የዛሬ ሶስት ዓመት ገደማ አብይ አብይ ወደ ሥልጣን ሲመጣ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በአዲስ መንፈስ ከልብ በሆነ መልኩ ለአብይና አጠቃላይ የለውጥ ወኪል ነኝ ላለው ቡድን ልዩ የሆነ ድጋፍ ሰጥቶ ነበር፡፡ ብዙዎችም በታላቅ መነሳሳት አገራቸውን ለመለወጥ ቆርጠው ነበር፡፡ እነ አብይ አህመድ መጀመሪያ ዛሬ እየከወኑትን ያለውን ሴራና ቁማር ያን ሁሉ አስፈሪ የሆነ ድጋፍ በማሰብ እንኳን አስበውት የነበረውን ሴራ ወደጎን ትተው የሕዝቡን ስነልቦታ መከተላ በቻሉ ነበር፡፡ የሆነ ሆኖ ያን የመሰለ እድል ገጥሟቸው ቀድመው የወጠኑት ሴራ እንጂ የሕዝብና አገር ጉዳይ አንዳችም ሊታሰባቸው ባለመቻሉ ይሄው አሁን እየሆነ ያለውን እናያለን፡፡ አዝናለሁ፡፡ እኔ ባቅሜ ብዙ ማሳሰቢያዎችን ስሰጥ ነበር፡፡ የሆነው ግን ያው ነው፡፡
ሁለተኛ ጊዜ አሁን እንኳን በወያኔ ላይ በተደረገው ጦርነት ትልቅ የሚባል ሕዝብን በአዲስ መንፈስ ወደ አገራዊ እይታና አቅድ ለማምጣት እድል ተፈጥሮ ነበር፡፡ አጋጣሚውን በማስተዋል ብዙ ለመወትወት ሞከርን፡፡ ነገሩ ያዳቆነ ሰይጣን አይነት ሆነና ጭራሽ አጋጣሚውን ለሌላ ሴራ ማዋል ተመረጠ፡፡ ይህ ያሳዝነኛል፡፡ ሌላ ቀርቶ ወያኔዎች ያን ያህል አረመኔ ሥራን ሰርተው በኋላም በለት አረመኔነታቸው ብዙዎቹ በአዛውንትነት እድሜያቸው የሆነባቸውን ስናይ እንደሰው እጅግ ያሳዝናል፡፡ ሆኖም ምርጫቸው ስለሆነ የፈለጉትን ሆኖላቸዋል፡፡ ያቆብ ወንድሙ ኤሳው ባሳደደው ጊዜ ያቆብ ከወንድሙ ጋር ጦርነት እንዳይገባ ብዙ ተጠነቀቀ፡፡ መጨረሻ ላይ ግን ኤሳውን የተከተለው ሴራ በምንም መልኩ ሊተወው ባለመቻሉ ሰራዊቱን ይዞ ያቆብን ለማጥፋት ዘመተ፡፡ የያቆብ ልጆች ኤሳው አጎታቸው ስለሆነ በሱ ላይ ቀስት መወርወርን አልደፈሩም፡፡ ይሁዳ ወደ አባቱ ያቆብ ቀርቦ አባቴ ሆይ እሱ ለእኛ እንዳንተ ነውና እኛ እሱን ቀስት ወርውረን ልንወጋው አንችልም አንተ ውጋው ብሎ ነገረው፡፡ ያቆብም በወንድሙ ላይ ቀስቱን ሳበ ወንድሙንም ገደለው፡፡ የያቆብ ሰራዊት የኤሳውን ሰራዊት ማሳደድ ያዘ ያቆብ ግን ወደኋላ ቀርቶ የወንድሙን አስከሬን በመረረ ሐዘን ቀበረ፡፡
ተንኮልና ሴራ ልክፍት ነው፡፡ ምን ሠላማዊ ለመሆን ቢሞክሩ የእውነተኞች አምላክ ተንኮለኞችን በራሳቸው ሴራ እንዲጠፉ ይፈልጋልና ለራሳቸው ክፋት አሳልፎ ይሰጣቸዋል፡፡ እንደዛማ ባይሆን ተንኮለኞች ስንቱን የቧህ ዘሩን ባጠፉት ነበር፡፡ ዛሬ በስልጣን ላይ ያሉት በሙሉ ማለት ይቻላል ከወያኔ ጋር በተንኮልና ሴራ ስላደጉ የቱንም ያህል ለማስመሰል ቢፈልጉም ከተለከፉበት ልክፍት መውጣት የቻሉ አይመስለም፡፡ ያ በኢትዮጵያዊነት የቃላት ጋጋታ ያሸበረቀው የለውጥ ኃይል ስልጣን ስልጣን ከመያዙ በፊት ሲያስባት የነበረቸውን ሴራ ለመተግበር ጊዜም አላባከነም፡፡ ቅድሚያ አዲስ አበባንና ዋና ዋና የፌድራል መዋቅርን ከወያኔ ትግሬ ወደ ኦሮሞ ኦነግ ስሪት ኦዲፒ መቀየር ትልቁ ጥድፊያ ነበር፡፡ እንግዲህ ይሄ እየታሰበና እየተፈጸመ ያለው በአይናቸው ሥር የወያኔን የ27ዓመት ግፍ እምቢ ብሎ የጣለውን የወያኔን ነገር እያዩ ነበር፡፡ እነ አብይ አህመድ ግን የታያቸው የኦሮሞ የቁጥር መብዛት እንጂ ያሰቡት ሴራን አደገኛነት አደለም፡፡ አዝናለሁ፡፡ ወያኔ ስድስ ሚሊየን ትግሬ ይዛ ይሄን ያሕል ከቆየች እኛ ይሄን ሁሉ ሕዝብ ይዘን ዘላለም እንገዛለን የሚለው ከድሮ ጀምሮ አንዴ ብቻ ስልጣን እጃቸው መግባትን ሲያሴሩ ስለነበር ያንኑ ነው በዚህ ሶስት ዓመት የፈጸሙት፡፡ ያሳዝናል፡፡
ሕዝብና ሰራዊቱን ወደ ወያኔ ጦርነት ባሰማሩበት ወቅት እንኳን ሴራ ሲጎነጉን የምናይባቸውን ነገሮች እናስተውላለን፡፡ በዚህ ወቅት ነበር በስልጣን ሽግሽግ በሚል ለብዙ ጊዜ እንዴት ያን ቦታ በኦሮሞ እንደሚያሲዙት ሲያስቡት የነበረውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነቱን ቦታ ሙሉ በሙሉ ለዲና ሙፍቲ የሰጡት፡፡ ያሳዝናል፡፡ ገዱ አንዳርጋቸው ከዚህ ቦታ እንደተነሳ ያወቀው እንደማንኛውም ሰው በቴሌቪዥን ነው፡፡ ገዱ ለቦታው የተለየ ሰው ነው እያልኩ አደለም፡፡ ቢያንስ ግን ዛሬ ሱዳን እየቀለደችብን ያለውን ጉዳይ እሱ ጥሩ አድርጎ እንደያዘው እናስባለን፡፡ ዲና ሙፍቲና ገዱ በብዙ ነገር በዛ ቦታ ስላልተስማሙም ይመስላል አብይ አህመድ ቦታውን ከገዱ ነጻ ማድረግ የሞከረው፡፡ ዲና ሙፍቲ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ላይ ሲያሴር የነበረ ሰው እንደሆነ አንዳንድ መረጃዎች አሉ፡፡ እንዲህ ባለበት ሁኔታ ደመቀ በተደራቢነት በሚል ቦታው ላይ በመመደብ ሥራውን ግን ሙሉ በሙሉ ለዲና ሙፍቲ ተሰጠ፡፡ ይሄን ጉዳይ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲያስቡበት እፈልጋለሁ፡፡ አሁን ከሱዳ ጋር ባለው ሁኔታ በጣም አስቂኝ ነገሮችን እናስተውላለን፡፡ መጀመሪያ ምንም መሬት እንዳልተወረረ፣ ከዛም የሆኑ ሚኒሻዎች የፈጠሩት የተለመደ ግጭት፣ ከዛም ነገሩ ይፋ እየሆነ ሲመጣ ደግሞ አንዴ ለቁራጭ መሬት ብልን ወደ ጦርነት አንገባም እስከማለት ደርሰዋል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ለማስመሰል ሱዳን የያዘችውን መሬት ለቃ ካልወጣች ድርድር የለም የሉናል፡፡ ችግሩ ከሱዳንና ግብጽ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ቤተመንግስትና የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንደሆነ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ልብ ሊሉት ይገባል፡፡ አዝናለሁ፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኩል ያለው የአለም ዓቀፍ ዲፕሎማሲው ነገር እጅግ አሳሳቢ ሆኗል፡፡ አገር የተወከለችው በቁማርተኞች ነውና፡፡ አሁን ባለው የዓለም የፖለቲካ ሁኔታ ደግሞ የባሰ ነበገር እንደሚመጣ እሰጋለሁ፡፡ ከሱዳንና ግብጽ ይልቅ ለእኛ ቅርብ የሆኑ እንደ እስራኤል ያሉ አገራት ሳይቀር ዛሬ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት እየሻከረ እንደመጣ እናስባለን፡፡ አብይ እስራኤልን በጎበኘ ጊዜ የተደረገለት አቀባበልና ራስ ዳሸን ተቃጠለ ሲባል እስራኤል ሄሊኮፕተር የላከችበት ከኢትዮጵያ ጋር ያለኝ ግንኙነት ማጠናከር እፈልጋለሁ፡፡ በወያኔ ጊዜ ብዙ ያሰብኩት የተፈለገውን ያህል ግንኙነት እንዲኖር አላስቻለም የሚል አንድምታ ያለው ነበር፡፡ ምንም እንኳን እስራኤል በተለይ በሟቹ ጠ/ሚኒስቴር ጊዜ ጥሩ የሚባል ግንኙነት ከኢትዮጵያ ጋር እንደነበራት ቢገመትም፡፡ ይህ አሁን የለም፡፡ ብዙዎችም መጀመሪያ ላይ ትልቅ ተስፋ አድርገው ነበር፡፡ አሁን ያ ሁሉ እንደጉም ብን ብሎ የለም፡፡ ሁሉም የጠፋው በሴራና ቁማር አገር እንመራለን በሚል በተሄደባቸው የእነ አብይ አህመድ መርጫ ነው፡፡ ያሳዝናል፡፡
በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳን ዶናልድ ትራምፕ ጊዜ ምንም እንኳ ዶናልድ ትራንፕ በግሉ ኢትዮጵያ ጠል ቢሆንም የእሱ ወኪሎች ግን በብዛት እንደ እውነቱ ከኢትዮጵያ ጋር ነበሩ፡፡ በእርግጥም አሁን ወደ አሜሪካ የተመለሱት በኢትዮጵያ የአሜሪካው አምባሳደር በግልጽ ከኢትዮጵያ ወግን ነበሩ፡፡ የውጭ ጉዳዮ ፓፒዮም ቢሆኑ ጥሩ ምልከታ ነበራቸው፡፡ ይሄን እንታዘባለን፡፡ ትራንፕም ቢሆኑ ክፍተቱ የዲፒሎማሲ እንደሆነ እንታዘባለን፡፡ ግብጽ የሄደቸውን ያህል ለትራምፕ ቀርቦ ለማስረዳትና የቻለ አልነበረምና፡፡ ከኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ይልቅ ሱዳኖች ስለ ኢትዮጵያ በዛን ወቅት ጥሩ አቋም ነበራቸው፡፡ ዛሬ ግን ይሄ ሁሉ የለም፡፡ ብዙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ የትረምፕ ብቻም ሳይሆን የፓርቲያቸው ሪፐብሊካን ሳይቀር ቀንደኛ ተቃዋሚ ሆነውም አይተናል፡፡ እንደምገምተውም ብዙዎች የመረጡት የዲሞክራቲክ ወኪሎችን ነው፡፡ ሆኖም እስካሁን በአየናቸው አውነታዎች ዲሞክራቶች ለኢትዮጵያ እጅግ መጥፎ የሆነ አስተሳብ እንዳላቸው እናያለን፡፡ ለወያኔ ትልቅ ደጋፍ ከሰጡት ብናይ የክሊንተንና የኦባማ አስተዳደር ነው፡፡ ይልቁንስ በኋላ የትረምፕ ወደ ሥልጣን መምጣት ለወያኔ መውደቅም የራሱን አስተዋፅኦ ነበረው፡፡ በግልጽም ከሕዝብ ጎን የትረምፕ መንግስት ቆሟል፡፡ በኋላም ኢትዮጵያ ወደተሻለ ሁኔታ እንድትመጣ የበኩሉን አድርጓል፡፡ ትረምፕ በቀጥታ ሳይሆን የትረምፕ አስተዳደር፡፡ በእርግጥም የገዛ ልጁ ሳትቀር ኢትዮጵያን ጎብኝታ ይበልጠውንም እንደውም የጫማ ፋብሪካ ሳይቀር ልትከፍት አስባለች ሲባል ነበር፡፡ ሆኖም ወደኋላ ላይ ሆኔታዎች የአሜሪካ መንግስትም እንዳሰበው አልሆኑም፡፡ በተለይ የኦሮሞን ጽንፈኞች እንቅስቃሴ በትኩረት ይከታተሉት ነበርና ነው፡፡ በተለያየ ጊዜም ቀድመው መረጃ ሲያወጡ ነበር፡፡ ከዛም አልፎ በሕዝብ ተወካዮቻቸው በኩል አሁን ያለው ለአንዳንድ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አሁን ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ጤነኛ እንዳልሆነ ጥቆማ ሲሰጡ ነበር፡፡ ይሄንንም ጥቆማ የሚሰጡት የአሜሪካ የሪፓብሊካን ወኪሎች ነበሩ፡፡ ዲሞክራቶቹ ጋር ትልቅ ችግር አለ፡፡ በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚሴሩ ሴራዎች አንዱ ሐይማኖታዊ ሴራ ከመሆኑ አንጻር ዲሞክራቶቹ እጅግ አሳዛኛ የሆነ እይታ ነው ያላቸው፡፡ አሁንም ቢሆን በባይደን በኩል እየተሾሙ ያሉ ሰዎች ለኢትዮጵያ ጥሩ ምልከታ ያላቸው አይመስለኝም፡፡ የተደራጀ የመረጃ ልውውጥ ቢኖር ቢያንስ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ምን እየተደረገ እንደሆነ እንዲያውቀው በተቻለ ነበር፡፡
አሁን ደግሞ ምርጫ ተብሎ ይሄው ቅስቀሳ እየተደረገ እያለ ሌላ ሴራ ተጀምሯል፡፡ አዝናለሁ፡፡ አሁን ማን ይሙት ለወያኔ የሚቀርበው የብልጽግና ባለስልጣናት ናቸው ወይስ አብን፣ ወይስ ባልደራስ፡፡ ሲጀምር ከወያኔ ጋር ሲገድሉና ሲዘርፎ የኖሩ ናቸው በቀጥታ በስልጣን የቀጠሉት፡፡ ሲቀጥል ሁሉንም የወያኔ ሥርዓት ሳይቀየር ወደ ምርጫ መሄድ የመረጡት አሁንም የብልጽግና የተባው ቡድ ነው፡፡ ሌላው አስቂኙ አብን ስጋት እንኳን ቢሆን ለአማራ ብልጽግና በኆነ፡፡ አብን ግን አስፈሪ የሆነበት የኦሮሞ ብልጽግና ነው፡፡ ይገርማል፡፡ የሰሞኑ የኦሮሞ ብልጽግና ሰልፍ ዓላማ ግልጽ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ነው ወደ ምርጫ እየተገባ ያለው፡፡ አዝናለሁ፡፡ ሕዝቡን ከአሸከሙት ባነርና መፈክር ሳያንስ በቀጥታ ባለስልጣናቱ ይሄው አብንና ባልደራስ ከኦነግ ሸኔ ጋር አንድ ናቸው የሚል ሽብር ጀምረዋል፡፡ ሲጀምር ኦነግ ሸኔ የሚባል ነገር የለም፡፡ የኦሮሞ ብልጽግና በገንዘብ እየረዳው ከአዲስ አበባ መመሪያ እየተሰጠው ንጹሐንን እያረደ ያለ የኦነግ ገዳይ እንጂ፡፡ ኦነግ ሸኔ በሚል ሊያደናግሩ ይሞክራሉ፡፡ የሆነ ሆኖ ኦነግ ሸኔም ይባል ሌላ ወዳጅነቱና ቅርበቱ ለኦሮሞ ብልጽግና እንጂ ለአብንና ባልደራስ አደለም፡፡ አብይ አህመድ በታዬ ደንደአ በኩል ሆን ብሎ ሴራ ይነዛል ከዛ በሰላማዊ ሰልፍና በሚዲያ በይፋ ሽብር ይጀምራል፡፡ ይህ አደገኛ ነው፡፡ አዝናለሁ፡፡ ወያኔም እንዲሁ ነው የጠፋቸው፡፡
በአጠቃላይ የአብይ አህመድ ነገር ይገርማል፡፡ ምኞቱና ሕልሙ አስቂኝ ነው፡፡ እውነተኛውን ምኞች ማለቴ እንጂ ኢትዮጵያ እያለ የሚናገራትን አደለም፡፡ ሌላ ቀርቶ እራሱን ለመጠበቅ ያዘጋጀውን ልዩ ኩማንዶ እንኳን ሲሰይም ስሙን የወረሰው ከቀድሞው የኢራቅ አምባ-ገንን መሪ ሳዳም ሁሴን ነው፡፡ የሪፐብሊካን ጋርድ በሚል የሚታወቅ ሰራዊት ያለው እሱ ነበር፡፡ ለማንኛውም ሴራው የት እንደሚያደርስ እንጃ፡፡ ከሁሉም የከፋው ሐይማኖታዊ ሴራ ግን የሚያመጣውም ውድቀት ከወያኔም በከፋ ሊሆን እንደሚችል ልብ ቢባል፡፡ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ወይብላ ማሪያም የሆነውን አይተናል፡፡ ሆኖም በዚህ ፈርቶ ከሐይማኖቱና ከሚያምንበት ወደኋላ የሚል ከመሰላቸው አዝናለሁ፡፡ ለማንኛውም ነገሮችን ከበጎ ይልቅ በሴራና ቁማር የመረጡት ከወያኔ የከፋ እጣ ፈንታ ሊመጣባቸው እንደሚችል ዛሬም እንኳን ልብ ቢገዙ እላለሁ፡፡
ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!