እንዳስቀመጧቸዉ  ስላሉ ነዉ ! – ማላጅ

በሰሞኑ ከ፯፻ ሽ በላይ  ህዝብ ገጎንደር በነበረዉ ጦርነት ተፈናቅሎ ወደ ትግራይ ሽሬ እና የመሳሰሉት የትግራይ አካባቢዎች መግባቱን የጊዚያዊ አስተዳደሩ መግለጡን ከሰሞኑ ጆሯችን ሰማ ፡፡

ጉዳዩ የሚገርም ወይም አዲስ ሆኖ ሳይሆን ቁጥሩ እና አካሄዱ ወይም ፍለሰቱ እና አቅጣጫዉ ነዉ ያልገባን ፡፡

አበዉ ከሳሽ ተከሳሽ የያዘዉን መልስ ቢያዉቅ ከቤት አይወጣም እንዲሉ ከባህርዳር ከክልል መስተዳደር የተሰጠዉ ምላሽ አንጀት እርስ እና ልብ አድርስ መሆኑን በግጥምጥሞሽ ስንሰማ ከሰሽ እናወቃሽ ምን እንደሚል እራሱ ይወቀዉ ፡፡

በአጭሩ የተሰጠዉ ምላሽ ይህን ያህል ቁጥር ያለዉ ህዝብ ጎንደር አልነበረም ኖሮም አያዉቅም በጭራሽ ዕዉነት የሚመስል ዕዉነትነት የሌለዉ ዕዉነት መሳይ ሀሰት ብለዉታል፡፡

ከዚህም ሌላ ክምዕራብ ትግራይ ማለት በተለይም መገናኛ ብዙሀን የማይጠበቅ እና የመረጃ ስርጭት ዝንፈት ያለበት እና ከሙያ ስነምግባር እና ኃላፊነት የሚጋጭ ነዉ እና ሊስተካከል እና በአማራ ክልል ስር ያለ ነዉ ብለዋል ፡፡

ይህ በግል አስተያየት ብቻ ሳይሆን በታሪክም ፣በተፈጥሮም ሆነ በየጥኛዉም ሠዉ ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ልኬት ዕዉነት እና ዕዉነት መሆኑን ግን የሚያጠያይቅ አይደለም ፡፡

ማንም ስለ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ፣የህዝቦች ማንነት ፤ደህንነት እና ዳር ድንበር እንዲነግረን ፤እንዲዘክረን የምንጠብቅ ካለን ትናንት የባህር በር ዛሬ ደግሞ መኖሪያ መቀበሪያ የምትሆነን ቀሪዋን አገር ኢትዮጵያ እና እኛነታችንን ላለማጣታችን ምንም ዋስትና አይኖረንም ፡፡

እዚህ ጋ ምላሹ በጎ እና የማያወላዳ ሆኖ ነገር ግን የመገናኛ ብዙሃን የጎንደርን የግዛት እና የመሬት አስተዳደር አካል የነበሩትን እና ያሉትን ( ሁመራ፣ወልቃይት እና ጠለምት) ምዕራብ ትግራይ ማለት አልነበረባቸዉም ፤የለባቸዉም ማለታቸዉ ነዉ ፡፡

ማን ሆነ እና ነዉ የኢትዮጵያን አንድነት እና ሉዓላዊነት ለመበረዝ እና ለመደለዝ ላለፉት ግማሽ ምዕተ ዓመት ለተደረገ የጥፋት ስብከት ሚና ሲጫወት የነበረዉ ፡፡

አሁንስ ቢሆን እነ (BBC,CNN,…………) የጥፋት መርዝ የሚረጩት በነዚሁ የዉስጥ የወሬ አርበኞች  በሚነገራቸዉ እና በሚደርሳቸዉ  እንጅ እንኳንስ እነርሱ የአገር ዉስጥ መገናኛ በታሪክ ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመት ባላሳለሰ የዜጎች ሞት፣ ዕንግልት፣ ስደት እና ዉርደት በአካል ተገኝተዉ ዕዉነት ሊናገሩ  ቀርቶ በጭብጨባ የነበረዉን ስርዓት ከመከደም እና የራሳቸዉን ድሎት ከማመቻቸት ያለፈ ምን እንዲያደርጉ ይጠበቃል፡፡

ከ ፫ ሽህ ዓመታት በላይ የአገረ መንግስት ታሪክ ያላትን አገር የ፻ ዓመት አንድ በአንድ የነበረች አገር እያለ የተባለዉን ሲያስተጋባ ከነበር እና የሽ ዘመናት የብሄራዊ ክብር  ሲያነዉር ለነበር የሀያ ዓመት ክህደትን ቢያስተጋባ  ዉሻ በበላበት  ነዉ እና  ጎንደር ኢትዮጵያ ጎንደርም ጎንደር ነዉ ብሎ አገሪቷም ህዝቧም ዳግም የነበር ስሙን እና ታሪኩን ማረጋገጥ እና ከማስቀጠል ዉጭ በጥቀም ባርነት ተቀፍድዶ ከሚገኝ መገናኛ ብዙሃን ምስክርነት መጠበቅ ድካም ነዉ ፡፡

እዚህ ላይ የራሳችንን እና የዓለምን ታሪክ ወደ ኋላ ዞር ብሎ ማየት ይቻላል ፡፡ ይኸዉም የኢትዮጵያ የቀድሞ የግዛት ወሰን ሆነ አሁን የምንገኝበትን የሰሩልን እና ያወረሱን ጀግኖች ኢትዮጵያን እንጅ የቀደሙትም ሆነ አሁን ያሉት የኢትዮጵያ እና ህዝቧ ጠላቶች በችሮታም ሆነ በጎ ፈቃድ የለገሱን አገር እናዳልሆነች አሁንም ሊያዉቁት ይገባል ፡፡

እነ ታላቋ ራሽያ እና አስራኤል አገራቸዉን እና ዳር ድንበራቸዉን እንዲሁም የወሰን ክልላቸዉን ያስከበሩት  በጠላቶቻቸዉ ምክር እና ይሁንታ አልነበረም ፤ሆኖም አያዉቅም ፡፡

አስራኤል እ.ኤ.አ. በ አስራ ዘጠኝ አርባ አካባቢ  ይመስለኛል እንደ አገር ለመመስረት ዕዉቅና ለማግኘት በጊዜዉ የነበረዉን የዓለም ህብረት / ሊግ ኦፍ ኔሽን / ስጠይቅ የመጀመሪዋ አስራኤልን አገረ መንግስትነት ዉድቅ ያደረገች የትናንቷ ጠላት የዛሬዋ ወዳጅ አሜሪካ እንደነበረች ከታሪክ ድርሳናት ይማሯል፡፡

የምስራቅ አፍሪካዋ ሶማሊ ላንድ  ዕዉቅና  የሰጣት የሩቅ አይደለም አፍሪካ ህብረት አላደረገዉም ፡፡ ምክነያት የጠባቂነት አባዜ ጠፍሮ እንደያዘን ነዋ………ቅኝ ግዛት ተፅዕኖ……ግን ሶማሊ ላንድ እንደ ህዝብ ህዝቧ ፤ እንደ አገር አገሪቷ ትኖራለች  ዓለም ባየበት እና  ከጀግኖች ጎን መቆሙ አይቀርም ጊዜ ነዉ  ማሳየዉ …..መስታዉት፡፡

እናም ሌላም ላክል እንዲያዉ ሠባት መቶ ሽ የሚባል ተፈናቃይ ዕዉነት ሠላማዊ /ሲቪል  ቢሆን ኖሮ ፣ኖሮ ወደ መሃል አገር ይመጣል እንጅ እንዴት ወደ ዳር አገር ሱዳን…..ሽሬ ይገፋል፡፡ እኮ የክልሉ ሠራዊት ወይም የትግራይ ሠራዊት የምትሉት ዕኮ ኢትዮጵያዊ ነበር እና እንዴት አሁን እርሱ ላለመሆኑ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር በምን ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡

ዕዉነት ተፈናቃይ ሠላማዊ ህዝብ እንኳን  ከመሃል አገር ከዕህት ህዝብ እና አገር ኤርትራ ፣ ከሶሪያ……መሀል አገር ሸዋ/ጨዋ-አዲስ አበባ እያየን እኮ ነዉ ፡፡

ከደቡብ አስከ ሰሜን ፣ ከምስራቀረ አስከ ምዕራብ የሚኖር ህዝብ እኮ አለ እና ምን ይሆን ሚስጥሩ ያን ያህል ከየት እና ወዴት !

ባህርዳር ፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ወልደያ፣ ደ/ማ…………ለምን አላላችሁም የሉም አትበሉን ያመናል ስላሉ ስላለን…… ሆድ ይፍጀዉ፡፡

እናም እባካችሁ ከሳሽ ሆይ  ካልረገጡት በቀር ወንዝ አይደፈርስም  የመሃል ኢትዮጵያን( ሰሜን ምዕራብ ይጨምራል) እናዉቀዋለን እና ብሶት ማባባስ በመተዉ ለዕዉነት እና ለዕዉነተኛ ማንነት ይሰራ ፡፡ በሀሰት እና በክፋት ማንነት  አስከ መቸ እኛ ብቻ እንጃ …..እንጃ፡፡

መገናኛ ብዙሃንም በአባላጫዉ ማለት ይቻላል በሉ ሲባሉ“ እንደተባለዉ ፣እንዳሉን……እንጅ እንዳየነዉ ብለዉ አያዉቀም ሊሉም አይችሉም ዱባ እና ቅል አበቃቀሉ እየቅል እንዲሉ ሠሪወቻቸዉ “እንደሰሯቸዉ እና   እንዳስቀመጧቸዉ ” በመሀኑ በስሪታቸዉ ማዕቀፍ ዉስጥ እንደነበሩ የሚገኙ “ የፋሲካ ባሪያ  ” መሆናቸዉ ን  እኛ ብነረሳ እነርሱ በስራቸዉ ያስታዉሱናል ብዙ ማስታወስ ከፈለግን አንቸገርም በየዕለቱ በመቅፅበት አንቱ ብለዉ አንተ የሚሉትን  ስንሰማ ፡፡ ብዙዎች እንደ አደራ ዕቃ በተቀመጡበት የሚገኙ ታማኝ አገልጋይ የመሆናቸዉን ቃል ኪዳን በቀላሉ አፍርሰዉ በጎንደር …..በኢትዮጵያ  ለማለት  እንደሚቸገሩም ከችግራቸዉ ብዝሃነት ልንረዳቸዉ ይገባል ፡፡ አሁንም ሮይተር እንዳስነበበዉ….. እንጅ በአገራችን ስላለዉ እና ስለሆነዉ ማለት ዕዉነተኛ የሙያ ስነምግባር እና ሠባዊ  ቁመና  ከህዝባዊ ወገንተኝነት ጋር  ማጣመርን ስለሚጠይቅ እንደቀደመዉ  እንደ ሰማነዉ ፣እንደተባለዉ ከማለት ዉጭ በቦታዉ እንደተመለከትነዉ  ለማለት  መመሪያ ስለሚጠብቁ  ….ጠባቂነት እንደ  ነጻነት ስለሚተረጎም ገና ነጻ አስተሳሰብ  ቀርቶ ገለልተኛ ንግግር አልተለመደም ፤ለመልመድም መመሪያ……እንዲያዉ ስንቱን ..ስንቱን  ፡፡

“  እናት፤ አገር ምን ጊዜም ትኑር

 

ማላጅ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን የጦር ሜዳ ውሎ ፤ የፖለቲከኞች ጡዘትና የድል ማግስት ተግዳሮቶችና ፈተናዎች 

western countires
Next Story

ለአሜሪካ ደፋር ጫና የአንድ ተራ ዜጋ ምላሽ – መነሻ (አንድነት ይበልጣል – ሐዋሳ)

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም
Go toTop