የኢትዮጵያን ሕዝብ አህዛብ የሚለው ሕገ-መንግስት ሳይቀየር ወደ ምርጫ መሄድና አደጋው – ሰርፀ ደስታ

January 28, 2021
13 mins read

ዛሬ በሥራ ላይ ያለው ወያኔና-ኦነግ የሠሩት ሕገ-መንግስትና ሥርዓት በግልጽ የኢትዮጵያውያን ጠላት እንደሆነና በግልጽም ዜጎች እየታረዱበት እየታየ አሁንም ሕገ-መንግስቱ አቻ የማይገኝለት እያሉ በመቃብራችን ላይ እንጂ አይቀየርብንም በሚል በዜጎች ደም ለመቆመር የቆረጡ ናቸው አገርን እንመራለን የሚሉት፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመት አንድም የሕግና የፖሊሲ ማሻሻያ ሳይደረግ ይልቁንም ወያኔ የሰራችውን ሥርዓት በደንብ በኦሮሞነት በመተካት እንዲቀጥል ከበፊቱም በከፋ ሁኔታ እጅግ አረመኔያዊ ክስተቶችን ተመልክተናል፡፡ ይሄ ያየንው እውነት ነው እንጂ ምስክር ማስረጃ መረጃ እየተባለ የሚጠየቅበት አደለም፡፡  ይሄን ሥርዓት ለማስቀጠል አሁን ደግሞ አንድም ለምርጫ የሚጋብዙ ነገሮች በሌሉበት ሁኔታ ምርጫ ወደሚባል ሌላ ደረጃ ሴራና ቁማር ውስጥ የተገባው፡፡ አዝናለሁ፡፡

የዛሬውቹ የወያኔና-ኦነግ ሕገ-መንግስት በመቃብራችን ላይ እንጂ አይነካብንም የሚሉት ይህ የአገሪቱ ዋና የሕግ የተባለው ሰነድ ገና ሲጀምር የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደ ሕዝብ ሳይሆን አሕዛብ ብሎ ጠርቶ ነው፡፡ እኛ ይላል ለማደናገር፡፡ ሕዝብን አሕዛብ ብሎ እኛ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እኔን ባይገባኝም አውነቱ እንዲህ ነው፡፡ እኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች (አህዛብ) ሲል ይጀምራል፡፡ የኢትዮጵያ የተባለው ሕገ-መንግሰት ኢትዮጵያውያንን አሕዛብ ብሎ ከጀመረ በኋላ ምን ቀሪውን ዝርዝር መግባቱም ባላስፈለገ፡፡ በእርግጥም የዚህ ሰነድ አዘጋጆች ኢትዮጵያውያንን በውስጥ ዝርዝርና በተዋረድ በየክልሉ በተዘጋጁ ሕገ-መንግስት ተብዬዎች በግልጽ ሕዝብን ከፋፍሎ አንዱን ሕዝብ ሌላውን አህዛብ ሲደረግ እናነባለን፡፡ ይሄ ነበር ሕገ-መንግስት እየተባለ እየተፎከረለትና እንሞትለታለን የሚሉን፡፡ ከአማራ  ጋምቤላ ሕገ-መነግስት ሰነዶች በቀር ሁሉም ክልሎች ለሆነ ሕዝብ ከተሰጡ በኋላ ሌላውን ኢትዮጵያዊ አህዛብ (ሌሎች ወይም መብት የሌላቸው) በሚል ነው የሚገልጹት፡፡ ለመሆኑ ይሄ ባለበት ስለ ምርጫ ማውራት በራሱ ሕሊና ላለው ከዚህ በላይ ጸረ-ሕዝብነት አለ?

በመጽሐፍ ሕዝብና አህዛብ ሲባል እናነባለን፡፡ የሁለቱ ልዩነትም ግልጽ ይገባናል፡፡ ሕዝብ ማለት እኛ ሲሆን አህዛብ (ሕዝቦች) ማለት ሌሎች ማለት ነው፡፡ አህዛብ (ሕዝቦች) ከእኛ ጋር የማይመሳሰሉ ማለት ነው፡፡ ከዚህ ሲያልፍም ከእኛ ጋር በጋብቻም በምንም የማንገናኛቸው የሚያረክሱን ማለት ነው፡፡  እንግዲህ ይሄ ነው በኢትዮጵያ ሕግ-መንግስት ተብሎ የተቀመጠውና በእርግጥም በተግባርም እየተፈጸመ ያለው፡፡ ወደ ሌላው ዝርዝር ላለመግባት ነው፡፡ ይሄ ሕገ-መንግስት የተባለው ሰነድ የተሸከማቸው ብዙ ጸረ-ሕዝብ(ኢትዮጵያዊያን) ሴራዎች አሉ፡፡  አሁንም እላለሁ ከምርጫ በፊት ሕግና ሥርዓት ይስተካከል፡፡ ይሄን የምለው ምስክር እንዲሆን እንጂ ሕግና-ሥርዓትን ለማስተካከል ፈቃደኝነት እንደሌለ ግልጽ ነው፡፡ ምርጫ ማድረግና በምርጫ ሥም ሥልጣን ቀጥያለሁ ለማለት እንጂ፡፡ የዜጎች መታረድ የሚያሳስባቸው ሳይሆኑ በዜጎች መታረድ ሥልጣናቸውን ለማቆየት የሚያሴሩ ናቸውና ዛሬም አገር መሪ ነን የሚሉት፡፡

ሌላው የብርቱካን ሚደቅሳ ጉዳይ ብዙ እያስተዛዘበን መጠቷል፡፡ ሰው ለሕሊናው ታማኝ ከሆነ ትልቅ አቅም አለው፡፡ እግዚአብሔርም ይረዳዋል፡፡ የብርቱካን ሚደቅሳ ጉዳይ ገራሚ ሆኗል፡፡ በወያኔ ዘመን ለፍትህ ብዙ እንደሆነች ብናስታውስም ቀስ እያለ ኦሮሞ ነኝ ብሎ የሚያስበውን ሁሉ እየጠለፋ ያለው የኦሮሙማ መንፈስ እሷንም የጠለፋት ይመስላል፡፡  ደስ እያላቸው የዘሩት ጥላቻ፣ ዘረኝነትና የተጨቆነናል የበታችነት መንፈስ ዛሬ ሊድኑት በማይችሉት ሁኔታ እያሰቃያቸው እንዳሉ እናያለን፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ብልሁ፣ ቅኑና ታላቁ ሚኒሊክ የመራው የአደዋ ድል በዓል መተዋወቅ ጀምሯል፡፡ በዚህ የዓለምን ታሪክ (የዓለምን አስተሳሰብ ሁሉ) የቀየረ ክስተት ዛሬ ኦሮሞ ከሚባለው ማህበረሰብ የወጡ ጀግኖች አባቶቻችን የአንበሳውን ድርሻ ነበራቸው፡፡ ዛሬ ላይ እነዚህ ታላላቅ አባቶች በኦሮሞ ዘንድ እርም ተብለው ከአእምሮው መሰረዝ ብቻም ሳይሆን በተቃራኒው ዋና ጠላት ሆነው ተስለውለታል፡፡ በምትካቸው መነገጃ ያደረጉትን እንዲያመልክ ተደርጓል፡፡ ይገርማል! ዛሬ ብዙ ኦሮሞ ምልክት አልባ ሆኗል፡፡ ጠላቶቹ በሞሉት ትርክት ተሞልቶ ማንነቱን አጥቶ እየባዘነ ይገኛል፡፡ ይሄን ገና ብዙዎች የቀሩ ቀስ በቀስ እየተቀላቀሉት የምስላል፡፡ ብርቱካንም እየገባች ይመስላል፡፡ መረራ ለብዙ ዘመን ሲንከራተቱ ቆይተው በኋላ በስተርጅና ይሄው ዋናው ሆነው ቁጭ ብለዋል፡፡ ወይ ኦሮሞነት፡፡ አሁንም ለመረጃ ኦሮሞ የሚለው ቃል ከ70ዓመት በኋላ የመጣ ነው፡፡ ጅማ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ሐርር፣ ቦረና ኦሮሞ አልነበረም፡፡

ሰሞኑን አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባን ዘረፋና ሕገወጥነት በመናገሯ ትልቅ ዘፈን ተጀምሯል፡፡ ብቻ ነገሮችን ሳስብ ይገርመኛል፡፡ አዳነች ስለተናገረቸው ከሆነ አላውቅም፡፡ የችግሩን ጥልቀት እነ እስክንድር በግልጽ እየነገሩን ነበር፡፡ እነ እስክንድር ይሄን ዛሬ የሚወራውን መሆን የለበትም በማለታቸው ወንጀለኛ ሆነው እስር ቤት ናቸው፡፡ እነ አዳነች እንዲህ በሰሞንኛ ወሬ ብዙሀን እንዳለ ስለተረዱ እንዲህ ባለ ሰሞንኛ ወሬ አንድ ሰሞን ይሄን ከፊት ሆኖ የሚዘፍናን አክቲቪስትና ተከታዮቻች በደንብ እንዲያራግቡ በማድረግ ሕዝብን ማደንዘዝ እደሚቻለ ገብቷቸዋል፡፡ ከሳምንት በኋላ የለም፡፡ ይሄን ሁሉ ወንጀል የሠሩ ጭራሽ ድርብ ሹመት ተሹመው ይታያሉ፡፡ በቃ ይሄ ስልት ነው፡፡ አዝናለሁ፡፡ አብዛኛውም ሰው  የተናገረቸውን ያስተዋለም አይመስለኝም፡፡ ባለቤት የሌላቸው ሕንጻዎች ስትል እንኳን እንዴት ሊሆን ይችላል ብሎ መጠየቅ አልታሰበም፡፡ ጉድ ተዓምር እያሉ ከማድነቅ በቀር፡፡ አስተውሉ እያንዳንዷን  ወንጀል የሰራ ለማወቅ ከተፈለገ ምንም የሚያግድ ነገር የለም እንኳንስ ሕንጻን የሚያህል ነገር ሰርቶ እያከራየ ያለን ወንጀለኛ ይቅርና፡፡ ሴትዮዋ ስትናገር በጥንቃቄ ነው፡፡ ወንጀሎችንም በአለፉት ሶስት አመት ሳይሆን ከ97 ጀምሮ ነው ያለቸው፡፡ እርግጥ ነው ከዛም ጀምሮ ይኖራል፡፡ ሆኖም በግልጽ ነገሮች የለየለት ዝርፊያን ወሮበላነት የሆኑት በአለፉት ሶስት ዓመታት እንደሆነ ይሰመርበት፡፡

ሌላው አዳነች አቤቤ በከተማችን በዓይነታቸውም በይዘታቸውም ለየት ያሉ ፕሮጄክቶች እየተከናወኑ ነው ስትለን ሰምተናል፡፡ እንግዲህ እንዲህ የምተኩራራበት ፕሮጄክቶች ከተማው አቅዶ እየሰራው ያለ እንድም እንደሌለ አለማስተዋላችንን ስለተረዳች እንጂ እንደ እውነቱ በከተማው እየተሱረ ያሉ ፕሮጅክቶች የከተማው አደሉም፡፡ አብይ አህመድ የኢትዮጵያን ሕዝብ ገንዘብ አልአግባብ እየደፋባቸው ያሉ እንጂ፡፡ አብይ አህመድ የአገሪቱን አጠቃላይ ፕሮጅክቶች ወደ መናፈሻና ፓርክ ሥራ ቀይሮ ስለሰራ ብዙዎች ተዓምር እያሉ ሲያደንቁ ታዝበናል፡፡ እንግዲህ ይሄ ሁሉ እየሆነ ያለው ደግሞ በሚሊየን በሚቆጠር ቀሪ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምና ደህንነት ሳይቀር ለአደጋ በመተው እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ በጠ/ሚኒስቴር ደረጃ አንድ ከተማ ብቻ ለመስራት ከታሰበማ እንኳ መናፈሻ ስንት ማድረግ በተቻለ፡፡ እንግዲህ አዳነች የዘረዘረቻቸው ፕሮጄክቶች በሙሉ እየተሰሩ ያሉት በከተማዋ እቅድና ፕላን ሳይሆን ጠ/ሚኒስቴሩ ሥራውን ትቶ እያሰራቸው ያሉ ብዙ ገንዘብ እየፈሰሰባቸው ያሉ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ በዚህ ላይ የተፈጸመውን ዘረፋ ወረራና ከተማዋን ማውደም ታዘቡ፡፡  ይሄ ሁሉ ተደምሮ የሚያደርሰውን የገንዘብ ኪሳራ ብቻም ሳይሆን ይዞት የሚመጣውን ሌላ ችግር አስተውሉ፡፡ ብቻ ነገሮችን በቅንነትና በአግባቡ አአስቦ መሥራትን የሕዝብንም አመኔታ በማግኘት የበለጠ መሥራት ሲቻል በሴራና ቁማር በሚያሳዝን ሁኔታ ሁሉም ነገር መስመር ስቷል፡፡ ሰዎቹ እንዴት እንደሚያስቡ እንጃ፡፡ አሳዳጊያቸው ወያኔ የሆነውን እንኳን አይተው መማር የፈለጉም አይመሰልም፡፡ ጥሩ አደለም!

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን          ይጠብቅ!አሜን!

ሰርፀ ደስታ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በጥላቻ የወረወርከውን በፍቅር ብትፈልገውም ላታገኘው ትችላለህና … – ይነጋል በላቸው

Next Story

እነስብሀት ነጋ ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop