ኢትዮጵያና ጎሳነት (በአልማዝ አሰፋ – ዘረ ሰው)

በአልማዝ አሰፋ – ዘረ ሰው
Imzzassefa5@gmail.com

ሰው ከመፈጠሩ በፊት መሬት ተፈጥራ ተዘጋጅታ በፍጥረ ዘመኗ ሰለቸኝ : ደከመኝ : በላዯ የሰፈሩት ጭነታቸው ከበደኝ ሳትል : የተሰጣትን ቋሚ ቦታ አቅጣጫ ሳትቀይር : የሰው ልጆችንና ሌሎችን ፍጡሮች ከትውልድ እስከ ትውልድ ታኖራለች:: መሬት ድንበር ሳትወስን : ክልል ሳታበጅ : በቆዳ ቀለም : በጎሳ : በብሔር : በእምነት ሳትለይ ለሁሉም ራሷን ክፍት አድርጋ የሰውን ልጆች እያስተናገደች ትገኛለች:: ሆኖም የሰው ራስ ወዳድነትና እርስበርስ ባለመተማመን ተሳስቦና ተስማምቶ ለመኖር ባለመቻል ሰዎችን ተቀብላ እስከሞታቸው ድረስ በሰላም ልታኖራቸው ፈቃደኛ የሆነችውን መሬት በላዯ ላይ ከሚገባ ጮቤ እየረገጡባት ያስቸግሯታል:: እሷ ግን ቻይና ታጋሽ በመሆኗ በትግስት ታኖራለች:: ይህ የሰዎች አለመግባባትና ሕግ ማፍረስ የተጀመረው : በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነቴ እንደተማርኩት (ሌሎች እምነቶች ምን እንደሚሉ ባላውቅም) አዳምና ሔዋን የተከለከለውን ፍሬ በበሉበት ሰአት ነው:: ይህም የአዳምና የሔዋን ድርጊት የሚያሳየው ከመጀመሪያውኑ የሰው ልጆች በጥርጣሬ ስለተበከሉ የፈጣሪያቸውን ትእዛዝ ማፍረሳቸው ዛሬ የሰው ልጆች ላሉበት ውጥንቅጥ ምክንያት ሆኗል ማለት ይቻላል::

 

ያ ራስ ወዳድነትና ስግብግብነት ያመጣው ዕዳ: የአዳምና የሔዋን ልጆች ድንበርና ወሰን ሳይከልሉ:ደከመኝ: ሰለቻችሁኝ : ከበዳችሁኝ : አቆረቆዛችሁኝ ባላለችው ቻይ ምድር ላይ በሰላም በፍቅርና በእንድነት ከመኖር ይልቅ : የእኔና የእኛ በማለት : ጎራ ለይተው እርስ በርስ መጠፋፋትን ነው:: መሬትም ዝምተኛና ታጋሽ በመሆኗና የሰው ልጆች በሷ ላይ ቆይታ ጊዜ እንደ አውሎ ንፋስ ዥው ብለው አላፊ እንደሆነ በመረዳት ይህ የርስበርስ ንትርክ: ድብድብ: ግድያ ለሰው ልጆች ትርፍ የሚያመጣላችሁ ከሆነ ቀጥሉበት : ራሳችሁን ከገፄ እስክታጠፉ እችላችሗለሁ ትላለች:: እኔም ለጠባብ ጎሰኞች የምለው መሬት እንኳን ለእናንተ ደንታ የላትም:: የምትኖሩበት ዘመን አጭር ነች:: እርስ በርሳችሁ መጠፋፋት ምርጫችሁ ከሆነ ቀጥሉበት:: እንበለዋለን ብላችሁ ያሰባችሁትን ሳትበሉ : እንደአረመኔው መለስ ዜናዊ እንደባነናችሁ ትሞታላችሁ:: እንደ ስዬም መስፍን : አንደ አቦዬ ፀሃዬ : እንደሞንጀሪኖና እንደአረመኔዎቹ የወያኔ ጁንታ አባላት ቀባሪ ሳታገኙ : በያላችሁበት የውሻ ሞት መሞት ከፈለጋችሁ : የያዛችሁትን ኢሰባአዊ አረመኔነታችሁን ቀጥሉበት:: አስክፊ አማሞታችሁ ለወለዳችሗቸው ልጆች ሰቀቀንና አሳፋሪ መሆኑን ብትገነዘቡ መልካም ነው:: ምክንያቱም በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም::

 

ድንበር : ወደብ : ክልል የሌለው አገረ-አልባ አናኗር የሰው ልጆች ቢፈጥሩ የሚለውን ተምኔታዊ አመለካከት ለጊዜው ወደ ጎን ገፍተን : ባለንበት በዘመኑ የሰው ልጆች አኗኗር አሰላለፍ ሃቅ ላይ ስናቶክር : አገር በደንብ የምትገለገለው ሁሉም የሕዝቧ ክፍሎች የየራሳቸውን የአገልግሎት አስተዋፅኦ ማበርከት ሲችሉ ነው:: ምክንያቱም አገር የመላው ተወላጆቿ የጋርዮሽ በመሆኗ ነው:: አንዱ የአገሪቱ የሥጋ ልጅ ሆኖ : ሌላው የእንጀራ ልጅ ተደርጎ ሲታይ (ይህም በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ግሙዝ ክልሎች በአማራ ኢትዮጵያውያንና የአማራ ዝርያ ያላቸው የክልሎቹ ተወላጆች ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈፅመው እረመኔነት) : አንዱ በጭንቅላት ጠባብነትና በአስተሳሰብ ብስለት ጉድለት ያጣውን ኃይል በገጀራና በጠመንጃ ጉልበት አገኛለሁብሎ ሲያቅራራ ውጤቱ አገሪቱን የሽብር መስክ ከማድረግ ሌላ አስደሳች ምርጫ የላትም:: የጠባብ ጎሰኞችና ጎጠኞችን የማስተዋል አቅምና ነገሮችን የመገንዝብ ችሎታ ማነስ የሚያሳየው : እነሱ ሌላውን ለማቃጠል የለኮሱት እሳት መልሶ የእነሱ መቃጠያ መሆኑን አለማጤናቸው ነው:: ሌላውን እየገደለ እያፈናቀለ እሱ ሰላምና እረፍት አገኛለሁ ብሎ የሚያስብ ካለ በአለም ዙሪያ ያሉትን የግጭት አውድማዎችን አለማስተዋሉን በየትኛው ዓለም ውስጥ እንደሚኖር ያስጠይቀዋል:: ሌላውን በፍቅርና በሰብዓዊነት ስሜት አቅፎ አንድነትን ከማዳበር ይልቅ እኔ አውቅልሃለሁ : ከመደማመጥ ይልቅ አዳምጠኝን ካበዛ አጥፍቶ የሚጠፋን ትውልድ መኮትኮትና ማብቀል ይሆናል:: ይህንን አገርና ሕዝብ አጥፊ አስከፊ ድርጊት ለማስወገድ ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያውያኖች እንጂ የጎሰኞችና የጎጠኞች አገር እንዳልሆነች ልብ ማድረግ ያስፈልጋል:: ሁሉም የአገራችን ክፍሎች ሕዝቦች “አንድ ለሁሉም : ሁሉም ለአንድ” የሚለውን የህብረት: ተጋግዞና ተሳስቦ የመኖርን ዘይቤ ተከትለው በዜግነት ግዴታቸው የአገልግሎት ድርሻቸውን ማበርከት ይገባቸዋል:: እያንዳንዱ የሕዝብ ክፍል አገሩን በየፊናው ካገለገለ ብልፅግና በአገራችን ይሰፍናል:: ብልፅግና ሰላምን ያመጣል:: ሰላም አመቺ ኑሮ ይፈጥራል:: አመቺ ኑሮ በሕይወት ለመቆየት ምክንያት ይሆናል:: ለዚህም መንግስት በአስተዳደርና በዲፕሎማሲ: ወታደሩ በመከላከያ : ገበሬው በግብርና : ሰፊው ሕዝብ በመተሳሰብና በመተጋገዝ : በዲያስፖራ የሚኖሩና የተቀመጡ የኢትዮጵያ ልጆችና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያ አገራቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ትውልድ አገር ባሉበት በማስተዋወቅና የበጎ ፈቃድ የአገራቸውና የቤተሰቦቻቸውን አገር አምባሳደሮች በመሆን : ማገልግል ግዴታቸው አድርገው ሲውስዱ ዛሬ አገራችንና ሕዝባችንን ካሉበት ስቃይ ተረባርበን ማውጣት ይቻላል:: መተሳሰሪያ ምልእክታችን በአረንጏዴ ብጫና ቀይ ቀለማት ያሸበረቀች አንድ ባንዲራ እንጂ የማህፀን ልጆችና የእንጀራ ወይ የጉድፈቻ ልጆች አድርገው የኢትዮጵያን ሕዝብ የለያዩትን ዘጠኙ የእንግዴ ባንዲራዎች ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያኖችን ሊገልፁ አይችሉም:: ከ110 ቋንቋ በላይ የሚነገርበት ከ80 በላይ ጎሳዊ ቤተሰቦች የሚኖሩባት የጋራችን አንድ አገር ኢትዮጵያ ወደአለፈው ክብሯና ሞገሷ የምትመለሰው የለከፈንን የጠባብ ጎሰኝነትንና የጎጠኝነትን ልክፍት በሽታ ከአእምሮአችንና ከአስተሳሰባችን መንቅረን አውጥተን ስናጠፋው : ማንኛችንም የሰው ልጆች መሆናችንን ስንገነዘብና በሰው ሰራሽ የመልክእ ምድራዊ አሰላለፍ ለዘመናት የተሰጠንን ኢትዮጵያዊነታችንን ያለአንዳች ገደብ በእኩልነት ተቀብለን ስናቅፈው ነው::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ባዶ ቤት በቁንጫ ይወረራል! - አገሬ አዲስ   

 

የጠባብ ጎሰኝነትንና የጎጠኝነትን ልክፍት በሽታ አጀማመር ስንመለከት : ጥቂት የግል ጥቅምና ስልጣን ፈላጊዎች : አጠቃላይ አገርን ለመምራትና ለማስተዳደር ባላቸው የአስተሳሰብ ችሎታቸውና የእውቀት መጠናቸው በራሳቸው ባለመተማመን : የመረጡትን የመንደር መሪነት ግባቸውን ለማሳካት የጎሰኝነትና የጎጠኝነት ፖለቲካ በማራመድ መሃይሙን የዋህ ሕዝብ በቋንቋው ጧት ማታ በፈጠራ ተረታዊ ታሪክ በመስበክ ከዘመዶቹ : ከጎረቤቶቹና : አብሮት ከኖረውና ከሚኖረው የአገሩ ሕዝብ ጋር እንዲጋጭ ማድረግ ነው:: ይህም አካሄዳቸው የሚሰራ ቢመስላቸውም : ያለሙት ሕልም ቅዠት እንጂ እውን ለመሆን የሚችልበት ምክንያት የውሃ ሽታ ነው:: ኢትዮጵያውያን ሲጋደሉና ሲጨፋጭፉ ይኖሯታል እንጂ ለ3000 ዘመናት የኖረችውን የተከበረች አገር አያጠፏትም:: በሃይማኖት በጎሳ ልዩነት ሳይለያዩ ቅድመ ቤተሰቦቻችን ያቆዯትን : አያቶቻችን ለወራሪ አንሰጥም ብለው ደማቸውን ያፈሰሱባትን : እኔና የእኔ መሰል ፈሪዎች ሸሽተን በዲያስፖራ ሰላማዊ ኑሮ ስንኖር ሳይሸሹ ለኢትዮጵያ ልዕልናና አንድነት ከፋፋዩ ባንዳው ወያኔ ጁንታን ሲፋለሙና ሲታገሉ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ሕይወታቸውን የሰዉባትን አገር ትፈርሳለች ማለት ዘበት ነው::

 

ኧረ ለመሆኑ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ ያገኘችው ጥቅምና የደረሰችበት ብልፅግና ምንድነው? ዛሬ ኤርትራውያን ወገኖቻችን አውጥተው ባይናገሩትም : በልቦናቸው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ማሩን የሚሉበት ሰአት ላይ ናቸው:: ምክንያቱም በኃይለ ሥላሴ ዘመንና በደርግ ጊዜም : ከተቀሩት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ግዛቶች የበለጠ የትምህርት እድል የተስፋፋባት ጠቅላይ ግዛት ነበረች:: በንግድ ረገድም በሰፊው ንግዱን ከሰሜን እስከ ደቡብ : ከምእራብ እስከ ምስራቅ: ከትልቅ ከተማ እስከ ትንሽ ቀበሌ ሲቆጣጠሩ የነበሩት በብዛት ኤርትራዊያን ኢትዮጵያውያን ነበሩ:: በመንግስት አስተዳደርም ሆነ በግል ኩባንያዎች ቁልፍ ቁልፍ ቦታ ተሰጥቶአቸው : ሲቀጥሩም በጎሳ እየተጏተት ሲጠቃቀሙ ነበር:: ግን የጎሳ ጠባብነት እንበለው በእራስ አለመተማመን የEPLF መሪዎች ትግላቸውን ETHIOPIAN PEOPLE LIBERATION FRONT ብለው ሰፊውን የኢትዮጵያን አሳትፈው ለመምራትና ለማስተዳደር ከመሞከር ይልቅ : Eritrean People Liberation Front ብለው ለትልቅ ኃላፊነት ብቃት እንደሌላቸው አስመሰከሩ:: ዛሬ አስመራ ያለው መንግስት ምንም እንኳ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ በሚል ጊዜያዊ አመቺ አቋም ከኢትዮጵያ ጎን ቢቆምም : የማይካድ እውነቱ የአረመኔው ወያኔ ጁንታ ስልጣን ኮርቻ መውጫ በመሆን ኢትዮጵያ ላለችበት የ30 አመታት ሰቆቃ አስተዋፅኦ ማድረጉ አይረሳም:: አረመኔው ወያኔ ጁንታና የኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት ጥቅም ባያጣላቸው ዛሬ የኢትዮጵያ እጣ ምን ይሆን እንደነበር ሁላችንም መገመት አያቅተንም:: የደሃውና የየዋሁ ኢትዮጵያውያን እንባና ፀሎት አገራችን ዛሬ ካለችበት በባሰ ሁኔታ ከመፈራረስና ከመበታተን ጠብቋታል:: ይህንን ያነሳሁበት ምክንያት በድህነትና በመሃይምነት ላይ መገንጠል ሲጨመር በተለይ በተገንጣይ በኩል የሚደርሰው ችግር የባሰ ሊሆን እንደሚችል ነው:: የኦሮሞ ጠባብ ጎሰኞችም : እኛ ባለተረኛ ስለሆንን ሌላውን በገጀራና በመጥረቢያ አስገድደን እንገዛለን : አለበለዚያ ኦሮሚያ አገር እናቋቅማለን ብለው የሚያስቡ ከሆነ ትርፉ ሶርያ ወይም ሱማሌ ነው:: ጠባብ ጎሰኞችና ጎጠኞች ስል ወክሉኝ ያላለውን ንፁህ ሕዝብ ሳይጠየቁ በጎሳ ስም እንውክልሃለን እናውቅሃለን እያሉ ሰብዓዊነት የተሳናቸውን ራሳቸውን የሾሙትን በሕዝብ ስም የሚነግዱትን የሰው ጭራቆችንና ከሕዝብ ጉሮሮ እየተነጠቀ የጥቂቶችን የስልጣን ሱስ ለማስጠበቅ ፕሮፓጋንዳ እንዲነዙ ሲከፈሉና እየተከፈሉ ያሉትን የወደቀው አረመኔ ወያኔ ጁንታ ቅጥር ተላላኪዎች ነው:: እነዚህ ጭራቆችና ተላላኪ ቡችላዎች ከሁሉም ጎሳዎች አሉ:: አዲሱን የኢትዮጵያን እንግዴ ልጅ ሳስብ የደቡብ ምእራብ ክልል አወቃቀር አራማጂዎች ይመጡብኛል:: በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ያለው ሕዝብ ችግሩ ድህነትና ድንቁርና ሆኖ ሳለ : ለመምራት የሚፈልጉት ግለሰቦች ባለው የአስተዳደር ቅንጅት ውስጥ ሆነው ለትምህርትና ለልማት ቅድሚያ ከመስጠት የመከፋፈያና የመለያያ ክልልና 10ኛ የእንግዴ ልጅ ባንዲራ በኢትዮጵያ ውስጥ ማምጣት ተቀዳሚ ስራቸው አድርገውታል:: ታዲያስ ይህ ደሃ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዴት ኑሮውን ያሻሽል?

ተጨማሪ ያንብቡ:  አባታችን “አዋቂ” ነው ያሉበት ንግግር አንድምታዎች* (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

 

ውድቀት ቀላል ነው:: ሽው ብለህ ታገኘዋለህ:: አስቸጋሪው የእድገት ተራራ ጫፍ ላይ መድርስ ነው:: በዚህ አቀበት ጉዞ መንሸራተት : መቧጠጥ : መንጠልጠ : ያገኙትን ትርፍ ጠበቅ አድርጎ መያዝ : መተጋገዝና መደጋገፍ በጣም አስፈላጊ ነው:: የዘመኑ ጠባብ ጎሰኞችና ጎጠኞች ከኤርትራዊያን ዕጣ ሊማሩ ይገባል:: የአገሬ ሰው ሲተርት ከአንድ ራስ ሁለት ራስ ይሻላል ይላል:: ከመገንጠልና ብቻ ከመሆን መደመርና አብሮ መሆን ያበለፅጋል:: እንኳን በድህነት እከኳን የምታክ : በልመና ስንዴ ሕዝቧን የምትቀልብ ኢትዮጵያ ትቅርና ያደጉት የአውሮፖ አገሮች በነጠላ ከሚያገኙት እድገት በአውሮፓ ህብረት ውስጥ በመሆን የሚያገኙት ጥቅም ስለሚያመዝን አንድነትንና ህብረትን መርጠዋል:: ጠባቡ ጎሰኛ ከዚህ መማር ትችላለህ?

 

በጣም የሚገርመው ነገር እነዚህ ትምህርት ያረከሱ የሰው ገለባዎች ምን ያህል ወኔቢስና ፈሪዎች መሆናቸው ነው:: እውነተኛና ሃቀኛ ታጋይ ለአመነበትና ለቆመበት አላማ በተባለው ቦታ ውስጥ : በጦሩ ሜዳ : በውጊያው አጥቢያ : ፊትአውራሪ ሆኖ ይታገላል : ይዋጋል : ይሞታል እንጂ : ከእሳቱ 4000 እስከ 10000 ኪሎሜትር ርቆ ምቾት ላይ ተቀምጦ : ኑሮውን እያሳካ : ሚስቱንና ውሽማውን አቅፎ እየተኛ : ልጆቹን እያሳደገ : የኦሮሞን : የአማራን : የትግሬን ደሃውንና ገበሬውን ልጆች : የጥይት ሰለባ ማድረግ አግባብ አይደለም::

 

ምንም እንኳ አገር ውስጥ የጎሰኝነትና የጎጠኝነትን ፖለቲካ ከሚያራምዱት ጎሰኞችና ጎጠኞች ጋር በ180 ዲግሪ የሚንፃራር አመለካከት ቢኖረኝም : ትክክል ባይሆኑም : ላመኑበት አላማ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በአገር ቤት ውስጥ የሚያደርጉት ትግል ድፍረታቸውንና ራሳቸውን ለመስዋእትነት ማዘጋጀታቸውን ስለሚያመለክት ጀግንነታቸውን አደንቃለሁ:: ጀግንነትን ማድነቅ ከአመለካከት ጋር መጣጣም የለበትም:: ከማይስማሙንም : ከምንቃወማቸውም ጀግንነትን መማር ስለሚቻል:: እነዚያ አሜሪካ አውሮፓ አውስትራሊያና አፊሪካ አገሮች ተቀምጠው ጧት ማታ በማህበረ ሰብ መገናኛና በየድረገፅ በመፃፍ ትናንሽ የጎሳ አገሮች በኢትዮጵያ ውስጥ እንፈጥራለን ብለው የሚያልሙ: ለጊዜው ሰላምን ያደፈርሳሉ እንጂ ቋሚ ዘለቄታ አይኖራቸውም:: እነዚህ ትምህርታቸውን የአሻሮ እንኩሮ ያደረጉትን ከንቱዎች: መንከስ የማይችሉ ጥርስ የሌላቸው መጮህ ልምዳቸው የሆነ ጭራ ቆይ ውሾች ናቸው:: በየዲያስፖራው ያሉት የኦሮሞ : የአማራ የትግራይ ሆነም የሌላ ጎሳዎች ጠባብ ጎሰኞችና ጎጠኞች እየጮኸ እንደሚያፈገፍግ ፈሪ ውሻ ናቸው::

 

በሌላው አኳያ የኢትዮጵያን ልዕልናና አንድነት ትንሽ የሚረብሸው ለጠባብ ጎሰኞችና ጎጠኞች አፀፋ ሲመለስ የሚፈጠረው ስህተት ነው:: ይህም በግልፅ ሲቀመጥ ጠባብ ጎሰኝነትና ጎጠኝነት በተመሳሳይ ሁኔታ መመለስ የለበትም:: የሚጎዳውና የሚበደለው በኢትዮጵያዊነቱ መሆኑን ትተን የእኔ ጎሳ ተበደለ ተጎዳ ስንል ጠባብ ጎሰኞችና ጎጠኞች የሚፈልጉትን በማሟላት አንድነታችንንና የአንድ አገር ማንነታችንን ማጣጣል ይሆናል:: ኢትዮጵያውያን ሰከን ብለን በማሰብ በኢትዮጵያዊ ቆዳ እንጅ በጎሳ ቆዳ እንዳንቀበር መጠንቀቅ ይኖርብናል::

 

ሁላችንም እንደምናውቀው ጠባብ ጎሰኞችና ጎጠኞች ከሚቆጣጠሩዓቸውና ከሚነዷቸው የውጭ ኃይሎች ጋር በመተባበር ያልሆነውን ሆነ እያሉ : ከሁሉም ጎሳዎችና ብሄሮች ተውጣጥቶ የሚያስተዳድረውን አመራርና አገዛዝ የአማራ አገዛዝ በማለት ለአመታት አማራ ኢትዮጵያውያንን በመጎንተልና በመቶንኮስ ሲነዘንዙት ከርመዋል:: ከዚያም አልፎ ባለፈው ሁለት አመታት ውስጥ በኦሮሞና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በአማራ ኢትዮጵያውያንና የአማራ ዝርያ ባለቸው በክልሎቹ ተወላጆች ላይ የሚፈፀመው ግድያ የሰው ጅምላ ጭፍጨፋ ሊባል የሚገባ ደረጃ ደርሷል::: ይህ በአማራ ኢትዮጵያውያንና የአማራ ዝርያ ያላቸው የክልሎቹ ተወላጆች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት አንድና ዋና አላማ አለው:: ይህም አማራ ኢትዮጵያውያንን ነጥሎ ከተቀረው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ እንደገዢ በማግለል የጥላቻ ተቀባይ ማድረግ ነው:: በዚህ ረገድ ኢትዮጵያን የጀርባ አጥንት አሳጥቶ ሽባ በማድረግ የኢትዮጵያን ውድቀት ማፋጠኛ ታላቅ ሴራ ሆኗል:: አንዳንድ አማራ ኢትዮጵያውያንም ይህንን የጥላቻ ውሸት ግትር ብሎ ትክክል አለመሆኑን ከማስተማር ይልቅ ስሜታዊ በመሆን በጎሳ በመደራጀት የሴረኞችንና የጠባብ ጎሰኞችን ፍላጎት እያሳኩ ይገኛሉ::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ስለ አማራ መደራጀት [ ክፍል ፩]

 

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ታሪክ ከአማራና ከትግራይ ኢትዮጵያውያኖች ታሪክ ጋር በሰፊው የተያያዘ ነው:: እነዚህም ሁለት የኢትዮጵያ ብሄሮች ለኢትዮጲያ የ3000 አመታት ልዕልናና መሰንበት ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል ብል ውሸት አይሆንም:: የሁለቱ ብሄሮች ባህሎችና ልምዶችም ቅርበት በገሃድ ይታያል:: ይህንን ስል የተቀሩት የኢትዮጵያ ብሄሮች በኢትዮጵያ ታሪክና ህልውና የተጫወቱት ሚናና ያበረከቱት ፀጋ የለም ለማለት አይደለም:: በአማራ ኢትዮጵያውያን ላይ በአሁን ጊዜ የሚፈፀመው ግፍ ለምን : ምን ለማድረግ እንደታሰበና ግቡስ ምን እንደሆነ ለማሳየት የአማራና የትግራይ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ታሪክ የተጫወቱትን የጎላ ሚና መጦቀም ስላስፈለገ ነው::

 

ከላይ ጠቀስ እንዳደረኩት ለረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ ክብርና ሞገስ የሚያንገሸግሻቸው ነፃነቷን ሳታስደፍር ለጥቁር የአለም ሰዎች ኩራት በመሆኗ የሚያንቀጠቅጣቸው የውጭ ተቀናቃኞች : ኢትዮጵያን ለማድከም አማራ ኢትዮጵያውያንን በሌሎች ኢትዮጵያውያኖች አጠላልተው ቅራኔ በሕዝቦች መሃል በመፍጠር ግጭት መመስረት ነው:: ይህንንም ለማሳካት ከሁሉም ጎሳዎች የተውጣጣውን አመራርና አገዛዝ የአማራ በማለት : አማራ ኢትዮጵያውያንን ገዢዎች ማስመሰል ነበር:: ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል እንደሚባለው : ይህ አይን ያወጣ ውሸት : በተሸጡ የውስጥ ጥቂት ጠባብ ጎሰኞችና ጎጠኞች የስልጣን ጥማተኞች ተቀባይነት አግኝቶ እየተራገበ : እንደከብት መንጋ በሚነዱ ምንም ባልገባቸው ተከታዮቻቸው ተሳትፎ የአማራ ኢትዮጵያውያንና የአማራ ዝርያ ባላቸው የክልሎቹ ተውላጆች ላይ ግፍ ተፈፅሟል: እየተፈፀመም ነው:: ይህን የተሳሳተና ከእውነት የራቀ የአማራ እገዛዝ ተብሎ የሚጠራውን የአማራ ኢትዮጵያውያን ውንጀላ በጊዜው ባለማስተባበል ኢትዮጵያ ዛሬ የጎሳዎች መሻኮቻ ሆናለች:: የሚያሳዝነው ይህ የአማራ ኢትዮጵያውያን የሌለ አገዛዝ ክስ : ወያኔ በስልጣን ላይ በነበረበት ዘመን : የትግሬ አገዛዝ በመባል ታውቋል:: ይህም የፖለቲካ ድርጅትንና ብሄርን ለይቶ አለመገንዘብ ነው:: ወያኔ ስልጣን ላይ በነበረበት ዘመን : የትግራይ ኢትዮጵያውያን ከተቀሩት ኢትዮጵያውያን የተሻለ አኗኗር አግኝቷል ብሎ የሚናገር ካለ የጎሳ ጥላቻ የተሞላበት ፍፁም ውሽታም ነው ከማለት አልመለስም:: ዛሬ ደግሞ ባለተረኛ ነው ተብሎ : አመራር ላይ ባሉት በጥቂቶች የኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ተወላጆች ምክንያት የኦሮሞ አገዛዝ ማለት ተጀምሯል:: ይህም የተሳሳተ ግምገማ ነው:: ዛሬም በወያኔ በደርግ በኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስታት የገዢው አካል ከሁሉም ጎሳዎች የተውጣጣ እንጂ በአንድ ጎሳ ሙሉ ቁጥጥር ኢትዮጵያ ተስተዳድራም አታውቅም::

 

ግን ጠባብ ጎሰኞችና ጎጠኞች ከተቻላቸው ሙሉ ስልጣን በመያዝ ሃብት ለማዳበር እንዲያመቻቸው የዛሬ ሰላሳ አመት የተጀመረውን የከፋፍለህ ግዛን የአስተዳድር ዘይቤ መቀጠል : ካልሆነ አገሪቱን በጎሳ ግጭት እያናወፁ የግል ጥቅማቸውን ማራመዱን ስራዬ ብለው ይዘውታል::

 

እንዴት ይህንን እንዋጋ ስንል : በመጀመሪያ ኢትዮጵያዊነታችንን አጥብቀን መያዝ አለብን:: አማራ ኢትዮጵያውያን ሲሞት :ኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ሲገደል : ትግራይ ኢትዮጵያውያን ሲጎሳቆል : ኢትዮጵያውያንነትን አውጥተን አማራ ሞተ : ኦሮሞ ተገደለ : ትግሬ ተፈናቀለ የምንል ከሆነ ጠባብ ጎሰኞችና ጎጠኞች የቆፈሩልን ጉድጏድ ውስጥ ገባንላቸው ማለት ነው:: ይህም አካሄድ አማራ ኢትዮጵያውያንን አውቀውም ሆነ ሳያውቁት የጠባብ ጎሰኝነትና ጎጠኝነት ወጥመድ ውስጥ ከቷቸዋል:: ቀዳማዊት ምሼል ኦባማ እንዳለችው “ሌሎች ወደታች ሲወርዱ : እኛ ወደ ላይ እንወጣለን::” የሚለውን ብንከተል ጎሰኞች ጠባብነታቸውን ሲያሳዩን እኛ ስፋታችንን አቃፊነታችንን ማሳየት ይገባናል:: ሌላው እበት ሲሆን : እኛ እበት በመሆን የአገርን ህልውናና ልዕልናን አናስጠብቅም : የሕዝብን አንድነት አናጎለምስም : የእረንጏዴ ብጫና ቀይ ባንዲራችንን ብርቅነት አናስመሰክርም:: ስህተት በስህተት አይታረምም::

 

በሰው ልጅ እኩልነት : በሰብዓዊነት በሚያምንና በአንድነት ፀንቶ በሚኖር ማህበረሰብ ውስጥ በምንም ቅርፁና ቀለሙ ጠባብ ጎሰኝነትና ጎጠኘት ትክክል የሚሆንበት: ትክክል የሚባልበት አጋጣሚ አይኖርም:: ቢቻል የአገራት ድንበሮች ተወግደው አገራት ዛሬ ያላቸው አደረጃጀት ፈርሶ የሰውልጆች ያላንዳች ገደብ በነፃነት የሚዘዋወሩባት አንዲት ዓለም ብንፈጥር ጥሩ ነበር:: ይህ የእኔ ተምኔታዊ ምኞት ነው:: ለሺ አመታት ብኖርም እውን የሚሆን አይደለም::

 

ስለዚህ እኛ ኢትዮጵያውያን የለከፈንን የጠባብ ጎሰኝነትንና ጎጠኝነትን በሽታ አስወግደን : ጎሳ ሃይማኖት ሳይሉ እናቶቻችን አባቶቻችን አያቶቻችንና ቅድመ ቤተሰቦቻችን ደማቸውና አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ከውጭ ገዢዎች ወረራ በነፃ ጠብቀው ያስረከቡንን ውዲት አገር እንደተረከብነው ኢትዮጵያን ከጎሳነት አላቀን በአንድነት ጠብቀናት ለሚቀጥለው ትውልድ ለማስተላለፍ እንስራ:: ይቻላል!!

 

4 Comments

  1. ኦሮሞ አክራሪዎች የኦሮሞ ልጆችን አፍነው ግብረሰዶምን በለጋ እድሜ የኦሮሞ ልጆች ላይ እየፈፀሙብን ይኸው በእነርሱ ቁጥጥር ስር ወድቀናል ቄሮዎች። ሌሎች ኢዮጵያውያንንም ስለ ግብረሰዶማውያን ግፍ ስንነግራቸው ለእኛ ለግስረሰዶም ተጠቂዎች የኦሮሞ ልጆች ከማዘን ይልቅ ስለሚያገሉን መድረሻ ስለሌለን ግብረሰዶማውያኖቹን እየተለማመጥን ትዕዛዛቾቻቸውን እየፈፀምን እንገኛለን። ግድያም አይከነክነንም እኛ ላይ ምን አይነት አሰቃቂ ግብረሰዶማዊነት ጥቃቶች እድሜ ልኮቻችንን እንደሚፈፀምብን ስለምናይ ታናናሾቻችንንም ኡ ኡ እስኪሉ እየተረባረብን ስላየን ጭካኔ እርስ በእርስ ስለለመድን አሁን እናንተ የምታወሩት ” ኢትዮጵያ በዘር ያልተከፋፈለች……” ቅንጦት ተረት ተረት ፣ ሊሆን የማይችል ፣ ሆኖም የማያውቅ ማታለያ ሆኖ ነው የሚሰማን። እስቲ እውነት እንነጋገር ከተባለ በግብረሰዶም የተደፈሩ እና የደፈሩ እየደፈሩም ያሉት ተከብረው ሰው እይና ፤ ወላጅ አልባዎችን ድረሱልን ሲሉዋችሁ ሳትደርሱላቸው ግብረሰዶምን እያለማመዱዋቸው ማን ደረሰላቸው? ወላጅ አልባዎችን አታግሉዋቸው። ወላጅ አልባዎችን ሳታገሉዋቸው ፣ ሳታሸማቅቁዋቸው ከግብረሰዶማውያን አድኑዋቸው።
    በኦሮሞ ጎሳ መሀከልም ግብረሰዶምንና ግብረሰዶማውያን ያልሆኑ በመባል መከፋፈል አለብን ግን ፤ እንኳን ሁላችንንም አንድ መቶ ምናምን ሚሊየን ዜጎች ኢትዮጵያውያን ተብለን ተጨፍልቀን በአንድ ዣንጥላ ስር ልንካተት።

  2. ጎሰኝነትን (ዘረኛነትን) ማስወገድ ስለ ማስፈለጉ የተጻፈው ምሥጋና ይገባዋል፡፡ ነገር ግን “ብሔሮች” በሚል ቃል መጠቀም በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ ኢትዮጵያ አንድ ብሔር (ሐገር) ነት፡፡ በተጨማሪም፤ በአሁኑ ጊዜ፤ ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት መሠረታዊ ሥርዓት በኢትዮጵያዊነት፤ በዲሞክራሲ፤ በሕግ የበላይነት፤ በእኩልነት፤ በሰላም፤ ወዘተ፤ የተመሠረተ ሕገ መንግሥት ተግባራዊ ማድረግ እንዲሁም የኢትዮጵያን ሕዝብ አሰቃቂ ከሆነው የድህነት አረንቋ የሚያላቅቅ የተሟላና ሥልታዊ የሆነ የልማት እቅድና መርሐ ግብር ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡

  3. ዶ/ር እብይ ባንድ አጋጣሚ የኢትዬጵያ ህዝቦች ሳንሆን አንድ ህዝብ ነን ሲል ሰማሁት፤ እሰየው ነው።ፓለቲካችን ወደ ቀልቡ እየተመለሰ መሆኑን ጠቁዋሚ ነው። ታዲያ አሁን ያለው ህገ መንግስት ለማን ሲባል ነው ለአንድ ቀንም ቢሆን ስራ ላይ የሚለው ? ለኦነግ ሽኔ ወይስ ለወያኔ የሙት መንፈስ እና ለመንፈስ ልጆቹ ? በጎሳ የተከፋፈለ ስርአት የእኩልነት የፍትህ እና የዲሞክራሲ ስርአት ከቶ ሊገነባ አይችልም ፤ ጊዜው ያለፈበት የሻገተ የባላባት ስርአትን መልሶ ለመፍጠር ካልሆነ በስተቀር።ይህም ቢሆን የኔ ጎጥ ያንተ ጎጥ በመባባል በራሱ የሚጠፋፋ /Self destructive /ስርአት ነው።ዛሬ አንዱ ዘር ተመርጦ ሲገደል እኔ ከገዳይ ዘር ነኝ ብለህ ዝም ያልክ ሁሉ፤ ነገ በመንደርህና በቀብሌህ ፣በወንዝህ ሲመጣብህ ብትባንን ያለቀ ስአት ነው የሚሆንብህ።
    Beware !Beware!Beware!

  4. ከ110 ቋንቋ በላይ የሚነገርበት ከ80 በላይ ጎሳዊ ቤተሰቦች የሚኖሩባት የጋራችን አንድ አገር ኢትዮጵያ ወደአለፈው ክብሯና ሞገሷ የምትመለሰው የለከፈንን የጠባብ ጎሰኝነትንና የጎጠኝነትን ልክፍት በሽታ ከአእምሮአችንና ከአስተሳሰባችን መንቅረን አውጥተን ስናጠፋው : ማንኛችንም የሰው ልጆች መሆናችንን ስንገነዘብና በሰው ሰራሽ የመልክእ ምድራዊ አሰላለፍ ለዘመናት የተሰጠንን ኢትዮጵያዊነታችንን ያለአንዳች ገደብ በእኩልነት ተቀብለን ስናቅፈው ነው::

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share