March 23, 2013
14 mins read

“እኔ ግን አልሞትኩም” – አላሙዲ

‹‹ጠ/ሚ/ር መለስን በማጣቱ ሰው ተደናግጦ ነበር፤ … እኔንም ገለውኝ ነበር፤ ግን አልሞትኩም እስከአሁን ከእናንተው ጋር ነኝ›› ሲሉ መናገራቸውን ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አል-አሙዲ መናገራቸውን ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ኢትዮቻናል ጋዜጣ ዘገበ። ዘገባው ለግንዛቤ ይጠቅማል በሚል ሳንጨምር ሳንቀንስ አቅርበነዋል – ያንብቡት።
በአሁኑ ወቅት በሥሩ 20 ግዙፍ ኩባኒያዎችን የሚያስተዳድረው የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ባለፈው እሁድ 10ኛውን የደምበኞች፣ የሠራተኞችና የቤተሰቦች ቀን በዓል አከበረ፡፡ የቴክኖሎጂ ግሩፑ ቺፍ ኤግዚክዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበዓሉ ላይ እንደገለፁት ‹‹የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ውስጥ መሪዎችም ሆንን ተመሪዎች ሁላችንም እኔንም ጨምሮ ሠራተኞች ነን፤ አሠሪ ቢኖር አንድ ሰው ብቻ ነው›› ነበር ያሉት፡ ፡ ዶ/ር አረጋ ‹‹ አንድ አሠሪ ብቻ ነው ያለን›› ያሏቸው ክቡር ዶ/ር ሼክ አል- አሙዲ በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግርም ‹‹ለአንድ ሀገር መመስረቻው ቤተሰብ ነው፡ ፡ ከዚያ ቀጥሎ ቤተሰብ ወልዶ ተዋልዶ ሠራተኛ ይፈጥራል፤ ሠራተኛውም ለሚያመርተውም ደምበኛ ያመጣል፡፡ … ከምወዳቸው ነገሮችና መገኘት የምፈልገው ይህንን ቀን ነው›› ብለዋል፡፡

‹‹የሜድሮክ ዕድገት አይገታም››

ክቡር ዶ/ር ሼክ አል-አሙዲ ሀገሪቱ እያደገች መሆኑን ነው በዕለቱ የገለፁት፡፡ በተለይ፤ ከኩባኒያዎቻቸው ጋር ተያይዞ ‹‹ይሄ ቤተሰብ ጥሩና ጠንካራ ሠራተኛ ፈጥሮልናል፤ ይህም ሠራተኛ ጥሩ ደንበኞችን ማትረፍ ይዟል፡ ፡ በዚህ ከቀጠላችሁ የሀገሪቱ ዕድገት የት እንደሚደርስና ምን እንደሚመስል ባለፈው 10 ዓመታት አይታችሁታል›› ሲሉ ነው የገለፁት፡፡ ይሁንና፤ ባለፈው ዓመት ከጠ/ሚ/ር መለስ ህልፈትን ተከትሎ ለጥቂት ሰዓታት ሰው ተደናግጦ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ ‹‹አስቀድሞ መሠረት ያለው አመራር ስለነበር፤ ነገሮች ሳይናጉ በተቀመጡለት መስፈርት ሁላችንም እየሄድን ነው፤ … ፈጣሪ ካመጣ ሞት አይቀርም፣ ሁላችንም ሟች ነን፡፡ እኔንም ገለውኝ ነበር፤ ግን አልሞትኩም፡ ፡ እስከአሁንም ከእናንተው ጋር ነኝ›› ብለዋል፡፡ እናም ‹‹በሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሥር ያሉ ድርጅቶች እያደጉ ነው እንጂ እየመነመኑ እንደማይሄዱ አረጋግጥላችኋለሁ›› ብለዋል፡፡

ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበኩላቸው የቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባኒያዎች እያደጉና ቁጥራቸው እየጨመረ ካፒታላቸውም ከፍ እያለ መምጣቱን ነው የገለፁት፡፡ ‹‹እስከ አሁን ድረስ ቀንቶናል፤ ወደፊት ግን ከበድ ያለ ሥራ ያጋጥመናል፡፡ ሀገራችን እያደገች ነውና ብዙ ተወዳዳሪዎች ይኖራሉ›› ሲሉም፤ ለመጪው ግዜ ኩባኒያዎች ለሚገጥማቸው ውድድር ከወዲሁ እንዲዘጋጁ አሳስበዋል፡፡

መተካካት በሜድሮክ

አሁንም ቢሆን ሜድሮክ እያደገ እየሰፋ ቢመጣም፣ ዕድገቱን ለማስጠበቅ ክቡር ዶ/ር ሼክ አል-አሙዲ ‹‹በተለይ እንደእኔ ያለው ዕድሜ ገፋ ያለ ሳይሆን ወጣቱን ትውልድ ይዘን የኢትዮጵያን ዕድገት ለዓለም እናሳያለን›› ሲሉ ‹‹አዳዲስ ወጣቶችን እያሰለጠንን መተካት ጥሩ ደረጃ ላይ ነው ያለነው›› ያሉት ደግሞ ዶ/ር አረጋ ባደረጉት ንግግር ላይ ነው፡፡

በጠቅላላ ኩባኒያዎቹ ሰው ተኰር የማኔጅመንት አካሄድና ፍልስፍና ተግባራዊ በማድረግ እየተጠናከረ መምጣቱን አፅንኦት የሰጡት ዶ/ር አረጋ ሥራውንና አለቆቹን የሚያከብር፣ ሀገሩን የሚወድና ሥነ-ሥርዓት ያለው እንዲሁም በሀገሪቱ መጥፎ ፀባዮች እንዲጠፉ ለማድረግ አቋም እንዳለው ነው የገለፁት፡፡ ለዚህ ደግም ‹‹ከመጠን በላይ ጥንቁቅ ከመሆናችን የተነሳ በአሁኑ ግዜ ሰው እንኳን ስንቀጥር አረንጓዴ ጥርስ ያላቸውና የሌላቸው መሆናቸውን እየተመለከትን ነው›› ብለዋል፡፡

‹‹እንደዚህ ዓይነት ባህል እኛ ጋ አይኖርም፡፡ ወደፊትም አይኖርም፡ ፡ ጥርት ያልን መሆን አለብን፡፡ ለፍተን ያገኘነውን ገንዘብ ጫት የምንበላበት ከሆነ ሌላ ነገር ነው›› ያሉት ዶ/ር አረጋ ‹‹ሀገሪቷ ጫት መሸጥ ከፈለች ግን እሱ ሌላ ነገር ነው›› ይላሉ፡፡ ‹‹የእኔ ኃላፊነት ሠራተኞቼ ጤነኛ ሆነው የሚያገኙትን ገንዘብ ለጤና እንዳያውሉትና ለልጆቻቸው እንዲያስተዳድሩበት ማድረግ ነው›› የሚሉት ዶ/ር አረጋ ‹‹ቅጠል መብላት ለፍየሎች ብቻ የተፈቀደ ነው›› ብለዋል፡፡

ምን ተከናወነ?

በበዓሉ ላይ ኩባኒያዎቹ ባለፉት ዓመታት በሥራዎቻቸው አብረዋቸው ለተጓዙት ደምበኞቻቸውና የአገልግሎታቸው ተጠቃሚ ለሆኑት ሁሉ እንደከዚህ ቀደሙ በላቀ ደረጃ አገልግሎት ለማበርከት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው ተገልጿል፡፡

በ2004 ዓ.ም ለኩባንያዎቹ ለስራ ማስኬጃ፣ ለማምረቻ፣ ለቋሚ ንብረት ግዢና ለፕሮጀክት ማስፈፀሚያ 2.2 / ሁለት ነጥብ ሁለት/ ቢሊዮን ብር በጀት የተያዘ ሲሆን፣ ኩባንያዎቹ በበጀት ዓመቱ ካስገኙት 1.6 /አንድ ነጥብ ስድስት/ ቢሊዮን ከታክስ በፊት ትርፍ ለመንግስት ካዝና ከ690 ሚሊዮን ብር በላይ በታክስና በሮያሊቲ ክፍያ ፈጽመዋል፡፡ በዚሁ ዓመት ለፕሮጀክትና ለማስፋፋት ስራ ከተያዘው በጀት ውስጥ ብር 262,488,746 /ሁለት መቶ ስድሳ ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ ሰማኒያ ስምንት ሺ ሰባት መቶ አርባ ስድስት/ በተግባር ላይ ውሏል፡፡

በቅርቡ የቴክኖሎጂ ግሩፑን የተቀላቀለው ሰሚት ፓርትነርስ ኃላ/ የተ/የግ/ማህር በ20ኛው የቴክኖሎጂ ግሩፑ አባል ሆኗል፡፡ በአሁኑ ወቅት በቴክኖሎጂ ግሩፑ ውስጥ 5,186 ቋሚና 1,797 የኮንትራት ሠራተኞች ሲኖሩ በድምሩ ለ6,983 ሠራተኞች የስራ ዕድል የተመቻቸላቸው ሲሆን፣ በ2004 በጀት ዓመት በተለያየ መልኩ የ183 / መቶ ሰማኒያ ሶስት ሚሊዮን ብር/ ክፍያ ተፈፅሟል፡፡

በበጀት ዓመቱ ለኩባንያ ሠራተኞች ለትምህርት በተሰጠው ዕድል በማስተርስ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በዲፕሎማ፣ በቴክኒክና ሙያ፣ በአንደኛና በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ 105 ሠራተኞች ሲሆኑ፣ የ2004 ዓ.ም የትምህርት ወጪው ብር 661,000 ነበር፡፡

ከቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያዎች መካከል የግብርና ውጤቶችን ለውጭና ለሀገር ውስጥ ገበያ እያቀረበ የሚገኘው ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር በሻሎ እርሻ ልማት የጠብታ መስኖ ፕሮጀክት በማስፋፋት ላይ ይገኛል፡ ፡

በነትሌ በመስኖ የተጀመረው የገበታ የወይን እርሻ ልማት ውጤታማ ሆኖ ምርቱ ለውጭ ገበያ እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን፣ በቅርቡ በክቡር ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ የተጎበኘው የአልፋ አልፋ የከብቶች መኖር የሙከራ ፕሮጀክትም ውጤት በማስገኘቱ ምርቱን በስፋት ለማምረት በጀት ተመድቦለት ስራ ጀምሯል፡፡

በነትሌ በመስኖ የተጀመረው የገበታ የወይን እርሻ ልማት ውጤታማ ሆኖ ምርቱ ለውጭ ገበያ እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን፣ በቅርቡ በክቡር ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ የተጎበኘው የአልፋ አልፋ የከብቶች መኖ የሙከራ ፕሮጀክትም ውጤት በማስገኘቱ ምርቱን በስፋት ለማምረት በጀት ተመድቦለት ስራ ጀምሯል፡፡

በተያዘው የ2005 ዓ.ም የበጀት ዓመት ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በመተከልና በመንታ ውሃ የሚያካሂደውን ማዕድን ፍለጋ በማጠናቀቅ ወርቅ ማምረት የሚያስችለውን ጥናት ጀምሯል፡፡ የወርቅ ማምረቻ የፋብሪካ ተከላ ለማካሄድ አስፈላጊው ጥናት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

አዲስ ጋዝና ፕላስቲክ ፋብሪካ ኃ.የተ.የግ.ማህበር አዲስ የካርቦን ዳይኦክሳይድ ማምረቻ፣ ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃላ/የተ/የት/ ማህበር ደግሞ በሀገሪቱ በግል ድርጅት የመጀመሪያ የሆነውን የግል ቆርኪ ማምረቻ ዘመናዊ መሳሪያ ተከላ እያከናወነ ሲሆን፣ ዩናይትድ የአውቶሞቢል ጥገና አገልግሎት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር ዘመናዊ የተሽከርካሪ ቴክኒክ መመርመሪያ መሳሪያ በመትከል ዓመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ሁዳ ሪል እስቴት በሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ስም የተሰየመውን የወልድያ ስታዲየም በ261 ሚሊዮን ብር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በመቂ /ነትሌ/ እና በሻሎ /ሐዋሳ አጠገብ/ በከፍተኛ ደረጃ የጠረጴዛ ወይንና የአልፋአልፋ ምርት በዘመናዊ መስኖ በማምረት ላይ ይገኛል፡ ፡0

በበዓሉ ከ4500 በላይ ሰራተኞች፣ ቤተሰቦች፣ የየኩባንያዎቹ ደምበኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ ከየኩባንያዎቹ ለተመረጡ ምርጥ የኩባንያ ደምበኞች፣ ምርጥ ሰራተኞች፣ የዓመቱ ምርጥ ስራ አስኪያጅ፣ ምርጥ ኩባንያና ምርጥ የሠራተኛ ማህበር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop