቶ፣ አሳፍሮ በመመለስ የራሱን ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ሕልውና ያረጋገጠው ጀግናው የአማራ ሕዝብ…” (ውሸት ነው)።
  “የትግሬና የኦሮሞ ጎጠኞች ከአማራ ሕዝብ ጋር በጥቁርነታቸው እየኮሩ ከመኖር ይልቅ የነጭ ባርያ መሆንን የሚመርጡ ነጭ አምላኪወች ናቸው፡፡
  ስለ አድዋ ጦርነት እንደ ሆነ የሚያወራው፣ ትክክሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው! (የምንሊክን ጦር አዝማቾች ስም መዘርዘር ጊዜ ይፈጃል፤ መስፍኔ ጎጠኛ ጎጠኛ ይላል፤ ራሱ ጎጠኛ እንደ ሆነ አላወቀም!)

  “… አማረኛንና ኪስዋሂሊን እናነጻጽር፡፡ ኪስዋሂሊ የተፈጠረው ታንጋኒካ በምትባለው በታንዛንያ ንዑስ ደሴት ውስጥ በሚኖሩ ንዑሶች ነው (ውሸት ነው)፡፡ ኬንያውያንና ታንዛንያውያን ግን ቅን ሕዝቦች ስለሆኑ” (ቅን ሕዝቦች የሚላቸው ውሸቱን እንዲደግፍለት ነው)፣

  “ኪስዋሂሊ አፍሪቃዊ ቋንቋ መሆኑን እንጅ የንዑስ ቋንቋነቱን ሳይመለከቱ፣ አስፋፉትና የቅኝ ገዥወችን ቋንቋ ለማስወገድ ተጠቀሙበት (ውሸት ነው፤ መስፍኔ ሰነፍ እና ዘረኛ ሆኖ እንጂ እንግሊዝኛ ቋንቋ በጠቀሳቸው አገራት ያለውን ሚና ባላጣው ነበር)፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.