
ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
መንግሥት ያወጀውን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ተከትሎ የህወሓት የሽብር ቡድን በራያ፣ በወልቃይት፣ በጠለምትና በዋግ ግንባሮች ጥቃት መክፈቱን አቶ አገኘሁ ገልጸዋል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት እና የክልል ልዩ ኃይሎች በጥምረት በወሰዱት የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በሽብር ቡድኑ ላይ ኪሳራ እያደረሱበት መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይ የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሽብር ቡድኑን በመመከት ረገድ እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ ታሪካዊ ነው ብለዋል።
የክልሉ ህዝብ በተለይ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ባለሀብቶችና የንግዱ ማኅበረሰብ ያደረጉት ድጋፍም የክልሉን መንግሥት አኩርቷል ነው ያሉት።
የክልሉ ተመላሽ የሠራዊት አባላትና የጦር መኮንንኖችም ሠራዊቱን ተቀላቅለው አሸባሪውን ጁንታ እየተፋለሙት እንደሚገኙ ገልጸዋል።
የክተት ጥሪው አማራንና ኢትዮጵያን የመታደግ ጥሪ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ሁሉም ጥሪውን ተቀብሎ ለሕልውና ዘመቻው እንዲዘጋጅ አሳስበዋል።
በክልሉ ውስጥ ማንኛውም የመንግሥትንም ሆነ የግል መሳሪያ የታጠቀ ለግዳጅ ብቁ የሆነ ወጣት ሁሉ እንዲከትም ጥሪ አቅርበዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።
ፀረ ኢትዮጵያ የሆነውን ከሃዲ ቡድን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ሁሉም መነሳት አለበት ነው ያሉት።
የትግራይ ሕዝብ ከሕፃን እስከ ሽማግሌ በአሸባሪው ጁንታ ፕሮፓጋንዳ ተታልሎ እየወጋን ነው፤ አሁን ግን እውነቱን በመረዳት ቡድኑን በቃህ ማለት አለበት ብለዋል፡፡
በክልሉ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በሰላም እንዲኖሩ እንፈቅዳለን፤ ከጠላት የሚያብሩ ካሉ ግን ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን ነው ያሉት።
ህብረተሰቡ የተጣሩ መረጃዎችን ከሚመለከታቸው አካላት እንዲከታተል እና በማህበራዊ ሚድያ በሚለቀቁ ያልተጣሩ መረጃዎች እንዳይደናገር አቶ አገኘሁ አሳስበዋል።