አበሻ አያድናችሁ ..ፈረንጅ አያድናችሁ”.. ትርክት ወደ ሱዳን/ግብጽ…አያድናችሁ እዉነታ ሲቀየር ፦ ሀዱሽ መለሰ

አገራችን ኢትዮጵያ በዘመናት ብዙ ችግሮች አጋጥመዋት ችግሮቹን ሁሉ በአሸናፊነት ተወጥታ እዚህ ደርሳለች፡፡ወያኔ ለ27 አመታት የሰራው ግፍ ጽዋው ሞልቶ ሲፈስ በህዝብ ትግል ከማእከላዊ ስልጣን ተሽቀንጥሮ ሸፍጥንና መርዝን አርግዞ ወደተወለደበት ትግራይ በመሸሹ በዚያው ተገድቦ ሊቆይ ተገድዷል፡፡ ይከዚያም ወያኔ ድጋሜ ለጥፋት ተዘጋጅቶ በክልሉ የነበረውን የአገሪቱን ብሄራዊ ጦር አባላት በስሌት አድብቶ በሌሊት በማረድ ጦርነቱን ከፈተ፡፡መሳርያ ዘርፎ ወደመሀል አገር ለወረራም ተንቀሳቀሰ፡፤ነገር ግን ጀግናው የአማራ ፋኖና ልዩ ሀይል ከባድ መስዋትነትን ከፍሎ ግስጋሴውን በጧቱ ቀጭቶ ህልሙን አጨናገፈበት፡፡ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊትም እየተከታተለ ድባቅ መታው፡፤ታሪኩ በአጭሩ ይህ ነው፡፡ታዲያ ይህ ያልጣማቸው ሁሉ ከየአቅጣጫው እየጮሁ ነው፡፤ ለነገሩ በኢትዮጵያ ላይ የማይጮህ የውስጥም የውጭም ጥቅመኛ የለም፡፡ ለምሳሌ ጃዋር መሀመድ ችሎቱ እሱ ወደታሰረበት እንዲመጣለት ሲጠይቅ አስተውለናል፡፡ የአገሪቱ ኤታ ማዦር ጀኔራል ብርሀኑ ጁላም ያለቦታው ገብቶ በፖለቲካ ሲዘባርቅና ገናና የነበሩ የአገሪቱን ቀደምት መሪዎችን ሲያንቋሽሽ ታዝበናል፡፡ በውጭው አለምም የወያኔው ቴዎድሮስ አድሀኖም ቅርብ የሆነችውን የተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ኮሚሽነር ወ/ሮ ሚሼልን ከአገሮችም ግብጽና ሱዳንን፡ ከዜና ማእከላትም ሮይተርስን፡ ቢቢሲንና አልጀዚራን…ወዘተ በከባድ ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ ላይ ተጠምደው ሲጮሁ አስተውለናል፡፡የሚገርመው ወ/ሮ ሚሼል ልክ እንደ አንድ ወያኔ አባል ነው ላይሳካላቸው ኢትዮጵያን የሚታገሉት፡፡

አሁን እጅግ ወደቆጠቆጠኝ የእለቱ ጉዳዬ ልመለስ፡፡ይህም አክብረው የነበረው የርዕዮት ሜዲያው ቴዎድሮስ ጉዳይ ነው፡፡ ቴዲ፦በሜድያህ ታህሳስ 18 እና 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ከመሰሎችህ ጋር ያደረግከውን ውይይት በአግራሞት ተመልክቸዋልሁ፡፡ ለካ የቀበሮ ባህታዊ ነህ፡፡ እስካሁን ድረስ ለሀቅ እንጅ ለዘር የቆምክ አልመሰልከኝም ነበረ፡፡ የወያኔ መቃብር ላይ ሳይታወቅህ ለቅሶህን ለቀቅከው፡፡ተጋለጥክ፡፤ ህዝብ ህዝብ ነው፡፤እናንተ እኮ የምትሉት በትግራይ እስካሁን ለ54 ቀናት ህዝቡ የባንክ አገግሎት ፡ውሀ፡ እርዳታ፡ ጸጥታ አላገኘም ነው፡፡ ሴቶች ተደፈሩ፡ ድርጅቶች ወደሙ፡ንብረቶች ተዘረፉ፡ ህጻናት ተራቡ፡ ተሰደዱ፡ ሰዎች ተገደሉ ወዘተ ነው የምትሉት፡፡ አንተና ጓደኞችህ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን ረሳችሁትን? የጦርነቱም መንስኤ በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ የአገሪቱን ጦር አባላት እብሪተኛው ወያኔ ራሳቸውን መከላከል በማይችሉበት ሁኔታ አቅዶ በማታ፡ በጭካኔ ያረደበትን ሁኔታ፡ አስክሬናቸውንም ጅብና አሞራ እንዲበላው ማስድረጉን አታዉቁምን? ረሳችሁትን? ወይንስ መካዳችሁ ነውን? በማይካድራም ወስጥስ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ንጹሀን አማራወችን ወያኔ ሰብስቦ ማረዱን አርዶም በጅምላ መቅበሩን አታዉቁምን? ረሳችሁትን? ወይንስ መካዳችሁ ነውን? ለጩሀታችሁና ወያኔ ለሰራው ወደር የለሽ ግፍ ሚዛናችሁ ይህ ነውን?? ቀጥሎስ ለአማራው የደም መሬት የሆኑት ወልቃይት፡ ጠገዴ፡ ጠለምትና ራያ ወደትግራይ ይካለሉ ብላችሁ ለቅሶ ልትቀመጡ ነውን? እናያለን፡፡ መጥቀስ ካስፈለገ እኮ ወያኔ ተዘርዝሮ የማያልቁ አያሌ ወንጀሎችን የፈጸመ ድርጅት ነው፡፡ወያኔ እኮ በአማራ ላይ የሰራው ስፍር ቁጥር የለሽ እልቂት እንዳለ ሆኖ እሬቻ ላይ ያንን ሁሉ የኦሮሞ ወጣት መፍጀቱ ሳያንስ አባዱላ ገመዳን “ለኦሮሞ ከኦነግ ይልቅ ወያኔ ይቀርበዋል ያስባለ” ድርጅት ነው፡፤በሶማሊያ ክልልም ከእነ አብዲ ኢሌ ጋር ሆኖ በህዝቡ ላይ የከፋ የመሬት ወረራና የከረፋ ኮንትሮባንድ ቁማር የተጫወተ ድርጅት ነው፡፤ በጋምቤላም ቢሆን በብዙ መቶ የሚቆጠር ንጹህ ህዝብን ያረደ ድርጅት ነው፡፡ለም መሬቶቹንም በትግራይ ተወላጆች ካስያዘ በኋላ እነዚያኑ የተረከባቸውን ባዶ መሬቶችን ከህግ ውጭ የብድር ማስያዣ (collateral) አድርጎ በማቅረብ ለእርሻ ልማቱ የወሰደውን በቢሊዮኖች የሚቆጠር ብር ወደውጭ አገር ያሽሸ ድርጅት ነው፡፡ በአፋር ክልልም እንዲሁ የጨው ማውጫ ታሪክንና የባለኮከብ ሆቴሎች ምስረታን በማሳበብ በብዙ ቢሊዮኖች የሚቆጠር ብር በቀረጥ ነጻ መብት ስም መመዝበሩ የሚረሳ አይደለም፡፤ ሁሉንም የወያኔ ወንጀሎች ዘርዝረን መጨረስ አንችልም፡፡ ሁሉንም ግን ታሪክ ለፍርድ መዝግቦ ይዟቸዋል፡፡እዚህ ላይ አሁን እጅግ የሚገርመው ነገር ተረኛው ኦሮሙማም ከዚሁ ትምህርት መውሰድና መታረም አቅቶት በተመሳሳይ ሳይሆን እጅግ በባሰ መልኩ በምዝበራው፡ በዘረኝነቱና በወደር የለሽ የጭፍጨፋ ተግባሩ ላይ ተጠምዶ መገኘቱ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  መስጠት ብቻ ወይንስ ስጥቶ መቀበል? (ጥሩነህ)

ቴዲ፦ አንተም ነገሮቹን ሚዛን ላይ አውጥተህ መመዘን ተውክና፡ አንተም የዘሬን ያንዘርዝረኝን ነውረኛ መርህ ተከተልክና በአገሪቱ ብሶትና ጭንቀት ላይ ከበሮ መምታት ጀመርክ፡፡ ያሳዝናል፡፤ ይህንን ከአንተ የጠበቀ አልነበረም፡፤ ምን ያደርጋል ዘመኑ ነው አንተም ወደ ዘርህ አብይ አህመድም ወደ ኦሮሙማው ባልተጠበቀ አሰላለፍ ወርዳችሁና ዘቅጣችሁ ተገኛችሁ፡፡ ነገሩ አሁን ተበላሽቷል፡፤ የወያኔም ነገር አልቆለታል፡፤ አታድኑትም፡፤ በተለይ አንተ የታሪክም ሰው ስለሆንክ በኢትዮጵያ ታሪክ ከሀዲ ማን እንደሆነ ጠንቅቀህ ታውቀዋለህ የሚል እምነት ነበረኝ፡፡ በዘረኝነቱና በዘራፊነቱ ወያኔን እያስናቀ የመጣው ኦሮሙማ ለኢትዮጵያ አጥፊ አንጅ የሚበጅ ሀይል እንዳልሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ ብልጽግናም የኦሮሙማ የግልቢያ ፈረስ እንደሆነ አልጠፋንም፡፡ በምንም መመዘኛ ግን አገሪቱ አሁን ለምትገኝበት ምስቅልቅል ሁኔታ ውስጥ ለመግባቷ ዋናና ተቀዳሚ ተጠያቂው ያንተው ወያኔ (አሁን የምታለቅስለት ስርአት) መሆኑ ምን ጊዜም የምንረሳው አይደለም፡፡ ስለዚህ አንተ አገሪቱን ከጥፋት ለማዳን ከሰልፉ በማፈንገጥህ ‘shame’ ብለንሀል፡፡ ሁሉም ያልፋል:: አገራችን ኢትዮጵያ ግን አታልፍም፡፡የፈጣሪ ቃልኪዳንም አላት፡፡ይህንኑም አንተም አብይ አህመድም በቃሎቻችሁ ዘወትር ትሉታላችሁ፡፤ ሁለታችሁም ግን ቃላችሁን በተግባር እታስመሰክሩም፡፡ ማን ያውቃል አብይ አህመድ እንደዚህ በመሸና ባለቀ ሰአት ወደ እውነታው ተመልሶና ንሰሀ ገብቶ ከዘረኝነት በጸዳ ንጹህ ልብ ሁሉንም በእኩልነት ለማገልገልና ዘረኝነትን ባስወገደ አዲስ የፌደራላዊ ህገመንግስት አገር ሊያስተዳድር ቢነሳስ? አልፎበታልን?? እንደ እኔ አላለፈበትም!! ወያኔን ግን ማዳን አይቻላችሁም፡፡ አልፎበታላ፡፡

ስለዚህ ቴዲ ሆይ ፦ እወቀው የመርዝ ብልቃጡ መሪያችሁ አንድ ወቅት ቅንጅቶችን “አበሻ አያድናችሁ ..ፈረንጅ አያድናችሁ”.ሲል መመጻደቁ ይታወሳል፡፡ አሁን ላይ ይህ የመመጻደቅ ትርክት መሬት ላይ ወዳለው ሀቅ ወደ << ፈረንጅ አያድናችሁ…. ሱዳን/ግብጽ አያድናችሁ >> እዉነታነት ተቀይሯል!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከራሳችን አልፎ በአምሳሉ የፈጠረንን እውነተኛ አምላክ ለምን ለመሸንገል እንሞክራለን?

 

ሀዱሽ መለሰ

1 Comment

  1. ሀዱሽ ፤
    ያልከው በውነቱ ትክክል ነው፡፤ አብይ አህመድን ጨምሮ ሁሉም ትምህርት ሊያገኙበት ይችላሉና ቀጥልበት፡፡ የነጮቹስ ይሁን፡፤ የገንዘብ ጥቅም ስለሚያገኙበት ነው እንበል፡፡ በተለይ የሚገርመው በውጭ አገራት የሚገኙ የወያኔ አቀንቃኞች ደጋፊወችና ተከፋዮች በመቀማጠል ኑሯቸውን እየገፉ የራሳቸውን ዘር ከሩቅ ሆነው ግፋ በለው በማለት አገር ያባላሉ፡፡ ያሳዝናል፡፡ ኦሮሙማም እንደሚታየው የባሰ እንጅ የተሻለ አይመስልም፡፡ እስኪ ጌታ ያውቃል !!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share