ንጉሱ ጥሩንባው ልጆቹ የት ናቸው? – በላይነህ አባተ

335FFFG 300x109 ንጉሱ ጥሩንባው ልጆቹ የት ናቸው?   በላይነህ አባተልክ እንደልማድህ ሕዝብን ታታለልከው፣
ልጆቹ ተገኙ ብለህ ተዋሸኸው፣
ድፍን ዓመት አልፎ መጣ ሁለተኛው፣
በላ ንገረና ንጉሱ ጥሩንባው፣
እኛ አንረሳቸውም ልጆቹ የት ናችው?

የታፈንከው አንተ ሆነህ ብንረሳህ፣
ተገኝቷልም እያልን ውሸት ብነፋብህ፣
ስቃይ ቦታ ሆነህ ምን ያስብ ህሊናህ?

አድገው ያልጨረሱ ልጆች አስፈጅተህ፣
ወላጆቻቸውን ደም እንባ እያስለቀስክ፣
እንዴት አድርጎ ነው እንቅልፍ የሚወስድህ?

በውሸት ኩሬ ውስጥ ህወሀት የጠመቀው፣
ተዋርዶ ማዋረድ ዛሬም ያልሰለቸው፣
ሕዝብ እያሳረደ ሙዙን የሚገምጠው፣
ብአዴንን ሰይጣን በምን ሌሊት ሰራው?

ባንዳው ብአዴንን ትውልዱን ስንቆጥረው፣
እጅግ የሚያሳፍር የሚያሸማቅቅ ነው፡፡

ፈረንጅና አረቡ ሻብያን ሲያበጀው፣
ሻቢያ በስሪያ ህወሀትን ደቀለው፡፡

ዲቃላው ህወሀትን አረቡ ሲያንባባው፣
ፈረንጁም ገፋፍቶ ፈንግል ደቅል ሲለው፣
ኢህዴን ቡችላን በሶስት ወር ደቀለው፡፡

ቡችላው ኢህዴን ሙሉ ውሻ ሲሆን፣
ተባለና አረፈው የ”አማራው!” ብአዴን፡፡

ውሻው ብአዴንም ጉርሻን እየላሰ፣
ሰላሳ ዓመት ሙሉ አማራ አስጨረሰ፡፡

አማራ አስጨፍጫፊው እርጉሙ ብአዴን፣
ንጉሱ የሚባል ጥሩንባ ሰራልን፡፡

ጥሩንባው ንጉሱ በረከት ሲነፋው፣
ሲወሸክት ኖረ ዛር እንደሚያስጎራው፡፡

ጥሩንባው ንጉሱ ጌታውን ቀይሮ፣
ጨጨብሳ እየዛቀ እየላሰ ገንፎ፣
ሲነፋ ይውላል በአብዮት ጉረሮ፡፡

ጥሩንባው ንጉሱ ህሊና የሌለው፣
የልጃገረዶች ደም ምላሱን ሳይመረው፣
አብዮት ሲያጎርሰው ገንፎ የሚውጥ ነው፡፡

ጥሩንባው ንጉሱ ማረግ ክብር የሌለው፣
ጆሮ ጠቢ አብዮት በላንቃው ሲነፋው፣
“ልጆች ተለቀዋል!” ብሎ የዋሸ ነው፡፡

ጥሩንባው ንጉሱ ሁሌ የሚነፋው፣
ለውሻው ብአዴን አንዱ ምልክት ነው፡፡

አማራ ቆም ብለህ በአጽንኦት አስበው፣
ውሻ ተከትለህ ገደል መግባትህ ነው፡፡

ተብአዴን አመራር ሰው ይወጣል ብለህ፣
የምትከራከር ውሻ አፍቃሪ ሆነህ፣
ያስጨፈጨፉት ነፍስ ሰማይ ይፋረድህ!

ብአዴን አመራር ንጉሱ ጥሩንባው፣
አንባሻ ሲጠግቡ ጨጨብሳ ተርበው፣
አማራ ሆይ! ስማ እያስጨረሱህ ነው፡፡

ለውሾችም ሆነ ለጉርሻ ጣያቸው፣
አማራን ተመንከስ የሚያስታግሳቸው፤
ኢትዮጵያን የሰራት ጎበዝ አለቃ ነው፡፡

እስቲ መልስልኝ አማራ ቀብራራው፣
ብአዴን አመራር ንጉሱ ጥሩንባው፣
የሚያስጨፈጭፉህ ስንት እስተምትቀር ነው?

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
ጥር ሁለት ሺ አስራ ሶስት ዓ.ም.

አጋሰስ https://www.youtube.com/watch?v=bbiw49XDFoA

2 Comments

  1. አረ ነዉር ነዉ ቤተሰብ አያጣም ጥሩምባዉ ከምትለዉ ቱሪናፋ ብትለዉ ይሻል ነበር

  2. bbeyu

    ምኑ ነው ነውር? ዘላለም እንደ ጥሩንባ ማገልገል ወይስ ጥሩንባን ጥሩንባ ብሎ በስሙ መጥራት?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.