በአገሪቷ ለዘመናት ሲታጨድ ሲወቃ የነበረን የክፉዎች ሴራ መንስኤ እና ዉጤት አብዝቶ መደጋገም እየደረሰ ላለ የዜጎች ሞት እና መጠነ ሰፊ ጥፋት ለማስፋፋት እና ለማስጠል ጊዜ ከመስጠት ያለፈ ትርፍ የሚያስገኝ አይደለም ፡፡
በአንዲት አገር ላይ ምንም ዓይነት ሰርቶ ለመኖር ደፋ ቀና ከማለት ወጪ በማንነት እና በዝነት ለይቶ የማሳድ ጅምር በ1960ዎች የተጠነሰሰ በአገር እና ህዝብ አንድነት እና ደህንነት ላይ የተሸረበ በጥላቻ የተዘራ እና የጎመራ የአገር ክህደት ሴራ መሆኑ ለ27 ዓመታት እየታወቀ እንደ አዲስ ነገር በችግር ላይ መመላለስ ለማንም አይበጅም ፡፡
ኢትዮጵያዉያንን ማሳደድ እና መግደል ከጨረቃ በታች የማንም መብት እና ስልጣን እንዳልሆነና ይልቁንስ ኢ-ሠባዊ እና ኢ-ተፈጥሯዊ ፀረ ኢትዮጵያዉያን ተልዕኮ ነዉ ብሎ በፊት ለፊት ከህዝብ ጎን እና ግንባር ከመቆም ይልቅ የንፁሃን ዜጎች ሞት …..እያሉ ለ27 ዓመት የነበረዉን የመከራ ዘመን ከማራዘም ዉጭ ትርጉም አልባ መሆኑን መዘንጋት ከንቱነት ነዉ፡፡
ከመሰረቱ ኢትዮጵያዊነትን ለማፍረስ ኢትዮጵያዊነት ማንነት እና እሴትን ማሳከር እንደ ዋና የትግል ዘዴ በመቁጠር ጭምር በጥላቻ ኢትዮጵያዊነት“አማራ ” እና መገለጫዎችን በማጥፋት ላይ ለዓመታት የሰሩ እየሰሩ ላሉት ሃይሎች ትክክለኛ መነሻ ፣ተግባር እና ዓላማቸዉን የሚገልፅ መጠሪያ ለመስጠት ህዝብ እና መንግስት አንድ መሆን ያልቻለበት ሚስጥር አጣያያቂ ከሆነ ሰብብቷል፡፡
ለመሆኑ በዓለማችን በሽብርተኝነት የሚፈረጁ እና የተፈረጁት እንኳን የኛን አገር ያህል ሲሶ በደል እና ግፍ በህዝባቸዉ እና በአገራቸዉ አልፈፀሙም፡፡
እኮ እኛ አገር ቆማጣን ቆማጣ ለማለት ይሉኝታ ነዉ ይሁንታ ፡፡ በአገር ማፍረስ፣ ህዝብ ማስለቀስ ፣ ለይቶ ፍጅት ፣ አገር ክህደት…..ቢሆን በዚህ በ21 ኛ ክ/ዘመን በእኛ አገር ከሆነ የዓማት ዘግናኝ ወንጀል እና ድርጊት በላይ ምን ይምጣ፡፡
በየትኛዉ ዓለም እና አገር ነዉ ? ከመሬት እየተነሳ መሬት ፤አፈሩን ልቀቁ እያለ ዜጎችን ከትዉልድ ቅየ እያሳደደ የሚገድል ፣ የሚበድል እና የሚያሳድድ ኃይል ከመንግስት አቅም ዉጭ ሊሆን የሚችለዉ ፡፡ ለመሆኑ የዓመታት የዜጎች ሞት እና መሳደድ አሁን ለደረስንበት ዘመን መማሪያ እና ማሳረጊያ ሊሆን እና ወንጀለኞች በአገር እና ህዝብ ላይ ላደረሱት ክህደት እና ጥፋት ዋጋ ሊከፍሉ ሲገባ እየተሸለሙ እና እየተሾሙ ባለበት አገረ ኢትዮጵያ ማን ይሆን ዕዉነትን ከሀሰት ለዩ ብሎ የዜጎችን ዕንባ የሚያብስ ?
ለዚህ መነሻ የሆነኝ ከሰሞኑ ከጀርመን ወንጀል በስሙ ይጠቀስ ወንጀለኛም ይጠየቅ የሚል ፅሁፍ መልዕክት አየሁና ደስታም ግርምታም ተሰማኝ፡፡
ለመሆኑ ላለፉት 27 ዓመት በኢትዮጵያችን በመበረዉ ብሄራዊ ስሜትን የማጥፋት እና የለይቶ ጥቃት ፣ፍጅት …..ወንጀል እና ተጠያቂነት ቢረጋገጥ ኖሮ አሁን አገሪቷ ካለችበት ትሆን ነበር ወይ፡፡
የዘር ፍጅትን የስልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ አድርገዉ የኖሩት እና በኋላም በህዝብ የቁጣ ማዕበል ጥግ የያዙት የህወሃት/ ትህነግ ከፍተኛ አመራሮች በዘር ፍጅት እና አገር ክህደት ዕኮ ሊጠየቁ ይገባ የነበረዉ መጋቢት 2010 ዓ.ም . ከስልጣን እብደወረዱ ነበር ግን ከዚያ አስካሁን ማሰብ አይደለም ማሳሰብ በራሱ ጥፋተኛ ያስደርጋል ዕኮ ለምን ያለ ማን ነዉ ?
ይህ ብቻ አይደለም በ1983 ዓ.ም የሽግግር ምስረታ የጥፋት እና ጥላቻ እሾክ በመዝራት ከዚያ አስካሁን ለይቶ ማጥፋት – ዘር ፍጅት – በማቀናጀት ፣በማደራጀት እና በመምራት ሚና የተጫወተ በዚሁ ደርጊት አስካሁን ሲቀጥልበት ይህን እና ድርጊቱን ተዉ ባይ በሌለበት እንዴት ይሆን ወንጀል በስሙ የሚባለዉ፡፡
ባለቤቱ ያቀለለዉን ባልዕዳ አይቀበለዉም እንዲባል ኢትዮጵያዉያን ኢትዮጵያ ማለት ዓማራ ነዉ ዓማራም ኢትዮጵያዊ ነዉ ከዚህ በተቃራኒ ለዓመታት የኢትዮጵያን እና ህዝቧን አብሮ የመኖር ዕሴት አደጋ የጣሉት ፀረ ኢትዮጵያን ናቸዉ ብሎ ለመጠየቅ ህብረት እና አንድነት ከወዴት አለ?
ለመሆኑ በእዉነት በኢትዮጵያ ዘመኑን እና ኢትዮጵያዊነትን የማይመጥን ወደር የለሽ ግፍ እና ሰቆቃ በህዝቦች ማንነት ለይ ተመስርቶ ለዓመታት ያልሆነ ምን ነበር ምን አለ?
ከዚህ በላይ ሽብር፣ ሞት፣ ስደት፣ ድህነት …..መጎሳቆል ለሚደርስበት ኢትዮጵያዊ ህዝብ ተጠያቂ የሚሆን አካል አለመጠየቅ ችግሩ የጥፋት አራማጅ ሳይሆን የህዝቦች ህብረት እና አንድነት አለመኖር ወይም አለመደራጀት ነዉ፡፡
በየትኛዉም መንገድ ለዘመናት ለተፈራረቁ ችግሮች መንስኤዉን እና ችግሩን ማስተጋባትም ሆነ ለሌላ አካል ማጋባት መፍትሄ የሚሆነዉ ራስ ለራስ እና ለአገር ደህንነት በህብረት እና አንድነት መንፈስ ዘብ መቆም እና አከፋዉን አካፋ ብሎ ህልናን መከላከል እና ማስከበር ይበጃል፡፡
ከዚህ ዉጭ የአንድ አገር ማህበረሰብ አካል የሆነ ህዝብ እና ዜጋ ከሞት ወደ ሞት የሚሸጋግረዉን መንስኤ እና ዉጤት ለሚያዉቅ ድርጊቱን በተግባር እያየ ለማዉገዝ ለማይፈልግ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ላለዉ ማንነት ላይ ያተኮረ የዓመታት ጥቃት ስም አዉጡልኝ ማለት አስቸጋሪ ነዉ ፡፡
ለዓመታት የነበር እና ያለ ችግር ስያሜ አይደለም ግልፅ ዓላማዉ ብሄራዊ አንድነትን ለማናጋት የሚደረግ የግማሽ ክ/ዘመን ዉጥን ተከታይ አካል መሆኑን ማንም ሠባዊ ፍጡር የሚያጣዉ ላለመሆኑም ግልፅ ነዉ፡፡
እናም ነገሩ ግራ ገብ ከመሆኑ የተነሳ ባለቤት የሆነዉ ህዝብ ሞት በቃ ብሎ በአገራችን ሞት እና ስደት ቁጭ ብለን አንጠብቅም ብሎ ራሱን እና አገሩን ከመጠበቅ ዉጭ ማን ምን እንዲል ነዉ?
የዛሬዋ አሜሪካ በኢትዮጵያ የዉስጥ ጉዳይ ገብታ ሠባዊ መብት አየያዝ ያሳስበኛል በማለት በቁስል ላይ መርዝ የምትነሰንስ ለአለፉት 27 ዓመት በሞግዚትነት ያስቀመጠችዉ መንግስት በኢትዮጵያ እና ህዝቧላይ ያደረሰዉን ሰባዊ፣ ብሄራዊ እና ቁሳአካላዊ ዉድመት አንድም ቀን አሳስቧት እንደማታዉቅ እያወቅን ዛሬ በኢትዮጵያዉያን -አማራ – የሚደርስ ሰቆቃ የዘር ፍጅት መሆኑን መስክሪልን ማለት ለእኛ ለኢትዮጵያዉያን ሞኝነት ነዉ ፡፡ ምክነያቱም አገልጋዮቿ ለሚያደርጉት ማንኛዉም ጥፋት ከለላ እና ዋስትና መስጠት ተግባሯ በመሆኑ እና ይህም የተቀደሰ የዲሞክራሲ መገለጫ ብላ ስለምትተረጉመዉ ነዉ፡፡
“ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ”
ማላጂ