የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተብዬው የመጣው ከጨረቃ ነው እንዴ?! [መስፍን ማሞ ተሰማ]

party
party

ሪፖርተር የአማርኛው ጋዜጣ August 8/2021 ባወጣው ዘገባ ላይ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ራሔል ባፌ (ዶ/ር) “ወደ ጦርነት የገቡት ሁለቱ አካላት ሁሉን አቀፍ ውይይት እንዲያደርጉ እንሰራለን።” ብለዋል ሲል ዘግቧል። “ወደ ጦርነት የገቡት ሁለቱ አካላት?” ይህ ምን ማለት ነው?! እንዴትስ ያለ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሰቆቃ ላይ የተሰነዘረ ማላገጥ ነው?! [እነዚህ የምክር ቤት አባላት ኗሪነታቸውና ዜግነታቸው ጨረቃዊ ነው?! ወይስ እንደ ሳማንታ ፓወር እንደ ሱዛን ራይስ አሜሪካዊ?!]

ይህ ምናልባት ድንገት ከጨረቃ አዲስ አበባ ላይ የወረደው ምክር ቤት የዘመናት የኢትዮጵያ ካንሰር የሆነውን ናዚስት ወአይሲስ ወያኔ ሽብርተኛ ተብሎ መፈረጁን ብቻ ሳይሆን ሀገራችንን ኢትዮጵያ ከሱዳንና መሰል ፀረ ኢትዮጵያ ሀይላት ወታደሮች ጋር ሆኖ እያደማት እንደሆነ አያውቅምን?!
ከሲዖል ደርሶ መልስ የናዚስት ወአይሲስ ስብስብ ወያኔ የሲዖል ሠራዊቱን አደራጅቶ ኢትዮጵያን ወደ መጣንበት ሲዖል ይዘናት እንገባለን ብሎ በአደባባይ ማወጁንና ወደ ተግባር መግባቱን “አስማማለሁ” ባዩ ምክር ቤት አያውቅምን?! ለመሆኑ ይህ ምክር ቤት አይን አለው ? ናዚስት ወያኔ የፈፀመውንና የሚፈፅመውን ሰቆቃ አላየም? አያይም?! ጆሮስ የለውም?! አልሰማም?! እኒህ የሲዖል ሠራዊት አዝማች የሆነው የወያኔ ጠበቆች እንዴት ሆኖ በምንስ አግባብ ነው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዲፕሎማቶችና ዓለም ዐቀፍ ተቋማት ሰብስበው “ወደ ጦርነት የገቡትን ሁለቱን አካላት እናደራድራለን” የሚል መግለጫ እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው??? የነ ሳማንታ ፓወር አንሶን ነው የኛን መልክ የያዙ “ነጮች” እናደራድራለን የሚሉት??? አሁንስ በዛ ተንዛዛ!!!
We are sick and  tired of these good for nothing empty drum heads psuedo politicians and their likes!! We are sick and  tired of these balloons hypocrites who waste the hard working Ethiopians tax money!!!
ይህ ምክር ቤትና አፈቀላጤዎቹ ወይ ወደ መጡበት እኛ ወደማናውቀው ዓለማቸው ይመለሱ! ወይ የሳጥናኤል ወያኔ ብርድልብስነታቸውን ይገፈፉና የሲዖል ሠራዊትን ተቀላቅለው የኢትዮጵያን ሕዝብ ይግጠሙ! ወይ ለሕዝብ ቆሜያለሁ የሚል መንግሥት ባለበት ሀገር በሕዝብ ቁስል እንጨት የሚሰደውን ተቋማቸውን ለሕዝብ ሲል ጥርቅም አድርጎ ይዝጋልን!!! ኢትዮጵያ ስንቱን ካንሰራም የጃጀ በሽተኛ ተሸክማ ማስታመም ትችላለች?!
ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ወክሎ ከናዚስት ወአይሲስ ትህነግ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ የሚደራደር የኢትዮጵያ መንግሥት የለም! አይኖርምም!! ይህ የኢትዮጵያውያን ሁሉ አልፋና ዖሜጋ የህልውና አቋም ነው!!!
ተጨማሪ ያንብቡ:  በወልቃይት የማንነት ጥያቄ ሽፋን የሽብር ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠሩ ክስ ተመሠረተባቸው

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.