” ሽርፍራፊ ስልጣን ለግለሰብ ኢጎ እና ጥቅማጥቅም እንደሆነ እንጂ ለህዝብ የተለየ አማራጭ ሃሳብ እንዲያገኝ አያደርግም ! ” ተክሌ በቀለ

tekle bekele
አቶ ተክሌ በቀለ (የኢዜማ የስራ አስፈጻሚ አባል)

አንዳንድ ወገኖች በተመሰረቱ የክልል ምክር ቤቶች እና እየተመሰረተ ባለው የፌደራሉ መንግስት የስልጣን አሰጣጥን ጨምሮ አንዳንድ ጉዳዮች እያነሱ የተለያየ ሃሳብ ሲሰጡ ይሰማል/ይነበባል ፡፡ እንደብዙው ሰው እኔም የመንግስት ምስረታ ላይ የምጠብቀው አዲስ ነገር የለም ፡፡ ወሳኝ ሰዎቹ በአባዛኛዎቹ እነሱው ናቸው ፡፡ ምናልባትም ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ በስተቀር ሌላው ሃሳብም ሆነ አሰራር ያው የድሮው ህወሓት/ኢህአዴግ ነው ፡፡ መሆን የሚችለው እና መሆን ያለበት ነው እየሆነ ያለው ፡፡

ይሁን እንጂ ለሃገር መረጋጋት ሲባል የሚመሰረተው መንግስት ነገሮችን በእርጋታ እሚያይበት ምቹ ግዜ እንዲኖረው እመኛለሁ ፡፡ ሃገር የሚረጋጋው ግን ፤

~ መዋቅራዊ ችግራችንን ( ህገ መንግስቱንየዚህን ሰነድ መሻሻል ተከትሎ ለሚመጡ መሻሻሎች) ለማሻሻል ስምምነት ላይ ስንደርስ እና ስራው ሲጀመር

~ የሊሂቃን ( የሃገራችን የፖለቲካው በሽታ አምጪ ዋና ተስህቦዎች ናቸው ብየ አምናለሁ) በታሪካችን እና በሌሎች ልዩነቶቻችን ስምምነት ሲኖር

~ በዘላቂ ሰላም ፤ በልአላዊነት በአንድነት ጎዳዮች ላይ ቅድመ ሁኔታ ሳያስቀምጡ በጋራ ለመስራት

~”የዲሞከራሲ ተቋማትን ለመገንባት ገዥው ፓርቲ ከተቃዋሚዎች ጋር በጋራ ለመስራት ሲስማማ እና ቅንነቱ እንዲሁም ቁርጠኝነቱ ሲኖር ወዘተ ነው ብየ አምናለሁ ፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ አሁን እየተመለከተን ያለነው ድክመት ካለ ፤ ነገም የሚፈጠር ግድፈት የሚኖር ከሆነ የህዝብ ችግር አይደለም ፡፡ ከአሁናዊ ሁኔታዎች እና ከገዥው ፓርቲ በላይ የኛው (ተቃቀዋሚ ተብየዎች) የፓርቲዎች ችግር ይብሳል፡፡

ዛሬም በገዥዉ ፓርም ሆነ በአጠቃላይ ፖለቲካችን ያለውን ችግር በመታገል እና የህዝብ ድምፅ በመሆን እንዴት ሚናችንን እንወጣ ሳይሆን መሰረታዊ ችግሩን በመዝለል የስልጣን ክፍፍል የሚያልም የተቃውሞ አመራር የስልጣን ኃይል እንጂ የለውጥ ኃይል ስለማይሆን እንኳን ለፓርቲው ለብልፅግናም አይበጀው ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዐቢይ አህመድ መንግስት ከትግራይ አሽባሪ ኃይሎች ጋር እንደሚደራደር መናገራቸው ተረጋገጠ

አብሮ መስራት ማለት በሃገራዊ ችግሮቻችን መነጋገር እና በችግር አፈታቶች ዙሪያ ለመስማማት እና ምፍትሄ ማፍለቅ መድረኩን እና የአሰራር ስርአቱን ማዘጋጀት እንጂ ሽርፍራፊ ስልጣን መጋራት ማለት አይመስለኝም ፡፡ ሽርፍራፊ ስልጣን ለግለሰብ ኢጎ እና ጥቅማጥቅም እንደሆነ እንጂ ለህዝብ የተለየ አማራጭ ሃሳብ እንዲያገኝ አያደርግም ፡፡

ምቀኛ እንዳትሉ ለብልፅግና ምክርቤቶች እና መንግስት የተረጋጋ የስልጣን ግዜን እመኛለሁ!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share