“በኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ለሚከሰተው የሰው ዘር ዕልቂት ተጠያቂው የግራኝ አህመድ አቢይ መንግሥት ነው” ለማለት ቃጥቶኝ ነበር፡፡ ግን ግን ይህ ለላንቲካውና በልማድ የሚነገረው ለአንድ ጥፋት ወይም ውድመት ኃላፊነትንና ተጠያቂነትን የሚወስድ አካል ወይም ግለሰብ የማፈላለግ ጉዳይ አሁን አሁን ጠቀሜታው እስከዚህም ነው፡፡ ጉዳትን ቀድሞ መከላከል እንጂ አንድ ኪሣራ ከደረሰ በኋላ ኃላፊነት የሚወስድን መፈለግ ከጉንጫልፋነት አይዘልም፡፡ የሩዋንዳን ዕልቂት ያስከተሉት አካላት ምን ሆኑ? ምንስ ቢሆኑ የተገደሉትን ዜጎችና የወደመውን ሀብት ንብረት መመለስ ቻሉ ወይ? ሂትለርና ሙሶሊኒ፣ ኢዲያሚንና ቦካሣ፣ አልቃኢዳና አልሻባብ… ያንን ሁሉ የሰውና የንብረት ውድመት አስከትለው ምናልባት ከተራ ሞት ወዲያ ምን ከባድ ቅጣት ደረሰባቸው? … ኃላፊነት የሚወስድ ወገን ቢመጣ በመተከልና በወለጋ፣ በሐረርና በአርሲ፣ በሻሸመኔና በጋምቤላ፣ በባሌና በሌሎች ብዙ ቦታዎች ላለፉት 30 እና 40 ዓመታት በማንነታቸው ምክንያት በአክራሪዎች የታረዱ ዜጎችን ሕይወት ይመልሳል ወይ? ስለዚህ ዋናው ቀድሞ መጠንቀቅ ነው፡፡ ጥንቃቄ ባለማድረግ እጅን አጣጥፎ መቀመጥ ለሰይጣኖች ምቹ ያደርጋል፡፡ በኦህዲድ/ኦነግ እየተደገሰልን ያለው ድግስ እጅግ ከባድ ነው!!
የትናንትናው የብልግና ፓርቲ ሰልፍ በተለይ በአማሮች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የታወጀበት ሰልፍ ለመሆኑ እማኝ መቁጠር አያሻም፡፡ እንደዚያ ያለ ሰልፍ በዓለም የመጀመሪያው ነው፤ ለሞኝ ግን ምንም ላይመስል ይችላል፡፡ በነግራኝ አቢይ ወሽመልስ አህመድ አብዲሣ የሚመሩት አክራሪ ኦሮሞዎች እውነትም ዙሩን እያከረሩት ነው፡፡ ከወያኔዎችም ብሰው አማራን ለማስፈጀት የመጨረሻውን ቀይ መስመር አልፈዋል፡፡ ይህም በታሪክና በእግዚአብሔር እየተመዘገበ ነው፡፡ ከወፈሩ ሰው አይፈሩ ነው፤ በእርግጥም ጥጋባቸው ገደብ አጥቷል፡፡ “ነፍጠኛ ከክልላችን ይውጣ” ብሎ ማስፎከር “አማራን በያለበት ፍጅ” እንደማለት ነው፡፡ ኦነግ ሸኔን ለይምሰል በመናጆነት አብሮ አስቀምጦ ሰላማዊ ታጋዮችን መወንጀልና እንዳሰሩ ማቆየት ልበድፍንነት ነው፡፡
ሰልፉ ጥሩ ምልክት ነው፡፡ የነፃነት ዘመን ቀርባለች፡፡ የመከራ ቀምበር ሊሰባበር ትንሽ ጊዜ ቀርቶታል፡፡ እነዚህ አክራሪዎች ደም አስክሯቸዋል፡፡ የዘረኝነቱ አባዜ አሳብዷቸው የሚሠሩትን አጥተዋል፡፡ በአንድ በኩል ጥሩ ነው፡፡ በሌላ በኩል ጥሩ አይደለም፡፡ ሟች ይዞ ባይሞት ጥሩነቱ ባመዘነ፤ ግን ብዙ ነገሮች እንደሚታሰቡት አይቀሉም፡፡ ያለ መስዋዕትነት ድል አለመኖሩ ተዘውትሮ የሚዘከረውም ለዚህ ነው፡፡ ክፉ ቀን እየመጣ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ህዝብ በተለይም ወጣቱ እንደከብት እንደሚነዳው የገጠር ቄሮ በጭካኔና በዕኩይ ተግባራት ተኮትኩቶ አላደገም፡፡ ገር ነው፤ ሩህሩህ ነው፡፡ በዘርና በጎሣ፣ በሃይማኖትና በባህል ልዩነቶች ተነድቶ አንዱ ሌላውን አይጎዳም፡፡ ያደገበትና ያሳለፈው ማኅበረሰብኣዊ መስተጋብር ክፉ ነገርን በማንም ላይ እንዲያደርግ አይፈቅድለትም፡፡ ከዚህ ተቃራኒ የሆኑት አክራሪ ወገኖች ይህን የአዲስ አበባ ህዝብ ጠባይ በመረዳትና “ምንም ጉዳት አይደርስብንም” ብለውም በማሰብ አዲስ አበቤን ለማፈን እየተራወጡ ነው፡፡ በሌላ በኩልም ዝምታውንና ትግስቱን ይፈራሉ፡፡ ስለዚህም ፀጥ ረጭ አድርገውና ወደ ግዑዝነት ለውጠው ቀጥቅጠው ሊገዙት ይጥራሉ፡፡ አንድም ወኪልና ብሶቱን የሚተነፍስለት አለሁህ ባይ እንዳይኖረው ቀን ከሌት ይማስናሉ፡፡
ዘረኝነት መጥፎ ነው፡፡ ዘረኛ ሰው “ከነሱ ደግ የኔ ክፉ ይሻለኛል፤ ከነሱ ሩህሩህ የኔው ዐረመኔ ይበልጥብኛል፤ ከነሱ ቸር የኔው ንፉግ ይሻለኛል፤…” በሚል እሳቤ የታወረ የስንኩል አእምሮ ባለቤት ነው፡፡ ይህን እውነታ በስዬ አብርሃ ወራዳ ተፈጥሯዊ ባሕርይ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ በጻድቃን ገ/ትንሳይ ብልሹ ጠባይ መገንዘብ ይቻላል፤ በአበበ ተ/ሃይማኖት ወልጋዳ ሥነ ተፈጥሮ ማየት ይቻላል፤ ከነሽመልስ ዕብሪት መረዳት ይቻላል …፡፡ ዘረኝነት መጥፍ ክርፋት ነው፤ ህክምና የሌለው ግማት ነው፤ ጥምባቱም የሽዎች ኪሎ ሜትሮች ርቀት አይገድበውም፡፡ ይህን በሽታ በድል የሚወጡ ቁጥራቸው እጅግ አነስተኛ ነው፤ ከምፈልገው አካባቢ ቁጠር ብባል አሥር ሰው የምደርስ አይመስለኝም፡፡ የዘርን አጥር ዘልሎ መውጣት የተራራ ያህል ከባድ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ሕዝብ ይጠንቀቅ፡፡ ኢትዮጵያውያን እንጠንቀቅ፡፡ የተደገሰልን መከራ ከባድ ነው፡፡ የመንግሥትን በትረ ሥልጣን የያዘ አካል ሙሉ ስፖንሰር ያደረገው የዘር ፍጂት በየበራችን ቆሟልና ወደ ፈጣሪ እንጸልይ፡፡ አንሞኝ፡፡ የሃይማኖት አባቶችና እናቶች በርትታችሁ ጸልዩ፡፡ ጥጆችንና ሕጻናትን ከጡት በማገድ ጭምር ወደላይ እንጩህ፡፡ እግዚአብሔር ቅጣቱን ቀለል እንዲያደርግልን ምህላና ሱባኤ እንግባ፡፡ እስካሁን ከታረደው ወደፊት የሚታረደው እጅግ ይበዛል፤ ጨለማው እየከፋ ነውና እንንቃ፡፡ የድንቁርና መብዛት ክፉ ቀንን ሸፍኖ አያስቀርምና ልባሞች እባካችሁን የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ፡፡ ቀን የሰጣቸው ሰዎች ኢትዮጵያን ይዘው እንዳይጠፉ ሀገራዊ ምህላ ይደረግ፡፡ ይህን የምለው ውድመቱ የትንሣኤውን ትሩፋት እንዳያደበዝዘው እንጂ ነጻነታችን የማይቀር ነው፡፡ ሩዋንዳ፣ የመን፣ ዩጎዝላቪያ፣ ሶማሊያ፣ … በመንግሥታችን አማካይነት ወደሀገራችን ተጋብዘው መጥተው እንደሚከፋፈል የሸቀጥ ዕቃ በቤተ መንግሥታችን ተከማችተዋል፡፡ በሻሞ ልንቀራመታቸው የኦነግ/ኦህዲድን ፊሽካ ብቻ እየተጠባበቅን ነው፡፡ ዕድሉ ያለው ይህን ወጥመድ ያክሽፍ፡፡ ዘንዶው ሥራውን እየሠራ ነው፡፡ ለጊዜው ሁሉን ተቆጣጥሯል፡፡ ግን ይከሽፍበታል፡፡ …