በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ከተማዋ ሊገባ የነበረ 49 ሺህ 300 ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ August 27, 2021 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email dollar በኮምቦልቻ ከተማ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኬላ ኮድ3 የሰሌዳ ቁጥር 89654 የሆነ መኪና መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ ወደ ኮምቦልቻ ሊገባ ሲል በብሔራዊ ደኅንነት፣ በፓሊስ እና ኬላ በሚጠብቁ ወጣቶች ትብብር በቁጥጥር ሥር መዋሉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ገልጿል። የጽ/ቤቱ የታክቲክና ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር አሊ ለአሚኮ እንደገለፁት ተጠርጣሪው ከምሽቱ 2:40 ሰዓት ላይ አሽከርካሪ በኬላው ላይ በነበረ ፍተሻ ከነዶላሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ወጣቶች በኬላ ፍተሻ እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ መሆኑን የገለጹት ኮማንደር አሊ ወጣቶች እየሠሩ ያሉትን አካባቢን በንቃት የመከታተል ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። በኬላ ጥበቃ ላይ አሚኮ ያነጋገረው በጎ ፈቃደኛ ወጣት ሐሰን እንድሪስ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ለመቅበር በግንባር ከሚደረገው ትግል ባለፈ አካባቢን የመጠበቅ ሥራ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጿል። (ኢ ፕ ድ) Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story “ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷ የመፍታት አቅም አላት”፦የጸጥታው ምክር ቤት አባላት Next Story የጀነራል አስራት ጉድይ አሳሳቢነት! ትኩረት መሰጠት ያለበት ነው