አቶ ታምራት ሆይ: “ተመክሬ ተመክሬ አልሰማ ያልኩ ሌባ ነኝ” ባሉ ወቅት

 

tamiratእርስዎ በብሄራዊ ቴሌቭዥን በተሰራጨው የፓርላማ ስብሰባ ላይ ቀርበው “ተመክሬ ተመክሬ አልሰማ ያልኩ ሌባ ነኝ” ባሉ ወቅት እኔ እድሜዬ ለአቅመ ፖለቲካ አልደረሰም ነበር። ይሁን እንጂ ንግግርዎን በአይኔ በብረቱ እያዩሁዎት በጆሮዬ ሰምቼዎታለሁ። የዚያን ቀን የወደቀብኝን ድንጋጤና ግራ መጋባት ፈጽሞ አልዘነጋውም። ስለ ሌብነት ነውርነት በተለይም የህዝብና የሀገር አደራን ስለ መጠበቅ እየተመከረ እንዳደገ አንድ ኢትዬጵያዊ ታዳጊ (ልጅ) በጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ ያለ አንድ ሰው የሀገር ንብረት እያሸሸ ከነጋዴ እየተመሳጠረ ህገ ወጥ ገንዘብ ይሰበስብ ነበር የሚለውን ነገር ከእርሶና ከባለደረባዎ አንደበት በጆሮዬ ባለስማ ኖሮ ፈጽሞ ለማመን እቸገር ነበር።

ይህ የእርሶ ተግባር ምን ያህል የውጣቱን ስነ ምግባር እንዳላሸቀውና መጥፎ ምሳሌ ለመሆንዎ ምንም አጠያያቂ አይደለም። እንድያውም በእኛ ሀገር በተለያዩ ነገሮች ላይ ክትትል እየተደረገ ስለማይጠና እንጂ ከዚያ በሁዋላ የተስፋፋው “ምን ችግር አለው? ጠቅላይ ሚኒስትር እንኳ በሚሰርቅባት ሀገር!” የሚለው አገላለጽ ዛሬ ሀገራችን ለተደቀነባት የሙስና ልማድና አስተሳሰብ የራሱን አስተዋጽኦ ሳያደርግ እንዳልቀረ እገምታለሁ። ~~ይህ ሁሉ ሆኖ የወቅቱ መንግስት ጥፋተኛ ነዎት ብሎ እስር ከፈረደብዎ በሁዋላ እስርዎን ጨርሰው ሲወጡ ምንም እንኳ የእርማት ጊዜዎን ቢያጠናቅቁም እንደ አንድ ሀላፊነት እነድሚሰማው ሰው ወይም በኢትዮጵያ ታሪክ በተመዘገበው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ማእረግዎ ሲሉና ያንን ተግባርዎን ወጣቶች እንዳይከተሉት በማሰብ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ሳይጠይቁ አዲስ ሀይማኖት መከተልዎን ብቻ በመግለጽ “ከአሁን ወዲህ ጌታን እንጂ ፖለቲካ አልከተልም” ብለው ሀገርዎንም ትተው ወጡ። የግል ምርጫዎ የተከበረ ነው።
~~~ ግን እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ የኢትዮጵያ መርገምት የሆነች ህወሓት ከሀገራችን ጫንቃ ላይ ስትወርድ መሰስ ብለው ወደ ፖለቲካው አለም ተመለሱ። ይህም የግል ምርጫዎ የተከበረ ነው። ~~ ነገር ግን ይህቺን መርገምት ከተጣለችበት ጉድጓድ ምሰው አውጥተው መልሰው ሊጭኑብን ~ ያውም በስማችን ሲዋዋሉ ስናይ ስንሰማ ~ በቡድን ተደራጅታችሁ አቅዳችሁ ያደቀቃችሁትን ሞራላችንን እንድታክሙ ባንጠይቃችሁም በገዛ ጥረታችን በሁለት እግራችን ልንቆም ድክድክ ስንል ዳግም ልትገዙን በልጆቻችንም ልትደግሙት ስትጣጣሩ ዝም የምንል አይደለንምና ~ ከነክብርዎ ኢትዮጵያን ለቀቅ አድርገው የጀመሩትን ጌታዎን ቢያገለግሉ ያዋጣዎታል ባይ ነኝ!!
የትነበርክ ታደለ

ተጨማሪ ያንብቡ:  መንግስት በኤፈርት ላይ ምርመራ እንዳልጀመረ ገለፀ

2 Comments

  1. Let him exercise his right. You can stop electing him but you never dictate him not to involve in politics unless you are stupid. I hope you are not stupid!

  2. ተመክሬ ተመክሬ አልሰማ ያልኩ ሙልጭ ያልኩ ሌባ ነኝ ባለበት አንደበቱ ዛሬ ተመልሶ ሰየ አብረሀና ያሬድ ጥበቡ ጋር ለሁለተኛ ዙር ከትግሬ ጋር ሊያጠፋን መጣ ነዉ የምትሉኝ። ብአዴን የአማራን ባንክ ሲያቋቁም የጋበዘዉ ይህን ሰዉ ነበር? “ታምራት ላይኔ የአማራ ባንክ ምስረታ ላይ መገኘት አዶልፍ ሂትለርን በአይሁድ ባንክ ምስረታ ላይ መጋበዝ ነዉ” ነበር ያለዉ የኢትዮጵያ አምላክ በክፉ ቀን ያመጣልን ታላቁ አቻምየለህ ታምሩ። መቼም ኢትዮጵያ ተመልሳ ስትቋቋም የመለስ ዘራዊ መታሰቢያ ፈርሶ የአቻምየለህ ይቆማል የሚል ግምት አለኝ። ይህን ሞላጫ ፓስተር ግን አምላክ አንድ ይበልልን ሰዉን አጭበርብሮ አምላክን አጭበርብሮ የት ይደርስ እንደሆን ማወቅ አይቻልም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share