February 3, 2021
14 mins read

2 ሚልዮን ብር ተሰረቅሁ ያለን የታዬ ደንደዓና የኦዴፓ ነገር /ከማስተዋል/

“አሁን ላሚቷም ጥጃዋም በእጃችን ገብተዋል:: ቁማሩንም ተጫውተን በልተናል” ሲሉ በአደባባይ የተዛበቱብን የኦዴፓ አመራሮች የአፍሪቃ ነፍሰበላ ናዚ ካልነው የሕወሓት ጁንታ በግብርም በተግባርም እጅግ እያስናቁ መጥተዋል:: ሃገር በፖለቲካ ሴራ በግፍና በተንኮል ልትመራ እንደማትችል ጠፍጥፎ ከሰራቸው ከትላንቱ የትህነግ ጁንታ አለመማራቸው እጅግ አስገራሚ ብቻ ሳይሆን አሳፋሪም ጭምር ነው:: የኦሮሞ ተወላጅ የታሪክ ምሁሩ ቄስ ግርማ ዘውዴ “የኔታ” በተሰኘ ማህበራዊ ድህረ-ገጽ በአንድ ቃለ መጠይቃቸው “በወለጋ ብቻ ኦሮሞ አካባቢውን ተቆጣጥሮ ሲስፋፋ 13 ነባር ጎሳዎችን እንዳጠፋ” መረጃ አጣቅሰው እንደነገሩን ሁሉ ዛሬም እንደ ታላቋ ትግራይ ወይም አባይ ትግራይ ሁሉ ታላቋን ኦሮሙማን እያለም በሸፍጥና በሴራ ፖለቲካ የመሬት መስፋፋትን ዋና የትግል ማዕከሉ ያደረገው ኦዴፓ እንደ ትህነግ ሁሉ ተቀናቃኜ ናቸው የሚላቸውን በፈጠራ ክስ እስር ቤት ወርውሮ ሀገር በታኝና ሰላምን የሚያደፈርስ እኩይ ተግባር ውስጥ ተዘፍቆ እያየነው ነው::

https://www.youtube.com/watch?v=Tt3T41l_QAk

በለውጡ ማግሥት እነ ለማ መገርሳ ከሕዝብ ተደብቀው አስመራ ድረስ ተሻግረው ከኦነግ ጋር ያደረጉት የሸፍጥ ስምምነትም ዛሬ ላይ የዚሁ እኩይ ዓላማቸው አንዱ ዕቅድ መሆኑን በግልፅ ለማስተዋል ችለናል:: የኢሳያስን የእርሻ መሬት በአፋበት በረሃ ሲጎለጉልና ሲያርም ለ 25 ዓመታት የኖረው የኦነግ ታጣቂ 1000 የማይሞላ ሰራዊቱን ይዞ ሀገር ቤት በመግባት እስከ ምርጫ ድረስ ከእነ ትጥቁ እንዲቆይ የተደረሰው ምስጢራዊ ስምምነት ዓላማና ግቡ ምን እንደሆነ ማብራሪያ የሚያስፈልገው አይደለም:: ይህን ሰራዊት በቁጥርም በወታደራዊ አቅምም ሆነ በፋይናንስ ለማጠናከር በአደባባይ በኢትዮጵያ ስም እየማሉ ከጀርባ ለንጹሃን ዜጎች እልቂት ካራ በሚስሉ የኦዴፓ አመራሮች እየተጫወቱት ያለው ሚና ቀላል አይደለም:: ከራሱ ክልል አልፎ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጭምር የመስፋፋት እቅድ ያለው ኦዴፓ በተለይም ተገዳዳሪዬ የሚለውን የአማራው ማሕበረሰብ ለማጥፋት እጅግ ዘግናኝና አረመኔያዊ ድርጊቶችን በኦነግ ታጣቂዎች በኩል እየፈፀመ ይገኛል:: ባለፉት 3 ዓመታት ከለውጡ ማግሥት ጀምሮ ከ 50 የሚልቁ ቤተ ዕምነቶች እንዲቃጠሉ በየትኛውም ዓለም ታይቶ በማይታወቅ የጭካኔ ጥግ ሕጻናትና ሴቶች ጭምር ታርደው በገዳዮቻቸው አካላቸው እንዲበላና ደማቸው እንዲጠጣ የተደረገው የክርስትና ዕምነትን እከተላለሁ በሚለው የአብይ አህመድ አስተዳደርና በኦዴፓዎች የሴራ ፖለቲካ መሆኑን ስናስብ ደግሞ የግለሰቦቹን የወረደና የዘቀጠ ሰብዕና ጠንቅቀን እንድንረዳ የሚያደርገን ነው:: ይህ ሰው በላ ቀማርተኛ ባለተራ የጁንታ አመራር ከአስመራ ሰብስቦ ያመጣቸው አራዊት የኦነግ ታጣቂዎቹ በጠራራ ፀሃይ ጭምር ከ 15 ያላነሱ ባንኮችን እንዲዘርፉ አድርጓል:: ስልጣኑን ስለተገዳደረው ብቻ አቂሞ ለጦርነት እጅግ አስቸጋሪ የመክአምድር አቀማመጥ ባለው የትግራይ ክልል የትህነግን ጁንታ በሶስት ሳምንት ድልነሳሁ ያለው ዓብይ አህመድ እራሱ ለእኩይ አላማው ከኤርትራ ያመጣው የሸኔ ሰራዊት ዛሬ ከአንድ ሺህ ተነስቶ በ 40 እና ሃምሳ ሺህ የሚገመት ታጣቂውን በአደባባይ አሰልጥኖ እንዲያደራጅ የራሱን ገዢ መሬት እንዲቆጣጠርና ተገዳዳሪ ኃይል እንዲሆን በተዘዋዋሪ መንገድ የትጥቅ ድጋፍ ሳይቀር ከማድረግ አልፎ ላለፉት 2 ዓመታት ፈጽሞ ሊያጠፋው እንዳልቻለ በመግለጽ በንፁሃን ደምና በሕዝብ ሰቆቃ እየቆመረ ይገኛል:: ሌላው ጉዳይ በሸኔው ታጣቂ ኃይል ስርቆት ተገርመን ሳናበቃ የኦዴፓ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊው ኦቦ ታዬ ደንደአም ግርግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ ከ 11 ወራት በፊት “አዳማ ላይ ስልጠና ለሚከታተሉ አመራሮች ለውሎ አበል የሚከፈል 2 ሚልዮን ብር በመኪና ጭኜ ስጓዝ እርቦኝ ቦሾፍቱ ላይ ምሳ ልበላ ከአንድ ሆቴል ገብቼ ተሰረቅሁ ሿሿ ተሰራሁ” የሚል ዜና አስነግሮ በወቅቱ ሌላ ሜቴክ መጣብን ወይ ማለታችን አልቀረም ነበር:: ልብ በሉልኝ! ከፋይናንስ ኃላፊዎች ውጪ ለ 400 ሰው አበል ክፍያ አንድ የሕዝብ ግንኙነት ሰራተኛ 2 ሚልዮን ብር በጆንያ ጭኖ ከአንድ ሆቴል ደጃፍ መኪናውን ትቶ አንድ ባለ ፌስቡክ ተጠርጣሪ ሰረቀብኝ የሚል ቃለ-ምልልስ በራዲዮ ሲሰጥ ሰምተን ጥርሳችንን ብቻ ሳይሆን አይናችንንም አስቆታል ብንላችሁ መቼም አትፈርዱብንም:: ዛሬ ላይ ስንት ሚልዮን ብር በምን ያህሉ ብሄርን ከፋፋይ አሻጥረኛ የፖለቲካ አመራሮች እጅ በሰበብ አስባቡ እንደገባ መቼም እሱ ይወቀው:: ቃለ-መጠይቁን ከራሱ ከታዬ ደንደአ አንደበት ማድመጥ ትችላላችሁ::

ዕብሪተኛና ማን አለብኙ የኦዴፓ አመራር ወያኔ በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በኦሮምያ ክልል ብቻ ከ 30 በላይ የሚልቁ ሰዎችን በፖለቲካ አመለካከታቸው አስሮ ሲያሰቃይና ገሚሶቹንም ሲገድል የኖረ የጁንታው ትሮያን ፈረስ ዳውላ ተሸካሚ አሽከር ነበር:: ከለውጡ ማግሥት ጀምሮ እንደ አብን እና ባልደራስን የመሳሰሉ ድርጅቶች መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም የአማራውን ማህበረሰብ “ነፍጠኛ” የሚል ታፔላ ለጥፎ በግፍ ከአማራው የቀማው ታሪካዊ ርስቱ ጥያቄ እንዳያስነሳበት የዘር እልቂት ሲፈፅምበት ሲያሳርደው ሲያፈናቅለውና እረፍት ሲነሳው የኖረው የሕወሓት ፓርቲ በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ መንግሥትንም ፓርላማውንም ሲማፀኑና ሲያሳስቡ መቆየታቸውን መለስ ብሎ ዜናና ሰነዶችን ወደኋላ ፈትሾ ማጤን ይቻላል:: የጁንታው ትህነግ ዋና አሽከርና ጠበቃ የነበረው የራሱን ብሄረሰብ አባላት ሳይቀር በጭካኔ ሲያሳርድ የኖረው ኦዴፓ መራሹ የዓብይ መንግሥት ግን ትህነግ እየወጋቸውና እየተሳለቀባቸውም ቢሆን በድፍረት ዛሬም ድረስ ይህን መወሰን ሳይችሉ ቀርተዋል:: ባለፉት 27 ዓመታት በመላው ኢትዮጵያውያን ላይ በተለይም ደግሞ በአማራው ማህበረሰብ በወልቃይትና ራያ ሕዝቦች ላይ ጄኖሳይድ ሲፈጽም የኖረን የመከላከያ ሰራዊት አባላትን በግፍ የረሸነነ በቅርቡም በማይካድራ ሳምሪ በተሰኙ በትህነግ በተደራጁ ወጣቶች የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ ቦኮሀራም ናይጄሪያ ላይ በተመሳሳይ ወር ከፈፀመው ወንጀል የበለጠ እንደሆነ ዓለም አቀፉ የፖሊስ ትብብር ተቋም ኢንተርፖል ማስታወቁና ይህም በፈረንጆቹ የዘመን አቆጣጠር በወርሃ ህዳር 2020 ዓ.ም በመላው ዓለም የተፈፀሙ 10 አስከፊ የሽብር ጥቃት ዋናው መሆኑ በተገለፀበት ሁኔታ ኦዴፓ ግን ትህነግ በፓርላማ አሸባሪ ሆኖ እንዳይፈረጅ ሲከላከል የኖረና አሁንም ሰላማዊ ታጋዮችን እነ እስክንድር ነጋን በግፍ አስሮ በፀረ-ሽብር ችሎት ጉዳያቸው እንዲታይ ውሳኔ የሰጠው ዘረኛ ስልጣን ናፋቂና አስመሳዩ የዓብይ መንግሥት በትግራይ የህግ ማስከበሩ ሂደት በቁጥጥር ስር የዋሉ የሕወሃት አመራሮችን የክስ ሂደት በልዩ የወንጀል ችሎት ከማየት ይልቅ በተራ ፍርድ ቤት እንዲመረመር ማድረጉ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ያለውን ጥላቻና ንቀት ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነው:: እነ ባልደራስና አብኖች ይህን ሁሉ ህልቆ መሳፍርት የሌለው የትህነግ ግፍ ተቃውመው ፓርቲው በአሸባሪነት ይፈረጅልን ሲሉ ቢቆዩም ዘረኛውና በተረኝነት እብሪት ያበተው ኦዴፓ ግን ጩኸቴን ቀሙኝ እንደሚባለው ተረት ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብታቸውን ጭምር ነፍጎ ራሱ ባደራጀው ሰልፍ “እነ አብን ጽንፈኞች የጁንታው ተላላኪ ቅጥረኞችና የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው” ሲሉ ዓብይ አህመድ በሰጣቸው መፈክር ጥላቻቸውን ማስተጋባታቸው የእብሪታቸውን ልክ ያሳዩበት በተለይም በአማራውና በሌላውም የድርጅቶቹ ደጋፊዎች ላይ ያላቸውን ጥላቻና የዘር እልቂት በአደባባይ ያወጁበት አሳፋሪ ተግባር ነውና በህግ ሊጠየቁ ይገባል:: ትላንት ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር ታግሎ ከህወሃት ጋር የፈፀሙበትን ግፍ በይቅርታ አልፎ አምኖ ለስልጣን እንዳላበቃቸው ሁሉ አፍታም ሳይቆዩ በልቅ አፋቸው “ነፍጠኛውን ሰባብረን ጥለነዋል” በሚል የጥላቻ ቅስቀሳ በመላው ኦሮምያ የአማራውን ማህበረሰብ እንዳስፈጁት ሁሉ ዛሬም ኦዴፓዎች የደገሱት የዘር እልቂት ሌላ መዘዝ ሳያመጣ በዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት እነዚህን አረመኔዎች ለማቅረብ በጋራ መንቀሳቀስ ይኖርብናል:: እነ ታዬ ደንደዓ ተድበስብሶ በቀረውና ገለተኛ አጣሪ አካል በሌለበት ተሰረቅኩ ባሉን በ 2ሚልዮን ብሩ የሿሿ ድራማ እንዳሻቸው ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየወጡ እንዲቦርቁብንም ዕድል ልንሰጣቸው አይገባም:: እስከመቼ ሀገር እንዳትፈርስ ተብሎ የግፈኞች ስልጣን ወዳዶችና አረመኔዎች መጫወቻ እንሆናለን???? እስከመቼ ንፁሃንን ሕጻናትና ነፍሰጡሮችን ሳይቀር እያረዱ በሚያስበሉና በሚበሉ የቀን ጅቦች የስቃይ ሰለባ እንሆናለን ??? ይህ የእኩያን ሴራ ነገ የእያንዳንዳችንን በር ሳያንኳኳ ዛሬ በአንድ ድምፅ ሁላችንም በቃ ይበቃል ልንል ይገባል!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop