December 12, 2020
19 mins read

ታሪክ እና ልክ አለማወቅ ቅድሚያ ዉድቀት ነዉ! – ማላጂ

ከሰሞኑ በአገር ሉዓላዊነት ፣በህዝቦች አንድነት እና አብሮ የመኖር የስጋት ምንጭ  የነበረዉ የዉጭ እና የዉስጥ ሴራ በአገር ወዳድ እና ህዝባዊ ዓላማ  አንግበዉ በተነሱ የቁርጥ ቀን ልጆች ፊዉታራሪነት እንዲሁም በማዕከላዊ መንግስት ህዝባዊ ወገንተኝነት ፣ በህዝብ ድጋፍ እና በአካባቢ የክልል አስተዳደር  የተቀናጀ ድጋፍ አገር የማዳከም እና የማክሰም ሴራ ዓለም እንዲያዉቀዉ እና ፀሃይ እንዲመታዉ በማድረግ እንዳልነበር ሆኗል ፡፡

ሆኖም በአገር እና ህዝብ አንድነት እና ደህንነት በማናጋት የግዛት መስፋፋት እና ራስ ገዝ አስተዳደር (አገር) የመመስረት የስልጣን አባዜ የተጠናወታቸዉ  እና መሰል ግብረ አበሮች  በክህደት እና ሀሰት የማስመሰል ጥረታቸዉ ህዝባዊም ሆነ ብሄራዊ ዓላማ እና ግብ ኖሮት ስለማያዉቅ በተስፋ መቁረጥ ስሜት አሁንም የመለያየት እና የጥፋት መርዝ በተለያየ ሁኔታ መርጨት እና ማሰራጨት ልማድ ስለሆነባቸዉ ከስራቸዉ የማድረቅ ስራ ጅምር በመንግስት እና በአገር ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ  በህብረት እና አንድነት ሊቀጥል ይገባል ፡፡

ምን አልባትም አዲስ አገር ወይም ግዛት ለማስፋፋት እና ለመመስረት ሲባል በዕብሪት እና በማን አህሎኝነት ሌላዉን የኢትዮጵያ ግዛት(ክፍለ ሀገር) ትናንትም እንደአምና በጉልበት እና በግፍ ለመዉረር የተደረገዉ ድብቅ ሴራ ገመድ ቢቆራረጥም ይህ ቁርጥራጭ እና ጉድጓድ ወጥመድ ለወደፊት የዕድገት እና አገር አንድነት ጠንቅ   ስለሚሆን አስከአሁን የተገኘዉ ብሄራዊ ድል የድል መጀመሪያ እንጅ መጨረሻ ባለመሆኑ ሊጠናከር እና ሊታሰብበት ይገባል፡፡

እዚህ ላይ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያንን  ከመከፋፈል እና ከመበታተን የታደጉትን የምንጊዜም ጀግኖች ኢትዮጵያዉያን  ከፍ ያለ ክብር እና ፍቅር በመቸር የአገር እና ትዉልድ ፈርጥ እና ኩራት ሲሏቸዉ ከዚህ በተቃራኒ በተለያየ በተዉሶ አፍ( የራሳቸዉ ባልሆነ)  የሆነ ያልሆነዉን የሚሉ የአዞ አንቢዎች መኖራቸዉን  ህዝብ ፣ አገር እና መንግስት አሳምረዉ  እና ጠንቅቀዉ እንደሚያዉቁት አንጠራጠርም ነገር ግን በሆነ አጋጣሚ ሁሉ ድብቅ እና የግማሽ ክፍለ ዘመን ግብ አልባ ከንቱ ምኞታቸዉ በመክሸፉ ዛሬም የማይፈነቅሉት ድንጊያ ፤የማይበጥሱት  ቅጠል የለም ይህም  ያሳዝናል ፤ያስተዛዝባል፡፡

እነኝህ  ኢትዮጵያን አፈሯን  ሲፈልጉ  ህዝቧን  እና ዜጎቿን በጠላትነት ዉጋ በፍለጋ የሚያሳድዱ መቸ እዉነት እንደሚሰሙ ፣ እንደሚናገሩ  መተንበይ  ባይቻልም እዉነት ምን እንደሆነ ግን ከጥቅምት ሃያ አራት አስከ አዚች ዕለት ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን እንደሆነ አይተዋል ለዚህ ነዉ አሁንም  የጥላቻ  ህመም  ቁራኛ እንደሆኑ የሚገኙት  ፡፡

ህመማቸዉም የዉስጥ ስለሆነ እንዲህ በቀላሉ የሚገመት እና የሚታይ  እንዳልሆነ ሁሉም በአገር ጉዳይ ያገባኛል ባይ ሊረዳቸዉ ግን በቃ ሊላቸዉ  ይገባል ፡፡

የራሳቸዉን በሽታ ለአገር እና ህዝብ ለማዳረስ የማይወጡት ዳገትም ሆነ የማይወርዱት ቁልቁለት አይኖርም እና ከሚያሳቃያቸዉ የጥላቻ እና ይትፋት አባዜ ጋር አስኪጠፉ አገርን እና ህዝብን ከጥፋት የማዳን ተግባር ሊቀጥል ይገባል ፡፡

ይህ በአገራችን የጀመረዉ የጥቅምት 24 የአገር ክህደት እና ጥፋት ከአምስት አስርተ ዓመታት ጀምሮ የተቦካ የክፋት እና የጥላቻ ደቦ መስራች እና አመቻች ፣መሪ ፣ አስተባባሪ እና ተባባሪ አካላት በሚነዙት የዕድሜ ልክ ዉዥንብር እና የወሬ ሽብር በኢትዮጵያ እና ህዝቧ ትንሳዔ  ህመማቸዉ  እንደሚያገረሽባቸዉ  ይታወቃል  ፡፡ ለዚህም የተለያዩ ምልክቶች የሚታይባቸዉ ለመሆኑ ቅድመ  እና ድህረ ጥቅምት 24 የሚሉት እና ሚያስተጋቡት ለአገር እና ህዝብ ቀርቶ ለራሳቸዉ የማይጠቅም የጥላቻ እና የሟርት( ክፉ ምኞት) እንደነበር በሌላዉ እንደሚታወቅ አለማወቃቸዉ ደግሞ ሌላዉ ችግር ነዉ ፡፡

ይኸዉም፡-

  • መንግስት ቀድሞ ጦርነት ቢጀምር በማሳጣት/ ዲፕሎማሲም ሆነ በጦርነት የበላይነት ርግጠኛ እንደነበሩ ሳይናገሩ የሚታወቅ እንደነበር፣
  • ጦርነት ለእነርሱ ደጋግመዉ እንደሚሉት ፤እንዳሉት መስራት እንደሚችሉ እና በጦርነት የበላይነትን የእነርሱ ብቻ ማድረግ የባዶነት ድምር እና ክምር ከአለፈ ታሪክ አለመማራቸዉ፣
  • ጦርነቱን ሲናፍቁ በናፈቁት ልክ አለመሆኑን ሲረዱ የናፈቁትን ጦርነት በድል እንደሚወጡ በምኞት ስካር ጦሩን በመበተን፤ ቀሪዉን የኢትዮጵያ ክፍል( ጎንደር እና ወሎን ክ/ሀገራት) በድንገት በመዉረር የአሸናፊነት ቅስቀሳ / ፕሮፖጋንዳ ማስተጋባት ….. ነበር አልሆነም ፡፡

ድህረ ጥቅምት 24 እና ጦርነት ፡

  • እነርሱ እና ቃል የገቡላቸዉ በምኞት እና ፀሎት ቢሆን ኖሮ አሸነፍን የሚሉት መንግስትን ነበር ግን ማጣፊያ ሲያጥራቸዉ በባዕድ ወረራ ሲሉ ተሰማ፣
  • ቀጥለዉ በዉስጥ ደቀመዝሙራት አማካኝነት ጦርነቱ ምክነያታዊ ነበር ፤አልነበር በማለት እና በማስወራት ዉዥንብር መንዛት ያዙ ፣

በመጨረሻም አገርን ከመፍረስ ፤ህዝብን ከተደጋጋሚ ጥፋት፣ ሞት እና ስደት ለማዳን በተደረገ ብሄራዊ ጥሪ እና  ዕልህ አስጨራሽ የሞት ሽረት ትግል(ዉጊያ) በድል ምዕራፍ ላይ የሚገኘዉን የመንግስት እና የህዝብ ኃይል የተለያየ ስም ሊሰጡት መዳዳታቸዉ በተለይም በህዝብ እና በአገር ስም እየተገዘቱ በአስተሳሰብ እና በተግባር የተለዩ ድብቅ አመላቸዉ ጋህድ የመዉጣቱ ጉዳይ አሁን አሁን ግልፅ እየሆነ ይስተዋላል ፡፡

በሰሜን አገራችን ትግራይ የተካሄደዉ ጦርነት ሳይጀመር  በዉድቀት(በሽንፈት)  መታጀቡን የምንረዳዉ በዉድቅት ለሊት በዕንቅልፍ የወደቀን ሠዉ (ሠራዊት ) ለምርኮ ማሰብ የኢትዮጵያን እና ህዝቧን ሆነ የራስን ታሪክ አለመረዳት ወይም ችላ ማለት እንደነበር ብዙ ማሳያ ለመጥቀስ ቢቻልም ይህ ባለቤት ስላለዉ አልፈዋለሁ ፡፡

 ይሁንና ከአገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በደጀንነት የቆመዉን “ የአፋር እና የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ አስተዳደር የፀታ ኃይል እንዲሁም የአካባቢ ህዝብ”  ራሱን ፣ አካባቢዉን እና እናት አገር ምድሩን ከመሬት ወራሪ ፣ ከተስፋፊ እና ከአገር አጥፊ መታደጉ ክብር፣ ፍቅር እና ሞገስ ሊቸረዉ  ሲገባ ያደረገዉ ተጋድሎ በስዉር የጥፋት ደቦ  አባላት ሲወቀስም ሆነ ሲገሰስ መስማት ኢትዮጵያዊ ለሆነ አይደለም የዘመናት የሩቅ እና የቅርብ ጠላቶች የሚመሰክሩት የጊዜዉ ሀቅ ነዉ ፡፡

በዚህ ብሄራዊ ድል የተከፉ በቻ አይደለም ያኮረፉ መኖራቸዉ የሚጠበቅ ነዉ ምክነያቱም የእነርሱ መርህ የቅኝ ግዛት ዘመን የበታችነት እና የጥላቻ ዕሾህ በጫንቃቸዉ እንደተሸከሙ ስለሆነ ይህ ራሳቸዉን ሠላም ነስቶ ህዝብ እና አገር ሠላም እንዲያጣ መስራት ተቋማዊ ልምድ እና አመል አድርገዉታል ፡፡

በ18ኛዉ ክ/ዘ የነበረን የባርነት አስተሳሰብ በዚህ በምንገኝበት የ21ኛ ክ/ዘ ዋዜማ የሶስት ሽ ዘመናት  የነጻነት ምድር በሆነች አገር እና ህዝብ መሀል እየኖሩ የነጻ አዉጭነት ካባ ደርቦ አገርን እና ህዝብን ነጻነት ለመንሳት መባዘን የማይደክማቸዉ ዛሬም በአመለካከት መለወጥ ባይችሉም የትግል መጠሪያ ስያሜ መቀየር አለመቻላቸዉ የሚያሳየዉ ለግማሽ ክ/ዘ ብሄራዊም ሆነ ህዝባዊ ዓለማ ያልነበራቸዉ አሁንም በዚያ ዘመን ቆመዉ በዚህ ዘመን ትዉልድ ዕድሜ መኖር የሚመኙት እንዳሉ ነዉ ፡፡

ሌላዉ በተገኘዉ ብሄራዊ ድል (አገርን የማዳን) በመንግስት የአስተዳደር አደረጃጀት አመራር የተለያየ ምልከታ መኖሩን የሚያስተጋቡት መኖራቸዉን ስንታዘብ እነኝህም ምን ያህል በአገር እና ህዝብ ስም እየኖሩ ለአገር እና ህዝብ የዘመናት ብሶት እና እንግልት ግድ የማይሰጣቸዉ በህዝብ እና አገር የመገልገል የስልጣን እና ተየያዥ ጥቅም ናፋቂዎች ፊት ለፊት ከሚገኙ የብሄራዊ አንድነት ጠንቆች ባላነሰ ክፉ አስተሳሰብ የተጠመዱ መኖራቸዉን የምንማርበት አጋጣሚ ነዉ ፡፡

በየትኛዉም ዓለም እና አገር የመንግስት አቋም የህዝብ እና የአገር ጥቅም  እና ልዑላዊነት የማስከበር ፣የመጠበቅ እና የማላቅ ጉዳይ ሲሆን በመንግስት አስተዳደር ወይም የፖለቲካ አደረጃጀት ተሰንቅረዉ የህዝብን አንድነት እና የአገርን ሉዓላዊነት አሳልፎ ለመስጠት የሚሰሩ ፣የሚደራደሩ እና የሚግደረደሩ እንደማይጠፉ የሚጠበቅ እና የሚታወቅ በመሆኑ ምንም እንኳ የግል ምልከታቸዉ ቢሆንም መንግስት እና ህዝብ በትኩረት ሊያየዉ ይገባል ፡፡

ለቡድን እና ለግለሰብ ጥቅም ሲባል ህዝብ እና ህዝብ ፤ህዝብ ከመንግስት ጋር አጋም እና ቁልቋል ሆኖ እንዲቀጠል በማድረግ ሌት ተቀን የሚባዝኑትን በጥገኛ አመለካከት አዙሪት የሚዋዥቁትን ዥዋ ዥዌ ተጫዋጮች ችላ አለማለት ቀጣይ እና አስተማማኝ ብሄራዊ አንድነት እና ዕድገት ለማምጣት ከፍተኛ ፋይዳ እናዳለዉ ሊሰመርበት የሚገባ የወቅቱ መሪ ሀቅ ነዉ ፡፡

ሁላችንም እንደ ሠዉ ፣ ህዝብ እና ኢትዮጵያዊ  መገንዘብ ያለብን ህነግም ሆነ አቀንቃኞች የሚወድቁት እና  የተጠለፉት  ምግባር እና ተግባር በሌለዉ በትዕቢት እና በራሱ የጥፋት ወጥመድ እንጅ የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት አቅፎ እና ደግፎ እየሞተ ያኖረ ባለዉለታቸዉ መሆኑን ቢያዉቁትም በጎ ዉለታን መመለስ ባይፈልጉም ለማጥፋት እና ክህደት መነሳታቸዉ ግን እጅን በእጅ የመቁረጥ ያህል እንደሆነ ህመሙ ዛሬ ቢጀምራቸዉም የሚሰማቸዉ ግን ዉሎ አድሮ ብቻቸዉን ከሙሉ ኃጢያት እና ጥፋት ጋር ሲቀሩ ነዉ ፡፡

ህዝብ እና መንግስት የወሰደዉ እርምጃ ተገፍቶ እና ተገዶ አገር እና ትዉልድ የማዳን እና የማስቀጠል ጉዳይ  እንጅ ዞትር እሽርሩ ለአገር ነገር ቀርቶ ለመንፈቅ ልጅ እሽታ መፍትሄ አይሆንም ፤ሆኖም አያዉቅም ፡፡
በአገር የማዳን ርብርብ አስቀድሞ ከሚገመት በላይ ህዝብ እና መንግስትን ዋጋ ጠይቋል ከተባለ ችግሩ የሚመነጨዉ ቀድሞዉንም የአገር እና ህዝብ ሠላም ዕጦት ችግር ሁሉ ምንጭ እና ምክነያት ፣የችግር አንጓ የነበሩትን የመፍትሄ አካል ይሆናሉ ብሎ የመዉሰድ እሳቤ ዉጤት ነዉ ፡፡

ሲጠቃለል ሁሉም ሊረዳ የሚገባ ዕዉነት ለትህነግ ዉድቀትም ሆነ ቀጣይ ዕጣ ፋንታ(ክስመት) ተጠያቂ ራሱ እና አለን ባይ ተባባሪዎች ብቻ ናቸዉ ፡፡ ለዚህም በሁለት መሰረታዊ ነገር ማሳየት የሚቻል ሆኖ  ይኸዉም የኋላ ታሪክን ካለማወቅ እና ከልክ ያለፈ ልክ ( የትቢት ፣ዕብሪተኝነት መንፈስ)  መያዝ አሁን ለሚገኝበት ተጨባጭ ሁነት ዳርጎታል፤ ብዙዎችንም ይዞ ገደል ገብቷል ፡፡

በምድር ላይ ከራሳችን ዉጭ ሌላ ጠላት እንደማይኖረን ብናዉቅም የራስን እና የተጓዳኝ ሠልፈኛን ታሪክ እና ልክ ለማወቅ መሞከር ከጥቃትም ሆነ  ካለ ጊዜ ሞት መዳን ያስችላል ፡፡

ወኔም፣ጀግንነትም ከደም እንጅ ከስም አይገኛኙም ግን ጊዜ እና ቦታ አላቸዉ እና እያዩ መራመድ አለመቻል እና አለማሰብ ጊዜ ሲያመጣዉ አበባም እንደ እሾክ ይሆናል ፡፡

ዛሬ ለዓመታት ዶለተዉ በአንድ ለሊት ለአገር እና ህዝብ ጥፋት እና ሞት የደገሱት ደባ ከእነርሱ አልፎ ለብዙዎች ሲተርፍ ማየት ተችሏል ፡፡ ይህ ክፉ ሞቶም ይገድላል እንዲባል በስሜት እና በክፋት የሚነዱ ሁሉ የለኮሱት  የጥፋት ዕሳት ሲያቃጥላቸዉ ማየት  “ለኃጥዓን የወረደ ለጻድቃን ይተርፋል” የሚባለዉን የአበዉ ብሂል  በማስተወስ ዳግም እንድንማር የሚያስችል ታሪካዊ አጋጣሚነቱን ማሰብ ያሻል ፡፡

ታሪክን መዘከር እንጅ ማወናከር፣ማደናገር ሆነ መርሳት አይከፍሉት ዋጋ ስለሚያስከትል ከአባቶቻችንን ታሪክ እንማር ፤እንዝከር ፡፡

 

ማላጂ

ምንጊዜም እናት አገር ትኑር

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop