ማይካድራ 80 – አሁንገና ዓለማየሁ 

maykadra

ፍታት፣ ሣልስት፣ ተዝካር ላልተደረገላቸው መንግሥት ይቅርና ቤተክርስትያን የሐዘን ቀን ላላወጀችላቸው፣ በሕወሃት ለተጨፈጨፉ የማይካድራ ንጹሐን የሰማንያ ቀን መታሰቢያ እንጉርጉሮ

ማይካድራ ሰማንያ 

ሽንፈትእርግጥ ሲሆን ለመሰናበቻ

በፋስበመጥረቢያ ሕይወት መጫወቻ

በሆነችበትቀን ያ ደሃ አማራ

ደሙያጥለቀለቀሽ ያቀላሽ ማይካድራ

ምንአሉሽ ነፍሳቱ ተለቃቅሞ ገላ

ጉድጓድውስጥ በዶዘር የገቡት በጅምላ?

የጀግንነትወሬ የጦር ሜዳ ውሎ

መቼምሰው አይኖረው ባዶ እጁን ተገኝቶ ሲታረድ ቁጭ ብሎ

ጠላትያላለው ሰው በገጀራ ሲያርደው ሲጨፋው በአሎሎ።

ታድያምን አወሩሽ ስለ አሟሟታቸው፤

ምንስተናገሩ ስለ እምነታቸው?

እንዲህነበር አሉሽ የቀብራቸው ደንቡ፤

እድሩእንዴት ነበር ግንብ ሰፈር ግንቡ?

እኩሉበጅምላ እጉድጓድ ሲገቡ

እኩሉንሊበላ አሞራና ጅቡ?

ጭካኔያረገው የአስከሬን ክምር

ምንያንጽ ነበረ የሕልማቸው ድምር?

ይኸውበግርግር ሰማንያ ቀን ሄደ።

ተረፈተብሎስ እየተራመደ

ስንቱበቁም ሞተ ስንቱ ስው አበደ!

የስንትእናት ማሕፀን በዳግም ምጥ ራደ!

ስንቱአባት ተመኘ ቀድሞም ባልወለደ!

በኢትዮጵያእውነት እንዲሆን ማይካድራ

በጠላትመዲና ስንት ሤራ ተሠራ?

የተረጨውአሲድ ምንጩ የት ነበረ ?

በየትኛውመርከብ ባሕር ተሻገረ?

ኧረእናንተ ሆዬ!

ከጨለማባሕር ጨለማ ይፈልቃል

ጀንበርበወጣበት ጨረቃ ይጠልቃል?

እንዲህእየሆኑ እንዴት ይዘለቃል?

የአንድእናት ልጆች አልቃሽና አስለቃሽ?

ምነውእናት ዓለም አምላክ ቢልሽ በቃሽ!

ጥር 23፣ 2013

ፍትሕና መታሰቢያ በጭካኔ ለተጨፈጨፉ ሰላማዊ ንጹሐን! 

 

 

በአላህ ቀጠሮ 

የማይካድራውገዳይ

ዛሬሱዳን መሬት

እርቦመቁነን ታዳይ

የገጀራውጌታ

የሳንጃውባለቤት

አንተምእንደ ምስኪን

ስትልአቤት አቤት

እንደተፈናቃይ

ተሰደህጎረቤት

በገመድሰው አንቀህ

በደምተጨማልቀህ

በእጅህንጹሕ ታርዶ

እጅህንአውሰህ ለሲዖሉ ዘንዶ

ዛሬስደተኛ

አንተምማዶ ዘልቀህ

በዓይንህመቅበዝበዝ

በፍርሃትህታውቀህ

ባትመጣምተይዘህ

በዘበኛታንቀህ

በራስህተጉዘህ

ትከፈላታለህ

ነጥብእስከ ዜሮ

የማይካድራንብድር

በአላህቀጠሮ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.