ቴድሮስ አድሐኖም ለሕወሓት ባለስልጣናት የሳተላይት ስልኮች የጤና ድርጅቱን ሽፋን በማድረግ ማስገባቱን የሚገልጽ ሰነድ ይፋ ሆነ

አያሌው መንበር
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከፍተኛ ሙስና እንደሰራ ሰሞኑን የወጣው መረጃ ግለሰቡ ሙስና የሰራው ህወሃትን ለመደገፍ በ “WHO” ስም በገዛው 70 የሳተላይት ስልክ መሆኑን የኦዲት ሪፖርቱ (ከታች ይመልከቱት) ያመለክታል። ሰሞኑን ዶ/ር ቴዎድሮስና ተቋሙ ባለፈው አምስት ዓመት በሙስናና ፆታዎ ጥቃት ሲታመስ ነበር የሚል የኦዲት ጥናት መቅረቡን እናስታውሳለን።
በዚህ ሪፖርት ውስጥ አንድ ገራሚ መረጃ አለ።ይኸውም “በኢትዮጵያ ባለው ፖለቲካ ምክንያት” በሚል ያለምንም አሳማኝ ምክንያት የWHO መኪናዎች የኢትዮጵያን ኔትወርክ እንዳይጠቀሙ የሚያደርግ መሳሪያ መኪናው ላይ ለመግጠም ታስቦ የተገዛው 70 የሳተላይት ስልክና ተያያዥ ቁሳቁሶች ጉዳይ ነው።ይህ ከኢትዮጵያ ኔትወርክ ውጭ ሲግናል የሚያገኘውና እነ ጌታቸው ረዳ በጫካ ውስጥ ሲጠቀሙበት የነበረው ስልክ (ሰሞኑን የፊንላንዷ ጋዜጠኛ ጌቾ ሳተላይት ስልክ ነው የሚጠቀም ያለችው) ያንን የWHO ስልክ እንደሆነ መገመት ይቻላል።
የዚህ May 17/2021 (ከአንድ ወር በፊት) የወጣው የWHO ዋና ኦዲት ሪፓርት እንደሚያመለክተው ዶ/ር ቴዎድሮስ ያለአሳማኝ ምክንያት “ለኮቪድ” በሚል በ2020 እንዲገዛ ያደረጉትና “የፖለቲካ አለመረጋጋት ስላለ” በሚል ገዝተው ወደ ኢትዮጵያ እንዲላክ ሲያደርጉ ተቋሙ ከዚህ የሳተላይት ቁሳቁስ አቅራቢ ድርጅቱ ጋር (WCO ይባላል) አግባብ ያልሆነ ሻጥር ሰርቷል ይላል።ገንዘብም ባክኗል ይላል።
ዋናው ነጥቤ የቴዎድሮስ ሙስና መስራት አይደለም።ሙስና እና ሴሰኝነት ከአጥንታቸውና ደማቸው ጋር የተጋባ የስሜት ህወሳቸው ነው።የእኔን ቀልብ የሳበኝ ለህወሃት እንዲውል አቅዶ የገዛው የሳተላይት ስልክ ጉዳይ ነው።የኢትዮጵያ መንግስት ሲወጋ የቆየው በእነዚህ መሰል አካላት ቀጥተኛ ትብብር መሆኑን ብንጠረጥርም እንዲህ ያለ ማስረጃ አይቸ አላውቅም።አሁንም ከዚህ ድርጊታቸው የታቀቡ አይመስልም።ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግስት ቢያንስ አሁን እነዚህ 70 ሳተላይት ስልኮች የት እንዳሉ አገር ቤት የ WHO ተወካዮችን በህግ አስገድዶ መጠየቅ ይቻል።ሌላው እንዲህ ያሉ መሳሪያቸውን ከአምራቹ ኩባንያ ጋር ተነጋግሮ ከአገልግሎት ውጭ ማድረግ ይቻላል።ዋናው ነገር ደግሞ ይህንን ማስረጃ ይዞ በአለማቀፍ መድረክ አንዳንድ አካላትን ተጠያቂ ማድረግም ይቻላል ባይ ነኝ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  ለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ተፈፀመ፣ ራዲዮ ፋና አመራሩን ቀየረ፣ አብይ አህመድ ሱዳን ናቸው፣ እነዚህና ሌሎች የዕለቱ አበይት ዜናዎች ተካተዋል። አድምጡት

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share