የአማራ ክልል አዲስ ርእስ መስተዳደር አገኘ

yilekal Kefyalew
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ
የቀድሞ የአማራ ክልል ረeስ መስተዳደር አቶ አገኘው ተሻገር ተነስተው በምትካቸው የአማራ ክልል አዲሱ ምክር ቤት  ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አስረስን   ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ መርጧል።

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በተለያዩ ትምህርት ኮሌጆች በመምህርነት፣ ዲን በመሆንና በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝዳንትና ፕሬዝዳንት በመሆን ውጤታማ ሀላፊነትን የተወጡ አመራር መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሆነውም ሲሰሩ ነበር፤፡
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አስረስ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል፡፡ ባደረጉትን ንግግር ቀዳሚ ተግባራቸው የክልሉን ሕዝብ ሰላምና መረጋጋት ማስፈን፣ የተጀመረውንም የሕልውና ጦርነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ መሆኑን ገልጸዋል።
——————————————

ስለ ርዕሠ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በአጭሩ

የአማራ ክልል ርዕሠ መስተዳድር በመሆን በዛሬው ዕለት የተሰየሙት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ትውልድና ዕድገታቸው በምዕራብ ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ነው።
የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሶሻል አንትሮፖሎጅ ከአዲስ በአበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የሶስተኛ ዲግሪያቸውን በሶሻል አንትሮፖሎጅ በህንድ ሀገር ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለዋል። በጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ መምህርነት፣ በደብረ ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከመምህርነት እስከ ዲንነት ሰርተዋል። የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንትነት እስከ ፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል። ርዕሠ መስተዳድር እስከተሰየሙባት የዛሬዋ ዕለት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ነበሩ።
ዶ/ር ይልቃል በስድስተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በደቡብ አቸፈር ምርጫ ክልል ብልፅግናን በመወከል ለክልል ምክር ቤት ተወዳድረው ማሸነፋቸው ይታወቃል።

ካሚሎት አማራ ሚዲያ

——————-

1 Comment

  1. New head of administration ? Are serious or kidding ? What does new mean in the real meaning of EPRDF or Prosperity that has been and continued to be the most devastating system of political crime ? Is he new because he is a “Dr”? Are you telling us that this guy and his colleagues who have been muddling in the very blood of innocent Ethiopians for a quarter of a century one way or another and continued muddling in a much terrible fashion at this very moment in time will make any significant difference I’m making things better? Absolutely stupid way of political thinking and behavior !!!
    I hate to say but I have to say that those individuals of the deadly political system of ethnocentrism of EPRDF or Prosperity which is led by The very dangerous political ideology and action of Oromuma will bring much worrisome consequences, not the other way round at all! If we keep being stupid about this very hard reality, we must be ready to be subjects of good for nothing !!!
    Extremely sad!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.