በመጀመሪያ ቀዳሚው ምክር ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዝብ በአጭሩ የሚከተለው ነው፡፡ከታች የተጠቀሱትን ሶስት ሀቆች ከመሆን ልታስቀሯቸው ስለማትችሉ ጊዜው ቢዘገይም ልትታረሙ ከፈለጋችሁ አሁኑኑ ታረሙ፡፡ የማትታረሙም ከሆነ ውጤቱን ጠብቃችሁ አግኙት፡፡ ሀቁ ግን ከመሆን አይቀርም፡፡
ሀቅ ቁጥር አንድ፡፤
በኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ አልቆለታል፡፤ዱሮ በትግራይ ቦታ አለኝ ይል የነበረው አሁን ላይ ቀን ከጎደለባቸው ጥቅመኞችና የተታለሉ ጥቂቶች በስተቀር በሰርቶ አደሩ ሰፊው የትግራይ ህዝብ ዘንድ ወያኔ ቦታ የለውም፡፤ ምክንያቱም ዱሮ በማታለል፡ በጉልበት፡ በማስፈራራት በንክኪና ይበልጡኑም ከአድዋ ተወላጅነት ጋር በነበረ ቁርኝት መሰረት ነበር ነገሮች ሁሉ ይቃኙና ይቀመሩ የነበረው፡፡ ጦርነቱ ወያኔ የሰሜኑን ጦር በዘር ለይቶ በአሰቃቂ ሁኔታ በማረዱ መነሾነት የተጀመረ ቢሆንም ጦርነት ጦርነት ነውና ለማንም አይበጅም፡፡ ምን ይሆናል ያ የወያኔ ሰቅጣጭ ጭፍጨፋ ያስነሳው ቁጭት ይቅር አያሰኝም፡፡ፍርድ በመሬትም በሰማይም አይቀርምና አጥፊዎች ፍርዳቸውን ማግኘት አለባቸው፡፡ ስለሆነም አሁን ላይ ጉዳዮች በሙሉ ለመላው የክልሉ ህዝብ ግልጽ ሆነውለታል፡፡ለአድዋ ምርጦች ብቻ ሳይሆን የመላው ትግራይ ተውላጆች ጥቅም የሚከበርባት ትግራይ ገሀድ እየሆነች እየመጣችም ነው፡፡የሚገርሙት በማይመለከታቸው ገብተው አፋቸውን የሚከፍቱት መራራ ጉዲና፡ ዳውድ እብሳና በቀለ ገርባ ናቸው፡፤ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወያኔን እንኩዋን ሊፈልገው ቀርቶ ወያኔ እንደሰው እንቅፋት መትቶት ቢወድቅ ‘እሰይ” “ደግ አደረገህ” ”ይድፋህ” “ምን ነው በዛው በቀረህ” ነው የሚለው እንጅ የሚያዝንለት የለም፡፤ ይህ ሀቅ ነው፡፤
ሀቅ ቁጥር ሁለት፦
ከኢትዮጵያ ውጭ በትግራይ ህዝብ ስም ስለወያኔ የሚራገበው ኡኡታ
በውጭ አገር የሚገኙ የወያኔ ርዝራዦችና ጥቅሞቻቸው የተቋረጠባቸው ወያኔ ከዘረፈው ገንዘብ ይከፍላቸው የነበሩ ፈረንጆች እንደዚሁም በርዝራዦቹ የተጭበረበሩ ጥቂቶች እዬዬውን ቀጥለውበታል፡፤ ሄዶ መዋጋት የጀግንነት ነው፡፤ እዚህ ቁጭ ብሎ እዬዬ ምንድን ነው?? ለኢትዮጵያ ብድር እንዳይሰጣት ለማስከልከል??፤ እርዳታ እንዳታገኝ ለማስደረግ?? ስሟን በየሜድያው ለማስጠልሸት?? ከዚህ ያለፈ ለሽህ አመታት ነጻነትዋን አስከብራና ወራሪዎችን አፈር ዲሜ አብልታ የኖረችውን አገራችንን እምዬ ኢትዮጵያን በውስጧ የተበላሸ የፖለቲካ አመራር ቢኖርም ስለራሷ ጉዳይ ራሷ የምትወስደውን ማንኛውንም እርምጃ ማስቆም የሚችል የውጭ ሀይል የለም፡፡ የአለም ምናምን ማህበር ….አሜሪካ …. አልሲሲ… ሱዳን ….ወዘተ እናንተው የፈለጋችሁትን ሙሉበት፡፡ እንኳን እንደ አገር ቀርቶ እንደ ስው እኛ ኢትዮጵያዊያን ለፈረንጅ ስብእናችንን አዋርዶንና ማንነታችንን ሸጠን አናውቅም፡፤ ከባንዳዎቹ በስተቀር ማለቴ ነው፡፡ እነዚሁም ባንዳዎች ከየትኛው የአገሪቱ ክፍል እንደሆኑ ታሪክን ማገላበጥ ብቻ ይበቃል፡፡እኛ ኩራት እራት ነው ሲባል እየሰማን ነው ያደግን ኩሩ ኢትዮጵያዊያን ነን፡፡ ህዝቧ ወቅቶች የሚፈጥሯቸውን የውስጥ ችግሮቹንና የተበላሹ አመራሮችን ለዘመናት ባካበተው ጥበብና ጀግንነት ራሱ ያስተካክላቸዋል እንጅ የዘመናችን ጉዶች የሆኑት የወያኔ ባንዳዎችና ተረኛ ኦሮሙማወች አሁን እንደሚያደርጉት ከአገሪቱ የውጭ ጠላቶች ጋር ግንባር ፈጥሮ አገሩን ለውርደት የሚሰጥ ኢትዮጵያዊ የለም፡፡ አልተፈጠረምም፡፡ የአገሪቱም የአያሌ ዘመናት አንጸባራቂ ታሪኳ የሚመሰክረው ይህንኑ እውነታ ነው፡፤
ሀቅ ቁጥር ሶስት፦
ከዚህ ሁሉ ጉድ የማይማረው የተረኛው ኦሮሙማ እጣ ፈንታ
በአገራችን እንደዋዛ ከሚነገሩ ጊዜ የማይሽራቸው አያሌ ምክሮች ውስጥ ላለንበት ሁኔታ የሚሳማሙትን ሁለቱን ብቻ ላንሳ፡፡ አንደኛው <ጎረበትህ ሲታማ ለእኔ ብለህ ስማ> የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ <ነግ በኔ> የሚባለው ነው፡፡ ሲጀመር አሁን ስልጣን ላይ ያለው ኦሮሙማ ከወያኔ የጨነገፈ የውርጃ ልጅ መሆኑን መርሳት የለብንም፡፡ ውርስ ነውና ብዙ ባህሪያት ያመሳስሏቸዋል፡ሆኖም ግን የህዝብ ሰላም ማጣትንና የመኖር ዋስትና አለማግኘትን የሚጠቁሙ መለኪያዎች እንደሚያሳዩት ወያኔ 27 አመት የወሰደበትን የማጭበርበር፡ የመዋሸት፡የሌብነት፡የዘረኝነት፡ የማፈናቀልና የጭፍጨፋ ስራዎች ኦሮሙማ እጅግ በከፋና በከረፋ ደረጃ በሶስት አመት ጊዜ ውስጥ በሚያስደንቅ ፍጥነት በብዙ እጥፍ አልፎት ሄዷል፡፡ ይህ የህዝብ የኑሮ ጉስቁልና፡ የነገን ተስፋ ማጣትና በሰላም ውሎ ለመግባት አለመቻልን ያባባሰው የኬኛ ፖለቲካ ህዝቡን መድረሻ አሳጥቶታል፡፡ አገሪቱ እንደዚህ በታሪክ ተዋርዳ አታውቅም፡፤ ህዝቡም እንደዚህ በዘር ተናክሶና በማንነት ተለያይቶ አያውቅም፡፤ በተለዬ ሁኔታም በአማራው ህብረተሰብ ላይ በየቦታው የሚፈጸመው አሰቃቂ ጭፍጨፋና ዘር ማጥፋት መንግስት መር ነው በሚባል ደረጃ እየተሰራበት ሲሆን ክስተቱም እየተባባሰበት እየሄደ ነው፡፤ ይህን በተንኮል የተቀነባበረ ነገር ግን መቼም ቢሆን ግቡን ሊመታ የማይችል ዘረኝነትን መሰረት ያደረገ የኬኛ ፖለቲካ በተደራጀ የኬኛዎች ስውር ካውንስል (ኮሚቴ) በመታገዝ በረቀቀ ስልት እየመራው ያለው የአገሪቱ መንግስት መሪ ነኝ የሚለው የኦሮሙማው ቁንጮ አብይ አህመድ ነው፡፤ በነገራችን ላይ ጩልሌው አብይ አህመድ ይህንኑ አሰራር በአፉ እያወገዘ በተግባር ግን እያስኬደው ያለበት ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለህዝቡ ግልጽ እየሆነለት መጥቷል፡፡ህዝቡ መሬት ላይ ያሉትን አሳዛኝ ሁኔትዎችና በተደጋጋሚም ከመሻሻል ይልቅ እየባሰባቸው መሄዱን እያዬ ከእንግድህ ወዲያ እንደ እስካህኑ በአብይ አህመድ ቅቤ ምላስ የሚታለል ኢትዮጵያዊ አይኖርም፡፡ ከሆዳሞችና ከራሳቸው ተረኞቹ በስተቀር ማለቴ ነው፡፡ኦሮሙማ የህዝብ ብሶትና ቁጣ በወያኔ ላይ ያስከተለውን እያዬ ትምህርት አልወሰደም፡ ነግ በኔ ብሎም ግፍ መስራት አላቆመም፡፡ ስለሆነም አጭሩ መፍትሄ በብልጽግና ስም ተለጣፊዎችን በስሩ ሰብስቦ እየጋለበ ያለውን ኦሮሙማን በጋራ ታግሎ ማስወገድና እንደ ህወሀት ታሪክ ማድረግ ብቻ ነው፡፤ ይህንን በማድረግ ነው ህዝቡ ከጥፋት አገሪቱም ከመፍረስ ሊድኑ የሚችሉት፡፡ ከዚህ ውጭ ያለው ምርጫ በኦሮሙማ እየተታለሉ ቀስ በቀስና ተራ በተራ ማለቅ ብቻ ነው፡፤ አገራችንንም አጥተን ከሞትና ጭፍጨፋ የምንተርፈውም ብንሆን ተበትነን እንቀራለን፡፡ስለዚህ ትግሉ እጅግ ከባድ እጅግ መራራና እጅግ ውስብስብ ቢሆንም ተባብረን እንነሳ፡፡እንወጣዋለን፡፡ ምክንያቱም እውነትና ሀቅ ከእኛ ጋር ናትና፡፤ ነግ በኔን የማያውቀው ኦሮሙማ የሰራብን ግፍ ጽዋው ሞልቶ ፈሷልና፡፤ ስለሆነም ኦሮሙማን ነቅሎ ለመጣል ዛሬዉኑ በጋራ እንነሳ !!