[ሰበር ዜና – Breaking News] የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በአቡነ መርቆሪዎስ ወደሚመራው ሲኖዶስ ተቀላቀለ

(ዘ-ሐበሻ) የዳላሱ ርዕሰ አድባራት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ዛሬ ባካሄደው ምርጫ መሰረት በአቡኑ መርቆሪዎስ ወደ ሚመራው ስደተኛው ሲኖዶስ ተቀላቀለ።
ላለፉት 21 ዓመታት በገለልተኝነት የቆየው የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ምዕመናኑ አባት ይኑረን፣ በገለልተኛነት መቆየት ይቅርብን በሚል ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ዛሬ ምርጫው ተጠናቆ በተደረገው ቆጠራ
– 140 ሰዎች በ4ኛው ፓትርያርክ አቡነ መርቆሪዎስ ወደ ሚመራው ስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲጠቃለል
– 2 ሰዎች በሃገር ቤቱ ሲኖዶስ እንዲጠቃለል፤
– 85 ምዕመናን በገለልተኝነት እንዲቀጥል ድምጽ የሰጡ መሆናቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል። በዚህም መሠረት በአሜሪካ ከቀደምት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ አብያተ ክርስቲያናት በትልቅነቱ ትልቅ የሆነውና በቀዳሚነቱም የሚጠቀሰው የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ስደተኛው ሲኖዶስን ተጠቃሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን አሜሪካ በገለልተኝነት የቆዩ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በቅርብ ቀናት በ4ኛው ፓትርያርክ ወደሚመራው ስደተኛው ሲኖዶስ ይጠቃለላሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የመኢአድ አመራር መንገድ ላይ ሞቶ ተገኘ

24 Comments

  1. May God bless this congregation for their gallant struggle of advancing the true legacy of our church. The day shall soon come, when God indeed heed all our prayer for the resurrection of Ethiopia.

    Wesebahat Le’Egziabher

    Bertu

  2. That is good news for us and bad for the woyane: no one should stand idile but should take a stand aganist the enemy of our country.

  3. Egziabher Ybarkachew yhen melkam wusane lewesenu hulu. Ewunet hulem Yashenifal. Egziabherm Wedelbonachen Yemelsen. Amen!!!

  4. Catch 22 for Houston Debre Selam Medhanealem. It was a marvouls move by Dallas to protect it from Woyanes. It was hitting the last nail on Mahebre Kidusan Coffin as well.

  5. I am glad to hear that good News for us..E/r yabakachew yehn melkan zena lasmachune hulu..And many more to follow,,,

  6. ereeee eseye selete semeere ere eseye selete semere
    le qedus mikael negerew neber

    EGEZIABHER ABEZETO YEBARKACHU VERY STRONG WESANE GENA ENEBEZALEN BERETU BECHA ENANTE BEFIKERE ENA BEANDENET NURU

  7. wow!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

    Qidus Michael Yibarkachihu.

    For those forward looking members of the church, realy God bless you.
    I understand it is not an easy way out since you have been for so long
    under “neutral”.
    Yes “ewunet timeneminalech enji atimotim”.
    egziabher yimmesgen for taking bold action.

    wey gud

  8. Here goes mixing politics with religion….
    EPRDF has given for the toxic Ethiopian Diasporas politicians a 1000 years assignment to meddle in church and politics. A good example is the London Debretsion church who became a laughing stock.
    Now what they need is a Decone and a priest from each political party ( OLF, ONLF, ESAT, Transition and counicl you name it …) in a fair distribution and It is also good to bring shabia into the mix.
    Finally, I am happy that the church came with their true color

  9. ኬንያ በደረስኩ ሰሞን ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም ፈልጌ በአቅራቢያው ካለ ብዬ የስደት *ሲንየሮቼን* ሳማክር እንዳለ ተነገረኝ። በመቀጠልም “የሐበሻ ይሻልሃል ወይንስ የኤርትራው?” የሚል ያላሰብኩት ጥያቄ ተከተለና ኪም ብዬ ቀረሁ።
    አሜሪካን ስደርስ ደግሞ “የወያኔ ይሻልሃል ወይንስ የስደተኛው ሲኖዶስ” ልባል ነው ማለት ነው።

    ይቅርታ አድርጉልኝ እና ፖለቲከኛ ወይ ተቃዋሚ ምድራዊ መንግስትን ፈርቶ ቢሰደድ የሚገርም ነገር የለውም። ነገር ግን የሰማሁት መንግሥት ይበልጣል፣ ለሐይማኖታችሁ ተዋደቁ፣ በዕምነታችሁ ፅኑ… እያለ የሚያስተምር ካህን ምድራዊ መንግስትን ፈርቶ ተሰድዶ *ስደተኛ ሲኖዶስ* መስርቻለሁ ሲል በጣም ይገርማል።
    አቡነ ጴጥሮስ ጣልያንን፣ አቡነ ቴዎፍሎስ ደርግን ፈርተው መሰደድ እየቻሉ የተሰዉት ለምን ይሆን?

    “ቤቴ የአምልኮ ስፍራ አንጂ… ” የሚል ቁጣ እንዳይመጣብን ተገኝተን እንፀልይ!

    • Demamu:
      Let me give you some points regarding your point of views, First I am a boundery and race free believing the almighty God Jesus Christ the only and single way that meant not how the modern relgions enterpreated. With out mentioned the name of abune gebre menfes kidus and other holy fathers I can not man. With out Virgin, holy, and clean MOTHER MARY and super fast mighty angels I am zero.

      My dear friend if you were in time of Lord Jesus christ when he emmigrated to egypt 100% you denied him because if he is the son of God christ why he run away to Egypt
      Abune merkoryos situatuon totally different. You can hear from tamirat layne, or from others. Abune merkoryos did not escape because of converssion of relgion. Abune merkoreyos told by the government directly to leave the church and they arranged the way to fly period. But ABUNE PETROS DIED FOR MILLIONS IDENTITY AND TRUTH . JUST RELAX THINK NINE TIMES speak ONES my brother. So conversion by forigen colonial power and replacing are not the same. If you think this is wrong. Ask lord jesus christ why he runaway with his mother?

    • ደማሙ, አቡነ ጴጥሮስ ኣዎ ከውጭ ወራሪ ጠላት ጋር ተጋፍጠው በብሔራው ጀግነት ተሰውተዋል። እንዲሰውም ያደረጋቸው ፋሺስት ኢጣልያ አብያተ ክርስቲያናትን እያቃጠለ ፥ ምዕመናንና ካህናትን በ250 አውሮፕላን በሰማይ መርዝ እየረጨ ሲፈጃቸው በማየታቸው ነው። ለመሰደድም የማይችሉበት ሁኔታ ነበር። ሚናልባት የማታውቅ ከሆነ ኢትዮጵያዊው ከፈተኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ ኋላ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ከንጉሡ ጋር አገር ጥለው ወደ አዉሮፓ ተሰደው ነበር። ስለዚህ የሃማኖት መሪዎች ይሰደዳሉ። ስደትም በራሱ መስዋዕትነት ነው። መሰደድ የማይገባቸው ወያኔዎች ”በኢትዮጵያ ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስን አምላኬ ብሎ የሚያመልክ ቢገኝ በሞት ይቀጣል ፥ አብያተ ክርስቲያናት ቤተ ጣዖታት መሆን አለባቸው ” የሚል አዋጅ አውጀው ቢሆን ኑሮ ብቻ ነው ለሐይማኖታቸው እየመሰከሩ መሞት የሚገባቸው የነበረው። ሁላችንም እንደምናውቀው ይህ ደግሞ አልተደረገም። የተደረገው ወያኔ በመሳርያ ኃይል የመንግስት ግልበጣ ሲያደርግ ፥ የነበሩትን ተቋማት በሙሉ ሲቆጣተርና አመራራቸውን በራሱ ሰዎች ሲተካ፥ የቤተ ክርስቲያኒቱንም አባት አባሮ በራሱ መነደር ሰው በነበሩት በአባ ጳውሎስ ነው የተካው። በዚህ ምክንያት ነው ፓትርያርኩ መስሪያ ቤቱን ለቀውለት ሥልጣናቸውን ይዘው ተሰደዱ። ራሱ መዳኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገና በሕፃንነቱ በሔሮስ ምክንያት ወደ ግብጽ ተሰዶል። ለምን ? ለማስተማር አርአያነቱን ለማሳየት። ትምሕርቱን በመሰደድ ነው የጀመረው ማለት ይቻላል። ግን ግብጽ ሁኖ አምላክነቱ ግብጽ ውስጥ ብቻ ተወስኖ ነበር ማለት አይደለም። በዓለሙ ሁሉ ላይ ነበር እንጅ ! አሁንም የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስና ቅዱስነታቸው የሚመሩት ቅዱስ ሲኖዶስ አሜሪካ ሁነው በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን መንፈሳዊ አመራር ከመስጠት የሚያግዳቸው ሰው ሰራሽ የሆነ ብሔራው ደንበር የለም። ለዚያም ነበር ግብጾች ለ1600 ዘመን ግብጽ ሁነው የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ሲመሩ የነበሩት። እውነታው ይህ ብቻ ነው !

  10. Bravo Dallas St. Mikael’s congregation for taking this righteous action to join your exiled Ethiopian Orthodox Christian brothers and sisters lead by his holiness Abune Merqorewos and the Holy Synod lead by him as well. It is very important for us all exiled Ethiopian Christian community to worship God by following our Holy Church’s Canon law. May God always be with you and give you his holy guidance towards peace and reconciliations to each other. I hope and pray those who voted for different way to be convinced in their heart and accept the majority’s decision and stay together as members of your congregation. They should not see this as a defeat. As Christians, they should rather see this as choice of the Holy Spirit. I hope they will !

  11. Yih yemit tar mejemerya new tilacha ena meleyayet sinegs gin gizew
    Siders balebetu meto yihn yepoletika akenkagne hulun kebetu yastedal
    Eske ezyaw gin bebetekrstianitu lay chefrubat sitfeligu densubat yezerachwatn
    Tachdalachu.

  12. Genre, You seem holy “tsadiq” but you your self is promoting politics. To remain neutral is the first step to be weyane but surely is lawlessness.
    To be under weyane’s synod is truly a political statement than to be under the legitimate holy synod. In fact it is the righteous religious move unlike your poisonous suggestion. We know you now. Weyanes can not hide by the sheep skin so called neutral.
    wey gud.

  13. Good news but it should be done long long time ago. By joining the exile synodos we will be voice the voicless and will give strength for the church by exposing ethnicl warloard criminals disguised as prists and monks who has no shame for dividing the church in tribe even in the monastries. I don’t know what they were thinking the member of this church for twenty something years while WEYANNE/TPLF tibal cadress rape the church.

  14. The article is false! Dallas St. Michael’s church is still neutral. In order to change its neutrality policy, there should be a vote of two-third majority in compliance with the church’s bylaws Art. 2.6, 2.7, and 11.1.

    No one in his right mind would side with the external “Synod” which has condemned 40-50 million EOTC followers in Ethiopia. It is also NOT acceptable side with the internal “Synod” as it has also condemned EOTC followers in the diaspora. Therefore, the policy of neutrality is the only option.

    A very important reason for maintaining the neutrality policy is the fact that it affords the possibility of pursuing the objectives of reconciliation, peace, and development within EOTC in general instead of continuing with the disgraceful engagement of mutual accrimony and animosity.

    Please think carefully!

    • Wodaje

      It is a devastating defeat you guys sustained. Never mind about the bylaw, you are one voted and when you lose badly here you go come out with something like this one. Believe it or not you lost, St. Michael won. We in Dallas heard that you guys are also heading to court for the fourth time. My brother/sister, take my piece of advice; don’t try the road once you lost. If that happen, we will not see each other.
      May the almighty God bless all of us. Lets learn from the our host country (USA). The democratic culture, honesty, and integrity.

  15. Genre
    ታላቅ ምስጋና

    ይህ የኔ መልክት በአጠቃላይ ስለ እውነት ጊዜያችሁን ወስዳችሁ እንደ GENRE አይነት የበግ ለምድ ለብሰው ለሚመጡ ተኩሎች መልስ ባይገባቸውም ከነሱ አልፎ ለዘርማንዘራቸው የሚሆን ጥሩ ትምህርት ለምትሰጡ የተዋህዶ ቆራጥ ልጆች ሁሉ ይሁንልኝ። በዚህ አጋጣሚ የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሰርቷል አሁንም በስደት ያላችሁ ገለልተኞች ሁሉ ወደ እውነት ፊታችሁን እንድታዞሩ የሰማይ አምላክ ይርዳችሁ። ህጋዊወ የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማርቆሬዎስ ናቸው።
    ስለ እውንት ሳትደክሙ የምትመሰክሩ ሁሉ እንኮራባቿለን አይቶ ሰምቶ ዝመ ከሚል ፈሪ ሰው የሚያውቀውን እውነት ለመመስከር የሚንተባተብ ሰው ታላቅ ነው።

    በዚህ አጋጣሚ እኛም በዋሽንግተን ዲሰ ርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቤተ ክርስቲያን የምንገኝ ካህናትና ምእመናን እየተነጋገርንበት ነው በዚህ አጋጣሚ የአስተዳደር ቦርዱ በስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር ለመሆነ እያደረገ ያለወን ታላቅ ጥረት ሳላደንቅ ማለፍ አልፈልግም በርቱ እላለሁ። ያው ሁላችንም በቅርብ ቀን አብረን እንቆማለን አይዟችሁ እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል።

  16. ዘተዋህዶ ተባረክ ወንድሜ
    ትክክል ብለሐል። የተሰሳቱ ወገኖቻችን ትምህርት ቢሆናቸው መልካም ነበር። በእርግጥም የበግ ለምድ ለብሰው የገቡ የአገዛዙ አገልጋዮች እኛ አንድ እንዳንሆን ቀን ከሌት ይደክማሉ። ተሳክቶላቸውም ይኸው እንደተለያየን አለን። ተመልከቱት በአማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ፍዳ። ለመሆኑ ይህች ቀን ስታልፍ ማነው የሚከፍለው። አንድ ሆነን እየፈረሱ ያሉ ገዳማትንና በአገሩ እየተፈናቀለ ለአራዊት የተጣለውን ወገን እንዳንደርስለት ታጥቀው የሚሰሩት እዚህ የስውር ደመወዝተኞች ናቸው። ቤተክርስቲያናችን በግፍ መሪወቿ ሲባረሩ፤ ደግ የተሰራ ይመስል አባራሪ ግፈኞችን ይደግፋሉ። የተገፋን ሲሳደቡ ይውላሉ። ከሁሉም የከፋው ነውራቸው ልክ እንደዘረኛው አገዛዝ በጎጥ ሲሳለቁ መስማታችን፤ ማየታችን ነው።

    የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል በምእመናኑ ጠንካራ ተጋድሎ ከ፪፯ አመት የገለልተኝነት ኑሮው ተገላግሎ ትክክለኛውን መንገድ ባለፈው መጋቢት ፩፯/፪፻፭ ጀምሯል። መልካሙን አድርግልን። ቅዱስ ሚካኤል ሦስት ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርቦ አሸንፏል። ዛሬም በጥሩ ድምጽ ምርጫውን አድርጓል። ወደኋላ ለመመለስ የሚሞክሩ ቀቢጸ ተስፋወች ስለ ፍርድቤት ቢናገሩ አይገርመንም። ትቂቶቹ ድብቅ አገልጋዮች ናቸውና። ግና ማወቅ ለሚፈልግ ሁሉም ነገር ብርሐን ነው ይቻለዋል። ለሚያደናቁር ደግሞ ሁሉም ነገር ጋግርት ጨለማ ይሆንበታል። ወደአለፈው መመለስ ግን ሀሰት ነው። በተረፈ ለርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ዲሲ ምእመናን አይዟችሁ በርቱ። እናንት ከሞከራችሁ ይጨመርላችኋል። ተስፋ ያለመቁረጥ ነው።

Comments are closed.

Share