እነስብሀት ነጋ ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል

የቀድሞው የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ የቄስ ልብስ ለብሰው መታወቂያቸውን ቀይረው ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን ፖሊስ ለችሎት ገለጸ።

በሀገሪቱ ሁከት በመቀስቀስ ሰዎች እንዲገደሉ እና እንዲፈናቀሉ ከማድረግ ጀምሮ የነዳጅ ዲፖ ዘረፋ መፈጸማቸውን የሚያመላክት ማስረጃ መሰብሰቡን መርማሪ ፖሊስ ለችሎት ገልጿል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መርመሪ ቡድን የቀድሞው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ከንግድ ባንክ በርካታ ገንዘቦችን እና ወርቆችን አውጥተው ወደ ደደቢት ማይክሮ ፋይናነስ ተቋም በማስገባት ከተጠርጣሪ ቤተሰቦች ጀምሮ እስከ በየበረሃው ለነበሩ አመራሮች ሲያከፋፈሉ እንደነበር ማስረጃ መሰብሰቡን ጠቅሷል።

መርማሪ ቡድኑ ይህን የገለጸው ዛሬ በእነስብሀት ነጋ ፤ አባይ ወልዱ እና ወ/ሮ ኬሪያ  ኢብራሂም ስም በተደራጀ ሶስት መዝገብ የተካተቱ 21 ተጠርጣሪዎችን ፍረድቤት ባቀረበበት ወቅት ነው።

በእነ ስብሀት ነጋ፤ አባይ ወልዱ እና ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ስም የተዘጋጁ ሶስት መዝገቦች የተካተቱ አጠቃላይ 21 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ለሁለተኛ ጊዜ በፍርድ ቤት ታይቷል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በቀዳሚነት በስብሀት ነጋ መዝገብ የቀረቡ አጠቃላይ 9 ተጠርጣሪዎችን በቀዳሚነት ተመልክቷል።

በዚህ መዝገብ አንደኛ  ስብሀት ነጋ፤ አምባሳደር አባዲ ዘሙ፤ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ፤ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋን ጨምሮ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ናቸው ጉዳያቸው በቀዳሚነት መዝገብ የታየው።

በሁለተኛ መዝገብ ደግሞ አባይ ወልዱ ፤ዶክተር አብርሃም ተከስተ፤ ዶክተር እረዳይ በርሄን ጨምሮ የ9 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ታይቷል።

በሶስተኛ መዝገብ በችሎቱ ጉዳያቸው የታየው የቀድሞው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚያብሔርንም ጉዳይን ችሎቱ ተመልክታል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቡድን በቀዳሚነት መዝገብ 1ኛ  ስብሀት ነጋ፤  ለፍርድ ቤቱ ባለፈው በተሰጠው የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ  ያከናወነውን የምርመራ ስራዎች አብራርቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እስክንድር፣ ጃዋር፣ በቀለ ገርባና ስብሃት ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ የነበሩ የፖለቲካ መሪዎች በምህረት ተፈቱ

በዚህም  የተጠርጣሪዎችን  የወንጀል ተሳትፎ በምርመራ የመለየት ስራ ማከናወኑን ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ከመንግስት መዋቅር ውጪ ተደራጀተው በቁጥጥር ስር ካልዋሉ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን በተለያዩ ጊዜያት ሁከትና ገጭት እንዲነሳ ሲያደርጉ አንደነበር ማስረጃ መሰብሰቡን አብራርቷል።

ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በሃገሪቱ የብሔር እና የሃይማኖት ግጭት እንዲነሳ የተለያዩ የወንጀል ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎችን  ከተለያዩ ክልሎች በመመልመል ወደትግራይ በመላክ አበል በመክፈል ንጹሃን ዜጎች እንዲገደሉና ከቄያቸው እንዲፈናቀሉ ሲያደረጉ እንደነበር የሚገልጽ ማሰረጃ መሰብሰቡን ለችሎቱ አብራርቷል።

በተለይ 3ኛ፣ 7ኛ፣ 8ኛ እና  9ኛ ተጠርጣሪዎች  የህዋሀት ከፍተኛ አመራሮች ሲሆኑ እነዚህ ተጠርጣሪዎቹ ካልተያዙ ግብረአበሮቻቸው ጋር በመሆን በተለያዩ ዞኖች በመዘዋወር ሌሎች ወጣቶች ለጦርነት እንዲነሳሱ ሲያሰተባብሩና ሲቀሰቅሱ እንደነበረም ማሰረጃ መሰብሰቡንም መርማሪው አክሏል።

ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የሰሜን ዕዝ ጦር እንዲመታ እና ግጭት እንዲፈጠር እንዲሁም የጦር መሳሪያ አንዲዘረፍ በማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ ጦርነት አስነስተው ሲመሩ እንደነበር የሚገልጽ ማስረጃ መሰብሰቡን አመላክቷል።

በተጨማሪም በዚህም ምርመራው  የቀድሞ የአዲስ አባባ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ እና የትግራይ ክልል ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ   የነዳጅ ዲፖን ሲያዘርፉ እንዲሁም ምሽግ የሚቆፍሩ መኪኖችን ሲያዘጋጁና ሲያስቆፍሩ አንደነበር የሚያሳይ ማስረጃ መሰብሰቡን ጠቅሶ የነዳጁ መጠኑን እያጣራ መሆኑን ገልጿል።

በስዩም መስፍን የሚመራ ቡድን ተቋቁሞ ለጥፋት ተልዕኮ ሲሰሩ እንደነበር የሚያሳይ ማስረጃ ማሰባሰቡንም የምርመራ ቡድን ለችሎቱ አስረድቷል፡፡

ሌሎችም ማስረጃዎችን መሰብሰቡን የገለጸው የምርመራ ቡድኑ በሰው ምስክር ደረጃ 15 ምሰክር ቃል መቀበሉንም ለችሎቱ አብራርቷል፡፡

በክልሉ የፈጠረውን ችግር ተከትሎ ሃገሪቱ ለተለያዩ ሀገራት ስታቀረብ የነበረውን የሃይል ሽያጭ አቅርቦት መጠን እያጣራ መሆኑንም አመላክታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰማያዊ ፓርቲ – እስርና አፈና የምርጫውን ችግር ሊሸፍን አይችልም!!

የደረሰውን የመሰረተ ልማት ውድመት ከኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት እና ከሌሎች ተቋማት የደረሰው ውድመት በጽሁፍ ምላሽ እንዲሰጠው ለየተቋማቱ መላኩን የምርመራ ቡድኑ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡

ጉዳዩን የሚያጣራ ተጨማሪ ቡድን ወደትግራይ ክልል መላኩን እና ሌሎች የሰው ምስክሮችን ቃል ለመቀበል እና የተጠርጣሪዎችን የስልክ ልውውጥ ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ምላሽ ለማግኘት ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲሰጠውም ጠይቋል፡፡

በሁለተኛ መዝገብ በተካተቱት የቀድሞ የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አባይ ወልዱ ፤ዶክተር አብርሃም ተከስተ፤ ዶክተር እረዳይ በርሄን ጨምሮ 9 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ  በተሰጠው 14 ቀን ወስጥ የሰራወን በርከታ ምረመራ አብራርታል።

የወንጀል ተሳትፎ ነበራቸው ሲል የሰበሰበውን ማሰረጃ ከምርመራ መዝገቡ ጋር ማያየዙን ጠቅሷል።

ከዚህ ውስጥም በተለይም የቀድሞ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ከንግድ ባንክ በርካታ ገንዘቦችን እና ወርቆችን አውጥተው ወደ ደደቢት ማይክሮ ፋይናነስ ተቋም  በማስገባት ከተጠርጣሪ ቤተሰቦች ጀምሮ እስከ በየበረሃው ለነበሩ አመራሮች ሲያከፋፈሉ እንደነበር ማስረጃ መሰብሰቡን ጠቅሷል።

እንዲሁም ለምሽግ ቁፋሮ መኪኖቸን ሲያዘጋጁ አንደነበር ፖሊስ በምርመራ ማስረጃ መሰብሰቡን ጠቅሷል።

በሶስተኛ መዝገብ በችሎቱ ጉዳያቸው የታየው የቀድሞው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ የወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚያብሔርንም ጉዳይን ችሎቱ ተመልክታል።

እነዚህ ተጠርጠሪዎች በዞን የጦርነቱ ቅስቀሳ በማድረግ በሃሳብና በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ መጠርጠራቸውን ተከትሎ ማስረጃ መሰብሰቡን ጠቅሷል፡፡

በዚህ መልኩ ተጠርጣሪዎቹ ማንነታቸወን ቀይረው አለባበሳቸወን ቀይረው ተደብቀው ሲቀሳቀሱ ነበር ብሏል ፖሊስ ለችሎቱ ሲያብራራ፡፡

የተጠርጣሪ ጠበቆች ማንነታቸውን ደብቀው ሲርመሰመሱ ነበር ማለቱ አግባበነት የለውም ብሎ ላቀረቡት መቃወሚያ መርመራ ፖሊስ ምላሽ ሰጥቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሮብአም ጥፋት በአብይ አህመድ አይደገም ታላቆች ገስጹ

በዚህም ምላሹ  የቀድሞ የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ የቄስ ልብስ ለብሰው መታወቂያቸውን ቀይረው ከነ መታወቂያቸው መያዛቸውን ፖሊስ ለችሎት አብራርቷል።

የተጠርጣሪ ጠበቃም ከባድ መሳሪያ ሲተኮስባቸው ቤታቸው ቁጭ እንዲሉ ነው ወይ የሚፈለገው ሲል መደበቃቸው ተገቢነት እንዳለው ሲከራከር ተደምጧል።

በዚህ መልኩ ጠበቆቻቸው ከዶ/ር ሰለሞን እና ከዶ/ር አብርሃም ውጪ ባሉት ተጠርጣሪዎች ላይ  የያንዳንዳቸው የወንጀል ተሳትፏቸው በግልጽ ተለይቶ አልቀረበም የሚል ሀሳብ አቅርበዋል።

ባለፈው ካቀረበው የምርመራ ውጤት የተለየ ነገር ይዞ አልመጣም ፤ የተጠቀሱትም በአገሪቱ በስፋት ሲነገሩ የነበሩ የፖለቲካ ይዘቶች ናቸው በዚህ መልኩ በዚህ ችሎት ሊገለጽ አይገባም ፤ እኛም መከላከል አያስችለንም ስለዚህ በዚህ ችሎት የፖለቲካ ጉዳዮች መቅረብ የለባቸወም ሲሉ ተቃውሞ አሰምተዋል።

ፍርድ ቤቱም እናንተም ጠበቆቸም  ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ሃሳቦች እያነሳቸሁ ነው በሁለታችሁም በኩል ሊነሱ አይገባም ሲል አጽንኦት ሰጥቷል።

ተጠርጣሪዎቹም ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ምስላቸው  መታየቱ ተገቢነት የለውም፤ በመገናኛ በዙሃን ሚዛናዊ ዘገባ ሊቀርብ ይገባል የሚሉ አቤቱታም አሰምተዋል።

በተጨማሪም ወ/ሮ ኬሪያና ወ/ሮ ሙሉ ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ ከብዙ ቀናቶች በኋላ ፍርድቤት መቅረባቸው ተገቢ አደለም የሚሉ መቃወሚያዎች እና የፖሊስን ምላሽ አጠቃላይ የግራ ክርክርሩን  ያደመጠው ችሎቱ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ለረጅም ጊዜ ቆይተዋል ለተባለው በሰጠው ገለጻ በመከላከያና በፌዴራል እየተያዙ የነበሩ በመሆኑ  የሌሎችም ተጠርጣሪዎች እስኪለዩ  መቆየታቸውን ከግምት ወስጥ መግባቱን ጠቅሷል።

ይሀን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የሁለቱ ተጠርጣሪዎች ምርመራ በተፋጠነ መልኩ እንዲከናወን አዟል።

በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ  14 የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ውጤቱን ለመጠባበቅ ለየካቲት 5 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

በታሪክ አዱኛ

.fanabc

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share