በአሸባሪው ቁንጮ ፃድቃን ገ/ትንሣይ የሚመራው የጠላት ኃይል መመታቱ ተገለጸ

tsadikan

ዓርሚ ሁለት የሚባልና በከሀዲው ሜጀር ጄነራል ዮኋንስ፣ በምክትሉ ከሀዲው ማዕሾ በየነ እና ከሀዲው ከበደ ፍቃዱ እንዲሁም በሜካናይዝድ አዛዡ ከሀዲው ኮሎኔል ገ/ስላሴ የተመራው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጠላት ሀይል ድባቅ መመታቱ ተገልጿል፡፡
በግንባሩ የተሰማሩ ሁለት ክፍለ ጦር አዛዦች እንደተናገሩት፣ መንግስት የተናጠል የተኩሥ አቁም እርምጃውን ካነሳ በኋላ ከበላይ በተሠጣቸው ትዕዛዝ መሠረት ጋሸናን ዋና ማዕከል በማድረግ ከዋድላ እስከ ላሊበላ መስመር ላይ የነበረውን የአሸባሪውን ኃይል መደምሠሳቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ጠላት በጀግኖቹ የሠራዊት አባላት፣ ልዩ ኃይል እንዲሁም የሚሊሻ አባላትና የአካባቢው አርሶ አደር ከበባ ውስጥ ሆኖ ይገኛል ነው የተባለው፡፡
ይህ የተዳከመ የጠላት ኃይል በጋሸና፣ መቄት፣ ሙጃ፣ በንፋሥ መውጫ አካባቢዎች እየተመታና እየተበተነ ይገኛል ብለዋል፡፡
በነዚህ አካባቢዎች በጠላት ላይ በተደረገ ጥቃት 3 ድሽቃ፣ 6 ሺህ የድሽቃ ጥይት፣ 87 የዕጅ ቦምብ፣ 229 ክላሽንኮቭ ነፍስ ወከፍ መሣሪያ፣ 5 ሺህ የክላሽ ጥይት፣ 1 የጦርሜዳ መነፅር ሲማረክ፣ በርካታ ቁጥር ያለው የሰው ኃይል እና ጠላት ይጠቀምባቸው የነበሩ 2 መድፎች እንዲሁም አንድ ዙ 23 መደምሰስ መቻሉን ዋና አዛዦቹ ገልፀዋል ሲል የመከላከያ ሰራዊት ገልጿል፡፡
ምንጭ∶- የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት
ተጨማሪ ያንብቡ:  °ከወለጋው የአማራው ጭፍጨፋ ጀርባ ያለው ስውር እጅ!°የአማራ ብልጽግና ለምን ዝምታ መረጠ?

1 Comment

  1. Top Urgent!!!

    ክብር ለጀግኖቻችን እና መስውዓት ለምትሆኑት፡፡ ሁሉንም በድል እስከምታጠናቀቁ እና የትህነግ ግባተ-መቃብሩ እስከሚፈፀም ግን ሳትዘናጉ ፍፀሚያቸውን ማፋጠን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እና ሰራዊቱ ታሪክ ዳግም እየሰራ ነው፡፡ ቢዘህ የትህነግ ፍፃሜ ሰዓት አሜሪካ፣ የተባበሩት መንግሰታት እና አጋሮቻቸው ዓላማቸው ስላልተሳከ የመጨረሻ ተፅዕኖ በአገራችን ላይ በመፍጠር አጋራቸውን ትህነግ ለማዳን እየተሯሯጡ ስለሆነ መንግስት አቋሙን ፍንክች ማድረግ የለበትም፡፡ ይህ ጉዳይ የመንግስት ጉዳይ ሳይሆን የህዝብ ጉዳይ ከሆነ ስለቆየ ማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በህልውናው ጉዳይ በታሪክ ተደራድሮ አያውቅምና ጠላቶች ከዚህ የህዝብ ማእበል ትምህርት ሊወስዱ ይገባል፡፡ መንግስት በዚህ መጨረሻ ሰዓት ከባድ መሳሪያ በመተኮስ እየተፍጨረጨረ ያለ ባንዳን በጀትና ድሮን ድምጥፋጡን ማጥፋት አቅቶት ነው??? ወታደራዊ ጦርነት ላይ ለጠላት አንድ ደቂቃም ቢሆን ጊዜ መስጠት መዘዙ የከፋ ስለሆነ አረ ፍጥነት ፍጥነት ያስፈልጋል፡፡ ደጋፊዎቻቸውም የሚያፍሩበት ጊዜ እየቀረበ ነው ለሊቱም ለብርሃን የሚስያስተላልፍበት ጊዜ እየቀረበ ነው፡፡

    ድል ለጀግኖቻን!!
    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share