ሙሥና የብልፅግና ፀር ነውና “ይበቃል ! “ ልንለው ይገባናል   (አባ መላ ዘ አብደናጎ)

የተቀናጀ እና እንደ ህጋዊ አሰራር የሚቆጠር ሌብነት   በፊደራል ና በክልል ገቢ ሰብሳቢ መሥሪያ ቤቶች እና በመንግስት የልማት ድርጅቶች  እንደሚሥተዋል ለአዲሱ ለብልፅግና መንግስት የተሰወረ አይደለምና መጪው ጊዜ የህዝቡን  ፤ የመንግሥት በጀትና እና የመንግሥት ፋብሪካዎችን እና የልማት ተቋማትን ሀብት የሚዘርፉትን ገዢው የብልፅግና ፖርቲ አይታገሳቸውም የሚል ፅኑ እምነት የህ ፀሐፊ አለው ።

የፊደራሉም ሆነ የክልል መንግሥታት ፣ ሥራን ያላገናዘበ  ከአገሪቱ አቅም በላይ ፣ ከደሞዝ ውጪ ለጥቅማ ጥቅም የተጋነነ ክፍያ  ፣ እሥከ መምሪያ ኃላፊዎች ድረሥ ይከፍላል ።ይሁን እንጂ  ይሄ ልዩ ጥቅም ተከብረው እንዲኖሩ አላስቻላቸውም ። ( ይህ ፀሐፊ አሳምሮ በሚያውቀው ፋብሪካ   ፣ ቤትም ጭምር በነፃ እያገኙ  ፣ እንደ ቀድሞ የኢህአዴግ ሹመኞች የመሬት ወረራ አዳማ ያለው ለሻሸመኔው ቢሮክራሲ መሬት በመሥጠት ሸጦ እንዲጠቀም እንደሚያደርገው ሁሉ፣ በተለያየ ሰራተኛ ሥም ና በፋብሪካ ሥም  ሲሚቶ ከሙገር ፋብሪካ  እየጠየቁ ፣ በሲሚንቶ ኮንትሮባንድ ኪሳቸው በብር የሞሉ እና ለሙሥና ተባባሪ ሠራተኞቻቸው ረብጣ ብር እንዲያገኙ ያደረጉ  ፣ የመንግሥትን አደራ የበሉ ኃላፊዎች እንዳሉ ያውቃል ። ) ከዚህ እውነት አንፃር ፣  የመንግሥት እንክብካቤ ለእነሱ ቀልድ ነው ፤ ማለት ነው ።

ይኽ ፀሐፊ ፣ በተጨባጭ በሚያውቀው ፣ በመንግሥት የልማት ድርጅቶችም ውሥጥ ፣ ኃላፊነት የተሰጣቸው ባለሥልጣናት ( አሰሪዎች ) ለመንግሥት ሀብት እድገት  በመወገን  ፣በህግ አግባብ ሠራተኛውን  ተቆጣጥረው በማሰራት ፣ ውጤታማ ሆነው   እንዲገኙ አደራ ተጥሎባቸው ሣለ ፤ የመንግሥትን ተልኮ መፈፀም ትተው ሞዝበራን “  በኔት ወርክ “  የመከወን ኩንን ተግባር ላይ ከተሰማሩ የብልፅግና መንግሥት ኪሳራን ሥለማይፈልግ በቸልታ እንደማያያቸው ፅኑ እምነት አለኝ ።

( እነዚህ የመንግሥት አደራ የተጣለባቸው አሰሪዎቹ ( የሥራ ኃላፊዎች ) ፣ የጁንታውን ዓይነት ኔት ወርክ በመፍጠር ፣ ዕውቀት ያለው ጠያቂ የሆነ ኦዲተር በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውሥጥ ዝር እንዳይል ያደርጋሉ ።አንዳንዶቹማ ፣  ራሱን ችሎ ፣ ውሳኔ የሚሰጥ   አሥተዳደር ፣ የሰው ኃብት መምሪያ ( ፔርሶኖል )  የላቸውም  ። ከዚህ የተነሰ አንድ ሰው ከመንግሥት የሥራ ሰዓት ውጪ እንደፈለገው ሰርቶ ትርፍ ሰዓት ቢከፈለው ለምን ብሎ የሚጠይቅ የሚመለከተው የሥራ ቡድን ኃላፊ የለም ።  በእውቀት የካበተ ልምድ ና ከሙሥና የፀዳ የፋይናሥ እና የንግድ መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም ኦዲተር  ከውጪ እንዳይቀጠር  በማድረግም ይህንን ገበናቸውን ሸሽገው ጡረታ ይወጣሉ ። ይህ ብቻ አይደለም  ተራ ቅጥር ሠራተኞቹም መብታቸው ሲረገጥ ፣ የእኔንን እግር ጅብ ቢበላው ምን አገባህ ባዮች እንዲሆኑ   ያለብቃታቸው በሙሥና  ይቀጥሯቸዋል ። )

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ትግል፣ ኢትዮጵያዊነትና የቴዎድሮስ ካሳሁን ዘፈን

ይህንን መሠል ጁንታዊ የኔት ወርክ ሙሥናዊ አያሌ  ተግባራት በዚች አገር እየተፈፀሙ ያሉት  የኢትዮጵያ መንግሥት በተደቀነበት ፋታ የማይሰጥ አገርን የማዳን ቀዳሚ ተግባር የተነሳ እንደሆነ ይህ ፀሐፊ ይገነዘባል ። የመንግሥት ትኩረት ዋናው ጁንታ ላይ በመሆኑ ፣ የኢኮኖሚ ጁንታዎች ለጊዜው ዘረፋቸውን ቀጥለዋል ። ሌብነትን የሚፀየፈው የብልፅግና መንግሥት  አያየንም ብለው ያለዩሉንታ የአገርን እና የህዝብን ሀብት መዝረፋቸው ግን ነገ ” አይነጋ መሥሎት…።” የሚባለውን ተረት እንደሚያስተርትባቸው ይወቁት ።

ነገ  ከነገ ወዲያ በሰፈሩት ቁና  እንደሚሰፈርላቸው ፈፅሞ ባለመጠርጠር ፣ ጠያቂ ባልሆኑት የጥቅም ተጋሪዎቻቸው የበላይ አካላት ፍፁም  ተመክተው ምንም ብዝበዛቸውን ዛሬ ቢያጦጡፉና ለአገር ብልፅግና ና ለላባደሩ እድገት ደንታ ባይኖራቸውም ፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶቹ ባለቤት የሆነው የፊደራል መንግሥት  በጊዜው ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድባቸው ይህ ፀሐፊ ያምናል ።

መንግሥት    አገርን እየበዘበዙ ያሉትን የሚያይበት የራሱ መነፅር እንዳለው ዛሬ ላይ ሆናችሁ ቆም ብላችሁ መረዳት ከነገ ከባድ ውድቀት  ያድናችኋል ብሎም ይመክራል  ። እወቁ ፣ የምትኖሩት ከህዝቡ ጋር ነው ። ህዝቡ ደግሞ አብጠርጥሮ ማንነታችሁን ያውቃልና ከወዲሁ ለንሥሐ ብትዘጋጁ መልካም ይመሥለኛል ። ጥፋት እንደ አውሎ ነፋሥ( እንደ ሱናሚ ) ሳይመጣባችሁ እሥቲ ዛሬ በቃኝን እወቁ ። እሥቲ ዛሬ ለህግ ፣ ለደንብና ለመመርያ ተገዢ ሁኑ ።

ለብዝበዛ የተመቻመቸ ገንዘብ በየፋብሪከው ሥታዩ ፤   ” የፍቅር ቀን  ” ( ቫላንታይን ደይ ) በማለት በኩርማን እንጀራ ና በአንድ ጥፊ ወጥ ሠራተኛውን በመደለል እናንተ በትልልቅ ሆቴል ከበላይ ኃላፊዎቻቸው ጋር በመሆን ፣ በውሥኪ አትራጩ ። …

” ተወው ይሄ ወዛደር እርስ በእርሱ ይንጫጫ ። እኛ በልተገባ ዕድገት ና የደሞዝ ጭማሪ እንዲሁም ፣ ተገቢው ቅጥር እንዳይፈፀም በማድረግ በመቅጠር እንዲሁም ያለህግ ፣ ንብና መመርያ  ፣ የትርፍ ሰዓት እንዲከፈለው ወይም ፊልድ እንዲወጣ በማድረግ ተጠቃሚ  አድርገነዋልና .. ሲሚቶ ከፋብሪካችን ሸጦገዝቶ በውድ ዋጋ ሽጦ ፣ ኪሱን አይቶት በማያቀው ገንዘብ እንዲሞላ ተባብረነዋል እና በቂ የፕሮፖጋንዳ ሃይል አለን ። አትሥጋ ። እዛ ቅንጥብጣቢ ጥለን እዚህ ውሥኪያችንን እናወራርዳለን ። …ማንም ህግን ተደግፈን በሰራነው ሙሥና ተጠያቂ ሊያደርገን አይችልም ። ”  በማለትም አትዘባበቱ ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከባህር ዳሩ የኦህዴድና ብአዴን ውይይት ጀርባ የተደበቁ እውነታዎችና ስጋቶች | አያሌው መንበር

(  ወዳጄ በዓመት አንዴ እንደ ፊውዳል ድግሥ  ‘ በእነ ገብሬ ጅራፍ እየተገረፍክ … ‘  በዩልነታ ተሰልፈህ  ሥጋ  በልተህ ከችግርህ አትላቀቅም ።  በሥምህ  አመካኝተው ሊበሉት ያሰቡት ብር ግን   ለአገርህ የዛሬ ችግሯ  ቢውል ፣ ሥምህ በመልካም ይጠራል ። )

ይህ ፀሐፊ  ፣  ይህንን እውነት በአደባባይ ያሰጣው    የብልፅግና መንግሥት  እውነቱን እንዲያውቅና አፋጣኝ እርማት እንዲወሥድ በመፈለጉ ነው ።ኃይለኛ የዘረፋ መረብ በመዘርጋት “ ምን ያመጣል ! “ በማለት  መዘበትና ማሾፍ “ በቃ ! “ እንዲባልም ነው ።

የየአንዳዳችን ንቃተ ህሊና ባልዳበረበትና  ህሊና በእውቀት ጥማት ማመዛዘኑን በተነቀበት አገር ፤ ጥቂት የፖለቲካ ልሂቃን ለራሳቸው ትርፍ ሲሉ በእውቀት ሰበብ ብልፅግና የራቀውን ህዝብ በተለያየ ሐሰተኛ ትርክት ወደፈለጉበት የጥፋት መንገድ ሊመሩት ይችላሉ። ከሙሥና አንፀርም ሁለት አሥርት ያሥቆጠረው የፌደራል ፀረ ሙሥና እና ሥነምግባር ተቋም የህብረተሰብን ንቃት ከማሳደግ አንፃርን የሚገባውን ሚና አልተጫወተም ።

በሚናው ደካማነት አንፃርም ፣  ሙሥናንን ለመዋጋት በማያሥችል ቁመና ለተደራጀው  ፀረ _ ሙሥና  መታረም የሚገባቸውን  “ የሌብነት ተግባራት “ መጠቆም  ዋጋ ቢሥ እንደሆነ ይህ ፀሐፊ ተገንዝቧል ።

የፊደራል  ፀረ ሙሥና ኮሚሽን ተቋሙ ፣   እጅግ የሸመገለና ጥርስ የሌለው አንበሳ ነው ። ቢያንሥ ለዚህ ፀሐፊ ።

ጥርሥ አልባነቱም ፤ የበላይ   አካላትን ሙሥና በሥውር መርምሮ እርማትም ሆነ እርምጃ የመውሰድ አቅም በማጣቱ  እናም…  የሙሥና ጉዳዮችን ( ሥልጣንን የአለአግባብብ መጠቀምና በሥልጣን መገልገል ና የማይገባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ ወይም እንዲያጭበረብሩ ፣ በመንግሥት ማህተም መጠቀም በራሱ ከባድ ሙሥና ነው ።) ወደ ፀረ ሙሥና ተቋሙ ወሥጄ መፍትሄ ለማግኘት ሥለማልችል  ጉዳዩን በቀጥታ ለህዝብ ፣ ለመንግሥትና ለራሱ ለተቋሙ በአደባባይ ይፋ ለማድረግ ተገድጃለሁ ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፖለቲካ እውነትም ሸር…ጣ  ነው! - ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

በነገራችን ላይ ፣ የሲሚንቶ የሌብነት ኔት ወርክ አንደነበረ እና ዛሬም ኔት ወርኩ እንዳልተበጠሰ  ይታወቃል ። ዛሬም ድረስ የሲሚንቶ መደበቂያ መጋዘኖች በየከተሞቹ ቀበሌዎች አሉ በተለይም በዋና  ዋና ከተሞች ። ኢትዮጵያን እወዳለሁ አገሬ እንድትበለፅግ እፈልጋለሁ ። የሚል ዜጋ ሁሉ ፣ ያለዩልንታ ሌብነትን ና ህግን ተገን አድርጎ ፣ ከደላሎች ጋር በመቀናጀት የሚደረግን ዘረፋ  ለመዋጋት ቆርጦ መነሳት አለበት ። የኢትዮጵያ ደላሎች ዜሮ አምሥት ሳንቲም ግብር  የማይከፍሉ  ሆኖም ግን በሚሊዮን ብር  ጢቢ ጢቢ  የሚጫወቱ በሌብነት የበለፀጉ ቱጃሮች ናቸው ።

በአሁኑ    ሰዓት ፣ ዛሬ ና አሁን ፣ አገርን ለማዳን  የህይወት መሠዋትነት እየተከፈለ ነው ። ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ የሚያመጣትን የአባይን የኃይል ማመንጫ ግድብ ለማጠናቀቅ ዜጎች ከመቼውም በላይ የሚጠበቅባቸውን እያደረጉ ነው  ። በተቃራኒው ደግሞ በመንግሥት ጉያ ውሥጥ የተደበቁ ሌቦችና  ደላሎች ፣ እንዲሁም  የጥቅም ተጋራዎቻቸው አሸሸ ገዳሚ  ነጋሪት ሲጎሰም ይሰማል ። ይህ ፀረ እድገት ፣ ፀረ ልማት የሆነ  ነጋሪት ጉሰማ “ በቃ ! “ ሊባል ይገባል ።  የአገር ብልፅግና እንቅፋት ነውና  !!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

 

 

2 Comments

 1. የፅሑፉ ዕይታ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የአገር መቃወስ የተፈጠረው ለበርካታ ዓመታት በሰንሰለት በሰፊው በተዘረጋ የዝርፍያ እና ሙስና አይደል፡፡ በዚህች ደሃ አገር ሙስና እንደጀብዱ ከታየ ቀጣይስ እንዴት ነው ብልፅግናን ማምጣት የሚቻለው፡፡ በትህነግ አመራር ሆን ብሎ በተሰራ ሴራ ፖለቲካውን ለመምራት ገንዘቡን ሁሉ በመዝረፍ የኢኮኖሚ የበላይነት መኖር አለበት በሚል ስንት ዝርፍያ ተደርጎ ይኽው እስከአሁን በሚደረግ ዘመቻ መንግስት ማጥፋት አልቻለም፡፡ መጀመሪያ አሁን ያለው አስተዳደር እኮ ትንሽ በጥረት ድርጅቶች ላይ ጀምርኩ አለና ነካ ነካ አድርጎ ተወው በሌላ በኩል ያለ የዘረፈ ግሩፕ ስንት የኢኮኖሚ ድጋፍ ለትህነግ ጦር ድጋፍ ሲያደርግ ነበር፡፡

  እንደዚች አገር የለየለት እና የተቀነባበረ ሙስና ዘረፋ የተደረገበት የለም፡፡ ስንቱ ቢሊየነር እና ሚሊየነር ሆኗል፡፡ ለትህነግ ኢዚህ መድረስ እኮ ይኸው ዘረፋ ነው፡፡ ከተማው ውስጥ ያሉ ትልልቅ ህንፃዎች እና አብዛኛው ቢዝነሶች የማን ናቸው? ከተማው ውስጥ በየመጠጥ ቤቱ ገንዘብ የሚበትን ማንስ ነው? ስንቱስ ነው በአስራዎቹ ሚሊየን የሚያወጣ መኪና ይዞ በከተማው የሚታይ ስንተስ ነው በውጪ አገር ባንኮች የተዘረፈ ዶላር በማስቀመጥ እና በውጪ አገር ቢዝነስ በመክፈት ልጆቹን በውጪ በዶላር የሚያስተምር፡፡ በሌላ መልኩ ምስኪኑ አብዛኛው ህዝብ አገር ውስጥ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ መብላት ወደ ማይችልበት ልጆቹን በአግባቡ ማስተማር የማይልበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ስለዚህ የተራ ተራ ዝርፍያ እንዳይሆን አሁን ያለው አስተዳደርም ቆራጥ የሆነ የሙስና መከታተያ እና ሰንሰለት የሚበጣጠስበት ስልት መዘርጋት አለበት፡፡ አሁንም እኮ ስንት ነገር እየተሰራ ነው ወረዳ፣ ክፍለ ከተማ ሌሎቹም ጋር በትሔድ ዝም ብለህ በደረቁ ነው እንዴ መጀመሪያ ተቀጣ እንጂ ትባላለህ፡፡ መቼ ነው ይህ የወረደ አይን ያወጣ አመለካከት ቀርቶ የህዝብ ሃብት በአግባቡ ለልማት የሚውለው፡፡ ስር ነቀል የአመለካከት ለውጣ ለማምጣት በጣም መሰራት አለበት፡፡ ለነገሩማ ተቋማቱ እኮ አሉ ግን የታለየ ለውጥ ግን የለም እንጂ፡፡

  እንደኔ እና ህዝቡ አመለካከት ሙስናና ለማጥፋት ከባድ ቁርጠኝነት/Commitment from Leaders/ ስለሚጠይቅ እንደ አንዳንዱ አገር ሙስናን ለማጥፋት የሞት ፍርድ ተግባረዊ ቢደረግ ጥሩ ነው፡፡ አለዚያ ውሃን በማሰሮ ቢበጠብጡት ቦጭ ቦጭ ና ነገሩ፡፡ ብልፅግና /Prosperity/ ዝም ብሎ አይመጣም በዚህ ላይ በደንብ መስራት ካልተቻለ፡፡ የኑሮ ውድነቱ እንደዚህ ጣራ ላይ እንዲደርስ የዚህ ሙስና ሰንሰለት፣ ስግብግብ ነጋዴ እና ደላለ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡ አንዱ እንደፈለገ ይኖራል ሌላው ዳቦ እንኳን ያርበታል፡፡ ይህ ተለውጥ ለማየት ህልም እየሆነ ነው፡፡

 2. የሚሰማ ጠፋ እንጂ የፅሑፉ ዕይታ በጣም ጥሩ ነው፡፡

  ይህ ሁሉ የአገር መቃወስ የተፈጠረው ለበርካታ ዓመታት በሰንሰለት በሰፊው በተዘረጋ የዝርፍያ እና ሙስና አይደል፡፡ በዚህች ደሃ አገር ሙስና እንደጀብዱ ከታየ ቀጣይስ እንዴት ነው ብልፅግናን ማምጣት የሚቻለው፡፡ በትህነግ አመራር ሆን ብሎ በተሰራ ሴራ ፖለቲካውን ለመምራት ገንዘቡን ሁሉ በመዝረፍ የኢኮኖሚ የበላይነት መኖር አለበት በሚል ስንት ዝርፍያ ተደርጎ ይኽው እስከአሁን በሚደረግ ዘመቻ መንግስት ማጥፋት አልቻለም፡፡ መጀመሪያ አሁን ያለው አስተዳደር እኮ ትንሽ በጥረት ድርጅቶች ላይ ጀምርኩ አለና ነካ ነካ አድርጎ ተወው በሌላ በኩል ያለ የዘረፈ ግሩፕ ስንት የኢኮኖሚ ድጋፍ ለትህነግ ጦር ድጋፍ ሲያደርግ ነበር፡፡
  እንደዚች አገር የለየለት እና የተቀነባበረ ሙስና ዘረፋ የተደረገበት የለም፡፡ ስንቱ ቢሊየነር እና ሚሊየነር ሆኗል፡፡ ለትህነግ ኢዚህ መድረስ እኮ ይኸው ዘረፋ ነው፡፡ ከተማው ውስጥ ያሉ ትልልቅ ህንፃዎች እና አብዛኛው ቢዝነሶች የማን ናቸው? ከተማው ውስጥ በየመጠጥ ቤቱ ገንዘብ የሚበትን ማንስ ነው? ስንቱስ ነው በአስራዎቹ ሚሊየን የሚያወጣ መኪና ይዞ በከተማው የሚታይ ስንተስ ነው በውጪ አገር ባንኮች የተዘረፈ ዶላር በማስቀመጥ እና በውጪ አገር ቢዝነስ በመክፈት ልጆቹን በውጪ በዶላር የሚያስተምር፡፡ በሌላ መልኩ ምስኪኑ አብዛኛው ህዝብ አገር ውስጥ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ መብላት ወደ ማይችልበት ልጆቹን በአግባቡ ማስተማር የማይልበት ደረጃ ደርሷል፡፡

  ስለዚህ የተራ ተራ ዝርፍያ እንዳይሆን አሁን ያለው አስተዳደርም ቆራጥ የሆነ የሙስና መከታተያ እና ሰንሰለት የሚበጣጠስበት ስልት መዘርጋት አለበት፡፡ አሁንም እኮ ስንት ነገር እየተሰራ ነው ወረዳ፣ ክፍለ ከተማ ሌሎቹም ጋር በትሔድ ዝም ብለህ በደረቁ ነው እንዴ መጀመሪያ ተቀጣ እንጂ ትባላለህ፡፡ መቼ ነው ይህ የወረደ አይን ያወጣ አመለካከት ቀርቶ የህዝብ ሃብት በአግባቡ ለልማት የሚውለው፡፡ ስር ነቀል የአመለካከት ለውጣ ለማምጣት በጣም መሰራት አለበት፡፡ ለነገሩማ ተቋማቱ እኮ አሉ ግን የታለየ ለውጥ ግን የለም እንጂ፡፡

  እንደኔ እና ህዝቡ አመለካከት ሙስናና ለማጥፋት ከባድ ቁርጠኝነት/Commitment from Leaders/ ስለሚጠይቅ እንደ አንዳንዱ አገር ሙስናን ለማጥፋት የሞት ፍርድ ተግባረዊ ቢደረግ ጥሩ ነው፡፡ አለዚያ ውሃን በማሰሮ ቢበጠብጡት ቦጭ ቦጭ ነው ነገሩ፡፡ ብልፅግና /Prosperity/ ዝም ብሎ አይመጣም በዚህ ላይ በደንብ መስራት ካልተቻለ፡፡ የኑሮ ውድነቱ እንደዚህ ጣራ ላይ እንዲደርስ የዚህ ሙስና ሰንሰለት፣ ስግብግብ ነጋዴ እና ደላለ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡ አንዱ እንደፈለገ ይኖራል ሌላው ዳቦ እንኳን ያርበታል፡፡ ይህ ተለውጦ ለማየት ህልም እየሆነ ነው፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.