እልቂትና ተዝካር     (ከአሁንገና ዓለማየሁ) 

የጉዞ ፍታቱ ምንኛ ረዘመ

ስንቱ እያለቀ ነው ሰዉ እንደቆዘመ

እድርተኛው ሁሉ ስለሟች ሲያወራ

ስንቱ ተቀጠፈ በሌላኛው ሥፍራ።

የሕወሃት ቀብር ድንኳን ሳይነሳ

ስንቱ ባለእስትንፋስ ተደረገ ሬሳ።

የጉዞ ፍታቱን ያረጉት ልቃቂት

ሊደብቁ ነው ወይ የቋሚውን እልቂት?

ግርም ያረገኛል ሰሞነኛው ዜና

ድባጤ ላይ ታርዶ ሰማንያ ሰው ሞተ

በገበሬ ሞቶ ተገኘ ተከሥተ

ቡለን ላይ ሶስት መቶ ገበሬ ታረደ

ስዩም መስፍን ሸሸ ጉልበቱ እየራደ

መቶ ሰው ተገድሎ አደረ ማንዱራ

ሌላ አዲስ መቃብር ተገኘ ማይካድራ

ጉበቱ ተበላ ሕጻኑ ልጅ ታርዶ

አቦይ ስብሐት መጣ ከገደል ሰርጥ ወርዶ

ጉባ ላይ ሃምሳዎች በጉምዝ ታረዱ

ፓሊሶች እጅ ገባ ተማርኮ ዓባይ ወልዱ

የጉሙዝ ሚሊሻ ዚገም ተሻገረ

ጄኔራል እንትና እንትን ተናገረ

ሕወሃት ከሞተች ከወርም በኋላ

የሕዳሴው ግድብ በሰው ደም ሲሞላ

የሰው እልቂት ሳይሆን ዜናው ሌላ ሌላ።

(ጉባ፣ ድባጤ፣ ማንዱራ፣ ቡለን፣ ዚገም ከጳጉሜ እስከ ጥር ዘር ተኮር ጭፍጨፋ

 የተደረገባቸው የመተክል (ጎጃም) አካባቢዎች ናቸው)

 

አሻድሊ ታድለህ

ሁሉንም ያስቻለህ

ምን ዓይነት ጌታ አለህ?

አንገት በገጀራ ታስቀነጥሳለህ

ከሽሜ ጋር ሸገር ኬኩን ትቆርሳለህ

ጓሮህ ከዝናሽ ጋር ሪባን ትቆርጣለህ።

አሻድሊ ባለቀን!

ፈላጭ ቆራጭ ማለት ከዚህ በላይ የታል

ያሻውን በጅምላ መቃብር ይከታል

ሲሻው ሸገር መጥቶ ጣፋጭ ኬክ ይቆርሳል

ቡለን ተመልሶ የሰው ደም ያፈሳል

ሪባን ይቆርጥና

ከቀዳሚ እመቤት ፎቶ አብሮ ይነሳል።

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  የቱ ነው ኦሮሞ? - መስፍን አረጋ

1 Comment

  1. ለግሩም ድንቅ ግጥምዎት ማመስገኛ የጫርኩት ነው ከምስጋና ጋር ።

    አብይ የሚያረገው እነትም አብይ ነው
    የሚለውን ሳይሆን ማየት ተግባሩን ነው ።
    የብልጽግናን ትልም በዛፍ ሊያለምለም
    ያጠጣው ጀመረ የሰው ደም የሰው ደም ።
    ወይ ሞኙ ገበሬ ተካዩን ጨፍጭሮ ቺግኝ የሚተክል
    ሀገርን አውድሞ ሊያበለጽግ ክልል
    በውሸት ድሪቶ አታሎ ሕዝቡን
    ሌት ተቀን ይሰራል ሊያሰፍን ኦሮሙማን ።
    ንቃ ያገሬ ሰው ሞኝ አትሁን ተላላ
    ማጠፊያው እንዳያጥርህ የኋላ የኋላ ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share