ከኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን የሰላምና የትብብር አድቮካሲ ግሩፕ ፤በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

November 18, 2020

ኢትዮጵያ የጠላቶቿን እኩይ ተግዳሮት ድልነስታ ወደከፍታ ትወጣለች!

ታፍራና ተከብራ ለዘመናት የኖረችው አገራችን ኢትዮጵያ ከጉያዋ በወጡ የራሷ ጠላቶች የደረሰባት ጥቃት በእጅጉ አስቆጭቶናል። በሌላ በኩልም የኢትዮጵያን አንድነት ለመጠበቅና የጠላቶቿን አፍራሽ ተልኮ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ በቆራጥነት ለተሰማራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፤ ለዐማራ ልዩ ሃይል፤ ፓሊስና ሚሊሺያ ያለንን ከፍተኛ አድናቆት እየገለጽን የኢትዮጵያን አንድነትና ህልውና ለማስከበር መንግሥት የሚያደርገውን ጥረት በሙሉ ልብ እንደምንደግፍና የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁነታችንን ስንገልጽ በታላቅ ኢትዮጵያዊ ኩራት ነው።
በራስ ሰው የተፈጸመ ጥፋትና ጥቃት ከሁሉም በላይ ይጎዳል። ምንም እንኳን የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪዎች አሁን ያደረጉት እኩይ ተግባር ዛሬ የጀመሩት ባይሆንም ያሁኑ ግን መጠነሰፊና የኢትዮጵያን መኖርና አለመኖር የሚወስን አገራዊ ክህደት ነው። እነዚህ ኢትዮጵያውያን ከገሃዱ አለም ያፈነገጡና ክፋት ከስብእናቸው የለያቸው የዘመናችን እንቆቅልሾች ቢሆኑም እነሱ ከምድረገጽ በመጥፋታቸው ከማዘን ውጭ ብዙ የሚኩራራ ቀና አሳቢ ኢትዮጵያዊ አይኖርም። ልዩነቶች በእርቅና በሰላም ቢፈቱ በተሻለ ነበር ሆኖም ሰላም ባንድ ወገን ፈቃደኝነት ብቻ ሊሳካ የሚችል ጉዳይ አይደለም።

ቀናውንና ስልጡኑን መንገድ ረግጠው ይህንን የጥፋት መንገድ የመረጡት እነሱ በመሆናቸው ሃላፊነቱም የእነሱ ነው።ቀድሞውንም ይዘውት የመጡት የጎሳፓለቲካ መዘዙ ዘርፈብዙና የጥፋት እንደሆነ ገና ከጠዋቱ ይታወቃል።አንዱን ብሄረሰብ በሌላው ላይ በማነሳሳት ፤ መጠነሰፊ ሙስናን ባገራችን ላይ በማንሰራፋትና ኢትዮጵያን ለማዳከምና ብሎም ለማጥፋት ሲያሟርቱና ሲያስፈራሩ የቆዩት እነዚህ ከሃዲዎች አሁን ፍጻሜያቸው ጫፍ ላይ መድረሱ እርግጥ ሆኗል።

ኢትዮጵያ ማስወገድ ያለባት እነዚህን የፓለቲካ ጉጅሌዎችን ብቻ ሳይሆን ያለፈቃዷ ከጫካ አምጥተው የጫኑባትን የዘመነመሳፍንት አይነት የጎሳ ፓለቲካቸውንም ጭምር ነው። አገራችን መገንባት ያለባት ፍትህና ርትእ ለሁሉም የሰፈነበት፤ሰብአዊ መብቱ፤ባህሉ ቋንቋው የተከበረበት ሁሉም እንደአቅሙና ችሎታው የሚሳተፍባት ዲሞክራሲያዊ ሥርአት ነው።ኢትዮጵያ ከዚህ ቦሃላ በመብት ሥም አዲስ የጎሳ ጋሻ ጃግሪዎች የሚፈነጩባት አገር ከቶ መሆን የለባትም። ለዚህም ትክክለኛው አማራጭ ወያኔዎችና ግርፎቻቸው የነደፉትና የተገበሩት ፀረ-አንድነትና ፀረ-ሕዝብ ሕገ መንግሥት ሲቀየርና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የጎሳ አጥር ሳያግደው አገሬ ብሎ የሚኖርባት ኢትዮጵያ ስትኖር ብቻ ነው። ስለሆነም መንግሥት ከድል ባሻገር ፓለቲካውን ሥልጡን የማድረግና የጎሳ ፓለቲካን ሥር የሚነቅል ቆራጥና ተከታታይነት ያለው እርምጃ እንደሚወስድ ይጠበቃል። ይህ ካልሆነ ግን ወደ ሌላ የጦርነት አዙሪት ላለመግባታችን ምንም ዋስትና የለም።

ክብር ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ልዩ ሃይል!
ክብር የጎሰኞችን ቀንበር ለአመታት ተሸክሞ የተሰቃየውና አሁን በድል ለተወጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ!
ኢትዮጵያ ለዘለዐለም ትኑር!
የኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን የሰላምና የትብብር አድቮካሲ ግሩፕ

 

2 Comments

  1. ከላይ የተሰጠው መግለጫ እንድተጠበቀ ሆኖ በተለያዩ ክፍለ ኣለማትም ሆነ በተለያዩ ትልልቅ እና አነስተኛ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፤የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲውች እና በግለሰብ ደረጃም ቢሆን በአሁኑ ሰዓት የመከላከያ ሰራዊት፤የአማራ ክልል ልዩ ሃይል እና ሚሊሺያ ሰራዊት እየወሰደ ላለው የማያዳግም እርምጃ እንዲሁም በኦሮምያ ክልልም እይተወሰደ ላላው እርምጃ ሙሉ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ከጎን ለመቆም መግለጫው ይቀጥል፡፡ከሀገራችንም የክልል እና የዘር ደንበር ይውደም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

tplf empire
Previous Story

ቢዘገይም አይከፋም –  ማላጂ

tigray tplf 40
Next Story

ዛሬስ – ትንሽዬዪቱ አብረህት ስታለቅስ ሕወሃታውያኑ ልባቸው ራርቶ ይሆን? –  በየነ ከበደ

Latest from Blog

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የውጪ ግንኙነት የቤተክርስቲያኒቱን የሺሕ ዘመናት ታሪክ እና እሤቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርባታል!!

በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) (ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደጻፈው) እንደመንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው ጽሑፌ መነሻ የሆነኝ- ባሳለፍነው ሳምንት በአፍሪካ ኅብረት ኔልሰን ማንዴላ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለአንድ ቀን የተካሄደው፤ ‹‹የአፍሪካ  መንፈሳዊ ቀን/The African Spiritual

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |
Go toTop