በደሴ ግንባር የሽብር ቡድኑ ሜይዴይ ክ/ጦር አዛዥ የነበረው ኮሎኔል ጉዕሽ ገብረ ተማርኳል

252801335 2128563800628290 7900408175516915658 nየሽብር ቡድኑ ያሰማራው ኃይል ከፍተኛ የስነ ምግባር ችግር ያለበት በመሆኑ በደረሰባቸው አካባቢዎች ግድያና ዘረፋ ይፈፅማል ሲል ሰሞኑን በደሴ ግንባር በመከላከያ ሠራዊት የተማረከው የሽብር ቡድኑ ሜይዴይ ክ/ጦር አዛዥ የነበረውምርኮኛው ኮሎኔል ጉዕሽ ገብረ ተናገረ ።
በመከላከያ ሠራዊት የተማረከው ኮሎኔል ግዑሽ ገብሩ እንደገለፀው፤ የሽብር ቡድኑ በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች ከስነ ምግባር የወጡ ተግባራትን እየፈፀመ ነው፡፡
የሽብር ቡድኑ ያሰማራው ኃይል የስነ ምግባር ችግር ያለበት በመሆኑ በወረራ በገባባቸው አካባቢዎች በርካታ የግድያና ዘረፋ ተግባራትን እየፈፀመ መሆኑን ገልጿል፡፡
የሽብር ቡድኑ ኃይል በርካታ የሀብት ዘረፋና ውድመት ማድረሱን በአይኑ መመልከቱንም አንስቷል፡፡
የሽብር ቡድኑ ካሰለፈው የሰው ሃይል ጋር የማይመጣጠን የጦር መሳሪያ ማስታጠቁን የገለፀው ምርኮኛው፤ ቡድኑ ኃይሉን ለጥይት ሲሳይ እያዋለው ስለመሆኑም ገልጿል፡፡
በተለያዩ ግንባሮች እድሚያቸው አነስተኛ የሆኑ ታዳጊዎችን ጨምሮ እድሜያቸው የገፉ ሰዎችንም በየጦር ግንባሮቹ የሽብር ቡድኑ ማሰለፉን ተናግሯል፡፡
“እኔ በምመራው ክፍለጦር ስምንት መቶ ሰው የታጠቀ ቢኖርም ከስደስት መቶ በላይ የሚሆነው ኃይል ደግሞ ያልታጠቀ በባዶ እጁ ወደ ጦር ግንባር በሽብር ቡድኑ የገባ ነው” ብሏል ምርኮኛው ኮሎኔል፡፡
በጀማል ታመነ
(ኢ.ፕ.ድ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.