April 10, 2021
29 mins read

ሁላችንም የእግዚአብሔር ንብረቶች የሆንን  ሰዎች እንጂ ቋንቋ አይደለንም – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

“ ሰው የተወለደው ነፃ ሆኖ ነው።የሁን እንጂ  ( በማስተዋል ብትመለከቱ ) እርሱ በየትም ሥፍራ በሰንሰለት ውሥጥ ነው ። “

( እንዴት ነው የታሠርንበትን ሰንሰለት በጣጥሰን ሰው መሆናችንን የምናውጀው ?)

Man was born free and everywhere he is in chains .”

Jean_Jacques  Rousseau

******************************

” The state of nature   has  a low  of  nature  to govern it which obliges everyone ; and reason , which is that law , teaches all man kind , who will but consult it ,  that  being all equal and independent , no one ought to harm another in his life , health , liberty or possession . ”

John  Locke

ተፈጥሮ የራሷ ህግ አላት ። ሰው ከተወለደ ጊዜ ጀምሮ በተፈጥሮ መሪነት እንደሚተዳደር ይታወቃል ።ተፈጥሮ  በአሥገዳጅ ምክንያታዊነት ሰውን ትቆጣጠረዋለች ።ተፈጥሮ  ከሁኔታዎች ተነሥታ ” ይህ ቢህን ይህንን አደርጋለሁ፤ ይህ ድንገት ቢፈጠርና ለአደጋ ብጋለጥ  ደግሞ በዚህ መንገድ አመልጣለሁ ። ” በማለት  ተፈጥሮ ራሷ በሰጠችው ህሊና እንዲያስብ ታስገድደዋለች ።

እያንዳንዱ ሰው በራሱ ክብር ያለው ና በተፈጥሮ ነፃ ሰው እንደሆነ ና ማንም ሰው የሌላውን ጤንነት ፣ ነፃነት ወይም የግል ሀብቱን መደፈር እንደማይገባውም በተግባር ታስተምረዋለች ።

ይህ ማለት ሰው ንብረትነቱ የፈጣሪ እንጂ በተናጥል ይሁን  በቡድን የገነነ የአምሣየው ሰው ንብረት መሆን እንደማይችል አስረግጦ ይነግረናል ።  ማንም ሰው ፣ ነፃነትን ፣ ጤንነትን ፣ ህይወትን ለለሌው ሰው ለመሥጠት አይችልም። ተፈጥሯዊ የሆነውን  የመናገር ነፃነቱን ፣ የመንቀሳቀስ መብቱን  ፣ ለመኖር መጣርና መጋሩን ማንም ሊቀማው አይችልም ።

ጆኑ ሎክ ሰው ፣ በገዛ ፍላጎቱ እንኳን የራሱን ህይወት ለማጥፋት የተፈጥሮ ህግ አይፈቅድለትም በማለት በፖለቲካዊ ፍልሥፍና መፀሐፉ አሥፍሯል   (…) ።

ዛሬ  በእኛ ምድር ፣ በኢትዮጵያ ፣  እንኳን የገዛ ህይወትህን በገዛ ራስህ እንዳታጠፋ የሚከለክል የተፈጥሮ ህግ  ሊበረታታ ይቅርና አንድ የሰው ቡድን ከመሬት ተነስቶ ፣ አንዳችም በደል ያላደረሰበትን ሰው ፣ በቆንቋው ልዩነት ብቻ በተኛበት ሲያርደው ይሥተዋላል።  ለውይይት እንፈልግሃለን በማለትም በመትረየስ  ሊረፈርፈው ይችላል ።

ለምን ይሆን  ከመጋቢት 24 /2010 ዓ/ም ጥቂት ወራት  በኋላ እንዲህ ዓይነቱ ፣ የጭካኔ ተግባር እየተስፋፋ እና አድማሱን እያሰፋ የመጣው  ?

በለሀገሩ ፣ የተፈጥሮ ቸርነትን ዘንግቶ ፣ መሬቱ ፣ አየሩ ፣ዝናቡ ና ፀሐዩ የፈጣሪ ትሩፋት መሆኑን ረሥቶ ነውን ? ወይሥ ለዓለም ተምሳሌት የሆነ አኩሪ ባህሉን ፣ በበአዳን በመነጠቁ ይሆን  ? ወይስ ኃይማኖተኛነቱን ዘረኝነቱ ሥለአሸነፈውና ፈጣሪን በመካድ ፣ህዝብ በራሱ ላይ ያመጣው መቅሰፍት ነውን ?

ሁለም ጥያቄዎች ጨዋውን የኢትዮጵያን ህዝብ አይወክሉም ። ዛሬም ጨዋው ባለሀገር ተፈጥሯዊ መብቱን የሚጠብቅ ፣ ለአምሳያው ነፍሥ የሚሳሳ ፣ ፈርሃ እግዛብሔር ያለው ነው ። የዲያቢሎስን ተግባር በየገጠር ከተሞቻችን እየፈፀሙ ያሉት በፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች የሚደገፉ ፣ ሰው መሆናቸውን ነዋይ እና ሃሽሽ  ያሥረሳቸው ና ህሊናቸውን ያጡ ባንዳዎች ናቸው ።

ከወያኔ አብዮታዊ ዴሞክራሲ   የጥርነፋ ፣ ከፋፍሎ በሪሞት ኮንትሯል የመግዛት   ሥርዓት መገርሰስ በኋላ እንደ አሸን መፍላታቸው ሰበቡ ደግሞ ” የኢትዮጵያ ብልፅግና በአዲሱ የአብይ መንግስት እውን ይሆናል ፡፡ ” በማለት የደመደሙ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ፤ ” ይህንን ኢትዮጵያን አስቀዳሚ ለውጥ መቀልበስ ፣ ጥቅማችንን ከሚያሳጣ አደጋ ይሰውረናል ፡፡ በማለት በማሰባቸው ነው ፡፡

የለውጡ ወይም የብልፅግናችን ደንቃራዎች ፣ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም  ፣ ወደሥልጣን የመጣውን ፣የኢህአዴግን አብዮታዊ ዴሞክራሲን የሚቃወመውን  “የለውጥ ኃይል ”  (ሲጀመር እነ ” ቲም ለማ ” (የለማ ቡድን ) ይባል ነበር ። በሥተኋላ በለውጡ መንገድ አቀበትነት ተዳክመው ይሁን በቁልቁለቱ ተዳፋትነት ተንከባለው ፣ አልያም በናዳ ተመተው አይታወቅም ፣ ዶ/ ር ለማ መገርሣ ከጫወታው ውጪ መሆናቸው ይታወቃል።) ከጅምሩ አለወደዱትም ነበር፡፡

ይህ ለውጥ ግን  በጠ/ሚ  ዶ/ር አብይ አህመድ ” መደመር ” በሚባለው ፍልሥፍና ወይም ደግሞ ” መደመራዊ ዴሞክራሲ ” ጉዞውን የህዝብን የልብ ትርታ እያስተዋለ መጎዝ ጀመረ፡፡ ይሁን እነጂ ከዓመት በኋላ ፣ ለውጡን በዋይታ ና በሰቆቃ ውሥጥ  ተዘፍቆ እንዳይላወስ የሚደርጉ እሳቶች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተጠና እና በከፋ መልኩ ተለኩሰው መቀጣጠል ጀመሩ ፡፡

የለውጥ ኃይሉም ያለእረፍት ፣ አገርን ለማፍረስ ከሚጥሩ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ጋር ውጊያ ጀመረ ፡፡  የለውጥ ኃይሉ ከአገር ገንጣይና አፍረሽ ባንዳዎች ጋር   ፣ ሌት ተቀን  እየተናነቀ ወይም  ኢትዮጵያን እሥከ ክብሮ ለትውልድ ለማሥረከብ ቆራጥ አመራራ እየሰጠ   ፤ ” አይዞችሁ ፣ ወደፍትህ ፣ ወደ ዴሞክራሲ ፣ ወደ ጋራ ተጠቃሚነት ፣ ወደ ሠላም ና ፀጥታ ወዘተ ። አሻግራችኋለሁ ፡፡ ብቻ ታገሱኝ ። ጊዜ ስጡኝ ፡፡ ”  እያሉ የለውጥ ጉዞው ቀጥሎ እነሆ    ሦሥተኛ ዓመቱን ጨርሶ አራተኛውን ተያያዘው ።

ጠቅላይ ሚኒስትራችን  ” ታገሱኝ ። ጊዜ ስጡኝ ” በማለት  የህዝብን ትዕግስት መጠየቃቸው ተገቢ ነው ። የአገራችን ችግር እንደ በጋ ጉም በተአምር ብን ብሎ የሚጠፋ ባለመሆኑ ዜጎችን ትዕግሥትና  ትብብር መጠየቃቸው አግባብ ነው ። ከ 60  ዓመት በላይ የዘለቀን  የጎሣ ፖለቲካን ወይም የቅኝ ገዢዎችን  የተቀነባበረ የቆዳ ማዋደድ የከፋፍለህ ግዛ  ቦንብን እና የአሜሪካ ና የአውሮፓ ቱጃሮችን ብዝበዛ ና የመክበር መሻትን ፣ በጣት በሚቆጠሩ ዓመታት ለመቀልበሥ አይቻልም ። በዚህ ላይ እውነቱ ሲነገራቸው የማይሰሙ ፣ የጎረቤቶቻቸው መራብ የሚያሥደሥታቸው ፤ በሤጣናዊ አሥተሳሱብ ህሊናቸውን ያጨቁ መሪዎች ፣ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ወይም የእግዜር ውሃ ተጠቅማ በፍትሐዊነት ለመበልፀግ  ሥላሰበች ፣ አንዳችም ጥቅም ሳይጎድልባቸው ፣ ገና ለገና” ኢትዮጵያ ከበለፀገች በትክክለኛው ፍትህና ርዕትህ በሰፈነበት  የዴሞክራሲ መንገድ ላይ መራመድ ከጀመረች ፣ የምናሥተዳድረውን ህዝብ በአባይ ፖለቲካ እያሥፈራራን ፀጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛ ማድረግ አንችልም ። ” በሚል ግላዊ የገዢነት ሥጋት  ፣   የግብፅንና የሱዳንን ህዝብ በማወናበድ በኢትዮጵያ ላይ  በጠላትነት  ለማነሳሳት እየቀሰቀሱ ፣ ድንበር እየገፉ ፣የለውጡ  መንግሥት በሙሉ አቅሙ የተቋም ግንባታ ላይ እንዳያተኩር እያደረጉት መሆኑንን ሥናሥተውል የመንግሥት መሆንን አበሳ እንገነዘባለን ። እናም ትዕግሥት ና ትብብር እንደሚያሥፈልግ የምንረዳው ሊውጡን ያሰፈሰፉትን ጠላቶቻችንን እና የቅጥረኛ ባንዳዎቻቸውን ሤራ በማሥተዋል ነው  ።

እርግጥ የዳቦ ችግሩ የበረታ ህዝብን ያለ ዳቦ ” ታገሥ..” በትለው  “ረሃብ ሥንት ቀን ይሰጣል ? “ብሎ ሊጠይቅህ ይችላል ። አንተም ፣ ” ተደምራችሁ ፣ ተበዳድራችሁ ፣ ” አንተ ትብሥ ፤ አንተ  ትብሥ ፡፡ ”  በመባባል ይህን ቀን አሣልፉ እንጂ ነገ ዳቦ በእርጎ ትመገባላችሁ ። ” ብትለው ፣ ( አትለውም እንጂ ) ” ምን ታሾፍብኛለህ ?! ”  ብሎ ግሣላ እንደሚሆንብህ ታውቃለህ ።

ዛሬ በአገራችን ላይ ያንጃበበውን የደህንነት ሥጋት እያየን በህዝብ የዳቦ ጥያቄ ላይ ማሾፍ ከቶም አንችልም ።”  የመደመር መንገድም ወደ ዳቦው ጋር ያደርሥኸል ፡፡ ” በማለት በከሰረ አራዳ ትወራ በዜጎች ተገቢ ጥያቄ ላይ አናፊዝም ።

በትወራ ደረጃ ብቻ ነገሮችን በማየት  በአገራችን በመደመር ፍልሥፍና አደበሥብሰን የማናልፋቸው የህግ ፣የሰብዓዊ መብትና የመሰረታዊ የተፈጥሮ መብት ጥያቄዎች እንዳሉ ይኽ ፀሐፊ ይገነዘባል ።

ሰዎች ያለመንግሥት እንኳን አሥከብረው የኖሯቸውን የየግል መብቶቻቸውን ፤ በቡድን ተደራጅተው የሚጥሱ ” በለዔ ሰቦች ” በኢትዮጵያ ተፈጥረዋል ።እነዚህን ሰው በላ ግለሰቦች በዋነኝነት የፈጠራቸው የሆድ ችግር መሆኑ መታወቅ አለበት ። እንዳሰማሯቸው የውሥጥ ሥግብግብ  ባንዶች እና በገንዘብ ከሚረዶቸው በሰው ደም ለማትረፍ እንደሚሯሯጡት ነገዴዎች ቢጠግቡ ኖሮ ፣ በሥለት ወገናቸውን ፣ አምሳያቸውን ምሥኪን ሰውን ሁሉ ዐይናቸውን ጨፍነው ቃላት በማይገልፀው ጭካኔ አያርዱም ነበር ።እነዚህ በሆድ ችግራቸው ሰበብ የዳቢሎስን ተግባር የሚፈፅሙ ሰዎች ፣  ንፁሐንን በሚዘገንን ጭካኔ ሲጨፈጭፉ ፣ አሥሮ ለማሥገረፍ፣ለማሳሰር ፣ ለማስገደልና ብቻቸውን እንደ ጅብ ለመብለት የተከለሉ ክልሎች የአደረጃጀት በህሪ የጎላ ትብብር እንዳደረገላቸው ይታወቃል ።  ይህንን ማንም ማሥተባበል አይችልም ። በተወካዮች ምክርቤት ሳይቀር ተንጸባርቋልና !!

የእኛ ሥርዓት ፣ ጎሣዊ ፣ቋንቋዊ ፣ ብሔር ብሔረሰባዊ ወዘተ ። በመሆኑ  ምክንያት ፣ እውነተኛ ዴሞክራሲን ለማስፈን እነደማይቻልም የቅርብ ጊዜው የፓርላማው ክስተት ይመሰክርልናል ፡፡

አውሮፖም ሆነ አሜሪካ ፣ ኢሲያም ሆነ አውስትራሊያ  ፤ የዴሞክራሲ ምንነት ገብቷቸው ባቋቋሙት  ዴሞክራሲ በሰፈነበት ሥርዓተ መንግሥት  ውሥጥ ፤ የብዙሃን ሃሳብ የሚተገበርበት  ፣ የአናሳው ሃሳብ የሚደመጥበት ግልፅ አሰራር በአንድ አገር መንግሥት ማዋቅር ውሥጥ አለ ። አናሳዎቹ  የትም ይኑሩ የት ከቀበሌ ጀምሮ እሥከ ክልል ሊወከሉ ፣ ከቀበሌ ምክር ቤት ጀምሮ እሥከ ክልል ምክር ቤት ውክልና ሊያገኙ  ይችላሉ። ዴሞክራሲ ባልሰፈነበት ወይም የተብራራ   ትርጉሙ እንኳን በአብዛኸኛው   ህዝቡ ዘንድ ባልታወቀበት በእንደእኛ ዐይነቱ ቋንቋ አምላኪ እና በቋንቋ ብቻ ለመበዝበዝ ግለሰቦች እንዲያመቻቸው የእግዜሩ መሬት ለእግዜሩ ሰው ሳይሆን መሬት በፖለቲካ ውሳኔ ተሸንሽኖ ፣ ለቋንቋ በተሰጠበት አገር የዴሞክራሲን ፅንሥ አሳብ በቀላሉ ማሥፈን ይከብዳል  ። መደመርንም ወደ ርዕዮት ለመቀየር አይቻልም ።

የመደመር ትወራ   ከአሳታፊነት ፣ ከህብረት ፣ ከአንድነት ፣ ሀብትን አቀናጅቶ ከመስራት  አንፃር ለዕድገት ና ለብልፅግና ጠቃሚ ሃሰብ መሆኑ የታወቀ ቢሆንም ፣ መደመር  ፣ “መደመራዊ ርዕዮት ” እንዲሆን ከመደመር በተፃራሪነት የቆሙት ፣ የብልፅግና አደናቃፊዎች በወጉ ተተንትነው የርዕዮተ ዓለሙ ፀር መሆናቸው መቀመጥ ና መደመር ፣ አሰሱንም ገሰሱንም ይዞ ብልፅግና ለማምጣት እንደማይቻል  በጉልህ በመፀሐፉ መቀመጥ ነበረበት ። ነብርና ፍየል ፤ ደመት ና አይጥ ፤ ጅብና አህያ በግና ቀበሮ ፤ ወዘተ ። በአንድ ላይ በሠላም ደምሬ አኗራለውሁ ማለትም አይቻልም ና ፍልሥፍናው የሚያካብታቸውን ወረቶች በግልፅ በመተንተን በቅንነት ፣ በመልካመነት ፣ በሁሉን አሳታፊነት ፣ ከሁሉም በላይ በእውነት ላይ የተመሰረተ መደመርን በተግባር ለመተርጎም የሚያሥችሉ አጠቃላይ ተንተናዎች ሊካተቱበት ይገባ ነበር ።

መደመር የፖለቲካ መሥመር ሊሆን የሚችለው አሰሱን ገሰሱን ሁሉ በመደባለቅ ፤ወይም ቀጣፊውን ከሃቀኛው እኩል መብት እንዲኖረው በማድረግ ከሆነ ፣ እንዴት ቅቡልነት ያገኛል  ? መደመር መቀነሥን ፣ ማባዛትን ፣ ማካፈልን ባላካተተበት አሠራር አሰስ  ና  ገሰሱን ሁሉ ሰብሥበን በመደመር መንገድ እንዴት ለመዝለቅ እንደምንችል በበኩሌ አይገባኝም ።

ጠ/ሚ አብይ አህመድ በመደመር መንገድ መፅሐፋቸው የገለፁትም የመንገዱን ፈታኝነት ነው እንጂ መንገዱ እንደርዕዮት የሚያገለግልበትን ንድፈ ሃሳብ አይደለም ። በበኩሌ መደመር ” ርዕዮተ ዓለማዊነቱ ” ሳይሆን ፍልሥፍናዊነቱ የጎላብኛል ።

ኢትዮጵያ በዓለም ተጨባጭ ሁኔታ ከኃያላኑ አገራት ጋር ሁሉ በጋራ ጥቅም ፣ በሰጥቶ መቀበል መርህ ተግባብታና ተሥማምታ ፣ ጥቅሞን እና ሉአላዊነቷን አሥከብራ አገርን በሚያበለፅግ አካሄድ ተግባብታ ፣ ተባብራ በመሥራት መኖር አለባት ።  ከቻይና ፣ ከሩሲያ ፣ ከጀርመን ፣ ፣ከአሜሪካ ፣ከእንግሊዝ  ፣ከፈረንሳይ ወዘተ ፤ ጋር … ፡፡ ደግሞም ፣  መደመር በውሥጡ ሁሉንም የሂሳብ ሥሌቶች አካቶ ለአገር ጠቃሚ የሆነውን በማባዛት ና በትበብር  ና በወዳጅነት ኢትዮጵያን ለማሥቀደም መጣር ነው ያለበት  እንጂ መደመርን ብቻ ይዞ ሙጭጭ ማለት አለበት ብዬ አላምንም ።

እኛ ኢትዮጵያኖች  የፈለግነውን ያህል ብንመራመር  የምንከተለው  ርዕዮት እና መንገዱ በዓለም ቅቡልነት ያለው መሆን እንደሚገባው የምንገነዘብ ነንና ከዓለም ህዝብ ያፈነገጠ  ርእዮት  ሊኖረን ከቶም አይችልም ።

የዓለም አካል የሆኑት ፣ ቻይና ና ሩሲያ የሶሻሊዝምን እና የካፒታሊዝምን ርዕዮት ቀይጠው ነው ፣ ከካፒታሊዝም አገሮች ጋር ተፎካካሪ ሆነው መዝለቅ የቻሉት ። የእኛ ጠ/ሚ የነበረው አቶ  መለሥ ዜናዊ ግን ፣ ኢትዮጵያን አፍርሼ ፣ እንደ ካርታ በውዤ  ፣ በጎሣ ና በቋንቋ ሸንሺኜ ፣ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ዘላለሜን አውራ ፖርቲ ሆኜ  እገዛለሁ ብሎ  ፣ በቅዠት የተሞላ ህልም በማለሙ ነው ፣ ለሥልጣን ያበቃውን ወያኔንን በአፍጢሙ እንዲደፋ ያደረገው ።

በዚህ በ21 ኛው ክ/ዘ አውሮፖ ሳልሄድ ፣አሜሪካ ሳልሄድ ፣ ቻይና ሳልሄድ ፣ ወዘተ ሳልሄድ እቤቴ ቁጭ ብዬ በኢንተርኔት ሁሉንም አገሮች መጎብኘት ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ ፣እና ኢኮኖሚያዊ እድገታቸውን በቅጡ ለመገንዘብ እችላለሁ ።  የዓለምን እውነት እያየው ፣ ለብልፅግና የበቁበትን መንገድ እየተረዳሁም በቅይጥ ፖለቲካዊ ርዕዮት አገር እንድትመራ በማድረግ ና ፣ በመላው አገሬ  ሰላምን ለማሥፈን ፣ በዘር ፣ በቋንቋና በጎሣ ላይ ያልተመሠረተ  ጠንካራ የመከላከያ ና የፖሊሥ ኃይል  አዋቅሬ ፣ አገሬን ከመከፋፈልና ከመገነጣጠል አድናታለሁ እንጂ ፣ መለሥ ዜናዊ የነበረውን ገነጣጣይ ሥርዓት እንዴት ይደመር እላለሁ  ?

የእኛ ሥርዓት ፣ ጎሣዊ ፣ቋንቋዊ ፣ ብሔር ብሔረሰባዊ ወዘተ ። በመሆኑ  ምክንያት ፣ እውነተኛ ዴሞክራሲን ለማስፈን አይቻልም ።

አውሮፖም ሆነ አሜሪካ ፣ ኢሲያም ሆነ አውስትራሊያ  ፤ የዴሞክራሲ ምንነት ገብቷቸው ባቋቋሙት  ዴሞክራሲ በሰፈነበት ሥርዓተ መንግሥት  ውሥጥ ፤ የብዙሃን ሃሳብ የሚተገበርበት  ፣ የአናሳው ሃሳብ የሚደመጥበት ግልፅ አሰራር በአንድ መንግሥት አሥተዳደር ውሥጥ አለ ። አናሳዎቹ  የትም ይኑሩ የት ከቀበሌ ጀምሮ እሥከ ክልል ሊወከሉ ፣ ከቀበሌ ምክር ቤት ጀምሮ እሥከ ክልል ምክር ቤት ውክልና ሊያገኙ  ይችላሉ። ዴሞክራሲ ባልሰፈነበት ወይም የተብራራ   ትርጉሙ እንኳን በአብዛኸኛው   ህዝቡ ዘንድ ባልታወቀበት በእንደእኛ ዐይነቱ ቋንቋ አምላኪ እና በቋንቋ ብቻ ለመበዝበዝ ግለሰቦች እንዲያመቻቸው የእግዜሩ መሬት ተሸንሽኖ በተሰጠበት አገር የዴሞክራሲን ፅንሥ አሳብ በቀላሉ ማሥፈን ይከብዳል  ። መደመርንም ወደ ርዕዮት ለመቀየር አይቻልም ።

የመደመር ትወራ   ከአሳታፊነት ፣ ከህብረት ፣ ከአንድነት ፣ ሀብትን አቀናጅቶ ከመስራት  አንፃር ለዕድገት ና ለብልፅግና ጠቃሚ ሃሰብ መሆኑ የታወቀ ቢሆንም ፣ መደመር  ፣ “መደመራዊ ርዕዮት ” እንዲሆን ከመደመር በተፃራሪነት የቆሙት ፣ የብልፅግና አደናቃፊዎች በወጉ ተተንትነው የርዕዮተ ዓለሙ ፀር መሆናቸው መቀመጥ ና መደመር ፣ አሰሱንም ገሰሱንም ይዞ ብልፅግና ለማምጣት እንደማይቻል  በጉልህ በመፀሐፉ መቀመጥ ነበረበት ። ነብርና ፍየል ፤ ደመት ና አይጥ ፤ ጅብና አህያ በግና ቀበሮ ፤ ወዘተ ። በአንድ ላይ በሠላም ደምሬ አኗራለውሁ ማለትም አይቻልም ና ፍልሥፍናው የሚያካብታቸውን ወረቶች በግልፅ በመተንተን በቅንነት ፣ በመልካመነት ፣ በሁሉን አሳታፊነት ፣ ከሁሉም በላይ በእውነት ላይ የተመሰረተ መደመርን በተግባር ለመተርጎም የሚያሥችሉ አጠቃላይ ተንተናዎች ሊካተቱበት ይገባ ነበር ።

መደመር የፖለቲካ መሥመር ሊሆን የሚችለው አሰሱን ገሰሱን ሁሉ በመደባለቅ ፤ወይም ቀጣፊውን ከሃቀኛው እኩል መብት እንዲኖረው በማድረግ ከሆነ ፣ እንዴት ቅቡልነት ያገኛል  ?

 

የመደመር ፍልስፍና ሌሎቹንም ስሌቶች አጣምሮ የሚጎዝ መሆኑን በተግባር ማረጋገጥ የሚችል ከሆነ ወደ ርዕዮት ዓለም ማደግ  ይችላል ፡፡  የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ  ፣ ህግ አሰሥከባሪውም የህግ የበላይነትን አክብሮ የሚያሥከብር  ፤ የሰዎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት የሚያከብር  ተደርጎ በመደመር ሃሰብ መዋቀርም ቀላል ይሆናል ። በመላ ኢትዮጵያ ወንጀለኞችን የሚያርበደብድ እና የሚያንቀጠቅጥ ግርማ ያለው ከሁሉም ጎሣዎች የተወጣጣ ፣ ” የተደመረ ”  የሠላም  አሥከባሪ  ሠራዊት ፣ መኖሩ ደግሞ ለአገር ክብርና ለህዝቡም ኩራት ነው ፡፡

በበኩሌ  መደመር የሚገባኝ እዚህ ላይ ነው ።  ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር የሚሉት ተረትም እውን የሚሆነው የኢትዮጵያ ጎሣዎች ሣይከፋፋሉ በኢትዮጵያዊነታቸው ኮርተው በጋራ ሲቆሙ ብቻ እንደሆነ በፅኑ አምናለሁ።   የለውጥ ኃይሉ የመደመር መንገድም በዓለም ህዝብ ቅቡልነት ካለው  ከፍትህ ፣ ከዴሞክራሲ ከነፃነት ና ከእኩልነት አንፃር ቢቃኝ የተሻለ ይመሥለኛል ።

የሰውን የተፈጥሯዊ መብትም መዘንጋት  ከባድ ዋጋ  እንደሚያሥከፍል ከእኛ በላይ የሚያቅ ሀገር ያለ አይመስለኝም ፡፡ የሀገሬ መንግሥት ይህንን በቅጡ ያውቃል ።ደግሞም  ማንኛውም ሰው ሲወለድ አንድ ቀን እንደሚሞት እንጂ አድጎ ና ጎልምሶ ንጉሥ ወይም ለማኝ እንደሚሆን በእርግጠኝነት ለማወቅ አይቻልም ፡፡ዛሬ የደላንም ፣ ያለንበትን የአሁን ድሎት ና ምችት ብቻ ሳይሆን ፣ ነገ በሞት ይህቺን ዓለም እንደምንሰናበት አንዘጋ ። ለገዛ ታሪካችን እና ለመጨው አገር ተረካቢ ተውልድ የምንጨነቀው ፤ ሰው ሁሉ በተፈጥሮ እኩል መሆኑን እና ተፈጥሮ ለማንም እንደማታዳላ ሥንገነዘብ ብቻ ነው ፡፡

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop