እንደገና የፈረጠጠው ጄኔራል ከበደ ፈቃዱ ማን ነው? – ፋሲል የኔዓለም

233810076 576039877184128 1662458110287968287 n 960x535 እንደገና የፈረጠጠው ጄኔራል ከበደ ፈቃዱ ማን ነው?   ፋሲል የኔዓለም

እንደገና ሌላ ጉድ። ከ ሌ/ኮሎኔል አማኑኤል አብርሃ ጀርባ የተቀመጠው ደግሞ ሽበታሙ ሰው ሌ/ ኮሎኔል ገብረመስቀል ነው። ሜቴክ ፓወር ኢንዱስትሪ ውስጥ የቤቶች ጉዳይ ክትትል ኃላፊ የነበረ ነው።
ሌ/ኮ አማኑኤል ምክትል ሳይሆን ዋና ስራስኪያጅ ነበር። ትራንስፎርመር እንሰራለን ብሎ አገሪቱን ያራቆተ ከክንፈ ዳኘው ቀጥሎ ያለ ሰው ነበር። መንግስት ሆይ እባክህ የመረጃና ደህንነት መዋቅርህን ፈትሽ፤ አሳ ነባሪ ይዘህ፣ ቤዞ አሳ እንደያዝክ አትተውን።

236992617 4144889025565879 6440148278151132128 n 720x960 እንደገና የፈረጠጠው ጄኔራል ከበደ ፈቃዱ ማን ነው?   ፋሲል የኔዓለም

 

በወልድያ ግንባር የመራውን ጦር ጥቁር ውሃ ላይ አስጨርሶ፣ እንደገና የፈረጠጠው ጄኔራል ከበደ ፈቃዱ ማን ነው?

የህወሃቱ ታጋይ ጄ/ል ከበደ በ1988 ዓም የ31ኛ ክ/ጦር 3ኛ ብርጌድ ፓራ ኮማንዶ ፣ የ1ኛ ሻለቃ አዛዥ ሆኖ ሰርቷል። በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት በ31ኛ ክ/ጦር ምክትል ብርጌድ አዛዥ ሆኖ አገልግሏል። በ1992 ዓም 35ኛ ክ/ጦር ስትፈጠር የ35ኛ ክ/ጦር 3ኛ ብርጌድ አዛዥ ሆኖ ተሹሟል።
በ1997 ዓም ኮር የሚባለው አጀረጃጀት ፈርሶ ዕዝ የሚባል አደረጃጀት ሲቋቋም፣ ግለሰብ የ35ኛ ክ/ጦር ም/አዛዥ ቀጥሎም የ33ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ሆኖ እስከ 2006 ዓ/ም ሠርቷል።
በ2006 ዓ/ም እነ ጄኔራል አበባው ታደሰን ለማስወጣት በተደረገው ግምገማ፣ ግለሰቡ የአበባው አሽከር ነህ ተብሎ ተፈርጇል። ይህን ተከትሎም ከክፍለ ጦር አዛዥነቱ ተነስቶ፣ የዕዙ ማሰልጠኛ ት/ት ቤት አዛዥ ሆኖ ተመድቧል።
የጡረታው ጊዜ ሲደርስ “ ተጠቅሞ ይውጣ” ተባለና ወደ አብዬ በሚሊቴሪ “ኦብዘርቨርነት” ተላከ። በአማራና ኦሮሞያ የነጻነት ትግል ሲቀጣጠልና የህወሃት ህልውና አደጋ ላይ ሲወድቅ፣ ህወሃት በጡረታ ልታስወጣው ያሰበችውን ሰው መልሳ፣ በ2010 ዓ/ም አጋማሽ ላይ የብ/ጄኔራልነት ማዕረግ ሰጥታ ለሌላ ተልዕኮ አጨችው። ከዚያም የ31ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ አድርጋ ሾመችው።
ሰውዬው በጣም ጨካኝ ነው ይሉታል አብረውት የሰሩት ሰዎች ሲናገሩ። “በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት፣ ወደ ኤርትራ በጥልቀት ገብተን እያለ፣ ወደኋላ እንድንመለስ ስንታዘዝ፣ ሻዕብያም መረጃው ደርሶት ሰለነበር፣ ከፍተኛ የከባድ መሳሪያ ድብደባ ማድረግ ጀመረ። በዚህ መሃል አዲስ ከመጡት ምልምል ወታደሮች መካከል አንድ ወጣት ተደናግጦ ራሱን አቆሰለ። ስለልጁ ድርጊት ለከበደ ሪፓርት ሲደረግለት፣ ‘አምጡት’ አለና፣ ሽጉጡን አውጥቶ ግንባሩን ብሎ ገደለው።”
በ2013 ዓ/ም ደግሞ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ሲፈጸም፣ የእሱ ምክትል የነበረውን ኮ/ል ሻምበል በየነን ( ባለከዘራውን) ለማስገደል አቅዶ፣ የክ/ጦሩ ም/አዛዥ እቅዱን ባለመቀበሉ፣ ከተማ ቀጥሮ በሽጉጥ ግንባሩን ብሎ ገደለው።
የብርጌድ አዛዥነቱን ተጠቅሞ ከኤርትራ ያዘረፈውን የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች፣ ስኳርና ከብት፣ ሽራሮ ላይ ሽጦ አክሱም ላይ ፎቅ ሰርቶበታል። ከጭካኔውና ሌብነቱ በተጨማሪ በቀላሉ ሊገለጽ የማይችል ዘረኛም ነው።
በለውጡ ማግስት አምባሳደር ስዩም መስፍን ከኮሎኔል ማዕረግ በላይ ያላቸውን ወታደራዊ አዛዦች በየሁለት ሳምንቱ እየሰበሰበ ግዳጅ ይሰጥ ነበር። ጄ/ል ከበደ ደግሞ ሽሬ ላይ ከፍተኛ መኮንኖችን እየሰበሰበ ከላይ ያመጣውን ተልኮ ወደታች በማውረድ ስራውን ይሰራ ነበር። ይህ ሁሉ ሲሆን ሰራዊቱ በተደጋጋሚ ለበላይ አለቆች ቢያሳውቅም፣ ምላሽ በማጣቱ፣ የጥቅምት 24ቱ እልቂት ተከሰተ። ከዚህ እልቂት ጀርባ ካሉት ቁልፍ ሰዎች መካከል አንዱ ይህ በተደጋጋሚ ታዳጊዎችን እያስጨፈጨፈ የሚፈረጥጠው ጄኔራል ነው።
%name እንደገና የፈረጠጠው ጄኔራል ከበደ ፈቃዱ ማን ነው?   ፋሲል የኔዓለም
Solomon Gadissa, Syit DA and 1.8K others
282 Shares
Like

 

Comment
Share

 

1፤ የደቡብ አፍሪካው ኤምቲኤን ኩባንያ ከሁለተኛው የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ጨረታ ራሴን አግልያለሁ ማለቱን የተለያዩ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኩባንያው በጨረታው እንደማይወዳደር የገለጸው፣ በኢትዮጵያ ያለው አሳሳቢ የጸጥታ ሁኔታ ስጋት ስለፈጠረበት እና ኢትዮ ቴሌኮምና የኬንያው ሳፋሪኮም በያዙት ገበያ ውስጥ ሦስተኛ ተወዳዳሪ ሆኖ መግባት አዋጭ እንደማይሆን በመጥቀስ ነው። በዚህ ወር ይወጣል ተብሎ የሚጠበቀው ሁለተኛው ጨረታ የሞባይል ገንዘብ ግብይት አገልግሎት መስጠትን እንደሚጨምር እና በመጀመሪያው ዙር ጨረታ ያሸነፈው የኬንያው ሳፋሪኮም በጨረታው እንዲሳተፍ እንደማይፈቀድለት የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ባለሥልጣን ገልጧል። ኤምቲኤን በመጀመሪያው ተሳትፎ ነበር።

2፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላልተወሰነ ጊዜ መሬት እና መሬት ነክ አገልግሎቶችን ላለመስጠት መወሰኑን አስታውቋል። አስተዳደሩ እገዳውን የጣለው፣ አንዳንድ ግለሰቦች ወቅታዊውን ሀገራዊ ሁኔታ እንደ ጥሩ እድል ወስደው በአቋራጭ ለመክበር ሲሉ ትኩረታቸውን ወደ ከተማዋ መሬት እና መሬት ነክ አገልግሎቶች በማዞራቸው እንደሆነ የአስተዳደሩ ፕሬስ ጽሕፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ ገልጧል።

3፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሽብር ዓላማ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ላይ ከትናንት ጀምሮ ርምጃ እንዲወሰድባቸው ትዕዛዝ እንደተሰጠ የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በኃይል ርምጃው በክልሉ ሰፍረው የሚገኙት የደቡብ፣ ሲዳማ እና ጋምቤላ ልዩ ኃይሎች እንዲሳተፉ ክልሉ ፈቅዷል። በክልሉ በተለይም በመተከል፣ ካማሺ እና አሶሳ ዞኖች ኦነግ ሸኔ እና የጉሙዝ ታጣቂዎች ለሚፈጽሙት ጥቃት ጀርባ ሕወሃት እንዳለ የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ገልጧል።

4፤ የቱርኩ ፌቱላህ ጉለን ንቅናቄ በአዲስ አበባ ያቋቋማቸው 11 ትምህርት ቤቶች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ “ማሪፍ ፋውንዴሽን” ለተባለ የቱርክ መንግሥታዊ ተቋም ተላልፈው እንደተሰጡ የቱርኩ አናዶሉ ዜና ወኪል ዘግቧል። ከ2 ሺህ በላይ ተማሪ ያላቸውን ትምህርት ቤቶቹን ንቅናቄው ቀደም ሲል ጀርመናዊያን ባለሀብቶች ላቋቋሙት የግል ድርጅት ሽጧቸው ነበር። ጀርመናዊያኑ ባለሃብቶች በሕጋዊ መንገድ የገዟቸውን ትምህርት ቤቶች ሊነጠቁ እንደማይገባ ለፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም። ከ5 ዓመት በፊት በፕሬዝዳንትነት ጣይብ ኤርዶጋን ላይ መፈንቅለ መንግሥት እንዳቀነባበሩ የሚጠረጠሩት ቱርካዊው ቱጃር ፌቱላህ ጉለን ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ያቋቋሟቸውን ትምህርት ቤቶች የቱርክ መንግሥት እየወረሰ ያለው፣ የፌቱላህ ጉለን ንቅናቄን በአሸባሪነት መፈረጁን ተከትሎ ነው።

5፤ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች በጸጥታ ችግር ሳቢያ የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡን የአከባቢው ነዋሪዎች እና የአስተዳደር ሃላፊዎች ለቢቢሲ አማርኛ ተናግረዋል። ደምቢዶሎ፣ ጊምቢ፣ ነጆ፣ ጊደሚ በተባሉ ከተማዎች ትራንስፖርት የተስተጓጎለው በአከባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ሳቢያ ነው። የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በዋና ዋና መንገዶች ላይ ከሹፌሮች መኪና እንደሚቀሙ የተናገሩት የዞኖቹ አስተዳዳሪዎች፣ የትራንስፖርት መስተጓጎል እንጅ ሙሉ በሙሉ የተዘጋ መንገድ እንደሌለ ተናግረዋል። ኦነግ ሸኔ በሁለቱ ዞኖች በመንግሥት ወታደሮች ላይ ጥቃት እንደከፈተ ሰሞኑን ተናግሯል።

6፤ በአማራ ክልል የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ደብረ ማርቆስ ላልተወሰነ ጊዜ የሰዓት እላፊ ገደብ እንደጣለ የከተማዋ አስተዳደር በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ከጸጥታ ኃይሎች ውጭ በከተማዋ ማንኛውም ሰው እና ተሽከርካሪ ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ እንዳይንቀሳቀስ አስተዳደሩ አግዷል። የሰዓት እላፊ ገደቡ የተጣለው፣ የአማጺው ሕወሃት ሰርጎገቦች ስውር መረብ እየዘረጉ እንደሆነ በመታወቁ እንደሆነ አስተዳደሩ ገልጧል። ሰዓት እላፊውን የጣሰ ማንኛውም ሰው የጠላት ተባባሪ እንደሆነ ተቆጥሮ ርምጃ ይወሰድበታል ተብሏል። በክልሉ ቀደም ሲል የባሕርዳር እና ደሴ ከተሞች ከምሽት ጀምሮ እስከ ንጋት በተሽከርካሪዎች ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ እንደጣሉ ይታወሳል።

7፤ የተቃዋሚው የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሬክ ማቻር ምክትል ሄነሪ ኤድዋር በፍቃዳቸው ከአንድነት ሽግግር መንግሥቱ በመልቀቅ በቅርቡ ማቻርን ከተቃወመው የደቡብ ሱዳን ነጸነት ንቅናቄ ሊቀመንበርነት እና ከፓርቲው ወታደራዊ ክንፍ አዘዥነታቸው አውርደናቸዋል ላለው የውስጥ ወታደራዊ አንጃ በይፋ ድጋፋቸውን እንደሰጡ ዘ ኢስት አፍሪካን ጋዜጣ ዘግቧል። የከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች አንጃ ማቻርን ከሁሉም ሃላፊነቶች አንስቻለሁ ያለው፣ ደካማ አመራራቸው የተቃዋሚውን ንቅናቄ ጎድቶታል በማለት ነው። ማቻር ግን አሁንም የንቅናቄው ሊቀመንበር እንደሆኑ ያስታወቁ ሲሆን፣ የማቻር እና ተቀናቃኞቻቸው የሥልጣን ሽኩቻ የሀገሪቱን የሽግግር አንድነት መንግሥት እንዳያናጋው ተሰግቷል።

 

[ዋዜማ ራዲዮ]

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.