ጠላት ሲሸነፍ እርግማን ያበዛል – አበበ ገላው

“እኛ ወርቅ ነን! ኢትዮጵያዊነት ወድቆ ይቀበራል! ትግራይ በአለም ፊት ታላቅ ትሆናለች!” የዚህ አይነት አሳፋሪ ፉከራና ድንፋታ የሚያሰሙት በውጭ የሚኖሩ የአሸባሪው ህወሃት ጭፍን ደጋፊዎች ናቸው። አዲስ ነገር አልተናገሩም። ጸረ ኢትዮጵያ አጀንዳቸው በሰነድ ተደግፎ ታሪክ የመዘገበው ሃቅ ነው። የህወሃት ዘረኝነት ትርፉ የለየለት ፋሺስታዊነትን መፍጠሩንም በተግባር እያየን ነው።

በአሁኑ ጊዜ የህወሃታዊያን ትግራይን እንገነጥላለን የሚል ማስፈራሪያ የቁራ ጩኸት ነው። ምን ተይዞ ጉዞ? የህወሃት መሪዎች እንኳን አገር ገንጥሎ ማስተዳደር ህጻን ልጅ ለመጠበቅ አምኖ የሚሰጣቸው ወላጅ እንደ ሌለ ይታወቃል። ህዝብን መምራት መሰረቱ ቅንነት እንጂ መግደል፣ መዝረፍ፣ ሰቆቃና ግፍ መፈጸም አይደለም። በርግጥ ከአውሬ ጋር እየተጋደለና እየተቋሰለ ለዘላለም መኖር የሚፈልግ ማንም የለም። መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ቢባሉ ግን መልሶ ማጠፊያው ያጥራቸዋል። እውነተኛው ምኞታቸው የኢትዮጵያውን ህዝብ በበላይነት ይዘው በድጋሚ ደሙን መምጠጥ፣ መግደል፣ መዝረፍና ማሰቃየት ነው። መቼም ምኞትም ቅዠትም ፈጽሞ አይከለከልም።

መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር መታረቅ ተስኗቸዋል። ህወሃት ጥቂቶችን በዝርፊያና የደም ንግድ ቱጃር አድርጎ ትግራይን ግን ከስንዴ ልመና ማውጣት ባለመቻሉ ከሁሉም በከፋ ሁኔታ ህዝቡ በረሃብ ያልቃል። አሁንም የተራበው ህዝብ በርሃብና በቸነፈር ከማለቁ በፊት በቅንጦት የለኮሰውን ጦርነት አቁሞ ምግብ ለተራበው እንዲደርስ ከማድረግ ይልቅ ህጻናትን የጦርነት እሳት ውስጥ ይማግዳል። ከዚህ በሁዋላ የህወሃት ጉዳይ አክትሟል። ዳግም እራሱን የኢትዮጵያ ህዝብ አናት ላይ ሊጭን አጽሞ አይቻለውም።
በእርግጥ ህወሃት በፈጠረው መጠነ ሰፊ ሽብርና የጥፋት አደጋ ምክንያት በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያውያን ዋነኛው ጭንቀት የአገራቸው የወደፊት እጣ ፈንታ ነው። በህወሃት መሪዎች እብሪትና ሴራ ምክንያት የደረሰው አላስፈላጊ የሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ታሪክ ይቅር አይለውም። ህወሃቶች እኛ የበላይ ሆነን የአፓርታይድ ስርአታችንን ካላስቀጠልን ኢትዮጵያ ትበታተን በሚል አደገኛና የተሳሳተ የቁማር እሳቤ ታውረው የጫሩት ጦርነት ያስከተለው ጥፋትና እልቂት ተዘርዝሮ አያልቅም።
የጥቃቱ የመጀመሪያው ሰለባ የሆነው የአገር ዋልታና መከታው የመከላከያ ሰራዊት ነው። የእነሱን ሰላምና ድንበር ለማስጠበቅ፣ ህይወቱን በገፍ የሰዋ ሰራዊት በተኛበት ተረሸነ፣

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ለኢትዮጵያ የ130 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ሰጠ

በህይወት የተረፈውም ምርኮኛና ቁስለኛ ሆነ። እንዲህ አይነት ውለታ ቢስነትና ክህደት በታሪክ ተሰምቶ አይታወቅም።
ህወሃቶች በስሙ ዘውትር የሚነግዱበት ምስኪኑ የትግራይ ህዝብም ያተረፈው ልጆቹን በድጋሚ ለጦርነት መገበር፣ ሞት፣ ስደትና ረሃብ ነው። ለትግራይ ህዝብም ይሁን ለኢትዮጵያ ህወሃት ከተፈጠረ ጀምሮ ትሩፋቱ ነጻነት ሳይሆን ማለቂያ የሌለው ሞትና ውድመት ነው።

አንድ መዘንጋት የሌለበት ሃቅ ግን ታላቁ የህወሃት ሴራ መክሸፉን ነው። ከንቱ እቅዳቸው ቢሳካ ኖሮ ዛሬ በድጋሚ ወይ የአፓርታይድ ስርአታቸውን መልሰው የኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ይጭኑ ነበር፣ ካልሆነም ህዝቡን በዘር ከፋፍለው እርስ በርሱ በማጫረስ ኢትዪጵያን የማፍረስ ህልማቸውን ያሳኩ ነበር።
በእርግጥ ዛሬም ህወሃት እንደገና በማንሰራራት የፈጠረው ችግርና ስጋት ቀላል የሚባል አይደለም። የጦርነቱን ቀጠና ወደ አፋርና አማራ ክልሎች በማስፋት ዘረፋ፣ ግድያና ሁከት

በመፍጠር ላይ ይገኛል። መጠነ ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በማድረግም ህዝብን ከማሸበር፣ ከመከፋፈልና ውዥንብር ከመፍጠር አልፎ የአለም አቀፉን ህብረተሰብ በማደናገርና የኢትዮጵያን ገጽታ በማጠልሸት ላይ ትኩረት አድርገው በስፋት እየተንቀሳቀሱ ነው።

ይህ አሸባሪና ጸረ ኢትዮጵያ ድርጅት እስካልጠፋ ድረስ አስተማማኝ ሰላም በቀላሉ ሊገኝ አይችልም። ዛሬም ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር እያሰሬ የአገርና የህዝብን ደህንነት አደጋ ላይ ጥላሏል። የሆነ ሆኖ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ህወሃት የደቀነበትን የህልውና አደጋ ለመመከት ከዳር እስከ ዳር ሆ ብሎ ተነስቷል። የኢትዮጵያ ህዝብ እረጅም ታሪክ የሚያረጋግጠው ይሄንኑ ሃቅ ነው። ህዝቡ የአገሩን ህልውናና ሉአላዊነት ለድርድር አያቀርብም።

ስለዚህም ህወሃት ሲኦልም ቢሆን ግብተን ኢትዮጵያን እናፈርሳለን ብሎ መደንፋቱ ከንቱ ቅዥት ነው። ኢትዮጵያ አትፈርስም! ህወሃትም በራሱ እኩይነት ከገባበት ሲኦል ተምልሶ ኢትዮጵያ ላይ የአፓርታይድ ስርአቱን መልሶ መጫን ፋጽሞ አይቻለውም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አላሙዲ የመንግስትን ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ዕዳ አልከፈሉም | "መንግስት ገንዘቡን አልቀበል አለኝ" ሜድሮክ

3 Comments

  1. አቤ እንኳን ድምፅህን እንደገና ሰማን። ያአንተ ድምፅ ለኢትዮጵያ ጠላቶች አዳፍኔ ነው። ያርበደብዳቸዋል። አትጥፋ ህዝብህን አነቃቃ።

  2. አበበ ገላው መቼም አንተ ብልሀት አታጣም መከራችንን የሚያበላው ዮሀንስ አብረሀም የሚሉት የዲሞክራቶች አማካሪ ነው የሚሉ በዝተዋልና ጆሮህን ወደዛ ጣል አድርግልን እስቲ።

  3. Hi Abe,

    Who knows እርግማን more than you? You did እርግማን to Meles Z. and he died. Now you`re accusing Tigawie for እርግማን. Well! If it worked for you, it might work for them as well. Just wait and see!

    Bye,

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share