ወሳኝ ጥያቄዎች ለአብይ አህምድ አፍቃሪዎች – ሰርፀ ደስታ

ዛሬ በአገራችን እየሆነ ያለውን እንዳይሆን በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ልንሰጥ የሞከርን ጥቂትም ብንሆን ነበርን፡፡ ሆኖም በሴራ አድጎ በሴራ የጎለመሰ ቡድን የገዛ ሴራው ይዞት እስከሚጠፋ ድረስ እንዳያስተውል የገዛ ክፋቱ አእምሮውን ያጨልምበታል፡፡ ታላቁ ፈላስፋ እግዚአብሔርን (እውነትን) ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን ለማይረባ የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ይላል፡፡ ይሄ የፈላስፋው ንግግር ሁሌም ይገረመኛል፡፡ ከኖህ ዘመን ጅምሮ ሰዎች ሞታቸው ከፊታቸው ቀርቦ እያዩ እንኳን እንዳያስተውሉ የሆኑበትን አንብበናል፡፡ ዛሬ በአገራችን እየሆነ ያለውን ሳሰብ እጅግ ይገርመኛል፡፡ እየገረመኝ ያለው የሴራው መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ አጫፋሪዎቹ ናቸው፡፡ አብይ አህመድ ኢትዮጵያነና ኢትዮጵያዊነትን ስልጣን ከያዘባት ቀን አንድ ጀምሮ በተግባር እያጠፋ አይናችን እያየ ብዙዎች የሚያዩትን የአብይ አህመድ ጸረኢትዮጵያዊነት እውነት ሳይሆን በአብይ አህመድ አዚም ተለክፈው የማይታየው የአብይ አህመድ ኢትዮጵያዊነት በግድ ለማየት የፈልጋሉ፡፡ እስኪ ልቦናችሁ ጭላንጭል ነገር ቢኖረውና እወነት ወደ ውስጣችሁ ቢገባ የሚከተሉትን የአብይ አህመድ ኢትዮጵያን የማፍረስና የኦነጋውያንን ሥርዓት የመተካት ሴራዎች በጥያቄ መልክ ላቅርብ ላቅርብ፡፡ እንግዲህ የማነሳቸው አብይ አህመድ በቀጥታ ራሱ ያደረጋቸውን ወይም አዞ ያስፈጸማቸውን ጥቂቶቹን ለማሳያ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡ይህ ባንክ ዛሬ እየተመራ ያው ከኦሮሚያ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ መስራች፣ ባለድርሻና የዚሁ ባንክ የቀድሞ ሥራ አስኪያች ነው፡፡

ለመሆኑ አብይ አህመድ ይሄን ግለሰብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥራ አስኪያጅ አድርጎ ሲሾም ሌላ ሌላ ሌላውን ትተን ግለሰቡ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ባላው የባለድርሻ ጥቅም የኢትዮጵያ በዘርፉ ዋና ተቀናቃኝ የሆነው የንግድ ባንክን ለኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አሳልፎ አይሰጥም? የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክና ሌላው የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ ባለፉት ሦስት ዓመታት እየተስፋፉበት ያለው ሂደትስ ምንን ያሳያል?

ዛሬ አብይ አህመድና ጋሻ ጃግሬዎቹ አሸባሪ ምናምን እያሉ የሚያጃጅሉን ለመሆኑ የገንዘብ ምንጫቸውና የገንዘብ መተላለፊያው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አይደለም? ከዚህ በፊት በዘረፋ ሥም ከሀያ በላይ በሆኑ ዘረፋዎች ለኦነጋውያን ገንዘብ እየተላለፈላቸው አልነበረም? ሚዲያ ላይ እየወጣ ስላሳጣቸው እንዳይወራ እንጂ አሁንስ ይሄው ሂደት አልቀጠለም? በሺዎች የሚቆጠር ሰራዊት በስታዲየም ሳይቀር እያሰመረቀ ያለው ኦነግ ገንዘቡን የሚሠጠውና የሚተላለፍለት እንዴት ነው? በአጠቃላይ የኢትጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ከገንዘብ ኪሳራው ይልቅ ለነፍሰ በላዎች ገንዘብ በመሥጠት አገርና ሕዝብ እያጠፋ እንደሆነ እንዲደረግ መዋቅሩን በኦነጋውያን ከዛም በላይ ከኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች ጋር ሳይቀር ግንኙነት ያላቸውን ግለሰቦች በባንኩ ቁልፍ ቦታዎች ያስቀመጠው ማን ነው? አብይ አህመድ አደለምን?

ተጨማሪ ያንብቡ:  የመስፍን አረጋ ድሪቶ - ኤፍሬም ማዴቦ

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ወሳኝ የዲፕሎማሲ ሥራ ባስፈለጋት ወቅት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በደመቀ (ምክትል ጠ/ሚኒስቴር) በተደራቢነት እንዲመራ ሲያደርግ ምን ማድረጉ ይመስላችኋል? ዛሬ ውጭ ጉዳይ እየተመራ ያለው በዋናነት በዲና ሙፍቲ አደለምን? ዲና ሙፍቲሰ ማን ነው? ሌሎች በሰበብ አስባብ ከቦታው ከሌሎችም ቦታዎች ሲነሱ ዲና ሙፍቲ እዚህ ቦታ ለምን ተቀመጠ? ለመሆኑ ግን ውጭ ጉዳዩን በተደራቢነት እየመራ ነው የሚባለው ግለሰብ (ደመቀ) ሥራው ምንድነው? ሁለቱም ጋር ሥራ ስለሌለው እንጂ አንዱ ጋር ሥራ ቢኖረው ሁለቱን ደርቦ የመምራጥ አቅም ይኖረው ነበር? ያም ሆኖ ለምን ብላችሁ ጠይቃችኋል?

አዲስ አበባ፡ አዲስ አበባን በቀጥታ ከኦሮሚያ እያመጣ እየሾመ ያለው ለምን ተብሎ እንኳን መጠየቅ ያስፈልጋል? አዲስ አበባ ውስጥ ባለፉት ሶስት አመታት የሆነው ምንድነው? ብዙዎች መናፈሻ ተሰራ መስቀል አደባባይ ተሰራ ይሉናል፡፡ በማን ገንዘብ? ሥንት ወሳኝ አገራዊ ነገሮች ተሰርዘው? ከሁሉም በላይ ዛሬ አዲስ አበባ ከወያኔ ወረራ ባልተናነሰ ወረራ አልተፈጸመባትም? ይሄን ሁሉ ያረገው ማን ነው?

የኢትዮጵያ መከላከያ፡ የኢትዮጵያን መከላከያ ከወያኔ ጊዜ በከፋ በኦሮሞነት ብቻ ያደራጀው ማን ነው? አብይ አህመድ ራሱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ (የሚያዘው ካለ)፣ ብርሀኑ ጁላ ታማጆር ሹም፣ ይልማ መርዳሳ የአየር ኃይል አዛዥ፣ ቀነዓ ያደታ የመከላከያ ሚኒስቴር( አሁን በትግሬ ተክቶታል)፣ ባጫ ደበሌ በተቋሙ ያለው ቦታ ባይገባኝም ዋና በሚመስል ደረጃ የሚፈነጭበት የሆነው በማን ነው? እስኪ ከእነዚህ ግለሰቦች ውጭ በመከላከየው ወሳኝ ሚና ያለው ማን ነው? ሣዕረን ያስገደለው ማን ነው? አሳምነው? በዚህ መልኩ እየተመራ ያለ ተቋም ዛሬ ለጠላት መሳሪያ እያስረከበ ስልታዊ ማፈግፈግ በሚል አብይ አህመድና ቡድኑ ጠላቴ ብሎ በሚያስበው አማራ ላይ ወረራ ቢፈጸም ለምን ይገርማል? በመከላከያው ውስጥ ያለው ዋናው ሴራ ከጀምሩ ከአራት ኪሎ አደለም? እዚህ ላይ ጉዳዩ የጸረኢትዮጵያ ኦነጋዊነት እንጂ የመሠረታዊ ኦሮሞነት አደለም፡፡ እንጂማ የአገሪቱ ታላላቅ ጀግኖችና የጦር መሪዎች የነበሩት እንደዛሬወ ሳይሆን ከኦሮሞ ሕዝብ የወጡ ነበሩ፡፡ የሚገርመኝ ወያኔ ትግሬን ሁሉ ለጦርነት አሰማርታ ባለችበት ሁኔታ የትግራይ ተወላጅ መከላከያ ሚኒስቴር የተደረገበት ነገር ነው? ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል? ግለሰቡ ከወያኔ ጋር ምንም ንክክ ባይኖረው እንኳን ዘመዶቹ ወራሪ በሆኑባት አገር የመከላከያ ሚኒስቴር ተደርጎ የሾመበት እውነትን እያየን ለምን ማስተዋል ተሳነን? ግለሰቡ የወያኔ ጠላት እንኳን ቢሆን በዛ ቦታ ሊሰየም የለበትም ነበር፡፡ አሁንስ እየተዋጋ ያለው ማን ነው?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጅብ የሚጮኸው መብላት ሲፈልግ ነው። - ከተማ ዋቅጅራ

እስክንድር ነጋ፡ በመጀመሪያ እስክንድር የታሰረው ለምንድነው? እስክንድር የታሰረው በማን ትዕዛዝ ነው? ከወያኔ በከፋ ያየንውንና የሰማንው የፍትህ ነወረኝነትን የዘረጋው ማን ነው? አብይ አህመድ አደለምን? በነገራችን ላይ እነ ጀዋርና በቀለ ለመታሰራቸው ምን ማስረጃ አለ? አሁን እያየነው ባለው ነውረኝነት አብይ አህመድ እነ ጀዋርን በሻራተን አልጋ ይዞ ሊያኖራቸው እንሚችል ነው፡፡

እንግዲህ የአብይ አህመድ አፍቃሪዎች ከምል አምላኪዎች ብል ይሻለኛልና ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ካላችሁ፡፡ ቀለል አደርጌ ነው የጠየኳችሁ፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን ጊዜው የመሸ ይመስለኛል፡፡ ከጅምሩ ለሁሉም መልካም ይሆን ዘንድ በመለክምነትና በቅንነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ሰው መስለውን አብይንም ሆነ ሌሎቹን አሳስበናቸው ነበር፡፡ አብይ አህመድ አሁንም ቁማሩንና ሴራውን ቀጥሏል፡፡ አገርን ከውጭም ከውስጥም አስወርሮ የሚቀርለት መስሎት ከሆነ ነገሮች ከሚጠብቀው ፍጥነት በላይ ወደእሱ እየመጡ ነው፡፡ የንጹሐን አማላክ ስለንጹሀኑ ደም አይፋረደኝም ብሎ ሴራውን ቀጥሏል፡፡ አዝናለሁ፡፡ ኢትዮጵያ በታሪክ እንዲህ ያለ ጠላት ገጥሟት አያውቅም፡፡ ያም ቢሆን እየሆነ ያለው ሁሉ መሆን ስላለበት ነው፡፡ የሁሉም ሴራ በጊዜው ይገለጽ ዘንድ እየሆነ ያለው ሊሆን ግድ ነው፡፡

ኢትዮጵያኖች ተጠንቀቁ፡፡ በአሜሪካ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን የአገራችሁን ጉዳይ ለወዳጅ አሜሪካኖችና ባለስልጣናት ጠቁሙ፡፡ አፍቃሬ አብይነት አያዋጣም፡፡ አሜሪካ በትረምፕ አስተዳደር ዘመን ኢትዮጵያ ከዘር ሥርዓት ተላቃ እኛ ወደምንፈልጋት ለማድረግ ብዙ ሞክረዋል፡፡ ችግሩ በወያኔ አድጎ የጎለመሰው አብይ የኦነጋውያን ተራ ነው በሚል ስንት ተስፋ የተደረገበትን ሁሉ አበለሻሸው እንጂ፡፡ እንደ ኦነጋውያኖች ቢሆን ከዚህም የከፋ በሆነ፡፡ ላለፉት ሶስት ዓመታት ያላየንው መቼም የለም ግን ከዚህም የከፋ ነገር እንዳይከሰት አሜሪካ ባለውለታችንም ነች፡፡ ከጅምሩ ወያኔ እንድትወገድ የትረምፕ አስተዳደር ሚና ነበረው፡፡ ኋላም የከፋ ቀውስ እንዳይፈጠር፡፡ ከዛም አልፎ ኢትዮጵያ ገንዝብ እንድትቀይርና አሸባሪዎች እንዲነጥፉ ያደረገቸው አሜሪካ ነች፡፡ በማግስቱ ግን ገንዘቡን አሳትሞ ለአረመኔዎቹ የሰጣቸው አብይና ለዛ ያደራጀው ባንክ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄን ሁሉ የሰራው የትረምፕ አስተዳደር ትረምፕ በተናገረው አንዲት ንግግር ትረምፕን የተበቀለ መስሎት የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላቶች ወደሥልጣን እንዲመጡ ትልቅ አስተዋጾ ነበረው፡፡ የትረምፕ አስተዳደር እስከመጨረሻው በተለይ የውጭ ጉዳይ የነበረው ፓምፒዮና የአፍሪካ ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት እንደሁመ ቀድመውም (1999-2002) በኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ቲቦር ናዤ ለኢትዮጵያ የነበራቸው ደጋፍ የሚገርም ነበር፡፡ የትረምፕ የተሳሳተ ንግግርም የመነጨው በዋናነት በዲፕሎማሲ ክፍተት ነው፡፡ ያ ባይሆንማ በተቃራኒው እኔ እያለሁ በኢትዮጵያ ላይ ጣት የሚቀስር ወዮለት ሊል በቻለ ነበር፡፡ ያም ሆኖ ከእኛ ጋር በቀጥታ የሚመለከታቸው የራሱ ውጭ ጉዳይና የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊው በኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ቲቦር ናዤ በእርግጥም ወዳጆቻችን ናቸው፡፡ ዛሬም ቢሆን ቲቦር ናዤ ለኢትዮጵያ ዘብ እንደቆሙ ነው፡፡ እንግዲህ በየአደባባዮ ከመውጣት በተሻለ የኢትዮጵያ ወዳጆች የሆኑ አሜሪካውያን ባለስልጣናትን መቅረብና እነሱንም ማገዝ ጠቃሚ ነው፡፡ እኔ ከጅምሩም ዛሬ ያሉት ከዚህ የተለየ እንደማያደርጉ አገምት ስለነበር በወቅቱ ባአቅሜ ኢትዮጵያውያንን ሳሳስብ ነበር፡፡ ግን ማን ይሰማል? እንዲህ ሆኖም በአይናችን የምናየውን እየካድን ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሃይማኖታችን የቅድሚያ ትኩረትና ርብርብ የሚባል ነገር አያውቅም እንዴ?

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ

አሜን

 

7 Comments

    • አሊ ጥላቻ የሚሆነው ማስረጃ ባያቀርብ ነበር በእሱ ፍቅር ተለክፈህ ካልሆነ መልእክትህ ከሰርጸ ትንታኔ ጋር አይጣጣምም።

  1. ሠርፀ እንኳን በሰላም ብቅ አልክ፤ ጠፍተህ ነበር (መሰለኝ)። ያልከው ሁሉ ትክክል ነው። ደመቀ ለስምና የሚታለል አማራ ያለ መስሏቸው ልክ እንደወያኔዎቹ ለታይታ – ሰው ጠፍቶ – እንዲሁ ኦሮሙማዎች የጎለቱት ነው – የአቢይ ከዳሚ ገረድ ሆኖ። የመከላከያ ሚ/ር የሆነው ዶር. አብርሃምም ልክ እንደደመቀ ነው – ትግሬዎችን ያታለለ መስሎት። ልዩነቱ ወያኔዎች በዚህ የአቢይ ተጨፈኑ ላሞኛችሁ ዓይነት የጅል ሥራ ትህነጎች ጥርሳቸውን ተነቅሰው ሲስቁበት አሽከሩ ብአዲን ግን አጨበጫቢ መሆኑ ነው። ደመቀ ተፈጥሮው ለአሽከርነት ያመቸ ነውና ከርሱ ምንም አይጠበቅም፤ አብርሃም ግን የማይሠራበትን ሥልጣን ባይቀበል ጥሩ ነበር። ለማንኛውም የመጨረሻው ትዕይንት እየመጣ በመሆኑ ጦጣዋ ገበሬው ምን ዘርቶ እንደዋለ ስትጠይቀው እርሷ የማትበላውን የእህል ዘር መርጦ ‘ተልባ’ ሲላት “ወርደን እናየዋለና!” እንዳለችው ነው።

  2. ለእኔ የሃበሻ ፓለቲካ ጥምቢራው የዞረ ነው። አሁንም ዞረን ተመልሰን የምናወራው የዘር ፓለቲካ ነው። የኦሮሞ ልጆች ከፍታ ላይ ወጡ ብሎ ማላዘኑ ዋጋ ቢስ ነው። መሰረታዊ ጥያቄው በተሰጣቸው ስልጣን ህዝባችን ዘርና ቋንቋ ሃይማኖት ሳይለዪ እንዴት ያገለግሉታል ነው መሆን ያለበት። ነጋ ጠባ በሆነ ባልሆነው ኡኡታ አይመችም። ወያኔን ህዝቡ የጠላቸው የትግራይ ልጆች በመሆናቸው አይደለም። አመራራቸው ከፋፋይ፤ ዘራፊና ገዳይ በመሆኑ እንጂ። የማን ወገን የማን ዘር ነው ይህንና ያን የሚመራው ከማለት ይልቅ ለሃገርና ለህዝብ ያላቸው ፍቅር የቱ ላይ ነው ብለን ነው መጠየቅ ያለብን። አሁን በስም የጠቀስካቸው የኦሮሞ ተወላጅ አመራሮች የሃገር ፍቅር ያላቸው፤ በሚቻለው ሁሉ የወያኔን ወረራ ለመቀልበስ የሚፋለሙ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው። ዘርና ቋንቋውን ወደ ኋላ በመተው ማንኛውም የበላይ አካል ሲያጠፋ በመረጃ ነገሮችን አቅርቦ መፋለም እንጂ የስማ በለው ወሬና እንደ እብድ ምንም ባልሆነ ነገር ላይ ተነስቶ ሰውን ጭቃ መቀባት በህግ ማስጠየቅ አለበት።
    ጠ/ሚ አብይን በተመለከተ አያሌ ነገሮች ከዚህም ከዚያም ጎን ይባላሉ። ግን አሁን ጠ/ሚሩን የምንወቅስበት ሰአት ላይ አይደለንም። የሃገርና የወገን መኖርና አለመኖር በውጭና በውስጥ ሃይሎች አጣብቂኝ በገባበት ሰአት ጠ/ሚሩን ማጥላላት፤ ያልሆነ ነገር መጻፍና ማስወራት ሰድቦ ለሰዳቢ መስጠት ነው። በጠ/ሚሩ አመራራ አጠያያቂ ነገሮች አልታዪም ማለት ግን አይደለም። ታይተዋል። እየታዪም ነው። ግን የዚህ ሁሉ የፓለቲካ እሰጣ ገባ የአማራና የአፋር ክልል በወያኔ መጨፍጨፍ ጠ/ሚሩ ሆነ ተብሎ የሚያደርገው እየተደረገ የሚወሸከተው ሁሉ የፓለቲካ ገመድ እንጂ ለማንም አይጠቅምም። ሰው ገድሎ ደስ የሚለው በምድራችን ወያኔና ተባባሪዎቹ ብቻ ናቸው። ይህ ግልጽ ሊሆን ይገባል። እየዘረፉ ተዘረፍን፤ እየገደሉ አለቅን፤ እያስራቡና ሊጥ ሳይቀር እየጠጡ ተራብን የሚሉት እነዚህ የምድር ላይ ሽንኮች ከሰው ልጅ ባህሪ የወጡ ናቸው። ገና ከጅምሩ ሰውን በሰውነቱ ሳይሆን ያሰለጠኑት በጥላቻ መርዝ ነው። ታላቋ ትግራይ እየናፈቀቻቸው አዲስ አበባ የገቡት እነዚህ እባቦች 27 ዓመት የገዟትን ሃገር ነው እኔ ካልበላሁት ልድፋው በማለት የድሮ ጭንቅላት ይዘው ምድሪቱን እሳት ውስጥ የከተቷት። በዚህ ግጭት ግን አትራፊ የለም። የትግራይ ህዝብም ከአማራና ከአፋር ተዘርፎ የተወሰደውን ሃብት አይበላውም። ይሻግታል ወይም ሌላ ዘራፊ ይመጣበታል እንጂ። ግፍ ግፍን ይወልዳል። ሞት ሞትን ያራባል። የወያኔ ጡርንባ ከእውነት የራቀው ገና ጫካ እንደገቡ ነው። የደርግ ጥይት ከጨረሳቸው የትግራይ ልጆች ይልቅ ወያኔ ራሱ የገደላቸው ስፍር ቁጥር የላቸውም። ግን ሁሌ ከበሮ እየተመታለትና ክራር እየተከረከረለት ጀጋኑ ከሚባል የጅምላ አስተሳሰብ ተሰላፊ አንጸባራቂ ሃሳብ ይወጣል ብሎ ማመን ተንጋሎ መትፋት ነው። የትግራይ ህዝብ በወያኔ በባርነት የኖረ ዛሬም ያለ ህዝብ ነው። ይህ የማይታያቸው የትግራይ ልጆች የቁም ሙቶች ናቸው። 27 ዓመት ሙሉ ዞር ብሎ ያላየውን የትግራይ ህዝብ አሁን ሻቢያ መጣብህ፤ አማራ በላህ፤ አዲስ አበባ ገብተናል እያለ የሚያስጨርሳቸው ለምን ሂሳብ እንደሆነ አንድም የትግራይ ልጅ ቆም ብሎ አይጠይቅም። አሁን ማን ይሙት ትግራይ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ ሃገር ሆኗ መኖር ትችላለች? ምን ተበልቶ? ነው ከኤርትራ ጋር ለመለጠፍ? የሆነው ቢሆን እኔ ግድ አይሰጠኝም። ግን አፋር ድረስ ዘልቆ ገብቶ እጽዋትን፤ እንስሳትን፤ ሰውን እያወደሙ ተወረሩን ማለቱ ለአሜሪካና በአጋሮቿ ሰሚ ያገኝ ይሆናል እንጂ በምድር ላይ ያለው እውነት ይህን የቱልቱላ ሂሳቤ አይደግፍም። ወያኔ ፋሽሽት ነው። ወያኔ ናዚ ነው። ወያኔ በምንም አይነት ሳሙናና የውሃ ሃይል በሌሎች ላይ ጥላቻ፤ ግድያ ሰቆቃ ከማድረስ አይጠራም። ወያኔን የሚገላግለው ሞት ብቻ ነው። ያ ደግሞ ለሁላችንም አይቀሬ ነው። ለዘመናት ደ/አፍሪቃን በአፓርታይድ ሲረግጣት ቆይቶ አሁን በ 85 ዓመቱ ይህችን ዓለም የተሰናበተው Frederik Willem de Klerk ትንፋሹ ከማለፉ በፊት የተናገረውን የስንብት ኑዛዜ ላዳመጠ የጉብዝና ሩጫ ቆይተው ሲያዬት ልክ እንዳልነበር ያሳያል። ይኸው አሁን ማንዴላ ወደ አለበት ተጉዟል። መጨረሻችን ያ ስለሆነ። የእኛም የዘር ፓለቲካ አስተሳሰብ ቆይቶም ቢሆን ሲገባን ጸጸት እንጂ ሰላም አይሰጠንም። ሰው ሰው ነው። ሰው የሚመዘነው በሰውነቱ ብቻ ነው። ሌላው ሁሉ ተቀራፊና ኋላ ቀሪ ሸክላ ነው። በቃኝ!

  3. ለሠርጸ ደስታ እስክንድር ነጋ ለምን ታሠረ በማን ትዕዛዝ ታሰረ በማለት የወሬ ስልቻህን ከመንፋት በላይኛው አካልህ የምታስብ ከሆነ እና የወያኔ አገልጋይ ካልሆንክ ከታሰረበት ቦታ ሂደህ መልሱን አግኝ።
    የውጭ ጉዳይ ሚስትርንም ሥራ በተመለከተ የሀገር አጥፊዎች የወያኔ እና የኦነግ ሸኔ የውጭ ጉዳይ ባለሟል እና የሱዛን ራይስ ክቲላ (ቡችላ) ስለሆንክ አገር ለማደባለቅ ትልቁን የማላዘን ስራህን ለመግፋት ለአንቶኒ ብሊንከ ዲፈረንሺያልህን አጎንብሰህ አገልግል።
    የኢትዮጵያን ንግድ ባንክን፤የመከላከያ ሚኒሥቴርን ፤የአዲስ አበባ አስተዳደርን ሹመትን በተመለከተ ደግሞ ስትመኘው ትኖራለህ እንጂ እንደአንተ ያለው የወያኔ አገልጋይ አይሾምልህም። አንተም ለመሾም በጎረቤትችህ ከጥዋት የቡና ሺታ በስተቀር እውቅና የለህም።
    በአሜሪካ ለሚኖሩ እትዮጵያውያን ስለአስተላለፍከው መልክትን በተመለከተ የሚገርመው ነገር ቢኖር የአሜሪካንን ባለሥልጣናት የሚወደው አንተና መሰሎችህ ምናልባት አሜሪካ የምትኖር ከሆነ በየአመቱ እንደ ባቄላ ልጂ እየፈለፈላ በምጻዋት ፎድ እስታፕ ከሚኖር በስተቀር በአሜሪካን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንማ ለፍርደ ገምድል የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተቃውሞአቸውን በተለያዩ ትይንተ ህዝብ አስይተዋል አንዱም በዚህ ሳምንት ሲሆን ሌላው ደግሞ በቨርጂኒያ አገረ ግዥ በተደረገው ምርጫ
    በተጨማሪ ደግሞ ለኢትዮጵያ እንባ የማይገደው፤ድምጽ የማይሳነው ።ለተራቡ እና ለተቸገሩ ኢትዮጵያውን መለመን የማይሳነው ታዋቂው ወንድማችን የኢትዮጵያ ልጅ ታማኝ በየን የአሜሪካን ፍርደ ገምድል ባላስልጣናት ለኢትዮጵያ ጠላት፤እንዳንተ ላለው አቆማዳ እና ኬሻ ወዳጅ መሆናቸውን በመረዳት አሜሪካ የነበረውን ትግል በመተው ይኸው ዛሬ፡ምሁራን በሙሉ በአንድ ላይ ቁማችሁ፤ ድምጻችሁን ስጡ ለኢትዮጵያ ሀገራችሁ። እያለ በታማኝ ሚዲያ ድምጽን እያሰማነ ስራውንም እያየነው ነው። ጂብ አንድ ቀን ያገኘውን አጥንት እስከ አልጠፋበት ድረስ ወይም እሱ ራሱ ቦታ እስካቀየረ ድረስ ሲሊስ ይኖራል በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት ለኢትዮጵያ የዘር ልዩነት ዲዲቲ አያስፈልጋትም።ቁልጭ ያለ ዘረኝነትህን ማጀት ውስጥ አስቀምጠው ወደፊት ትደርስበታለሕ። አስተሳሰብህ እና አመለካከትህንም ከታችኛው አካልህ ሣይሆን ከላይኛው አካልህ አድርገው።አስተያትህም በላይኛው አካል ይጻፍ ።

  4. ለአምባው በቀለና ተስፋ ታላቅ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ እንደእናንተ ብዙ ሰው ቢበዛልን ይህን የመከራ ጊዜ እናልፋለን:: ፀሀፊው ያልሰለጠነ በስሜት የሚነዳ ጎጠኛ ስለሆነ ምንም መልስ አይኖረኝም በኢትዮጵያ ውስጥ ነፃ ምርጫ ለሚቀጥለው 5 አመታት ተደርጏል ዐቢይ መውደድ ሳይሆን የህዝብን ድምፅ ማክበር ከጤናማ ሰው ይጠበቃል:: በዚህ ወቅት የተከበረውን የመከላከያ ሰራዊት የሚያጠቃ የወያኔ አጫፋሪ ብቻ ነው::

  5. እኔን ግብግብ አድርጎ የሚቆጨኝና ሰው መሆኔን ሳይቀር እንድጠላና አ3ንድጠየፍ የሚያደርገኝ ከነአምባው፣ ከነዘብዛባው ተስፋና ስም ጠፍቶ ከነእውነቱ ተብዬው ጋር ተቆጥሬ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን ያህል ሚሊዮን ሆነ” መባሉ ነው። ተረዳችሁኝ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share