የወያኔ ታጋዮችና የትግራይ ሕዝብ በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ፖሊሲው በቀጥታም በተዘዋዋሪም የማይነጣጠሉ ትስስሮች አድርገዋል

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
1/27/2021

ይህ ርዕስ ለማቅረብ የተገደድኩበት መነሻ፤ ያለፈው የወያኔ እና የትግራይ ሕዝብ ቁርኝት (እስካሁንም የቀጠለው የሞቀው ድጋፍና ፍቅር) እንዳልነበረ ለማድረግ በየሚዲያው የማደምጣቸው አሽቃባጭ ምሁራን እንደ እሬት ስለመረሩኝ አውነታውን ላስቀምጥ። ያው ድሮም የሸዋ ትግሬ ወይንም ጸረ ትግሬ የሚል ስም ስለተለጠፈብኝ፤ ተቃዋሚዎቼ ለኔ አዲስ ስላልሆኑ እውነታው ዛሬም ቢመራችሁ የሆነውን ላስቀምጥላችሁ መረጥኩ።

ሁለት ጉዳዮችን እንመለከታለን ።

 

ወያኔን ወደ ሥልጣን ያመጣው ከሰማይ የመጡ ጦረኞች ሳይሆኑ፤በትግራይ ሕዝብ ትግልና አውቅና ነው። ወያኔና የትግራይ ሕዝብ በመተባበር ያካሄዱት የ17 አመት ዕድሜ ያስቆጠረው ረዢሙ ቢላዋ ያነጣጠረው ልክ የጀርመን የናዚዝም የዘር ፣ የፖለቲካ እና የግዛት ምኞቶችን በአንድ ዘር ላይ የበላይነት ለማሳካት እንዳደረገው ሁሉ በትግራይ ክ/ሃገር የተነሳው የብሔረተኛው ህወሓት ጦር ተመሳሳይ ነበር እንጂ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች፤ ምሁራኖችና ትግሬዎች እንደሚወሻክቱት ስለ ዲሞክራሲ እና ስለ አንድነት ጥበቃ የተደረገ ትግል አልነበረም። ስለ ዲሞክራሲ ማምጣት ትግል ተውትና ስለ አንድነትና ሉዓላዊነትን በከፋ መልኩ እንዴት እንደተከናወነና ማን እንዳከናወነው እናውቀዋለን! አደለም እንዴ? ። ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ያደረገው ማን ነበር? “ትግሬዎች ናቸው’ አደለም እንዴ?

አሁንም የቆየው “ትግሬዎች በዘመነ ወያኔ ልዩ ተጠቃሚዎች” አልነበሩም ሕዝብና ድርጅት ለያይተን እንመልከት የመባለው የተሳሳተው መስመር በዚህ ጦርነትም ብሶበት ምሁራኑና ጋዜጠኞች ሲያሽቀብጡ እየደመጥኩ ነው።

 

በጣም የሰለቸኝ ደግሞ የትግራይ ሪፑብሊክ ለመመስረት የተነሱት የትግራይ ብሄተረኞቹ ከጦርነቱ በኋላ በለስ ቀንቷቸው ከረጅም ጊዜ በኋላ መንግሥትነት ከያዙ በሗላም ይሁን ዛሬ ከሥልጣን ከተወገዱም ቢሆን የትግራይ ሕዝብም ሆነ ተጋዮቹ በጅምላ ጭፍጨፋ እና ከወያኔ የዘር ማጥፋት ፖሊሲ ጋር በተያያዙ ሌሎች ወንጀሎች ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፎ አላደረገም፤ የተደረገው ፍልሚያ ለዲሞክራሲና ለአንድነት ነበር የሚል አፈታሪክ አሁንም መቀጠሉ የሚገርም ነው፡፡

አሁን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት በትግራይ ላይ ርሃብ መከሰቱን አስመልክቶ በተከታታይ በዜና አውዶችና ውይይቶች የሚጋበዙ ምሁራን የሚሰጡት አስተያየት የማደምጠው ይትግራይ ሕዝብ በ17 አመቱ በታላቁ ሴራ አልተካፈለም ፤ ከዚያም አልፎ የትግራይ ሕዝብ በዘመነ ወያኔ ከሌሎች “አፓርታይድ ክልሎች” የተለየ ጥቅም አልተደረገለትም ሲሉ አድምጫለሁ።  ይህ መስመር ከእውነት የራቀ ነው ፡፡ ለማን እንዳደሩ ባላውቅም “አድርባይነትም” ነው።

ምሁራኖቹ የተዘረጉት የልማትና የትምሕርት የጤና “ሱፕራ እና ኢንፍራ” የሚባሉት እስትራክቸሮች/ተቋማት/ ምን ያህል ስፋት እንዳላቸው እያወቁም ቢሆን በቅርቡ ስለተከሰተው ርሃብ ምክንያት አስታክከው ትግራይ ላይ ምንም የልማትና የጤና፤የትምህርት ስላልተደረገ ሕዝቡ ባጭር ወቅት ለርሃብ ተዳርጓል የሚል ክርክር ማስተጋባት ጀምረዋል። በየ ጉሙዝና ኦሮሞ ክልሎች እየታረደና እየተፈናቀለ ያለው የአማራ ማሕበረሰብ ይህንን ቢሰማ ምን ይል ይሆን? ዛሬም እኮ ትግሬዎች ሳይሆኑ አማራዎች ናቸው መፈናቀሉና መታረዱ በገፍ እየተፈጸመባቸው ያለው። የጀነሳይድ ተመራማሪው “ዶ/ር ግሬገሪ እስታንተን” እንደተነበዩት ቢሆን ኖሮ ዛሬ ትግሬው ነበር በየ ክልሉ የዘር ጽዳት ሊደርሰው የነበረው። አንዳንድ ክስተቶች የታዩ ቢሆንም “ያ የተተነበየውና የተፈራው ጥቃት ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋነት እንዳይከሰት አድርጎታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በሁሉም አከባቢዎች ያሉ ፀረ-ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኞች ሃገር የቆመበትን ምሰሶ የሚቦረቡሩ ቅንቅኖች ናቸው!!!

ትግሬዎች ወያኔ ንጉሥ በመሆኑ ትግሬዎች ከዚህ ንጉሥና ቡድን ምንም አልተጠቀሙም የሚል ክርክር ለመማፍረስ ለበርካረታ አመታት በማስረጃ በመጽሐፍ በተለያዩ ሰነዶች አቅርበን ገልጸናል። ሌላ ቀርቶ ለምሳሌ ወያኔዎች ወደ ሥልጣን ሲገቡ ኤርትራኖችና ትግሬዎች ለነገዳቸው ጥቅም ለማስጠበቅ ሲሉ ሲያደርጉት የነበረውን “አገር አቀፍ ዘረፋ”

The pillage of Ethiopia by Eritreans and their Tigrean surrogates Paperback – January 1, 1996 by Assefa Negash (Author) Amazon የሚገኘው በዶ/ር አሰፋ የተጻፈውን መጽሐፍ ማንበብ ማስረጃ ይሰጣችሗል።

አልተጠቀመም ባዮቹ ግን እስከዚህችኛው የጦርነት የርሃብ ወቅት ምንም ተጨባጭ ሰነድ አላቀረቡም። ማስረጃ ብለው ሲናገሩ ያደመጥኩት ነገር ቢኖር፤ ለምሳሌ በቅርቡ ምኒልክ በተባለው “የዩትዩብ ሚዲያ” ቀርበው ያደመጥኳቸው የታሪክ የሕግ እና እንዲሁም ጋዜጠኞች የሚል ማዕረግ ያላቸው ምሁራን “የትግራይ ሕዝብ በወያኔ ዘመን ልዩ ጠቀሜታ ያልተደረገለት መሆኑን ማስረጃው በሁለት ሳምንት ዕድሜ ያስቆጠረው ጦርነት 4 ሚሊዮን ለርሃብ መዳረጉ “ልዩ ጠቀሜታ ሳይደረግለት ሃብት ሳያጋብት መቆየቱ ማስረጃ ነው” ሲሊ ነበር እንደ ማሰረጃ ሲያቀርቡልን የነበሩት።

በተለይ ደግሞ አበርሃ በላይ የተባለው ኢትዮ ሚዲያ ጋዜጠኛ የግብጹ ሙባረክን ለመጣል የተደረገውን ሕዝባዊ አመጽ ለሳምንታት ሲደረግ ታሕሪር እስኩየር (የነጻነት አደባባይ) በተባለው ቦታ ሕዝቡ ለሳምንት ሲመሽግ ‘ምግብና ሻይ’ በየቀኑ ከሕዝቡ ሲቀርብ የምጣኔ ሃብት ያለው ሕዝብ ስለሆነ ትግራይ/ኢትዮጵያ ግን ካንድ ቀን በላይ ማድረግ አይቻለውም ሲል ንጽጽር ሲያሰርግ ሰምቻለሁ። አብርሃ ያላወቀው ግብጸች የመጨረሻ ድሆች ናቸው። ዜጎቿ አባይ ወንዝ ላይ ከበርካታ ልጆቻቸው ጋር ዝናብና ቁር በላያቸው ላይ እየወረደ ስብርባሪ ጀልባ ሃይቁ ውስጥ እየተንሳፈፉ የሚኖሩ የምድር ድሆች ያሏት አገር ነች።፡ ያም ይሁን እና ፤ አብርሃ የዘነጋው ያለፉት የተካሄዱ ኢትዮጵያ አብዮቶች ከማአከላዊ ከተሞች ሳይሆን ድሃ ከሚባሉት ኢትዮጵያ ከተሞችና ገጠሮች ሥርዓቱን ለመቋቋም ለበርካታ ወራት እንዴት ሥርዓቱን አስጨንቆ ብዙ ለውጦች እንዳመጣ ረስቶታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የህልዉና እና ነፃነት ትግል ታሪካዊ ይዘት እና ምንነት !

በዚህ ሁለት ሳምንት አጭር ጦርነት 4 ሚኪዮን የትግራይ ሕዝብ ለርሃብ የተጋለጠው ወያኔ አደህይቶት ስለነበር ተሎ ለርሃብ ተጋልጧል የሚለው የነ አብርሃ ሆነ የነዚያ ምሁራን እምነት የማልስማማበት ምክንያት 1ኛ- ወያኔ ሲኖር 4 ሚሊዮን ሕዝብ ለርሃብ አልተጋለጠም፡ አሁን የተጋለጠበት ምክንያት ብዙ ምክንያቶች አሉት “መዋቅሩ ፈራርሷል” በወያኔና በጦርነቱ ሰበብ ማለት ነው። ስለዚህም እንደ ሶሪያ እና ሊቢያ ሁሉ ጦርነት ባለበት አገር ሁሉ ርሃብ እውን ሆነ።

ኢንፍራስትራክተሮችና ሲፈራርሱ በጣም ሃብታም ከሚባሉት ኢራቅ፤ሶሪያ እና ሊቢያ ጦርነት በተነሳ በሳምንት ውስጥ የውሃ፤የመብራት፤የስልክ ፤ የምግብ እና የባንክ አገልግሎት ተቋርጠዋል።

 

በነዚያ አገሮች እንደተከሰተው ትግራይም ውስጥም ‘ርሃብ፤ ሞት ፣ ወሲባዊ ዓመፅ ፣ የምግብ እጥረት ፣ ፣ ህመም እና መድሃኒት ዕጥረት እንዲሁም የአካል ጉዳተኝነት ተከስቷል። በነዚህ አገሮች ከጦርነቱ በሗላም ድብርት እና ጭንቀት (PTSD) የታዩ የጦርነት ውጤቶች ታይተዋል ፡፡ ስለዚህ ትግራይ ውስጥ ባጭር ወራት የጦርነት ውጤት የሆነው ርሃብ የመከሰቱ ክስተት ድሃ ስለነበር የሚለው ቁንጽል ሙግት ስሕተት ነው።

ያውም አብሮ መዘከር ያለበት “የትግራይ ሕዝብ በዘመነ ወያኔ ልዩ ጠቀሜታ ኖሮት (በመላ አገሪቷ ባለ ሃብት ሆኖ) አልፎም ያልተገራ “የሕሊና ኩራት” ፤ እንዲሁም “የበላይነት ስሜት” (ሱፕረማሲ) አያንጸባርቅም ነበር ማለት “አድራበይነት ወይንም ጅልነት” ከመሆን አያልፍም።

ሕዝብ ስንል በማንኛውም ታሪክ አጋጣሚ “ሙሉ ሕዝብ እያንዳንዱ ሰው” ማለት እንደሆነ የሚሰጠው ትርጉም እውነታውን ለመሸፈን ካልሆነ በስተቀር በታሪክ ሙሉ የሚባል ሕዝብ አይራብም፤ ጦርነት አይሳተፍም፤ ሃብት አያካብትም። ሕዝብ የሚባል በትግራይ ውስጥ ብዙውን ታይቶ በማይታወቅ ብዛት የትግራይ ነገድ/ዘውግ በተለይ “ትግርኛ ተናጋሪው” በሃብትና በሥልጣን ተጋሪነት የበላይነት ይዞ ለ27 አመታት ተጠቃሚ ነበር። ይህ ደግሞ ምሁራኖቹ የሚገልጹት ቀለል አድርገው ክብደቱን ለመሸሸግ ሲሉ የሚገልጹት “ጥቂት የወያኔ ጀሌዎች ተጠቅመዋል” በሚል ሲገልጹት እሰማለሁ።  ይህ በጣም የተሳሰተ ያሰለቸን እና ያንድ ብሔረተኛ የመነሻ ፖሊሲው ትርጉም አለማወቅ ነው።

አንድ ብሔርተኛ የሚነሳው ቆሜለታለሁ ለሚለው ነገዱ ፤መጥቀም እና ለመከላከል እንዲሁም ሥልጣን ይዞ ምጣኔ ሃብቱን ለነገዱ ለማስረከብ መሆኑን ከወያኔ ዘመን አገዛዝ ሌላ ማስረጃ ማቅርብ አይቻልም። በተግባር ያየነውም ይኸው ነው።

ዳኝነቱ፤መከላከያው፤የሚኒሰትሮች፤የመገናኛዎች፤ኢንቨየስተሮች/የንግዶች. ወዘተ…ወዘተ ባንድ ነገድ (በትግርኛ ተናጋሪው ትግሬ) ተይዞ ነበር። ዛሬም በሌሎች ባለ ተራ ዘውጌዎች ተሸጋግሮ አያየን ነው። ሃቁ ይህ ነው። የዛሬዎቹ ባለተራ ኦሮሞዎች ደግሞ ማንን እየጠቀሙት እንዳሉት በግሃድ እየታየ ነው። እነዚህ ይህንን ማድረጉን ካመናችሁ፤ እነኚህ ከማን እንደተማሩ ማወቅ አይቸግራችሁም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የብሄር እኩልነት!

በጣም የገረምኝ ደግሞ እዛው ምንልክ በተባለ ሚዲያ አንድ የሕግ ምሁር የተባለለት እንግዳ “በረሃብ የተጠቃውን የትግራይ ሕዝብ የአማራ ማሕበረሰብ ለመከላከያው በሬ እና በግ ገዝቶ ከማገዝ አልፎ ትግሬውን ከዚያ በዘለለ ማገዝ ይጠበቅበታል ሲል አስገርሞኛል። ሃሳቡ የሚከፋ ባይሆንም፡ እኔ የምለው “አማራው” ከትግሬው በምን ተሽሎት ነው ይህ ሁሉ ሃላፊነት ሊጠየቅ የበቃው። እኔ የምለው የትግራይ ሕዝብ 27 አመት እነሱ ባነገሱት የፋሺሰት ቡድን ሲቀጠቀጥ፤ሲታረድ ሲታረዝ፤ ሲባረር “ምሁራኖች” ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርባችሁላቸው ነበር? ካላቀረባችሁላቸውስ ለምን አልጠየቃችሗቸውም? ወይንስ እራሳችሁም 27 አመት አማራ ሲንገላታ “ዝምታ ውስጥ ነበራችሁ” ።

ለመሆኑ ትግሬው ቪክተማይዝድ ተደርጎ እየቀረበ ያለው ተጠያቂው ማን ነው? ትግሬው በኢትዮጵያዊያን አልተበደለም። ሃቁ ይህ ነው። ያውም ከማንኛውም ክፍለሃገር የከፋ የብቀላ ብትር አልተሰነዘረበትም። ለዚህም ኢትዮጵያዊያን መምስገን አለባቸው። እንደ እውነታው ቢሆን ኖሮ አስቀድሜ ከላይ እንደጠቀስኩት “የጀነሳይድ ተመራማሪው “ስንታንተን” የተናገሩት መርሳት አይገባም። እሳቸው ያሉት “እኔ የምሰጋው ወያኔ ከሥልጣን ሲወገድ የማዝነው ለትግራይ ሕዝብ ነው” ነበር ያሉት። የተፈራው ባይደርስም (በሕዝብችን ደግነትና አስተዋይነት የተሰጋው ቆሟል) ፤

የሚገርመው ደግሞ “ጦሱ” ከሌላ የተቀሰቀሰ ሳይሆን ግን ባራሳቸው አካባባቢ ተለኩሶ እነሱን ራሳቸውን ተመልሶ እየለበለባቸው ነው። ይህ እንዳይደርስ ለብዙ አመታት “ወያኔ” የሚባለው ቡድን እና ፖለቲካ እንዳትቀበሉ “መጨረሻ ራሳችሁን ይበላል” እያልን ስንጮሕ ከሕዝቡ የሰማነው ምላሽ ምን እንደነበር ታውቃላችሁ።  አሁን ይህ ሁሉ መከራ ሲደርስበት ተጠያቂው ማን ነው? ተጣያቂ 1ኛ፤የትግራይ ምሁርን እና ሕዝቡ እራሱ ነው፤ 2ኛው ተጠያቂ የኦሮመዎቹ መንግሥት የሆነው አብይ አሕመድ የሚመራው ሥርዓት ነው። የተቀረው የውጭ ጦሰኛ ካለ መጀመሪያ ልጅህን ማስታገስና መስመር ማስያዝ በተገባ ነበር። ያ ሳይሆን እንደኳስ ጨዋታ “አየኹም ናይና” (የኛዎቹ አይዟችሁ) እየተባለ በየ አደባባዩ ሽማግሌና አሮጊት እናቶች ሳይቀሩ የወያኔ ባንዴራ ታጥቀው ሲዘሉና እስከስታና ፉከራ ከማየት ምን የከፋ ትዕይንት አለ?

የትግራይ ሕዝብ ከማንም በላይ ጦርነት አይቷል፤ ጉዳቱንም ያወቀዋል ተብሎ ሲነገር ነበር። አይደለም እንዴ? የጦርነት ምንነት ያወቀ ሕዝብ እንዴት በአንድ ሓላፊነት በማይሰማው፤ አገር ገንጣይ ትምሕርት ተከትሎ በጊዜው ጦርነቱን መግታት ተሳነው?

 

2ኛው ርዕስ

የወያኔ ታጋዮች ለዲሞክራሲ ትግል ነበር በረሃ የወጡት የሚለው የተሳሳተ ትርክት በሚመለከት፡

4 Comments

  1. ጣድቅ የሚባል እንደዚህ አይነቱ በፅናት እውነትን የሚናግ ር ሰው ነው፡፡ ሌላው ምሁር ወለወልዳና ለመወደድ ሲውሸለሸልና ባዶ ድስኩር ሲቀባጥር የሚውል ነው፡፡

    ተባረክ አቶ ጌታቸው ረዳ!

  2. ግርማ ጥሩ ብለሀል ስለዚህ ወንድማችን ብዙ አልተባለለትም ። ከረጅም ጊዜ ጀምሮ እንደ ታዘብነው አቋሙ እንደ ማስመሪያ ቀጥ ያለ ነው ያውም ኢትዮጵያዊነት ነው ።በትግሬነቱ ሊያገኝ የሚችለውን ርካሽ ጥቅም ገፍትሮ ኢትዮጵያዊነት ጋር በጽናት የቆመ ነው። ዛሬ በየሚዲያው ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉት ብዙ ጊዜ ሲለዋወጡ ከጠላት ጋር በጥምረት ሲሰሩ ይህ ወንድማችን ከኢትዮጵያ ጋር በችግሯ ሁሉ አብሮ ቁሟል ኢትዮጵያ ተመልሳ ስትቆም ከምትዘክራቸው ዜጎች አንዱ ይሆናል እዚህ ላይ ከራያው ጌታቸው ረዳ እንዳይመሳሰልብን ጌታቸው ወልደ ኢትዮጵያ ብንለው ቅር የሚለው አይመስለኝም።

  3. ጥቂት ሐቀኛ ሰዎች ቀርታችኋታል ኢትዮጵያችን። እናንተን ያብዛልን።

    የተናገሩት መሬት ላይ ጠብ የማይል ነው።
    ሃብታም በምትባለው አሜሪካ፣ ያለ ጦርነት ወይም ሌላ ጉዳት ለሳምንት ብቻ በድንገት መንገዶች ቢዘጉ፣ ባንኮች ባይሠሩ፣ ኤሌክትሪክ ቢጠፋ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ለረሃብ ሊዳረግ ይችላል። ይሄ ማለት ግን ሕዝቡ ከዚህ ክሥተት በፊት ራብ ላይ ነበር አያስብልም። ይሁንና በደሃ አገር ላይ ሕወሃት ምን ከነገም ጭምር ሲዘርፍ ቢውል 6 ሚልዮኑን የትግራይ ሕዝብ ሁሉ ሃብታም ለማድረግ አይችልም። የሕዝቡን ተጠቃሚነት ልናስተያይ የሚገባው ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አኳያ እና ራሱም ሕዝቡ ከ27 አመታት በፊት ከነበረበት መነሻ ነው። በተጨማሪም ምን ያህሉ ወደ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ፈልሶ በሥርዓቱ ምክንያት በተለየ ተጠቅሟል?
    ለትግራይ የተለየ ፍቅር ስላላቸው ሳይሆን ወይም አማራውን በተለይ ስለጠሉ ሳይሆን ባእዳን በአድዋ ድልና በነጻነት ታሪካችን የአንድነት ምሶሶ ሆነው ለውርደት የዳረጓቸውን አምዶች ለመናድ በማለም በአማረኛ ቋንቋ፣ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ፣ በተዋሕዶ እምነት እና በኢትዮጵያ የባሕር ይዞታዎች ላይ የተቀነባበረና የተሳካ ዘመቻ አካሄደዋል። በዚህም ገዢ ቢለዋወጥም፣ የጥቃቱ ዒላማ ሳይለዋወጥ ዛሬም ቀጥሏል። ሕዝቡ ጨዋ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ባእዳን የጫኑብን ትርክት እንዲጠፋና እንዲዘመትበት የቀመረው ስሌት የአማረኛን ቋንቋ በመሆኑ ነው ዛሬም ጦርነት በሌለበትም ተጠቂው አማረኛ ተናጋሪው ሕዝብ እና ቤተክርስትያን የሆኑበት። ወይም ጄኖሳይዱ በጽሑፋቸው የተጠቀሰው ፈረንጅ ጸሐፊ እንደተነበየው ሳይሆን የወያኔ/ኦነግ ሕገ መንግሥታዊ አፓርታይዳዊ የጎሳ ሥርዐት በተቀደደለት ቦይ ዛሬም ውሉን ሳይስት አማራው ላይ ያነጣጠረ የሆነበት ምክንያት።
    አቶ ጌታቸው እንዳሉት ጎሰኞች የራሳቸውን ጎሳ ለይተው የመጥቀም እቅድ ነድፈው ይንቀሳቀሳሉ። ይህም ከጎሳ ፍቅር ወይም ለጽድቅ ብለው የሚያደርጉት ሳይሆን በሦስት መንገድ ራሳቸውን መልሶ ስለሚጠቅማቸው ነው።
    1. ተጠቅሚያለሁ ብሎ የሚደግፋቸውን የጎሳ አባል ያበዛል
    2. በአድልዎ ተጠቅሟል ተብሎ በሌላው እንዲገፋና ይበልጥ እነሱን እንደ አለኝታ እንዲያይ ያደርጋል
    3. የኢኮኖሚ አቅሙ ሲበረታ ለባለውለታው የጎሳ ድርጅት/መንግሥት ጠንካራ ድጋፍ ለማድረግ ይችላል
    a. ለምሳሌ በሕወሃት ትግል አንድ ዶሮ ሲያዋጣ የነበረው ዛሬ አንድ ሚሊዮን ብር ለማዋጣት ይችላል።

    ብዙ ምሑራን “በዋሽቶ ማስታረቅ” ተጠምደው ይታያል። ምን ያህል ይጠቅም እንደሆነ አይታወቅም። በኤርትራ የመገንጠል ትግል ጊዜ ብዙ ማባበልና የ“ዋሽቶ ማስታረቅ” ስራዎች ተሰርተዋል። ደርግ እንኳን እጅግ ጨለማ የሆኑ ብዙ ኋላ ቀር የኢትዮጵያ ክፍሎች እያሉ፣ ያቺኑ ያለችውን የሀገር ሃብት በተሻለ እድገት ላይ በነበረችው ኤርትራ ውስጥ ተገንጣዮች የሚያፈራርሱትን መዋቅርና ሌላም ብዙ አዳዲስ ነገር በመገንባት ሲታትር ነበር። ይህንን ከሌሎች እህት ወንድሞቹ አፍ ቀምቶ ለአልቃሻው ልጅ የማጉረስ ውለታ አልቃሻው ልጅ ያመሰግነዋል ወይ ወይም ይህን የመንግሥት አድላዊ ድጎማ፣ በዘመኑ ተበደልን ሲሉ የነበሩት ኤርትራውያን አመስግነውታል ወይ የሚለው ተገቢ ጥያቄ ነው።

  4. I Thank you all of you. I also thanks ZeHabesha for posting my article sent to Zehabesha website by somebody who is truly patriot Ethiopian. Truly, I didn’t think the ZeHabesha not only Zehabesha but, other opposition Diaspora websites will honor my exceptional position in the Ethiopian politics different than the majority diluted Ethiopian elites position. I am just surprised seeing my commentary posted on Zehabesha after many, many years. Anyways, I thanks Zehabesha editor and I thanks all of you for your positive complimentary. Ethiopia will prevail.- Getachew Reda -Ethio Semay

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share