የናዚስት ትህነግ 3ቱ የህልውና መሰረቶች! [መስፍን ማሞ ተሰማ]

ጦርነት ሠላም ነው።
ነፃነት ባርነት ነው።
ድንቁርና ጥንካሬ ነው።
****

tplf

WAR IS PEACE.

FREEDOM IS SLAVERY.
IGNORANCE IS STRENGTH.
****
ጆርጅ ኦርዌል 1984 ብሎ በሰየመው ዝነኛ መፅሐፉ ላይ አምባገነን፣ ዘረኛ፣ ሶሻሊስታዊ ፋሽስታዊና ናዚስታዊ የሆኑ መንግሥታትን መለያ ባህሪ የገለፀበት ቃል ነው። እነሆ የትህነግ/ወያኔ/ የህልውና እስትንፋስ የቆመውም በእኒህ ሶስት ኦርዌል ባስቀመጣቸው የባህሪ ምሶሶዎች ላይ ነው። ትህነግ የተወለደው፣ ተወልዶም ያደገው፣ አድጎም የጃጀው እኒህን ሶስት የተቃርኖ ውህድ መነሻና መድረሻው አድርጎ ነው።
ከፅንስ እስከ እርጅና ዘመኑ ናዚስትነቱን የሙጥኝ እንዳለ በጣዕረ ሞት ላይ የሚገኘው ትህነግ /የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር/ ከሠላም እንደተቃረነ፣ ከነፃነት እንደተጣላ፣ እውቀትን እንደጠላ ከደደቢት በረሃ አዲስ አበባ ገባ። ለሀያ ሰባት ዓመት በዘለቀው ዘረኛና ናዚስታዊ አገዛዙ በድፍን ኢትዮጵያ በከፋፍለህ ግዛው መርሁ፥ ጦርነት ሠላም ነው፤ ነፃነት ባርነት ነው፤ ድንቁርና ጥንካሬ ነው፤ ሌብነት ሥራ ነው፤ ዘረኝነት ወርቅ ነው፤ እያለ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ሲጠረንፍና ደቀ መዛሙርቱን ሲያጠምቅ ኖረ።
በድቡሽት ላይ በቆመው ጥንካሬውና ዕውቀቱ ሲመፃደቅና ሲራቀቅ የኖረው ትህነግ እነሆ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሀቅ ማነቅ አልቻለምና ከአራት ኪሎ ደደቢት በረሃ በስተርጅናው ተመልሷል። ጦርነት ህይወቴ፣ በባርነት መግዛት ነፃነቴ፣ ድንቁርና ጥንካሬዬ፣ ቅጥፈት ተፈጥሮዬ፣ ዝርፊያ ሥራዬ ነው ብሎ በኢትዮጵያ ላይ የምፅዐት ጦርነት ካወጀ ሰንብቷል። ናዚስት ህወሃት በሲዖል ሠራዊቱ የፍፃሜውን ፍልሚያ በከፋና በከረፋ ጭካኔ ተያይዞታል። የአብራክ ክፋዩ የጀርመኑ ናዚ በተባበረው ዓለም ክንድ የሲዖል ሠራዋቱ ተደምስሶ ናዚስቶችም ግብዐታቸው ተፈፅሞ ታሪክ ሆነዋል።
ጥቁሩ ናዚስት ወያኔም በተባበረው የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሠራዊትና መከላከያ ሠራዊት ክንድ ታሪክ ይሆናል። ደደቢት በረሀ ተወልዶ ኢትዮጵያን የወረረው ካንሰር ተንቤን ላይ ተቆርጦ እስከወዲያኛው ይቀበራል። ኢትዮጵያ ለዘመናት ከተጣበቀባት መዥገርና ከወረራት ወያኔ ከተባለ ካንሰር ከፈጣሪዋ እርዳታ ጋር መፈወሻዋ ዘመን አሁን ነው። ድል ለኢትዮጵያ ፈውስ ለሚዋደቁት ሕዝባዊ ሠራዊትና መከላከያ ሠራዊት ይሁን!!!!
_._,_._,_
ተጨማሪ ያንብቡ:  ቴዲ የኩዋስ ሜዳ ልጅ ነው - (ሄኖክ የሽጥላ -ገጣሚው)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share