በስሜን አሜሪካ ከምንኖር የቅማንት ተወላጆች ስብስብ

በኢትዮጵያ የመከላካያ ሠራዊት የስሜን ዕዝ ጦር እና በማይካድራ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ ትሕነግ ያደረሰውን የጀምላ ጭፍጨፋ በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ ም ትሕነግ በአገራችን ኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የስሜን ዕዝ ጦር ላይ የፈጸመውን ጥቃትና ይህንን ተከትሎ በማይካድራ ኗሪ ኢትዮጵዊያን ላይ ማንነታቸውን መሰረት አድርጎ ያካሄደውን የጀምላ ጭፍጨፋ የሰማነው በከፍተኛ ኃዘንና ቁጭት ነው።

ትሕነግ የተባለው ፀረ ኢትዮጵያ ቡድን ሽፍትነት ከጀመረበት 1967ዓ ም ጀምሮ የአማራን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ ከጥላቻ ፕሮፖጋንዳ እስከ ዘር ማጥፋት ድረስ የዘለቀ ወንጀል ሲፈጽም እንደነበር ተጠቂው የአማራ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በተለያየ ጊዜያት ድርጅቱን ጥለው የወጡ የቡድኑ አባላትም የመሰከሩት ሐቅ ነው።

ይህ ከሃዲ ቡድን በ1983 ዓ ም የኢትዮጵያን መንበረ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ ይህንን እኩይ ተግባሩን ሕገ መንግሥታዊ ቅርጽ በማስያዝ ሕዝብን ከሕዝብ፣ ጎሳን ከጎሳ በማጋጨት የበርካታ ወገኖቻችን ሕይወት እንዲጠፋ፣ ንብረታቸው እንዲዘረፍና እንዲወድም በማድረግ ከፍተኛ ወንጀል ሲፈጽም ቆይቷል።በተለይም የዚህ እኩይ ተግባሩ ዋነኛ ዒላማ በሆነው የአማራ ብሔር ላይ ለ27 ዓመታት ሲፈጽም የነበረው ግፍና የዘረ ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል ወደር የማይገኝለት የክፍለ ዘመኑ ሂተለራዊ ድርጊት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

ትሕነግ ከ27 ዓመታት የግፍ አገዛዝ በኋላ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአካሄደው መራራ ትግልና መስዋእትነት ከሥልጣኑ ተግፍትሮ መቀሌ ከከተመ በኋላም ቢሆን በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በአደራጃቸው፣ በአሠለጠናቸው ፣ በአስታጠቃቸውና የፋይናንስ ድጋፍ በሚአደርግላቸው ጽንፈኛ አሸባሪ ቡድኖች አማካይነት ኢትዮጵያዊያን በማንነታቸውና በዕምነታቸው ተለይተው በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ፣ንበረታቸው እንዲወድምና እንዲፈናቀሉ በማድረግ አገራችንን የሲኦል ምድር አድርጓት ቆይቷል።

አሸባሪውና ዘረኛው ትሕነግ በዚህ ብቻ ሳያበቃ በሰሞኑ ደግሞ እጅግ በሚአሳፍርና ለማመን በሚከብድ ሁኔታ የአገር አንድነትንና ሉኦላዊነትን ለማስከበር በተሰማራው የኢትዮጵያ የመከላካያ ሠራዊት የስሜን ዕዝ ጦር ላይ ድንገተኛ ጥቃትና ጭፍጨፋ በመሰንዘር ከፍተኛ የአገር ክህደት ወንጀል ፈጽሟል።

በዚህ ግንባር የተሰማራው ሠራዊት ከውስጥ የሠራዊቱን መለዮ በለበሱ የራሱ አባላት፣ ከውጭ የክልል ልዩ ኃይል ብሎ በአደራጀውና ከፍተኛ ቁጥር ባለው ሚሊሻ አማካይነት የሠራዊቱን አባላትና መሪ መኮንኖች እረሽኗል፤ የሰው ልጅ ሊፈጽመው ቀርቶ ሊያስበው ይችላል ተብሎ በማይገመት ሁኔታ የሞቱ ወታደሮችን አልባሳት በመግፈፍ አስከሬናቸውን ለአውሬና ለአሞራ ስጥቷል። በሕይወት የተረፉትንም በተማሳሳይ ልብሳቸውንና ጫማቸውን በማስወለቅ እራቁታቸውን ከክልሉ አባሯቸዋል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የሠራዊቱ አባላትንም በምርኮነት ይዞ በማሰቃየት ላይ ይገኛል።

ገና በጥዋቱ አብረውት በረሃ የገቡ የራሱን አብሮ አደግ ጓደኞች በተኙበት በማረድ ክህደትን ‘ሀ’ ብሎ የጀመረው ትሕነግ በሠራዊቱ ውስጥ የነበሩት አባላቱ እነሆ ከ50 ዓመት በኋላም በሕግ ከተሰጠው የአገርን ሉኦላዊነትና የሕዝብን አንድነት የማስክበር ግዳጅ፣ በተጓዳኝ የትግራይን ደሃ ገበሪዎች ሰብል በመሰብሰብ፣ትምህርት ቤትና ጤና ጣቢዎችን በመሥራት፣ ከቀለቡ በማካፈልና አንበጣን በመከላከል ለ21 ዓመት አብሮአቸው የኖረውን ሠራዊት በመክዳትና ከተኙበት በመረሽን ያነን የበሰበስ የክህደት ወንጀሉን ደግሞታል።

ይህ ከሃዲ ቡድን በዚህ ሳይረካ ከ1983 ዓ ም በፊት ጀምሮ በማን አለብኝነት ወደ እራሱ ግዛት ጠቅሎ በወሰደውና የጎንደር ክፍለ ሐገር አካል በሆነው የማይካድራ ኗሪ ሰለማዊ ኢትዮጵያዊያን ላይ እጅግ አሰቃቂ ግድያ ፈጽሞ ቦታውን ለቆ ሸሽቷል።

ትሕነግ ከአሁን በፊት በአርባጉጉ፣ በበድኖ፣ በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በሻሽመኔ፣ በአርሲ ነገሌ፣ በባሌና በምዕራብ ወለጋ፤ በደቡብ ጉራ ፈርዳ፣ በቤንሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች በተላላኪዎቹ አማካይነት በአማራ ህዝብ ላይ የፈጸመውን አረመኔያዊ የጅምላ ጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት ወንጀል በማይካድራም ደግሞታል።

ስለዚህ፤

1       መንግሥት ይህንን አሸባሪ ቡድን ለሕግ ለማቅረብና አገራችንን ከጥፋት ለማዳን እያካሄድ ያለውን ዘመቻ አጠናክሮ አንዲቀጥልና ይህን ቡድን በአሸባሪነት እንዲፈርጅ አያሳሰብን እኛም ከጎኑ ቆመን ለዚሁ ተግባራዊነት  የበኩላችን አስትዋፀኦ የምናደርግ መሆኑን አንገልጻለን።

2       የኢትዮጵያ የመከላካያ ሠራዊት በዚህ አሸባሪ ኃይል ላይ እየወሰደ ካለው እርምጃ ጎን ለጎን ይህን የውስጥ ችግር እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከውስጥም ሆነ ከውጭ የአገራችንን አንድነትና ሉኦላዊነት ለማናጋት የሚሞክርን ጠላት በንቃት እንዲጠብቅ እያሳሰብን የተጣለበትን ከፍተኛ አገራዊ ግዳጅ ለመወጣት በሚአደርገው ትግል ከጎኑ መሆናችንን እናረጋግጣለን።

3       ትሕነግ የስሜን ዕዝ ሠራዊት አካል በሆነውና በዳንሻ ግንባር በነበረው የ5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ጥቃት በሰነዘረበት ወቅት የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና በአካባቢው የነበረው ሚሊሻ ፈጥኖ በመድረስና የከበበውን  የትሕነግ ሠራዊት በመበታተን ስለአከናወነው አስደናቂ የውጊያ ብቃት አድናቆታችንን እየገለጽን ከኢትዮጵያ የመከላካይ ሠራዊት ጎን ተሰልፎ እያደረገ ያለውን ጅግንነት የተሞላበት ውጊያ አጠናክሮ እንዲቀጥል እያሳሰብን አኛም ክጎኑ መቆማችንን አንገልጻለን።

4       ሰፊውና በትሕነግ ፋሽሽስታዊ ቡድን እስታሊናዊ አገዛዝ ከአራት አስርት ዓመታት በላይ ታፍኖ የኖረው የትግራይ ሕዝብም በስሙ ተደርጅተውና በስሙ እየማሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲገሉ፣ሲዘርፉና ከአገር ሲያአሰድዱ የኖሩትንና አሁን ደግሞ ደህንነቱንና አንድነቱን ለማስከበር ተሰማርቶ በነበረው የመከላክያ ሠራዊት ላይ እጅግ አሳፋሪ ክህደት የፈጸሙትን የትሕነግ አመራር አባላት ለሕግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ዘመቻ ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን በመሰለፍ የአገሩን አንድነትና ሉኦላዊነት አንዲአስከብር ወገናዊ ጥሪአችንን አናቀርባለን።

 

የውድ አናት አገር ኢትዮጵያ አንድነትና ሉኦላዊነት በልጆቿ የተባበረ ክንድና መስዋእትነት ይከበራል!!

ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያሸንፋል!!!

ኢትዮጵያ በአንድነቷ ጸንታ ለዘላላም ትኑር!!!

 

ኅዳር 9 ቀን 2013 ዓ ም

ስሜን አሜሪካ (USA)‘

1 Comment

  1. የተሰጠው መግልጫ እንደተጠበቀ ሆኖ፡፡በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ በተለያዩ ቦታዎች የኢትዮጵያ ተወላጆች ይህን የመሰለ ድጋፍ መልካም ነው፡፡ እንዲሁም ይህንን የትውልድ አክባቢ፤የብሔር እና የጎጥን አስተዳደር የፈጥሩት ገና ከጥንሥሡ ደደቢት በነበሩበት ጊዜ ስለነበር ያ ፍልስፍና ያረጀ እና የፈጀ በመሆኑ ቀብራቸው ደርሶአልና አብሮአቸው ይቀበር እላለሁ፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.