እነ ደብረ ፂዮን ፤ የትግራይ ህዝብ ከኋላው ጠመንጃ ተደግኖበት እሳት ውሰጥ ግባ የሚባል አሳዛኝ መንጋ እንዲሆን አድርገዋል

debre1 725x719 እነ ደብረ ፂዮን ፤ የትግራይ ህዝብ ከኋላው ጠመንጃ ተደግኖበት እሳት ውሰጥ ግባ የሚባል አሳዛኝ መንጋ እንዲሆን አድርገዋል

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

የመንጋ ህሳቤ ( Mob mentality ) ማለት እልፍ ሰው ፣ በግላሰብ /ዎች/ አመለካከትና አስተሳሰብ የተጠረነፈበት ፣ አቤት ና ወዴት የሚፈቀድበት ፤ አንዳችም ተቃውሞ የማይቀርብበት ፤ በአንድ ግለሰብ ትዕዛዝ ሺዎች በጥቂቶች ላይ ከምላስ ጀምሮ ገጀራ የሚያነሱበት ነው ፡፡

በመንጋ ህሳቤ የተጠረነፈ የህዝብ እልፍ አእላፍ ፣ያለ ጥያቄ የቡድኑ አውራ ያለውን ተቀብሎ የሚተገብር ፤ የመቀበል ( Heard ) አስተሳሰብ ብቻ የሰረፀበት ነው ፡፡

የመንጋ ህሳቤ ያላቸው ሰዎች ፣ በአንድ ቀፎ ውስጥ እንደሚኖሩ ንቦችም ይመሰላሉ ፡፡ የቀፎ ንብ አስተሳሰብ ያላቸው ፡፡ (hive mentality) ንቦቹ ፣ መላ ህይወታቸውን ሙሉ የሚለፉት ለንግስትዋ አገልግሎት እንጂ ለራሳቸው እንዳልሆነ ይታወቃል ፡፡ የሰው መንጋዎችም ለአንድ ግለሰብ ድኩም አላማ ብለው ህይወታቸውን እሰከመሰዋት ይደርሳሉ ፡፡ የመንጋውን መሪ ብቻ የሚሰማ ና ትዕዛዙን የሚተገብር ህሊና ያላቸው አሳዛኝ ፍጥረቶች ፡፡ እስከ ደም ጠብታ የቀፎዋን ንግስት ንብ የማገልገል ዐይነት ተግባር ተመሳሳይ ወይም መንጋዊ ህሊና ( mob mentality ) ባላቸው ሰዎች ሲከወን ስታዩ ቀፎው የተነካበት ንብ ምህረተ ቢስ ወረራ ትዝ ይበላቸው ፡፡ ›››

ከላይ የሰፈረው የካት ብሩሸ ( Kate Brush ) ፅሐፍም የሚያረገግጥልን ይህንኑ እውነት ነው ፡፡ የጋርዮሽ ወይም የስማ በለው የጭፍን ጉዞ አስተሳሰብ ፤ግለሰቦች በተፈጥሮ የታደሉትን ህሊና እና በራሳቸው ላይ ራሳቸው የመወሰን ስልጣንን ፤ በስሜት ተገፋፍተው ፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለመንጋው ሃሰብና አመለካከት እንዲገዛ አሳልፈው ሲሰጡ የሚስተዋልበት ነው ፤ መንጋነት ፡፡ ሰዎች አንዴ ወደመንጋነት ከተቀየሩ በኋላ የተቀላቀሉትን ቡድን አላማ ከማራመድና ትዕዛዙን ከመፈጸም ውጪ ምንም ክፍት አማራጭ የላቸውም ፡፡ ህሊናቸውን የመንጋው ያደረጉ ሰዎች ሁሉ ፤ ልክ እነደ ንብ ቀፎ ጠባቂ ንብ ፣ አንዱ በቀፎው ዳር የሚሄድን መንገደኛ ለመንደፍ ሲቀሳቀስ ፣ ያንን ሰላማዊ መንገደኛ ለመንደፍ አብረው እንደ ሚንቀሳቀሱ ንቦች ናቸው ፡፡ ወይም የንቦቹን ቀፎ ፤ አንድ ተንኮለኛ ሰው ቢመታው ፣ ያንን ተንኮለኛ ሰው ለይተው አያጠቁትም ፡፡ ጥቃታቸው የጭፍን እና የመንጋ ጥቃት ነው ፡፡ በመንጋ በመንቀሳቀስ ፣ በዙሪያቸው ያገኙትን ማንኛውንም ፍጡር ፤ ሰው ና እንስሳ ሁሉ በመንደፍ ፤ አካባቢውን በማሸበር ፣ በትብብር አጠቃላይ ውድመት ነው የሚያስከትሉት

ለዚህ ነው መንጋነት እጅግ አደገኛ ነው ፡፡ የሚባለው ፡፡ አደገኛ የሚሆነው በመንጋነት የተሰባሰቡት ሰዎች በየግላቸው የሚየስቡበት ህሊና ወይም ማሰብያ አእምሮ ስለሌላቸው ነው ፡፡ መንገኞችን በመንጋ ለጥፋት የሚሰባስባቸው አንድ ከእነሱ በንቃት የተሻለ ና ሥልጣን ለማግኘት ተሥፋ ያለውና ገንዘብ ያለው ሰው ነው ። ወይም ሥልጣንና ገንዘብ ያለው ሰው ከኋላው እልፍ አእላአፍ ጭፍን ደጋፊ ፣ አደርግ የሚለውን ያለጥያቄ የሚፈፅም ተከታይ ያፈራል ። ከእነዚህ ለየት ባለ መልኩ ደግሞ የሚኖርበትን ህዝብ ሥነ _ ልቡና በውል የተረዳ ግለሰብም ፣ ያለውን እውቀትና ተሰሚነት ተጠቅሞ ሺዎችን ለመጥፎ ዓላማ በመንጋነት ማሠለፍ ይችላል ፡፡

ለጥፋት አላማ ሺዎች ከተሰለፉ ደግሞ ህዝብ ነው የሚባሉት ፡፡ ማሰብ የተሰናቸው ጭንቅላት አልቦ ህዝብ ፡፡ አሥቀድሞ ነገር በመንጋ የሚጓዝ ህዝብ ፣ በገዛ አእምሮው ማሰብ ያቆመ ፣ በጥቅሉ ትዕዛዝ ተቀባይ ጆሮ ብቻ ያለው ህዝብ መሆኑ የተረጋገጠ ነው ። ህሊናው በመንጋው መሪ ፕሮፖጋንዳ ተሰልቧልና ላይፈረድበት ይችላል ። ሆኖም ግን መንጋው ፣ መንጋው አንጎለ ቢስ ነው ።

ይሄ ግልጽ የሆነ እና የልተሸፈነ እውነት ነው ፡፡ ቢያንስ ፣ ቢያንስ ያ መንጋ ህዝብ ከአንድ ሰው ፣ ወይም ከአንድ ቡድን ጀርባ ለተሰለፈበት ጉዳይ አንጎል አልባ ነው ። ( ጭንቅላታቸው ተቆርጦ ሆኖም ገጀራ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ፣ ፊት አልባ ሆኖም አለዓይን እንደ ልብ የሚራመዱና በቡድን ሆነው ሰላማዊውን ባለፊትና ባለ አንጎል የሚያጠቁ ሰዎችን ጭካኔ የሚሳ የፊልም እስክሪፕረተ በመጻፍ አንድ ድንቅ አስተማሪ ፊልም ወደፊት ይሰራል ብዬ በመገመት ሃሰቡን እንካችሁ ብያለሁ ፡፡ )

መንጋዊ ህሊና ያለው ፣የራሱ ህሊና የተወሰደበት ጭንቅላት አልቦ ሰው ፤ በቀቢፀ ተሥፋ ና በህልም ምኞት እንደ ደራሽ ወንዝ ወይም እንደ ቅሥፈታዊ አውዳሚ መአበል “ ሱናሚ “ የሚሆነውም አንጓል አልባ በመሆኑ ነው ። አንድ ግለሰብ ለሚመራው ጉዳይ ማሰብ ፣ መጠየቅ ፣ እእንዴት ? ማን ? ለምን ? መቼ ና የት ? ብሎ የሚጠይቅ አንጎል የለውም ፡፡ መንጋው ያለጭንቅላት ነው የሚጓዘው ፡፡ ለማንኛውም ጥፋት በአንድ ወይም በጣት በሚቆጠሩ ተንኮለኞች ነው የሚመራው ፡፡ ወይም የሚንቀሳቀሰው ፡፡ ያለአንዳች ማሰብ ነው ፤ የጥቂቶችን ሃሰብ የሚተገብረው ፡፡ ለምን ? በምን ምክንያት ? መቼ ? የት ? ማን አይቷል ? ማስረጃ አለህ ወይ ? ወይስ በመረጃ ብቻ ነው ? ይህንን ስትል ፤ ብሎ ከመንጋው መሀል ማንም አይጠይቅም ፡፡

የመንጋው አባል ሁሉ ፣ አንገቱ ላይ ጭንቅላቱ መቀመጡ እውነት ቢሆንም ፤ በተግበራዊ ስራው ላይ ግን የለም ፡፡ ጭንቅላታቸው ዞር ብሎ እስከሚያየው አንገታቸው በአገልግሎቱ ላይ አታገኙትም ፡፡ መንጋዎች ፣ ” አንገት እና ጭንቅላት አለን ፡፡ ” ብለው ያስባሉ ፡፡ ይበሉ እንጂ በአስተሳሰብ ደረጃ ፣ ጭንቅላትም ሆነ አንገት የላቸውም ፡፡

የመንጋዊ አስተሳሰብ ድርጊት ፤ ማስተዋል ላለው ና ለመብላት ብቻ ለማይኖረው ሰው እጅግ አስገራሚና አሳዛኝ ሆኖ እናገኘዋለን ፡፡ አሳዛኝ ፍጥረት ያደረጋቸውም ጭቅላታቸውን በጥቅማ ጥቅም ፤ በቀቢፀ ተስፋ ና በማይረባ ገንዘብ ማስቆረጣቸው ነው ፡ ፡፡ ልክ እንደ አሳዛኙ ትህነግ መንጋ ጦር ፡፡

እናም በሉ የተባሉትን ፤ አድርጉ ና ፈጽሙ የተባሉትን ማንኛውንም ሤጣናዊ ተግባር ሳያቅማሙ ተገደው ይፈፅማሉ ፡፡ ለኢትዮጵያውያን ክብር ፣ ሠላም ፣ ፀጥታ ፣ ፍትህ ፤ የተሞላ ሰላም ፤ ደህንነት እና የጋራ ብልፅግና የሚቆረቆር ህግ አስከባሪ በመላው አገራችን ፣ በተቋም ደረጃ እስከሌለ ግዜ ድረስም፣ እዚህ ግባ በማይባል ጥቅማ ለሚደልል ና ጭንቅላትን በመቁረጥ ለሚያስፈራራ ፀረ አገርና ፀረ ህዝብ ኃይል ሁሉ ተገዢ ይሆናሉ ፡፡ ያልተልከሰከሰ ፣ ልጨኛ ና ለፍትህ ሟች ህግ አስፈፃሚ አካል ፤ ህዝብ ( ዜጎች ) በሚፈልጉት ደረጃ ተቋማቱን አጠናክሮ ፤ አንገት ቆራጭና ህሊና ቢስ አድራጊ እጀ እረዢም ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎችን ሴራ በአንድ ልብ በማሰብ ካላከሸፈ በስተቀር ፤ መሰል የጥላቻ ተግበራት ከድል በኋላ አይከሰቱም ለማለት አንደፍርም ፡፡ ፡፡

እናም ፣ በየዋሃን ህፃናት ሞት ዕድሜያቸውን የሚያራዝሙ ና ዛሬም ብዝበዛቸውን ለማፋጠን የሚሯሯጡ የውስጥና የውጪ ሤጣናት ሁሉ ፤ ዳግም በኢትዮጵያ ምድር እንዳይከሰቱ ፣ በሰረቁት ሀብትም እየተጠቀሙ የትግራይን ህዝብ እንዳያስጨርሱ በተፋጠነ መንገድ ይኽንን ጦርነት ለመቆጨት ይኖርብናል ፡፡ ደሞም እንችላለን ፡፡

5 Comments

  1. Yes, that is true! But what and how about the very stupid and brutal faction of EPRDF/so called Prosperity which controls the palace politics of Arat Kilo ??? Are you saying that they are different political entities as far as the very hard reality on the ground is concerned? I hate to say but I have to say that this kind of very clumsy and tragically skewed political mentality is one of the very nagging or lingering challenges the people of Ethiopia are facing !!! Painfully sad !

    • ጠገናው ጸሀፊው የጻፈው በሰጠው አርእስቱ ተገድቦ ነው ስለ ብልጽግና ደግሞ ስለ ብልጽግና ሲጽፍ ይጽፋል። ብልጽግና ያበለጽገናል ብሎ የጻፈበትን ጊዜም አላስታውስም በታየ ደንዳ መሪነት ብልጵግና ይመጣል ብሎ የሚያስብም አይመስለኝም ብልግና ካልሆነ በስተቀር። እንግዲህ አይነት የመሪ ድርድር በታሪካችን ደርሶብን ያውቃል? አዳነች አቤቤ፣ታየ ደንዳ፣ሌንጮ ለታ፣ አባ ዱላ ገመድ፣ሱሌማን ደደፎ፣ታከለ ኡማ፣ዲማ ነገዎ፣አረጋዊ በርሄ፣አርከበ እቁባይ ……ሌላው ቢቀር የስራ ልምድ ለማግኘት ብቃት የሌላቸው ናቸው።

  2. ‘Ethio-KKK’ዎች’ እስካሉ ጊዜ ድረስ፣ every evil Thing stays ‘Successful’, including woyane የወሮበላዎች production fabric!

    • ዘር ያዕቆብ ሻቢያ ነህ? ጽሁፍህን ሳጠናው በኢትዮጵያዊነት የቅ ስልክ ይመስላል።

  3. አይገባኝም ከወደዚህ ያሉት ተንታኞች ከትግሬ እናቶች በላይ ለትግሬ ልጆች አዛኝ መሆን ግራ የሚያጋባ ነው። ያገኙት የነበረውን ጥቅምና ወደፊት ሊያገኙ ያሰቡትን ጥቅም የሚያውቁት ትግሬዎች ናቸው ።ስለ ትግሬ ትግሬ ይናገር ያልበላችሁን ታካላችሁ ነው የሚሏችሁ። በፈቄደኝነት ይዋጋሉ ሲያዙ ተገደን ነው ይላሉ እዚህ ምርጥ ተመግበው ፈርጠም ሲሉ ዳግም ወደ ጻድቃን ይሄዳሉ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.